ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በኢራን ጦርነት የአጋሮቿ ወታደራዊ ድጋፍ እንደማያስፈልጋት ገለጹ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገሪቱ ጦር ኃይል በኢራን ጦርነት ውስጥ "ከእንግዲህ ወታደራዊ እርዳታ አያስፈልገውም" ሲሉ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በራሳቸው "ትሩዝ ሶሻል" (Truth Social) ማህበራዊ ትስስር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፤ የአሜሪካ ጦር ኃይሎች በኢራን ጦርነት ውስጥ ከማንም ወገን ወታደራዊ እገዛ እንደማይሹ ገልጸዋል።
ይህ የፕሬዝዳንቱ መግለጫ የወጣው፣ ለነዳጅ ዝውውር ቁልፍ የሆነውን የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ (Strait of Hormuz) ክፍት ለማድረግ እና ደህንነቱን ለመጠበቅ አጋር ሀገራት ድጋፍ እንዲያደርጉ ቀደም ሲል ያቀረቡት ጥሪ በአብዛኞቹ ተቀባይነት ካጣ በኋላ ነው።
ቀደም ሲል አሜሪካ ከሌሎች የአውሮፓ እና የቀጣናው ሀገራት ጋር በመተባበር በባህር ሰርጡ ላይ ያለውን ስጋት ለመመከት ጥሪ ስታቀርብ የነበረ ቢሆንም፣ አጋሮቿ ለጥሪው አዎንታዊ ምላሽ ሳይሰጡ መቆየታቸው ይታወሳል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሁን ባወጡት መግለጫ ግን አሜሪካ ብቻዋን የጥቃቱን እርምጃ ለመቀጠል ሙሉ ወታደራዊ አቅም እንዳላት አመልክተዋል።
ይህ የፕሬዝዳንቱ አቋም አሜሪካ በቀጣናው በምታደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ላይ ያላትን የግል ውሳኔ ሰጪነት የሚያጠናክር እንደሆነ ተገምቷል ሲል የዘገበው አል አረብያ ነው ።
ልዑል ወልዴ

3 months ago