ጥቂት ስለ ግጥምና ገጣምያን!
ደረጀ በላይነህ
ገጣሚና ሐያሲ
#ethiopia | ግጥም እንደ ቋንቋ ጥንታዊና ሁለንታዊና መግባቢያ ስለሆነ፣ጥንታውያኑ ተጠቅመውበታል፤ዘመናውያኑ ደግሞ ኮትኩተውታል ይላሉ-ፕሮፌሰር ሎረነስ ፐሪኔ።
ግጥም ከሥነ ጽሑፍ ዘውጎች ተወዳጅና አክሊል የሚባለውም እንደ ጥንቅሽ እየተላጠ ተበልቶ ትዝታው ስለማይጠፋ፣የዋሽንቱ ዜማ ከልብ ስለማይገሠሥ ነው።
ዜማዊነቱ ለአይረሴነቱ ሰበብ ሲሆን፣ እምቅነቱ፣ምናባዊነቱ፣ተውኔታዊነት፣ቁጥብነት ወዘተ መለያ ባህርያቱ ናቸው።
ሌላው ብርቅ ከሚያሰኙት አንዱ ደግሞ አተያዩና ፍካሬው ነው። እንደ አልማዝ የተለያዩ ነጸብራቆች ስላሉት የዚያ ብርቅርቅታና ቀለም የገጣሚውን ምናብ ይለካዋል።
ግጥም ይፈላሰፋል፤ግን ፍልስፍና አይደለም። ገጠመኝን አሳምሮ፣በምናብ ወልውሎ ያመጣል እንጂ!
Its primary concern is not with beauty,not philosophical truth,not eith percuation,but with experience. ይላሉ።
ፊትን በመስታወት እንደማየት ይመስላል፤ ጥሬ ምስል አይደለም። ብዙ ቀለም በርካታ ቅርጾች አሉት። ምናልባትም በተሰባበረ መስተዋት እንደማየት ሊሆን ይችላል።.
በቅርጹም ወይ ተራኪ፣ተውኔታዊ፣አሊያም ሌሪክ ይሆንና እንደገና በየፈርጁ ይሸነሸናል።...በተለይ ስሜት ንክር፣ሙዚቃዊ የሆነው ሌሪክ የስሜት ዳንሶች ይዞ በሙሾ ሊያላዝን፣በፍቅር እስክስታ ሊመታ፣በትዝታ ቆርፍዶ እንባው በረዶ ሊሆን ይችላል።...እንጉርጉሮ ቢሆን፣ ጸሎትና ምሕላ፣ሽለላና ቀረርቶም እንደዚሁ።
ቃላት ለግጥም አንዱ መታበያው፣የቁመናው ጌጥ፣የመጋረጃው ዘርፍ ነው።...በተለይ ዘይቤያዊ ቃላት ደመና ላይ ሰቅለው ቼ! በለው የሚሉበት የከፍታው ጉልላት ነው።
ቃላቱንም እማሬያዊና ፍካሬያዊ ብለን ብንለያቸው፣በአብዛኛው ከዘወትራዊው ይልቅ በተምሳሌታዊና አምሳያዊ ትዕምርቶች በወደድነው ሥፍራ ብንዶላቸው ጣማቸው ይጨምራል።
ወይም ስሜት የነሸጠውን ያየንበት ትዝብት ውል ሲልብን፣እንደ መንግሥቱ ለማ፦
በጠራ ጨረቃ በእኩለ ሌሊት
ዓይኖቿ እያበሩ እንደክዋክብት
"ሳማት ሳማት"አሉት"ዕቀፍ ዕቀፋት"
አላወላወለም፤ወጣቱ ታዘዘ፤
ወገቧን አንገቷን፤በእጅና እጁ ያዘ፤
ከንፈሩ በረአድ ወዳፏ ተጠጋ።
-ምንም እንኳ ጡቷ እንደሾህ ቢዋጋ
ጣቷ በመሆኑ የበረዶ አለንጋ፤
ጆሮግንዱን ሰማው በጥፊ ሲናጋ።
በጠራው ጨረቃ በእኩለ ሌሊት
ዋ ጀማሪ መሆን ፤ዋ ተማሪነት፣
ዋ ትዕዛዝ መፈጸም፣ዋ ምክር መስማት።
እንግዲህ ተራኪው ግጥም እንዲህ ያለ መልዕክት፣ሲያስላልፍ ሥዕሉ ደምቋል። ጣቶቿ አለንጋ፤ጡቶቿ ሹል፣ሲል የልጅቷ ዕድሜ ከውስጥ ፤ቁመናው ከላይ ይታዩናል። ከዚህም አልፎ ደግሞ የምንበረብረው ሳጥን አለ። ከንፈሩ ለምን ቀዘቀዘ?...ፈርቷል። የፈራው ለምንድነው?...ልጅቷ እንዳትቆጣ!...ያኔ በዘመኑ ዐውድ ልጃገረ በእጅ መንካት ሽጉጥ ያስመዝዛል። ግን ተማሪ ጓደኞቹ አሳሳቱትና ጥፊ ቀመሰ።ቅምሻ ብቻ አይደለም ተናጋ። ሲናጋ ድምፅ አለው።
እዚህ ጋ ምሰላ ይመጣል- ድምፅ፣እላይ አጎጠጎጤ- ምስል፤ዐይኖችዋ መጉላት-ዕይታ።
ግጥም እንዲህና እንዲያ ነው። ሙዚቃው ያግባባል፤ሐሳቡ ሆድ ይገባል።
ግጥም የየዘመኑን ዳና ያስቀራል ስንል፥ ፖለቲካው፣ሥነ ልቦናው፣ፍልስፍናው ባሕሉ ወዘተ ቀለሙ ውስጥ ታትሞ ይኖራል። የረሃብ ይሆን ጥጋብ፤የጸብ ይሁን ፍቅር የትውልዱን ትዝብት፣ የነውጡን ንፋስ ፈትል ሰማይ ላይ ረጭቶ፣ የትካዜው ፉጨት፣የሳቁን ዜማ፣የትዝታውን ጥላ፤ ሻካራና እሾሁን፣ ሕመምና ጥዝጣዜውን፣ሳቅና ፍካቱን፣...
የአማርኛ ግጥሞች ዕድሜ ብዙ ሩቅ አይደለም።በዚያ ላይ አዳዲስ ፈርጆችን ይዞ አላስደነቀም። ከፖለቲካው ሥርዐትና ርዕዮት ጋር የቀየረው ቅርጽ የለም።ርዕዮቶችን በአንቀልባ እያዘሉ ከማውረድ የተለየ ሚናም አልነበረው። እንደ ፈረንጆቹ፣ወይም እንደላቲኖቹ፣ካልሆነም እንደመካከለኛ ምሥራቋ እሰራኤል የቤት ዐመታት ላይ የመጣው ለውጥ አልተመዘገበም።
ዘውጉን ሳይለቅ የቁመና ለውጥ ያመጣው ባለፉት አርባ ዐመታት ይመስለኛል። ያም ከፖለቲካዊና አገዛዛዊ ሸምቀቆ ጋር ተያይዞ የመጣ መጉበጥ ይመስላል።
አጫጭር ግጥሞች መብዛታቸውም፣የመታከት፣ብዙ ለመተንተን ሰሚ በማጣት የተፈጠረ መሰልቸት ይመስላል፤ዝም ብሎ ለመተንፈስ ብቻ። ቢጨንቀውና ሰሚ ቢያጣ መሬት ቆፍሮ ለመሬት እንዳወራው ሰው ዓይነት።
በዚሁ ተመሳሳይ ዘመን ሌላም ነገር ታይቷል። በግጥሙ መዝጊያ ላይ አንድ መገረሚያ ማምጣት። ትንሽ ቆይቶም፣
የአዳራሽ ግጥሞች በሙዚቃ እየታጀቡ መቅረብ መጀመራቸው ዘለግ ያሉና መድረክ ላይ የሚያቆዩትን አመጣ። እነዚህ የተንዛዙ ግጥሞችን ወደ ኅትመት ሰፈር ሲመጡ ዘልዛላ ሆኑ።
የመጀመሪያ መጻሕፍታቸው ያማሩላቸው ገጣምያን ሳይቀሩ ግጥሞቻቸው ለዛቸውንና እምቅነታቸውን ነጠቋቸው።
ከዚህ ዘመን ገጣምያን አንዷ ሜሮን ጌትነት ነበረች። ሜሮን ነገሮችን የምታይበትና የምትፈትልበት መንገድ ግሩም ነው። "ዙረት" በሚለው የግጥም መጽሐፏ አንገት በሚያስነቀንቁ፣ልብ በሚንጡ ግጥሞቿ አስመሰከረች።
መድረኮች ላይ ስትወጣ ግን፣እንደነምሥራቅ፣እንደነ ዶክተር በድሉ፣አረዘመቻቸው። ከነርዝመቱ ለዛውን ጠብቆ የሚሄደው አሳየኸኝ ረጋሳ ይመስለኛል። ትዕግሥት ማሞም አንዳች የማይረግብ ገሞራ አላት።
በግጥም ኅትመት ዓለም ብዙዎቹ የመጀመሪያ መጽሐፋቸውና ቀጣዮቹ እኩል አይደምቁም። ስስነትና እርግበት ይታይባቸዋል። በዚህ ፈተና ያልወደቀው ጋዜጠኛ ዲበኩሉ ጌታ ነው፤የእነ ደበበ ሰይፉን ደጅ እያንኳኳ ይመስላል።እነ አበረ አያሌው ገና አልተፈተኑም። ትዕግሥት ዓለምነህም ወደፊት በመጀመሪያ ግጥሟ ልክ ከመጣች፣ተዐምር ነው።ቋንቋ፣አተያይዋና Allusion አጠቃቀሟ ድንቅ ነው።
ወደ ሜሮን አዲሱ መጽሐፍ ልምጣ ። ስሜት የሚያሞቁት ከበሮ ድብደባዎች፣በቀጭን የሚመጡት ሳቆቿ ፣አንገት የሚያወዛውዙት ግርምቶች፣በአጫጭር ግጥሞቿ የምታደርጋቸው ተዐምራት የቀነሱ ይመስላል።
ቆንጆ ግጥሞች አሏት?...አዎ። ግን እንደድሮ አይደሉም። አዳዲስ ውበቶችና የቃላት ውበት ጨምራለች።
ግጥሞቿ፣ይስበኩን አይባልም። poetry does not teach:but it inspires.ይላሉ የዘርፉ ሰዎች።...ለነገሩ በዚህ የሚያምኑት ሊቃውንት በርካታ ናቸው።
እስቲ ከሜሮን ልምዘዝ፦
መተላለፍ 2
ሐቀኛ ነጋዴ በአመድ ገበያ ላይ ዱቄት ይዟል ማልዶ፣
የታይታ ሀብታም ሰው በሥጋ ወረፋ ይሰለፋል ማዶ።
ዘመን ሰውነትን ሸቀጥ አርጎ አውጥቶ ዐየን እንደዋዛ፣
የወረቀት ገንዘብ ወርቅ ሕልም እየገዛ።
ይህ ግጥሟ ሐሳቡ ብቻ ሳይሆን የቤት መምቻው ድምፅ ደማቅ ነው። ይህን ያደረጉት አናባቢዎቿ ናቸው። ሐሳቡም ግዙፍና የነፋሱን ዘመን በእፍኝ የሰፈረ ነው። ወርቅ ሕልም ፣በወረቀት እየሸጠ፤ዕንቁ በእሪያዎች ፊት እየተጣለ።
ልበ...
የአንተም ልብ ድንጋይ...
የእኔም ልብ ድንጋይ...
(ለዚያ ነው መሰለኝ)
በተጋጨን ቁጥር በፍቅር የምንጋይ።
ግጥም ሙዚቃ፣ ሥዕልም የተካተቱበት የሥነ ጽሑፍ ዘውግ ሰለሆነ፣ነፍስ ያፍነከንካል ፤ትርዒት ያሳያል።
ጋሽ ጸጋዬ በዘይቤዎቹ መዐዛ፣ በምሰላዎቹ ምትሐት ቀልብ ሲስብ፣ ገብረክርስቶስ በሜሎዲዎቹ ብብት ይኮረኩራል። ደበበ ሐሳብ እንደሽንኩርት እየላጠ ያስደምማል። ሁሉም በየራሳቸው ድንኳን የሚሰጡን ጣ'ም አለ።
ላምቦርን("ዶ/ር)ስለዚህ ሲጽፉ፦ Since every one likes pictures and most find pleasure in music,the common indifference to poetry must be due to a failure to realize that poetry is really both.

2 months ago