(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል በኢራን የኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ እስካሁን ከተፈጸሙት ሁሉ እጅግ የከፋ የተባለለትን የአየር ድብደባ ለማካሄድ እቅድ ማውጣታቸውን ሲቢኤስ ኒውስ ዘገበ። ጥቃቱ በዚህ የሳምንቱ መጨረሻ ሊፈጸም እንደሚችል በርካታ ምንጮች ጠቁመዋል።
የአየር ድብደባው በአሜሪካ እና በዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ገበያ ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተጽዕኖ በመስጋት፣ ሰኞ የፋይናንስ ገበያዎች ክፍት ከመሆናቸው በፊት ዘመቻውን ለማጠናቀቅ ውይይቶች መደረጋቸው ተገልጿል። ሆኖም የዘመቻው ማብቂያ ጊዜ ገና በግልጽ አልጸደቀም። የአሜሪካ ምንጮች እንዳረጋገጡት፣ ለእስራኤል ማሳወቂያ የተሰጠ ሲሆን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በቅንጅት እየሰሩ ይገኛሉ። ነገር ግን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጥቃቱ የመጨረሻውን የትዕዛዝ ማረጋገጫ ገና አልሰጡም።
የጥቃቱ እቅድ አርብ ዕለት በካምፕ ዴቪድ በተካሄደው የፕሬዝዳንት ትራምፕ የካቢኔ ስብሰባ ላይ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፣ አንዳንድ የዋይት ሀውስ የፖለቲካ አማካሪዎች ሀሳቡን አጥብቀው ቢቃወሙም፤ ትራምፕ በስብሰባው ላይ ለጋዜጠኞች "በጣም በኃይል እንመታቸዋለን። በአንድ ወቅት፣ 'ከዚህ በላይ መቋቋም አንችልም' ማለት ይጀምራሉ" ሲሉ ተደምጠዋል። የኃይል ማመንጫዎችን እና የነዳጅ ማጣሪያዎችን ጨምሮ መሰረተ ልማቶች ዋነኛ ኢላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ የተጠቆመ ሲሆን፣ በመላው ቴህራን መብራት ስለማቋረጥ በከፍተኛ ደረጃ ውይይት የተደረገ ቢሆንም እስካሁን የተላለፈ የመጨረሻ ውሳኔ የለም።
የዋይት ሀውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮላይን ሌቪት ለሲቢኤስ ኒውስ በሰጡት መግለጫ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በካቢኔ ስብሰባቸው ላይ እንዳሉት፣ አሜሪካ እንደምታሸንፍና በእሳቸው የሥልጣን ዘመንም ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንደማይኖራት አረጋግጠዋል። የፔንታጎን ዋና ቃል አቀባይ ሾን ፓርኔል በበኩላቸው፣ ፕሬዝዳንቱ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጡ ድረስ ፔንታጎን ስለ ኢላማዎቹ አስተያየት እንደማይሰጥ ገልጸው፣ የጦርነት መምሪያው በማንኛውም ሰዓት የፕሬዝዳንቱን ትዕዛዝ ለመፈጸም ሙሉ ዝግጁነት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል። በሌላ በኩል አንድ የእስራኤል ባለስልጣን ለእስራኤል በኢራን ላይ በሚደረግ ወታደራዊ እርምጃ እንድትቀላቀል ጥያቄ እንዳልቀረበላትና ሙሉ ወታደራዊ ዘመቻ ስለመጀመሩ መረጃ እንደሌላት ተናግረዋል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በተገናኙበት ወቅት፣ የአቅርቦት መስመሮች ላይ ያተኮሩትን ጨምሮ ሦስት የጦርነት አማራጮችን ማቅረባቸው ይታወሳል። ኔታንያሁ ከአሜሪካው የመከላከያ ጸሃፊ ሄግሴት (Hegseth) ጋርም ተወያይተዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ በሚጓዙ መርከቦች ላይ ለሚሰነዘር እያንዳንዱ ጥቃት የኢራንን የኃይል ማመንጫ ወይም ድልድይ አጋያለሁ ሲሉ በ‘ትሩዝ ሶሻል’ (Truth Social) ገጻቸው መጻፋቸው አይዘነጋም። የቀድሞ የአሜሪካ ወታደራዊ ባለስልጣን እንዳብራሩት፣ የኃይል መሰረተ ልማቶችን መምታት የኢራን ጦር አገልግሎት የመስጠት እና አገሪቱን የማስተዳደር አቅም ክፉኛ ያሽመደምደዋል።

2 months ago