2 hours ago
ንብ ባንክ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነዉን "ንብተራ ደረሰኝ "የተሰኘ ዘመናዊ የክፍያና የዲጂታል ደረሰኝ አገልግሎት አስጀመረ
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከፕራይም ኦል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነዉን ሁሉን በአንድ የያዘ "ንብተራ ደረሰኝ " የተሰኘ የዲጂታል ስርዓትን መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም አስጀምሯል ።
በዚህ ወቅትም የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ ከበደ ባንኩ ያስጀመረዉ ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ ነጋዴዎች ፣በገቢዎች ሚኒስቴር ዕዉቅና የተሰጠዉን የፕራይም ኦል ትሬዲንግ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ እና የድርጅት ሀብት አስተዳደር ስርዓትን ከንብተራ ኦንላይን ጋር በማቀናጀት በአንድ ስማርት ፓስ አማካኝነት የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ እንዲያወጡ ፣የክፍያ እና የንግድ ስርዓታቸዉን እንዲያዘምኑ ያስችላቸዋል ማለታቸዉ ብስራት ሬዲዮ ሠምቷል ።
"ንብተራ ደረሰኝ "ነጋዴዎች ለደንበኞቻቸዉ ጊዜ ያለፈባቸዉንና እርስ በእርስ የማይገናኙ ባህላዊ የሽያጭ መመዝገቢያ ካሽ ሬጂስተሮችን በአንድ እጅ ብቻ በሚያዝ ዘመናዊ ስማርት ፖስ በመተካት የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላቸዋል ተብሏል ።
የፕራይም ኦል ትሬዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዉብሸት አዝመራዉ እንደተናገሩት ይህ አዲስ የክፍያ ስርዓት ነጋዴዎች የተነጣጠሉ መሳሪያዎችን በመጠቀም ሲሰጡት የነበረዉን ኃላቀር አገልግሎት ያስቀራል ብለዋል ። በንግዱ ዘርፍ ላይ ሲስተዋሉ የነበሩትንም የአሠራር ፈተናዎች በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚያግዝ ተገልጿል ።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል

ፖል ቴርጋት (Paul Tergat)፡
የኬንያው የረጅም ርቀት ሩጫ ኮከብ፣ የዓለም ሻምፒዮንና
* የሃይሌ ገብረሥላሴ ታላቅ ተቀናቃኝ ለግራንድ አፍሪካን ረን እና ለአፍሪካ ኢምፖክት አዋርድ 2026 ዝግጅት ዋሽንግተን ዲሲ ደርሷል።
#ethiopia | ፖል ቴርጋት (Paul Tergat) በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ታሪክ ውስጥ ስሙ በታላቅ አክብሮት ከሚጠቀሱ የረጅም ርቀት ሯጮች አንዱ ነው።
አምስት ተከታታይ የዓለም ክሮስ ካንትሪ ሻምፒዮና የግል የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ፣ በኦሊምፒክ ሁለት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘትና የማራቶን የዓለም ክብረወሰንን በመስበር በስፖርቱ ውስጥ የማይረሳ ታሪክ ጽፏል።
ከኢትዮጵያዊው ታላቅ አትሌት ሃይሌ ገብረሥላሴ ጋር የነበረው ከፍተኛ ፉክክር የዓለም አትሌቲክስን በታላላቅ የስፖርት ትዝታዎች ካደመቁ ውድድሮች መካከል ይጠቀሳል።
በተለይም በ1996ቱ የአትላንታና በ2000ው የሲድኒ ኦሊምፒክ የ10,000 ሜትር ፍጻሜዎች ሁለቱን ታላላቅ አትሌቶች በታሪክ ውስጥ የማይረሱ ተቀናቃኞች አድርገዋቸዋል።
የሕይወት ታሪኩና የሩጫ ጅማሬ
ፖል ቴርጋት ሰኔ 17 ቀን 1969 በኬንያ ካባርኔት ተወለደ። በልጅነቱ የስፖርት ፍላጎት የነበረው ሲሆን፣ ወደ ሩጫ በመግባት በቀስታ ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ደረሰ። እ.ኤ.አ. በ1992 የኬንያ ብሔራዊ ክሮስ ካንትሪ ሻምፒዮናን በማሸነፍ የታላቅ የስፖርት ሕይወቱን መሠረት ጣለ።
የቴርጋት የሩጫ ችሎታ በተለይ በክሮስ ካንትሪ፣ በ5,000 ሜትር፣ በ10,000 ሜትር፣ በግማሽ ማራቶንና በማራቶን ውድድሮች ታይቷል። ይህም ከትራክ ሩጫ እስከ መንገድ ሩጫ ድረስ በተለያዩ ርቀቶች ራሱን ማረጋገጥ እንደቻለ ያሳያል።
አምስት ተከታታይ የዓለም ክሮስ ካንትሪ ሻምፒዮና ድሎች
የፖል ቴርጋት በጣም አስደናቂ ስኬቶች አንዱ ከ1995 እስከ 1999 ድረስ በየዓመቱ በዓለም ክሮስ ካንትሪ ሻምፒዮና የወንዶች ከፍተኛ የግል ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፉ ነው።
ይህንን ድል ለአምስት ዓመታት በተከታታይ ማስመዝገቡ በክሮስ ካንትሪ ታሪክ ውስጥ ከሚታወሱ ታላላቅ ስኬቶች አንዱ አድርጎታል።
1995 — ዱራም፣ እንግሊዝ
1996 — ስቴለንቦሽ፣ ደቡብ አፍሪካ
1997 — ቱሪን፣ ጣሊያን
1998 — ማራካሽ፣ ሞሮኮ
1999 — ቤልፋስት፣ ሰሜን አየርላንድ
ከዚህም በተጨማሪ በእነዚህ ውድድሮች የኬንያ ቡድን የበላይነትን ለማጠናከር ትልቅ ሚና ተጫውቷል።
በተለይ የ1999ኙ የቤልፋስት ድል አምስተኛው ተከታታይ የግል ሻምፒዮና ስለነበር በስፖርት ሕይወቱ ልዩ ቦታ ይይዛል።
. ከሃይሌ ገብረሥላሴ ጋር የነበረው ታሪካዊ ፉክክር
የፖል ቴርጋትን የስፖርት ታሪክ ስናነሳ የሃይሌ ገብረሥላሴን ስም አለማንሳት አይቻልም። ሁለቱ አትሌቶች በዓለም አትሌቲክስ ውስጥ የረጅም ርቀት ሩጫን ደረጃ ያሳደጉ ተቀናቃኞች ነበሩ።
የ1996ቱ የአትላንታ ኦሊምፒክ
በአትላንታ ኦሊምፒክ የ10,000 ሜትር ፍጻሜ ሃይሌ ገብረሥላሴ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያሸንፍ፣ ፖል ቴርጋት የብር ሜዳሊያ አገኘ። ይህ ውጤት በሁለቱ መካከል የነበረውን የውድድር ፉክክር ይበልጥ አጉልቶ አሳየ።
የ2000ው የሲድኒ ኦሊምፒክ
በሲድኒ ኦሊምፒክ የ10,000 ሜትር ፍጻሜ ሁለቱ አትሌቶች እጅግ በተቀራረበ ውድድር ተፋለሙ። ሃይሌ የወርቅ ሜዳሊያውን ሲያስጠብቅ፣ ቴርጋት በ0.9 ሰከንድ ያህል ልዩነት በሁለተኛ ደረጃ በመጨረስ የብር ሜዳሊያውን አገኘ።
ይህ ውድድር ከውጤቱ ባሻገር የሁለቱን አትሌቶች የፍጥነት፣ የጽናትና የውድድር ስልት በግልጽ ያሳየ ነበር። ሃይሌና ቴርጋት በስፖርት ሜዳ ተቀናቃኞች ቢሆኑም፣ የነበራቸው ፉክክር ለዓለም አትሌቲክስ ትልቅ እሴት አበርክቷል።
. በግማሽ ማራቶን የተመዘገቡ ታላላቅ ድሎች
ቴርጋት በትራክና በክሮስ ካንትሪ ብቻ ሳይወሰን በመንገድ ሩጫም የላቀ ብቃት አሳይቷል። በግማሽ ማራቶን ውድድር ሁለት ተከታታይ የዓለም ሻምፒዮና ድሎችን አስመዝግቧል።
1999፡ በፓሌርሞ፣ ጣሊያን የዓለም ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮናን አሸነፈ።
2000፡ በቬራክሩዝ፣ ሜክሲኮ የሻምፒዮና ድሉን ደገመ።
እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ2000 በሊዝበን የግማሽ ማራቶን ሩጫን በ59 ደቂቃ ከ6 ሰከንድ በማጠናቀቅ የዓለም ክብረወሰን አስመዘገበ።
እነዚህ ስኬቶች ቴርጋት በተለያዩ የሩጫ ርቀቶች ላይ ያለውን ብቃት ከማሳየታቸውም በላይ ወደ ማራቶን ውድድር ለመሸጋገር ጠንካራ መሠረት ፈጥረውለታል።
. የበርሊን ማራቶን 2003፡ የዓለም ክብረወሰን
የፖል ቴርጋት የስፖርት ሕይወት ከፍተኛ ምዕራፍ ከሆኑ ውድድሮች መካከል በ2003 የበርሊን ማራቶን ይጠቀሳል።
እ.ኤ.አ. መስከረም 28 ቀን 2003 በጀርመን ዋና ከተማ በተካሄደው ውድድር ማራቶኑን 2 ሰዓት 4 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ የወንዶች ማራቶን የዓለም ክብረወሰንን ሰበረ። ይህም ከ2 ሰዓትና 5 ደቂቃ በታች የተመዘገበ ታሪካዊ ውጤት ነበር።
ይህ ውጤት ቴርጋትን በዓለም ማራቶን ታሪክ ውስጥ ከታላላቅ ሯጮች መካከል አስመዘገበው። ክብረወሰኑ ለአራት ዓመታት ያህል ቆይቶ በ2007 በኬንያዊው አትሌት ሳሙኤል ዋንጂሩ ሳይሆን በኬንያዊው አትሌት ሃይሌ ገብረሥላሴ በበርሊን በ2:04:26 ተሻሽሏል።
ከዚያ በኋላም ቴርጋት በ2005 የኒውዮርክ ማራቶንን በማሸነፍ በመንገድ ሩጫ ያለውን ብቃት አረጋግጧል።
6. የአትሌቲክስ ስኬቶቹ በአጭሩ
5
ተከታታይ የዓለም ክሮስ ካንትሪ የወርቅ ሜዳሊያዎች
1995–1999
2
የኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያዎች
1996 እና 2000
2
የዓለም ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ድሎች
1999 እና 2000
2:04:55
የማራቶን የግል ምርጥ ውጤት
በርሊን፣ 2003
ከሩጫ ሜዳ ባሻገር፡ ማኅበራዊ አስተዋጽኦ
ፖል ቴርጋት ስፖርትን በማሸነፍና በሜዳሊያ ብቻ የሚለካ እንዳልሆነ በሕይወቱ በኋላ ባከናወናቸው ሥራዎችም አሳይቷል።
በ2004 የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆኖ ማገልገል ጀመረ።
በ2005 ደግሞ የፖል ቴርጋት ፋውንዴሽንን መሠረተ፤ የድርጅቱ ዓላማ በስፖርትና በትምህርት አማካይነት የተጎዱና ዕድል ያነሳቸውን ሕፃናትና ወጣቶች ሕይወት ማሻሻል ነው።
በተጨማሪም በኦሎምፒክ ስደተኞች ፋውንዴሽን ቦርድ ውስጥ ከ2021 ጀምሮ አገልግሏል። ይህ ከአትሌቲክስ ውድድር በኋላም ስፖርትን ለማኅበራዊ ለውጥና ለወጣቶች ዕድል መፍጠሪያ ለመጠቀም ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
የፖል ቴርጋት ውርስ ምንድን ነው?
የፖል ቴርጋት የስፖርት ሕይወት በሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ሊጠቃለል ይችላል።
ጽናት፡ በክሮስ ካንትሪ፣ በትራክና በመንገድ ሩጫ ለብዙ ዓመታት ከፍተኛ ደረጃውን ጠብቋል።
ተቀናቃኝነትና የስፖርት ታሪክ፡ ከሃይሌ ገብረሥላሴ ጋር ያደረገው ፉክክር ለዓለም አትሌቲክስ ታላላቅ የውድድር ትዝታዎችን ፈጥሯል።
ማኅበራዊ ኃላፊነት፡ በፋውንዴሽኑና በሰብአዊ እርዳታ ሥራዎች ለወጣቶችና ለማኅበረሰቡ የሚጠቅም አስተዋጽኦ ለማድረግ ቀጥሏል።
መደምደሚያ
ፖል ቴርጋት ከኬንያ የተነሳ ብቻ ሳይሆን በዓለም አትሌቲክስ ታሪክ ውስጥ የራሱን ልዩ ስፍራ ያረጋገጠ ታላቅ ሯጭ ነው። አምስት ተከታታይ የዓለም ክሮስ ካንትሪ ሻምፒዮና ድሎች፣ ሁለት የኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያዎችና በ2003 የተመዘገበው የማራቶን የዓለም ክብረወሰን የስፖርት ታሪኩን የሚያስታውሱ ዋና ዋና ስኬቶች ናቸው።
ከሁሉም በላይ ግን የቴርጋት ታሪክ የሚያስተምረን ስኬት በድል ብቻ እንደማይገለጽ ነው። ጽናት፣ ተግሣጽ፣ የረጅም ጊዜ ዝግጅትና ከውድድር ሜዳ ባሻገር ለሰዎች የሚደረግ አስተዋጽኦ አንድን ሻምፒዮን በታሪክ ውስጥ የሚያኖሩ እሴቶች ናቸው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#paultergat #hailegebrselassie #athletics #marathon #kenya #ethiopia #worldathletics #getutemesgen #ጌጡተመስገን

3 hours ago
#assosauniversity
በ2019 ዓ.ም አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ወደ 1ኛ ዓመት ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 16 እና 17/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
@tikvahuniversity

4 hours ago
ካፒታል ሆቴል እና ሆሴ ሪል እስቴት ለሜቄዶንያ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) መስከረም 29 "የካፒታል ሆቴል ቀን" ተብሎ መሰየሙን የሜቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር ገልጿል።
ካፒታል ሆቴል ከሆሴ ሪል እስቴት ጋር በመተባበር ለማህበሩ በጥሬ ገንዘብ እና በዓይነት በአጠቃላይ የ4.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን የሜቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር አስታውቋል።
የካፒታል ሆቴል ዋና ስራ አስኪያጅ አ/ቶ ተስፉ ፍፅም እንደገለጹት፤ ሆቴሉ በጥሬ ገንዘብ አንድ ሚሊዮን ብር እንዲሁም በዓይነት 1.5 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።
በተጨማሪም ሆሴ ሪል እስቴት የ2 ሚሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 4.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል ።
ከዚህ በተጨማሪም ከ350 በላይ የሚሆኑ የካፒታል ሆቴል ሰራተኞች እና አስተዳደር አባላት ከደመወዛቸው በመለገስ ማህበሩን ለመደገፍ ቃል ገብተዋል ።
የሜቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች ቢንያም በለጠ በበኩላቸው፣ ተቋማቱ እና ሰራተኞቻቸው ላደረጉት ቀጣይነት ያለው አጋርነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ማህበሩ ቋሚ የውጭ ፈንድ ወይም ገቢ የለውም ያሉት መስራቹ ከ9 ሺህ በላይ ሰዎችን ለመመገብና ለመንከባከብ የሁሉም አጋርነት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

5 hours ago
ቤትና መኪና የሚያስገኝ ሎተሪ ደርሶናል በማለት የማታለል ወንጀል የፈፀሙ 3 ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ ተያዙ።
አርሴማ ማስረሻ፣ ታደሰ ነሪ እና ዮሴፍ ተሾመ የተባሉት ተጠርጣሪዎች የማታለል ወንጀሉን ፈፅመው በቁጥጥር ስር የዋሉት በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ቤቴል አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን ለመፈፀም አስበው በተከራዩት የሰሌዳ ቁጥር ኮድ3A-73299 አ.አ የሆነ ቪቲዝ መኪና እየተንቀሳቀሱ እያለ የግል ተበዳይ የቀበሌ መታወቂያ ለማሳደስ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር በሚሄዱበት አጋጣሚ ያገኟቸዋል።
ከሦስቱ ተጠርጣሪዎች መካከል ታደሰ ነሪ የተባለው ግለሰብ ቤትና መኪና የሚያስገኝ ሎተሪ ቢደርሰውም በቅርቡ ከክፍለ ሃገር ስለመጣ የአዲስ አበባ ከተማ መታወቂያ እንደሌለውና ጉዳዩን ለማስጨረስ የግል ተበዳይን እርዳታ እንደሚፈልግ በመናገር አታለው መኪና ውስጥ ያስገቧቸዋል።
ግለሰቦቹ ለ3 ሠዓታት ያህል የግል ተበዳይን በተለያዩ ቦታዎች ሲያዞሯቸውና ሲያንገላቷቸው ከቆዩ በኃላ የተለያዩ የማሳመኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ለጉዳዩ ማስጨረሻ በሚል ማታለያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና እናት ባንክ 100 ሺህ ብር አውጥተው ለተጠርጣሪዎቹ ይሰጧቸዋል።
በዚህ የማታለል ወንጀል ያላበቃው የተጠርጣሪዎቹ ተግባር ቤቴል ወረዳ 6 አካባቢ ከሚገኝ የአንድ ግለሰብ ህንፃ አጠገብ ሲደርሱ በሎተሪ የደረሳቸውን ቤትና መኪና መውሰድ የሚችሉት በዚህ ህንፃ ቢሮ ውስጥ መሆኑንና ገብተው እንዲያስጨርሱላቸው ካሳመኗቸው በኃላ ቢሮ ውስጥ ሲገቡ የወርቅ ጌጣጌጥና ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት እንደማይቻል፤ ጉዳዩን አስጨርሰው እስከሚመጡ ድረስ የግል ተበዳይ ንብረት በእነሱ እጅ እንዲቆይ ያደርጋሉ።
የግል ተበዳይም 220 ሺህ ብር የሚያወጣ 11 ግራም የአንገት ሃብልና የጆሮ ጌጥ ወርቅ እንዲሁም 17 ሺህ ብር የሚገመት ሳምሰንግ ሞባይል ስልክ በአጠቃላይ 337 ሺህ ብር ግምት ያለው ንብረት ለተጠርጣሪዎቹ አስረክበው ቤትና መኪና የደረሰን ሎተሪ በሚል በትንሽ ካኪ ወረቀት ውስጥ የታሸገ 75 ሺህ ብር የሚል ፅሁፍ ያለው የተፋቀ የፈጣን ሎተሪ ወረቀት ሰጥተዋቸው ከመኪናው እንዲወርዱ ካደረጉ በኃላ የግል ተበዳይን ንብረት ይዘው ለማምለጥ ሲሞክሩ በፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የቤቴል አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅትም ሴት ተጠርጣሪዋ የማታለል ወንጀሉን ለመፈፀም በአርቴፊሻል ፀጉር እራሷን እንደምትቀያይር የግል ተበዳይ የሰጡት ቃልና የምርመራ መዝገቡ እንደሚያስረዳ ፖሊስ መምሪያው ገልጿል።
ወንጀል ፈፃሚዎች የተለያዩ የማታለያ ዘዴዎችን በመጠቀምና የሰዎችን እንቅስቃሴ በመከታተል መሰል ወንጀል ሊፈፅሙ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ወንጀል ከተፈፀመም በአፋጣኝ ለፖሊስ ማሳወቅ ተገቢ መሆኑን በመልዕክቱ አስተላልፏል።

#bulehorauniversity
በ2019 ዓ.ም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ወደ 1ኛ ዓመት ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 16 እና 17/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
@tikvahuniversity
በ2019 ዓ.ም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ወደ 1ኛ ዓመት ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 16 እና 17/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
@tikvahuniversity
6 hours ago
7ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር “ንቁ ዜጋ ደህንነቷ ለተጠበቀ ሀገር” በሚል መሪ ቃል ይከበራል
አዲስ አበባ፡ መስከረም 29/2019 ዓ.ም “ንቁ ዜጋ ደህንነቷ ለተጠበቀ ሀገር” በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ አንድ ወር የሚከበረውን 7ኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር አስመልክቶ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ።
ከጥቅምት 1 እስከ 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በሚቆየው በዚህ ሀገራዊ መርሃ ግብር ላይ በሀገራችን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት በፍጥነት ማደጉን ተከትሎ በዜጎች፣ በተቋማት እና ቁልፍ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣትቱን ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሯ አክለው እንደገለጹት በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገራችን ደረጃ የሳይበር ጥቃት መጠንና የሚያስከትለው ጉዳት በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ይገኛል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ዓመታዊ የኢኮኖሚ ኪሳራው ከ9.5 እስከ 10.5 ትሪሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ በኢትዮጵያም የጥቃት ሙከራው ከአመት ወደ አመት እያደገ መጥቶ በ2018 በጀት አመት ብቻ ከ71 ሺህ በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን አንስተዋል።
በመሆኑም ወሩ የተቋማትን እና የኅብረተሰቡን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና በማጎልበት፣ ለጉዳዩ ተገቢ ትኩረት እንዲሰጡ እና ራሳቸውን ከሳይበር ጥቃት መከላከል እንዲችሉ ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አጽንኦት ሰጥተዋል።
የዘንድሮው የሳይበር ደህንነት ወር በዋናነት የህጻናት የበይነ-መረብ ጥብቃ (Child Online Safety) ላይ ትኩረት አድርጎ ይከናወናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ ከዚህም ባሻገር የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የሳይበር ደህንነት (AI & Cybersecurity) ፣ በዲጂታል 2030 ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ዝግጁነት፣ እንዲሁም የቁልፍ መሠረተ ልማትና ተቋማት የሳይበር ደህንነት ዝግጁነት ማሳደግ የሚሉ ቁልፍ አጀንዳዎች መካተታቸዉን ጠቁመዋል።
በወሩ ውስጥ የሚከናወኑ ዋና ዋና መርሃ ግብሮችን በተመለከተ፤ የመክፈቻ መርሃ ግብር ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም በኢመደአ ዋና መሥሪያ ቤት የሚካሄድ ሲሆን፤ በዕለቱም “የህጻናት የበይነ-መረብ ጥብቃ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የተሰራ ሀገራዊ ጥናት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ ወ/ሮ ትዕግስት ተናግረዋል።
በወሩ ታዳጊዎችንና ወጣቶችን የሚያሳትፍ Catch the Flag (CTF) ውድድር የሚካሄድ ሲሆን የሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ደግሞ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የሳይበር ደህንነት ላይ ትኩረት በማድረግ ከአዲስ አበባ ውጪ በአንድ የሀገራችን ክልል ላይ የውይይት መድረክ ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የጥቅምት ወርን ሙሉ የሕብረተሰቡን እና የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና የሚያጎለብቱ የሚዲያ ንቅናቄ ሥራዎች በስፋት ይሰራሉ።
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ የሳይበር ደህንነት ክበባትን ለማበረታታት ሥራዎች የሚሰሩ ሲሆን፤ ዜጎች ስለሳይበር ደኅንነት ያላቸውን ግንዛቤ እየተፈተኑ የተለያዩ ሽልማቶችን የሚያገኙባቸው እና ከፍተኛ ሽልማት የሚያስገኙ የማህበራዊ ሚዲያ ንቅናቄና የአጭር ፊልም ውድድሮች መዘጋጀታቸዉን በመግለጫቸዉ አንስተዋል።
በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተሯ ኢመደአ የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነት የማስጠበቅ የመሪነት ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸው፤ የመንግስትና የግል ተቋማት የሳይበር ደህንነትን የማረጋገጥ ሥራ የሁሉንም የጋራ ኃላፊነት የሚጠይቅ በመሆኑ የጥቅምት ወርን የሰራተኞቻቸውን ንቃተ-ህሊና በሚያሳድጉ መልኩ እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል። እንዲሁም የሚዲያ አካላት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥተው ግንዛቤ እንዲፈጥሩ አሳስበዋል።
የሳይበር ደህንነት ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ23ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ7ኛ ጊዜ መከበሩ ተመላክቷል።
#7ncsm

8 hours ago
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም ወደ ታሪካዊ ስፍራው ተመልሶ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የተቋሙ መነሻ እና ታሪካዊ ስፍራ የሆነው ብሔራዊ ፓስታ ሙዚየም ወደ ቀድሞው እና ታሪካዊ ቦታው ተመልሶ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን መደረጉን አስታውቋል፡፡
ተቋሙ ይህንን ያስታወቀው በዛሬው ዕለት መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም " አንድ የፖስታ አውታረ መረብ ገደብ የለሽ ዕድሎች " በሚል መሪ ቃል የዓለም የፖስታ ቀንን ባከበረበት ወቅት ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖስት ሙዚየም በዋናው የፖስታ አገልግሎት ተቋም ውስጥ ከ50 ዓመታት በላይ አገልግሎት ሲሰጥና ታሪካዊ ነገሮችን ለጎብኚዎች ሲያስተዋውቅ እንደነበር የኢትዮጵያ ፖስታ የአቅርቦትና አስተዳደር ሃላፊ አ/ቶ ጋሻው መርሻ ተናግረዋል።
በተለይም ከዛሬ ጀምሮ ክፍት የተደረገው ይህ የብሔራዊ ፖስታ ሙዚየም ለተማሪዎች ፣ ለተመራማሪዎች እንዲሁም ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ አገር ጎብኝዎች ምቹ በሆነ ሁኔታ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን አብራርተዋል።
የማሻሻያ ስራው የታሪክ ቁሳቁሶችን እና የቴምብር ስብስቦችን ለጎብኚዎች በጥራት ለማቅረብ እንዲሁም የዲጂታል እና የተቋሙ ሀብቶችን በጥቅም ላይ በማዋል ዘመናዊ እና ምቹ አከባቢን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ገልፀዋል።
ታሪክን ጠብቆ ማቆየትና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የተቋሙ ትልቅ ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው ተቋሙ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን የተደረገው በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት እምብርት እና የሀገሪቱ የመገናኛ ታሪክ የጀመረበት ትልቅ ታሪካዊ ቦታ ላይ ነው ብለዋል።
በተመስገን ተጋፋው

ራሚስ ባንክ በኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ባለስልጣን የምዝገባ ፈቃድ አገኘ
👉ራሚስ ባንከ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ታሪከ አዲስ ምዕራፍ የከፈተለትን ታላቅ ስኬት በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል
በይፋ አብስሯል፡፡
ባንኩ በነባር ባለአክስዮኖች ተይዘው የሚገኙ 2 ሚልየን 101ሺ 106 አክስዮኖች በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ECMA) በይፋ መመዝገባቸውና የምዝገባ መግለጫው በመጽደቁ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) ዋና ገጽ ላይ ለመመዝገብ ያቀረበው ማመልከቻ ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።
ይህ ታሪካዊ ስኬት ራሚስ ባንክ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ታሪክ ውስጥ በ ESX ዋና ገጽ ለመመዝገብ የመርህ ደረጃ ፈቃድ ካገኙት ከመጀመሪያዎቹ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አንዱ አድርጎታል።
የራሚስ ባንከ የዳይሬከተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ራቢ ሼክ ሁሴን፥ ባንኩ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በፅኑ የሸሪዓ መርሆች፣ በግልጽነት እና በጠንካራ ተቋማዊ አስተዳደር ላይ በመቆም የህብረተሰቡን እምነት ያተረፈ ሲሆን፣ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርሙን በመጠቀም በምስራቅ አፍሪካ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ዋና ማዕከል የመሆን ታላቅ ሀገራዊ ግቡን ለማሳካት በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ማለታቸውን ብስራት ሰምቷል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሊ እንደገለጹት ይህ በካፒታል ገበያ ባለስልጣን የተሰጠው የምዝገባ ፈቃድ የራሚስ ባንክን የፋይናንስ ጥንካሬ፣ የኮርፖሬት አስተዳደር ብቃት እና ተቋማዊ አስተማማኝነት በግልጽ ያረጋገጠ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልፀዋል።
ሰላማዊ ነጋሲ

9 hours ago
#wolkiteuniversity
በ2019 ዓ.ም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ወደ 1ኛ ዓመት ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
@tikvahuniversity
በ2019 ዓ.ም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ወደ 1ኛ ዓመት ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
@tikvahuniversity
Sponsored by
Surafel
10 hours ago
ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ የሴንቸሪ ሪልስቴት የብራንድ አምባሳደር ሆነ
ሴንቸሪ ሪልስቴት በተለያዩ የልማት ዘርፎች ያለውን ተሳትፎ ለማጠናከርና አዳዲስ የሥራ አጋርነቶችን ለመፍጠር የድምፃዊ ዳዊት ጽጌን የብራንድ አምባሳደርነት በይፋ አስታውቋል።
የሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተፈራ ለማ እንደገለፁት ድርጅቱ በሪልስቴት፣ በኮንስትራክሽን ግብዓት፣ በብረታ ብረት፣ በኬሚካልና በማዕድን ዘርፎች በመሰማራት ለሀገራዊ ልማት አስተዋፅዖ እያደረገ ይገኛል።
በተለይም ባለፉት 10 ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ ዘመናዊ የመኖሪያ፣ የንግድና የቢሮ ሕንፃዎችን በመገንባት በሪልስቴት ዘርፍ የራሱን አሻራ ማሳረፉን ተገልጿል።
ኩባንያው በቀጣይም በኦሊምፒያ የሚገነባውን ሴንቸሪ ኦሊምፒያ፣ በሜክሲኮ አደባባይ የሚገኘውን ቫልዩ ፕሮጀክት፣ ሜጋ ፒኮክ ኦፊስ ኮምፕሌክስን እንዲሁም በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የሚገነቡ ዘመናዊ አፓርትመንቶችን በትኩረት እንደሚያስቀጥል አስታውቋል።
ከ70 ዓመታት በላይ የንግድ ልምድ ያለው ሴንቸሪ በተለያዩ የኢንዱስትሪና የልማት ዘርፎች ከ30 ዓመታት በላይ ሲሠራ ቆይቷል።
ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ ኩባንያው ከሪልስቴት ሥራው ባሻገር በማኅበራዊ ኃላፊነትና በበጎ አድራጎት ሥራዎች የሚያደርገውን ተሳትፎ በመመልከት ከድርጅቱ ጋር ለመሥራት መስማማቱን ገልጿል።ሴንቸሪ ሪል እስቴት ያከናወናቸውን ሥራዎችና የወደፊት ዕቅዶቹን ለማስቀጠል “ደሞ በዚህ ላይ... ሥራዎቻችን ምስክሮቻችን!” በሚል መሪ ቃል አዲስ ዘመቻ መጀመሩም በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

11 hours ago
ራሚስ ባንክ 2 ሚሊዮን በላይ አክስዮኖቹን በካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አስመዘገበ!
ራሚስ ባንክ በነባር ባለአክስዮኖች ተይዘው የሚገኙ 2 ሚሊዮን 101 ሺህ 106 አክስዮኖች በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በይፋ መመዝገባቸውን እና የምዝገባ መግለጫው መጽደቁን ገልጿል።
በተጨማሪም ባንኩ በኢትዮጵያ የሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ (ESX) ዋና ገጽ ላይ ለመመዝገብ ያቀረበው ማመልከቻ የመርህ ደረጃ ፈቃድ ማግኘቱን አመልክቷል። ይህ ስኬት ራሚስ ባንክ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ታሪክ ውስጥ በ ESX ዋና ገጽ ለመመዝገብ የመርህ ደረጃ ፈቃድ ካገኙት ከመጀመሪያዎቹ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አንዱ አድርጎታል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሊ እንደገለጹት፣ ይህ የምዝገባ ማጽደቅና የመርህ ደረጃ ፈቃድ የባንኩን የፋይናንስ ጥንካሬ እና ተቋማዊ አስተማማኝነት አረጋግጧል። በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ራቢ ሼክ ሁሴንም በበኩላቸው፣ ተቋሙ በጠንካራ ተቋማዊ አስተዳደር ላይ በመቆም በምሥራቅ አፍሪካ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ዋና ማዕከል የመሆን ግቡን ለማሳካት በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።
Via Capital
@YeneTube FikerAssefa

ሴንቸሪ ሪልስቴት ድምፃዊ ዳዊት ጽጌን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሰየመ
መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሪል እስቴትና በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ያከናወናቸውን ሥራዎችና ዕቅዶች ይፋ አድርጓል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ አዲስ የብራንድ አምባሳደር ስምምነት ከድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ጋር ተፈራርሟል ።
የሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተፈራ ለማ ሴንቸሪ በሪል እስቴትና በኮንስትራክሽን ግብዓት፣ ብረታ ብረት፣ ኬሚካልና ማዕድን ዘርፎች ላይ በመስራት ለሀገራዊ ልማት አስተዋፅዖ ማድረጉን ገልጸዋል።
የሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከፍተኛ አማካሪና የቦርድ አባል ፕሮፌሰር አበበ ድንቁ በበኩላቸው፣ ተቋሙ ላለፉት 70 ዓመታት በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች መስራቱን ገልጸዋል።
የሴንቸሪ ሪል እስቴት ዋና ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር አቶ ፈለቀ ሹሜ፣ ድርጅቱ ላለፉት 10 ዓመታት በአዲስ አበባ ለመኖሪያ፣ ለንግድና ለቢሮ የሚውሉ ሕንፃዎችን መገንባቱን ገልጸዋል። የግንባታ ግብዓቶችን በራሱ ማምረቱ የተለየ ጥቅም እንደሚሰጠው ጠቁመዋል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ ሴንቸሪ ሪል እስቴት የድምፃዊ ዳዊት ጽጌን ብራንድ አምባሳደር በማድረግ “ደግሞ በዚህ ላይ... ሥራዎቻችን ምስክሮቻችን!” በሚል አዲስ ዘመቻ መጀመሩ ተገልጿል።
ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ በበኩሉ፣ ድርጅቱ በሪል እስቴት ዘርፍ ከሚያከናውነው ሥራ ባሻገር በማህበራዊ ኃላፊነትና በበጎ አድራጎት ሥራዎች የሚያደርገውን ተሳትፎ በመመልከት ከሴንቸሪ ሪል እስቴት ጋር ለመስራት መስማማቱን ገልጿል።
በቃልኪዳን ኃይሌ

12 hours ago
#injibarauniversity
በ2019 ዓ.ም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ወደ 1ኛ ዓመት ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 12 እና 13/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ፣
● አንሶላ፣ የለሊት ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
በ2019 ዓ.ም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ትምህርት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ወደፊት በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

14 hours ago
ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈቼ የሚወስደው መንገድ ለሁለት ቀናት ይዘጋል ተባለ
በአዲስ አበባ ከጎሮ አደባባይ በኮዬ ፈቼ በኩል ወደ ቱሉ ድምቱ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለሁለት ቀናት ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።
በመንገዱ ላይ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር መሠረተ ልማት ሥራ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የመሬት ውስጥ የሚቀበሩ መሠረተ ልማቶችን ለመዘርጋት የዋናው አስፋልት መንገድ ክፍል ተቋርጧል።
በመሆኑም ከዛሬ መስከረም 28 እስከ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈቼ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች በጎሮ–ቦሌ ኤርፖርት መንገድ አቅጣጫ በመጓዝ በቡልቡላ በኩል ወደ ኮዬ ፈቼና አካባቢው ሊጓዙ ይገባል ተብሏል።
እንዲሁም ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ አደባባይ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች ከኮዬ ፈቼ አደባባይ በቡልቡላ በኩል ወደ ጎሮ አደባባይ የሚወስደውን የቦሌ ኤርፖርት–ጎሮ አዲስ መንገድን ጨምሮ ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ባለሥልጣኑ አሳስቧል።
አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ የተመላላሽ መንገዶችን ሊጠቀሙ ይገባል ሲሉየባለሥልጣኑ ምክትል ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
@Yenetube Fikerassefa

23 hours ago

Seledadotio

" በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም " - ጌዲዮን ጤሞቲዮስ (ዶ/ር)
👉 " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም ! "
ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በመግለጽ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) በደብዳቤ አሳወቀች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ (ዶ/ር) ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት ደብዳቤ መጻፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በዚህም ደብዳቤ፤ የኤርትራ ሠራዊት ድንበር አልፎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በሁለት የተለያዩ ጊዜያት ለፀጥታው ም/ቤት አባላት በላከችው ደብዳቤ " ኤርትራ በተደጋጋሚ በፈጸመችው ጸብ አጫሪነት እና ድንበር ጥሶ የመግባት እርምጃ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ አደጋ መደቀኑን " በመጥቀስ ትኩረት እንዲሰጠው መጠየቃቸውን አስታውሰዋል።
" ኤርትራ የፀብ አጫሪነት ድርጊቷን በአሁኑ ጊዜ ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግራ ሜካናይዝድ ክፍሎችን ጨምሮ ወታደሮቿን በጥልቀት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት አሰማርታለች " ያሉት ጌዲዮን (ዶ/ር) ፥ " ይህም ሦስት የትግራይ ዞኖችን በማካተት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከ30 አስከ 60 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ርቀት ወደ ውስጥ ገብተዋል " ብለዋል።
ሚኒስትር ጌዲዮን የኤርትራ ድርጊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ውስጥ የሰፈሩትን መሠረታዊ መርሆዎች በግልጽ የሚጥስ ነው በማለት " ይህም ኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል ሕጋዊ መብት እንድትጠቀም የሚያስገድድ ነው " ሲሉ ጽፈዋል።
ለፀጥታው ም/ቤት የጻፉት ደብዳቤ የተፈጸመውን ወረራ ለማሳወቅ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ለምትወስደው የመከላከል እርምጃ ድጋፍ ጠይቀዋል።
" በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም " በማለት ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ የገጠማትን ሁኔታ በመረዳት ድጋፍ እንዲደያርግላት እና ከጎኗ እንዲቆም ጠይቀዋል።
ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራ በኩል ለረዥም ጊዜ ሲፈጸሙ ለነበሩ ትንኮሳዎች በትዕግሥት እና ራስን በመቆጠብ መቆየቷን አመልክተዋል።
በመሆኑም " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም " ብለዋል።
" ኤርትራ ወራሪ ናት፤ ኢትዮጵያ ደግሞ የወረራ ሰለባ ናት። ኤርትራ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እየጣሰች ነው " ሲሉም አሳውቀዋል።
ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌላትም ገልጸዋል።
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሕግን መሠረት በማድረግ ሉዓላዊነቷ እና የግዛት አንድነቷን የመከላከልና የማስጠበቅ ሕጋዊ መብት እንዳላት አሳወቀች። የተባበሩት መንግስታት (UN) ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና ጄን ሙሀመድ አዲስ አበባ ይገኛሉ። ዛሬ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው መክረዋል። ሚኒስትሩ፥ ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ እየፈጸመች ስላለው ቀጣይነት ያለው የጠብ አጫሪነት ተግባና…
👉 " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም ! "
ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በመግለጽ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) በደብዳቤ አሳወቀች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ (ዶ/ር) ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት ደብዳቤ መጻፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በዚህም ደብዳቤ፤ የኤርትራ ሠራዊት ድንበር አልፎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በሁለት የተለያዩ ጊዜያት ለፀጥታው ም/ቤት አባላት በላከችው ደብዳቤ " ኤርትራ በተደጋጋሚ በፈጸመችው ጸብ አጫሪነት እና ድንበር ጥሶ የመግባት እርምጃ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ አደጋ መደቀኑን " በመጥቀስ ትኩረት እንዲሰጠው መጠየቃቸውን አስታውሰዋል።
" ኤርትራ የፀብ አጫሪነት ድርጊቷን በአሁኑ ጊዜ ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግራ ሜካናይዝድ ክፍሎችን ጨምሮ ወታደሮቿን በጥልቀት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት አሰማርታለች " ያሉት ጌዲዮን (ዶ/ር) ፥ " ይህም ሦስት የትግራይ ዞኖችን በማካተት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከ30 አስከ 60 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ርቀት ወደ ውስጥ ገብተዋል " ብለዋል።
ሚኒስትር ጌዲዮን የኤርትራ ድርጊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ውስጥ የሰፈሩትን መሠረታዊ መርሆዎች በግልጽ የሚጥስ ነው በማለት " ይህም ኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል ሕጋዊ መብት እንድትጠቀም የሚያስገድድ ነው " ሲሉ ጽፈዋል።
ለፀጥታው ም/ቤት የጻፉት ደብዳቤ የተፈጸመውን ወረራ ለማሳወቅ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ለምትወስደው የመከላከል እርምጃ ድጋፍ ጠይቀዋል።
" በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም " በማለት ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ የገጠማትን ሁኔታ በመረዳት ድጋፍ እንዲደያርግላት እና ከጎኗ እንዲቆም ጠይቀዋል።
ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራ በኩል ለረዥም ጊዜ ሲፈጸሙ ለነበሩ ትንኮሳዎች በትዕግሥት እና ራስን በመቆጠብ መቆየቷን አመልክተዋል።
በመሆኑም " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም " ብለዋል።
" ኤርትራ ወራሪ ናት፤ ኢትዮጵያ ደግሞ የወረራ ሰለባ ናት። ኤርትራ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እየጣሰች ነው " ሲሉም አሳውቀዋል።
ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌላትም ገልጸዋል።
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
24 hours ago
በናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት የተመራው ልዑክ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎበኘ
*****************
በናይጄሪያው ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ የተመራው ከፍተኛ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ አድርጓል፡፡
ከፍተኛ ልዑኩ በኦሮሚያ ክልል ያደረገው የመስክ ምልከታና የልምድ ልውውጥ ከስንዴ ክላስተር እስከ ማኑፋክቸሪንግ ባሉ ስትራቴጂካዊ የልማት መስኮች ላይ ያተኮረ እንደነበረ ተገልጿል፡፡
ልዑኩ በጉብኝቱ የኩቃ ዓሳ እርባታና የሉሚ እርሻ ኩርፊሳ ፕሮጀክትን፣ የ'ባሃሪ' አትክልት ልማት ኢኒሼቲቪን እንዲሁም የጃቡዱ ሞተርስ የጋራ አክሲዮን ኩባንያ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጉብኝቱ በከተሞች መስፋፋት፣ በግብርናና ገጠር ሽግግር፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ዙሪያ ያተኮረ እንደነበር ገልጸዋል።
በክልሉ የተካሄዱት የመስክ ምልከታዎችም የግብርና ሽግግር እንቅስቃሴና የሕዝቡን የኑሮ ለውጥ በተግባር ያሳዩ እንደነበርም ጠቁመዋል።
በክልሉ ግብርናን ማዘመን የኢኮኖሚ ሽግግር መነሻ እንጂ የመጨረሻ ግብ አይደለም ያሉት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ ዋናው ዓላማ ሕዝቡን ከልማት ተመልካችነት ወደ ለውጥ ባለቤትነት ያሸጋገረ፣ ሀብት የሚያፈራና የተመጣጠነ ምግብ የሚያገኝ አምራች ገበሬ መገንባት መሆኑን አብራርተዋል።
በልዩ እሸቱ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #nigeria #agriculture

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሱዳኑ አልሂላል ክለብ ወደኢትዮጵያ ለሚያደርገው ጉዞ ‹‹የደህንነት ዋስትና›› ጠየቀ፡፡ የሱዳኑ አል ሂላል ኦምድሩማን ክለብ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ግጥሚያ ከሲዳማ ቡና ጋር የሚጫወት መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይህ ግጥሚያ አንድ ሳምንት የቀረው መሆኑን ተከትሎ ክለቡ ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) አስቸኳይ ደብዳቤ ፅፏል፡፡ ‹‹ይድረስ ለካፍ የደህንነትና ፀጥታ ሀላፊ›› በሚል የተፃፈው ይህ ደብዳቤ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ስላለው የፀጥታ ችግር ቀጥተኛና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ከሚገኙ መረጃዎች ለማወቅ እንደተቻለ ጠቅሶ ጉዳዩ እንዳሳሰበው ይገልፃል፡፡ በክለቡ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዋና ፀሀፊ ዶክተር ሀሰን አሊ ኢሳ አማካኝነት የተፃፈው ይህ ደብዳቤ ሲቀጥልም ‹‹የአል ሂላል ቡድን አባላት ወደኢትዮጵያ ለመጓዝ ዝግጅት እያደረጉ በመሆኑ ለአባሎቻችን ደህንነትና ጥበቃ ቅድሚያ የምንሰጥ መሆኑን ለማስታወቅ እንወዳለን›› ካለ በኋላ ካፍ ከደህንነትና ሎጅስቲክስ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ለሚከተሉት ነጥቦች አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ ከእነዚህ ነጥቦች የመጀመሪያው የክለቡ አባላት ወደኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የአውሮፕላን ጉዞ ደህንነት ምን አይነት ዋስትና ተዘጋጅቷል? የሚል ነው፡፡
ይህ ጥያቄም የቡድኑን አዲስ አበባ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረስንና ከዚያም ጨዋታው ወደሚካሄድበት ድሬደዋ ከተማ የሚካሄደውን የአገር ውስጥ በረራ እንደሚያካትት አስረድቷል፡፡ ሁለተኛው ጥያቄ የአል ሂላል ቡድን አባላት አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ ድሬዳዋ እስከሚሄዱ ድረስ ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ምን አይነት ዝግጅት ተደርጓል? የሚል ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ ልኡካን ቡድኑ በድሬዳዋ ቆይታው በማረፊያውና ልምምድ በሚያደርግበት ቦታ ምን አይነት የደህንነት ጥበቃ ይደረጋል? የሚል ነው፡፡ በአራተኛነት ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የክለቡ ተጨዋቾች፣ የቴክኒክና የአስተዳደር ቡድን አባላቱ በሰላም ወደኪጋሊ እንዲመለሱ ለማስቻል የተደረገው ዝግጅት እንዲገለፅለት ጠይቋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት (UN) ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና ጄን ሙሀመድ አዲስ አበባ ይገኛሉ። ዛሬ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው መክረዋል።
ሚኒስትሩ፥ ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ እየፈጸመች ስላለው ቀጣይነት ያለው የጠብ አጫሪነት ተግባና ይህም በቀጠናው ሰላምና ጸጥታ ላይ ሊያስከትለው ስለሚችለው አደጋ ጥልቅ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ለጉዳዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግልጽና መርህን የጠበቀ አቋም ይዞ አስቸኳይ ምላሽ ሊሰጥበት እንደሚገባ ጌዲዮን (ዶ/ር) አጽንኦት ሰጥተዋል።
የኤርትራ ወታደራዊ ኃይሎች ከኢትዮጵያ ግዛት በአስቸኳይ እንዲወጡም አስጠንቅቀዋል።
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሕግን መሠረት በማድረግ ሉዓላዊነቷን እና የግዛት አንድነቷን የመከላከልና የማስጠበቅ ሕጋዊ መብት እንዳላት አረጋግጠዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia Photo
1 day ago
🚨 «"መላውን የትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ለማዋል ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ የሚገኙ ሦስት ከተሞች ብቻ ቀርተዋል" — ጃዋር መሐመድ»
የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊትና የትግራይ የሰላም ኃይል መላውን ክልል ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ለማዋል ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ የሚገኙ ሦስት ከተሞች ብቻ እንደቀሯቸው ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ ገለጹ።
🔹 ዋና ዋና ነጥቦች፦
የቀሩ ከተሞች፦ ሠራዊቱ ክልሉን ሙሉ በሙሉ በእጁ ለማስገባት የቀሩት አክሱም፣ ዓድዋ እና ዓዲግራት ከተሞች ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።
የኃይሎች ማፈግፈግ፦ የህወሓትና የኤርትራ ኃይሎች በድንበር አካባቢ ኃይላቸውን መልሰው ለማደራጀት ወደ ኋላ እያፈገፈጉ እንደሚገኙ ተጠቅሷል።
የቀጣይ ሂደት አቅጣጫ፦ ከዚህ በኋላ ያለው ሂደት የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ውሳኔ የሚጠይቅ እንደሚሆን የጠቆሙት ጃዋር መሐመድ፣ ጄነራሎቹና ወታደሮቻቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ በስኬት ለማጠናቀቅ በቂ ዝግጅት እንዳላቸው በተግባር ማሳየታቸውን አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊሆን አይችልም!
*******************
ከጥንታዊቷ እስከ ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ቀይ ባህር የግዛቷ አካል ሆኖ መርከቦቿ ሲጠቀሙበት የኖሩ ሲሆን ጥንታዊት ኢትዮጵያን በአለም ላይ ከነበሩት ታላላቅ ሀይሎች አንዷ እንድትሆን ያደረጓት በወቅቱ ታስተዳድራቸው የነበሩት ወደቦቿ፣ የንግድ ትስስሮቿ እና "ባህረ ነጋሽ" የሚለው የማእረግ መጠሪያ ስያሜ እንደነበሩ ይታወቃል።
ሆኖም ሀገራችን በታሪክ አጋጣሚዎች እና በተደረጉባት እኩይ ሴራዎች ምክንያት ከሶስት አስርት አመታት በላይ የባህር በር አልባ ሆና በመቆየቷ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ የጂኦ ፖለቲካ እና የብሄራዊ ደህንነት ማነቆዎች ተዳርጋ ኖራለች።
በተባበሩት መንግስታት የንግድና ልማት ጉባኤ መረጃ መሰረትም የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከአለም አማካይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ወጪ በላይ ተጨማሪ ክፍያ ለማውጣት የሚገደዱ በመሆኑ ይህ ተፅእኖ በዜጎች እለታዊ የሸመታ አቅም፣ በሀገራችን የኢንቨስትመንት እድሎች እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዲጂታል መረጃ በሚያስተላልፉት ከባህር በታች ያሉ የፋይበር ኦፕቲክስ መስመሮች ተጠቃሚነት ላይ ከፍተኛ ጫና ሲፈጥር ቆይቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግስት ምስረታ ወቅት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደገለፁት የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን ሊሆን አይችልም፡፡
በመሆኑም በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት አጥብቀን እንሰራለን ያሉም ሲሆን፤ ይህንን ታሪካዊ ስህተት እና የትውልድ ቁጭት ለመቅረፍ "የመደመር መንግስት" የባህር በር ጥያቄን ከወቅታዊ ፖለቲካ እና ከፓርቲ ወገንተኝነት በላይ በሆነ ትውልድ ተሻጋሪ ብሄራዊ አጀንዳ አድርጎ እንደሚሰራበት ተናግረዋል።
የመደመር መንግስት በያዘዉ ጠንካራ አቋም የኢትዮጵያ ስልጣኔና እድገት ያለ ባህር በር እውን ሊሆን ስለማይችል ሀገራችን በሰጥቶ መቀበል በጋራ ተጠቃሚነት እና በሰላማዊ ዲፕሎማሲ መርህ ወደ አለም የምትወጣበትን መስመር የማረጋገጥ ጉዞዋ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
እውነተኛ ብሄራዊ ደህንነትና ሉአላዊነት የሚረጋገጠው ስትራቴጂካዊ ቁሳቁሶች ያለ ምንም የውጭ ጫና እገዳ ወይም የጎረቤት ሀገራት በጎ ፈቃድ በቀጥታ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ሲችሉ እንደመሆኑ መጠን ቀጥተኛ የባህር በር ማግኘት የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት እድሎችን በመክፈት የወጣቶችን ስራ አጥነት ከመቅረፉ ባሻገር ኢትዮጵያ በቀይ ባህር እና በስትራቴጂካዊ የውሃ አካላት ቀጠናዊ ውሳኔዎች ላይ ያላትን የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ተሰሚነት ከፍ ያደርገዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ አካል እንጂ ከሩቅ የመጣች እንግዳ እንዳልሆነችና በጂኦ ፖለቲካዊ ሴራዎች የባህር በር አልባ እንድትሆን መደረጓን ለአለም እያስረዳች ትገኛለች።
ኢትዮጵያ ቀይ ባህር ላይ እግሯን እንዳትተክል የሚደረጉ የተለያዩ የፖለቲካ የዲፕሎማሲ እና የፕሮፓጋንዳ ሸፍጦች አልቆሙም እነዚህን ሸፍጦች ሲጠነስሱ እንቅልፍ አጥተው የሚያድሩ አካላት መፍጨርጨራቸው ባይገታም ኢትዮጵያን በዘላቂነት ሊያግዷት አይችሉም።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም እና የአካባቢያዊ ትስስር ዋና ምሰሶ እንደመሆኗ የባህር በር ማግኘቷ ለአካባቢው ሀገራትም ቢሆን ትልቅ የኢኮኖሚ ጥቅም የሚያስገኝ በመሆኑ በቅርብም በሩቅም ያሉ ሀገራት ለኢትዮጵያ ቀና ምላሽ በመስጠት በጋራ መስራትን ተመራጭ ያደርጋሉ።
ፈጣን እድገት እያስመዘገበ ያለው ኢኮኖሚና ትልቅ ህዝብ ያላት ሀገር መሆኗም ይህን ግስጋሴ የሚያስተናግድ የባህር በር የማግኘት ትልሟን እውን ለማድረግ ትልቅ አቅም ይሆናታል።
በአጠቃላይ የታሪክ እውነታ የህግ መብት እና የህልውና ጥያቄ የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ አይቀሬ ያደርጉታል።
ይህንን አገራዊና ታሪካዊ ሀላፊነት ከግብ ለማድረስ የውስጥ አንድነትን ማፅናትና ደህንነትን ማረጋገጥ የሃሳብ ፖለቲካን ማጠናከር እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር ወሳኝ መፍትሄ ነው።
በአለም አቀፍ የባህር ህግጋት እና በዲፕሎማሲያዊ አማራጮች የታገዘው ይህ ጥረት የመጪውን ትውልድ መብትና እድል የማስከበር የታሪክ ጥሪም ሲሆን ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ ገንብቶ ለዘላቂ ብልፅግና የሚያሸጋግር ጨዋታ ቀያሪ ምእራፍ ነው።
ዛሬ ብርቱዋ ኢትዮጵያ ለሶስት አስርት አመታት ካቀረቀረችበት ቀና ብላለች የቀይ ባህር ተጋሪነቷን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ማናቸውም ሸፍጦች ጊዜያዊ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ እንጂ የህዝቧን የታሪክ እና የተፈጥሮ መብት ሊያጠፉ አይችሉም።
ኢትዮጵያ አትቆምም የጂኦ-ፖለቲካ ሴራዎችን ሁሉ በጣጥሳ ከባህሩ ትደርሳለች ባህር ሀይሏና መርከቦቿም በቀይ ባህር ዳግም ይጓዛሉ።
በብሌን ደምበሎ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #seaaccess #redsea #diplomacy

Tigray Region 📍
መቐለ
እስከ ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም. ባሉት ቀናት ውስጥ የመቐለ ከተማ መደበኛ የፖሊስ አባላት ወደ መደበኛ የሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
የመቐለ ከተማ ፖሊስ፣ አባላቱ በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ሪፖርት ካላደረጉ በራሳቸው ፍላጎት ከሥራ እንደለቀቁ እንደሚቆጠሩ አሳውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባገኘው መረጃ ዛሬ አንዳንድ ፖሊስ አባላት በቀረበው ጥሪ መሰረት ወደ ስራቸው ለመመለስ ሪፖርት ማድረግ መጀመራቸውን ተረድቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ መቐለ አሁን ላይ ካለፉት ቀናት በተሻለ መረጋጋት እና ወደ መደበኛው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እየገባች ትገኛለች።
ቃለቸውን የሰጡን ነዋሪዎች፤ የሚፈጸሙ ዝርፊያዎች እና የፀጥታ ስጋቶች በእጅጉ መሻሻል አሳይተዋል።
የሀገር መከላከያ እና የትግራይ ሰላም ኃይል እንቅስቃሴ
የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ የሰላም ኃይል የደቡባዊ እና ደቡብ ምስራቅ አካባቢዎችን ከተቆጣጠሩ በኋላ ወደ ሰሜናዊ ምዕራብ፣ ምስራቃዊ እና ማዕከላዊ ዞኖች አምርተዋል።
በማዕከላዊ ዞን ሶስተኛዋ ትልቅ ከተማ የሆነችው ዓብዪ ዓዲን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በኩል፥ የዞኑን መቀመጫ የሆነችው የእንዳስላሴ (ሽረ) ከተማን ለመቆጣጠር በቅርብ ርቀት ላይ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በምስራቃዊ ዞን የአጉላዕ እና ውቕሮ ከተሞችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ወደ ዞኑ ዋና መናገሻ ዓዲግራት ከተማ እያመሩ መሆኑ ተነግሯል።
የኤርትራ (ሻዕቢያ) ሰራዊት
የኤርትራ (ሻዕቢያ) ሰራዊት ወደ ኢትዮጵያ ምድር ትግራይ ክልል ዘልቆ መግባቱ ይታወቃል።
ኤጀንሲ ፋራንስፕሬስ (AFP) በርከታ ምንጮች የኤርትራ ወታደሮች ዓዲግራት ከተማ ዙሪያ መሰማራታቸውን እንደገለጹለት ዘግቧል።
የግጭት ክትትል ተቋም የሆነው ACLED ይፋ ባደረገው መረጃ፤ በዓዲግራት አካባቢ "የኤርትራ ወታደሮች" ላይ ያነጣጠሩ በርካታ የድሮን ጥቃቶች መፈጸማቸውንና ኃይሎቹ መመታታቸው ተገልጿል።
በስማቸው እንዳይገለጹ የጠየቁ የዓይን እማኞች ለAFP እንደተናገሩት፤ " ትናንት በርካታ የድሮን ጥቃቶች ነበሩ። የኤርትራ የጭነት መኪኖች ወድመዋል። ከዛ በኋላ በጎዳናዎች ላይ አልታዩም " ሲሉ አስረድተዋል።
ሌላው እማኝ በሌሊት ከፍተኛ ፍንዳታዎችን መስማቱን እና በድሮን ጥቃት የተመቱ የኤርትራ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን በአይኑ መመልከቱን ገልጿል።
ሦስተኛ እማኝ ደግሞ ከጥቃቶቹ በኋላ የኤርትራ ወታደሮች ወደ ሰሜን አቅጣጫ እያፈገፈጉ የሚመስል እንቅስቃሴ ላይ ናቸው ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ደግሞ " የሻዕቢያ ሰራዊት " በዛላንበሳ መስመር ማፈግፈጉን ጠቁመዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከርም 28 ቀን 2019 ዓ/ም

ዛሬ ሹመታቸውን የተቀበሉት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ ጋር ውይይት አደረጉ
#ethiopia | የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ጄን መሐመድ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።
ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸውም በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ የፀጥታ እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡
ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት ምክትል ዋና ፀሐፊዋ አሚና ጄን ሙሀመድ ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅድሚያ በሚሰጧቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ እንደሚመክሩ ተመላክቷል፡፡
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

#diredawauniversity
በ2019 ዓ.ም ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 07 እና 08/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣
● አንሶላ፣ የለሊት ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
በተለያዩ ምክንያት 1ኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ለመልሶ ቅበላ ጥቅምት 10 እና 11/2019 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

አዲስ የታሰረ የቃል ኪዳን ተስፋ በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር
****************
ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ማካሄዷን ተከትሎ፣ አዲሱ የመደመር መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ተመስርቷል።
ይህ ዕለት የኢትዮጵያ አዲስ የተስፋ አድማስ የተበሰረበትና የሕዝቡ ዲሞክራሲያዊ ውሳኔ ዕውን የሆነበት ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
አዲሱ የመደመር መንግሥት ምስረታ ላለፉት ዓመታት የተጣሉትን የዕድገትና የተስፋ መሠረቶች አጠናክሮ በማስቀጠል፣ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ያለመ ነው።
የመደመር እይታ ያለፉ ስኬቶችን በማስቀጠል፣ ክፍተቶችን በመሙላትና የቀጣይ ትውልድን ተስፋ በማገናኘት ሀገራዊ አንድነትንና ትብብርን ማዕከል ያደረገ አሰራርን ይዞ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ላለፉት ዓመታት በመደመር መንግሥት ከተከናወኑ አበይት ተግባራት መካከል በቴክኖሎጂ፣ በኢንዱስትሪ፣ በማኅበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች፣ በምግብ ሉዓላዊነት፣ በከተማ ልማት እንዲሁም በዲፕሎማሲ የተመዘገቡት ስኬቶች በዋናነት ይጠቀሳሉ።
በተጨማሪም የሕዳሴ ግድብን ማጠናቀቅና የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ራዕይ ሌሎች ማሳያዎች ናቸው።
አዲሱ የመደመር መንግሥት በተመሰረተበት የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የ2019 ዓ.ም የመደመር መንግሥት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችንና ግቦችን አብራርተዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው፤ በሀገራችን ዘላቂ ሰላምን፣ ኅብረትንና ትብብርን ማስፈን፣ ጥራትን መሠረት ያደረገ መዋቅራዊ ሽግግር ማድረግ እንዲሁም የትምህርት፣ የጤና እና የማኅበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶችን በጥራት ማሳደግ ዋነኛ ትኩረቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ወደ 65 በመቶ፣ የጤና መድኅን ሽፋንን ወደ 85 በመቶ፣ እንዲሁም የተማሪዎች የምገባ ሽፋን ወደ 70 በመቶ ማሳደግ የተያዙ አበይት ግቦች መሆናቸውን አንሥተዋል።
በመሆኑም የመደመር መንግሥት ምስረታ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር፣ የሕግ የበላይነትን በማስከበርና የሕዝቦችን አብሮነት በማጠናከር ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የሰላም፣ የፍትሕና የልማት ምዕራፍ የሚያሸጋግር አዲስ የቃል ኪዳን መስመር ይከፍታል።
በልዩ እሸቱ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #medemergovernment #statebuilding

#woldiauniversity
በ2019 ዓ.ም ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
በ2019 ዓ.ም ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጥሪ በሌላ ማስታወቂያ እንደሚደረግ ተገልጿል።

አዋሽ ባንክ ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር አምስት አዳዲስ የክፍያ ካርዶችን ይፋ አደረገ
#fastmereja I አዋሽ ባንክ ከአለም አቀፉ የክፍያ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ማስተርካርድ ጋር በመተባበር፣ የደንበኞችን ፍላጎት ያማከሉ አምስት አዳዲስ እና ልዩ ጥቅም የሚያስገኙ የውጭ ምንዛሬ እንዲሁም የሀገር ውስጥ የክፍያ ካርዶችን ይፋ አደረገ። ባንኩ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. በኢሊሊ ሆቴል ባካሄደው ይፋዊ ስነ-ስርዓት፣ አዲሶቹን የካርድ ክፍያ አማራጮች ለግል ተጠቃሚዎች እና ለድርጅት ደንበኞች አስተዋውቋል። አዲሶቹ ካርዶች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ገበያን ለማሻሻል ካወጣው መመሪያ ጋር ተጣጥመው የተዘጋጁ መሆናቸው ተገልጿል።
በዚህም መሰረት ይፋ ከተደረጉት አምስት የካርድ አይነቶች መካከል ለአለም አቀፍ ግብይት የሚያገለግሉት፡- “አዋሽ ወርልድ ኤሊት ዴቢት” (Awash World Elite Debit)፣ “አዋሽ ፕላቲነም የቅድመ ክፍያ” (Awash Platinum Prepaid)፣ “አዋሽ ጎልድ የቅድመ ክፍያ” (Awash Gold Prepaid) እና ለድርጅቶች የታለመው “አዋሽ ኮርፖሬት የቅድመ ክፍያ” (Awash Corporate Prepaid) ካርዶች ይገኙበታል። በተጨማሪም በሀገር ውስጥ በኤቲኤም (ATM) እና በPOS መሳርያዎች ላይ በንክኪ አልባ (Contactless) ቴክኖሎጂ የሚሰራው “አዋሽ ፕላስ” የዴቢት ካርድ ለተጠቃሚዎች ቀርቧል።
እነዚህ ካርዶች የውጭ ምንዛሬ ሂሳብ ላላቸውም ሆነ ለሌላቸው ዜጎች፣ ለኦንላይን (E-Commerce) ግብይት፣ ለጉዞ እና ለተለያዩ የድርጅት ወጪዎች አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሺፈራው እንደገለጹት፤ አዲሶቹ የካርድ ምርቶች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወሰደው የፋይናንስ ሪፎርም መሰረት የተዘጋጁ እና የደንበኞችን የዲጂታል ክፍያ ፍላጎት ዘመናዊ በሆነ መንገድ የሚያሟሉ ናቸው። የማስተርካርድ ምስራቅ አፍሪካ እና ህንድ ውቅያኖስ ደሴቶች ሲኒየር ምክትል ፕሬዚዳንት እና ካንትሪ ማኔጀር ሸህሪያር አሊ በበኩላቸው፣ ከአዋሽ ባንክ ጋር የተደረገው ይህ አጋርነት በኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ ስነ-ምህዳርን ለማጠናከር እና አካታች የፋይናንስ አገልግሎትን ለማስፋፋት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
አዲሶቹ የካርድ ምርቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ለአጠቃቀም ቀላል እና ደንበኞች በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ያሉ የዲጂታል ክፍያዎችን በቅልጥፍና እንዲፈጽሙ የሚያስችሉ መሆናቸው ተመላክቷል።

ትግራይ ክልል አሁናዊ ትክክለኛ መረጃ‼️
በትግራይ ክልል በተለይ በሶስት አቅጣጫ ወጊያው ቀጥሏል።
📌ከመቀሌ-ሀገረ ሰላም-አብዪ አዲ(ተንቤን-አድዋ መስመር አንዱ የውጊያ መስመር ሲሆን በዚህ መስመር መከላከያ ሰራዊት የተንቤን ዋና ከተማ የሆነችውን አብዪ አዲን ተቆጣጥሯል፣አድዋ ከተማ ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴ ቆሟል ብለዋል።
📌ከመቀሌ-ውቅሮ-ነጋሽ-አዲግራት-ዛላንበሳ---- ሌላኛው ውጊያ እየተደረገበት ያለ መስመር ሲሆን በዚህ የውጊያ መስመር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ መስከረም 28 ከሰዓት በኋላ ውቅሮን አልፎ ነጋሽ የምትባል ከተማን ተቆጣጥሯል።
በውቅሮ መከላከያ ሰራዊት ፓትሮል መጀመሩን የአዩዘሀበሻ ምንጮች በምስል አጋርተዋል።
📌ከማይፀብሪ-አዲ ገብሩ-እንዳ ባጉና-ሽሬ-አክሱም ---ሌላኛው የውጊያ መስመር ሲሆን የህወሓት ተዋጊዎች ከእንዳባጉና እና ሽሬ ለቀው ቢወጡም መከላከያ ሠራዊት ገና እንዳልገባ የአካባቢው ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
📌አዲግራት በዛሬው ዕለት ተደጋጋሚ የጀት ድብደባ ተፈፅሟል፣ የደረሰው ጉዳት አልታወቀም።

አርሰን ቬንገር ከ22 ዓመታት በኋላ በ2018 ክረምት አርሰናልን ሲለቁ የክለቡ የበላይ አካላት አዲሱን አሰልጣኝ ለመምረጥ ሰፊ ፍለጋ አደረጉ።
በወቅቱ የክለቡ ስራ አስፈፃሚ የነበረው ኢቫን ጋዚዲስ የዝውውር ሃላፊው ስቨን ሚስሊንታት እና ራኡል ሳንሌሂ ያካተተው ኮሚቴ ለአርሰናል አሰልጣኝነት ካጩዋቸው ዋና ዋና ስሞች አንዱ ሚካኤል አርቴታ ነበር።
አርቴታ በማንቼስተር ሲቲ በፔፕ ጓርዲዮላ ስር ረዳት ሆኖ በሰራበት ወቅት ባሳየው የረቀቀ የታክቲክ እውቀት እና አርሰናልን በካፒቴንነት በመምራቱ የነበረው ሰፊ ግንዛቤ ክለቡን ማርኮት ነበር።
ይሁን እንጂ በወቅቱ የቦርዱ አባላት ለአርቴታ የነበራቸው ጥርጣሬ ገና በስልጠናው ዓለም አዲስ በመሆኑ እና የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው ይበልጣለ በሚል እምነት ክለቡ ኡናይ ኤመሪን እንዲሾም አደረጉ። አርቴታም በወቅቱ በሲቲ መቆየቱን መረጠ።
ከዛ ኡናይ ኤመሪ መጡ በአርሰናል የቆይታ ጊዜያቸው ግን ቡድኑን ከውድቀት ማዳን አልቻሉም፤ በዲሲፕሊን ማጣት፣ በታክቲክ አለመረጋጋት እና በደጋፊዎች ተቃውሞ ምክንያት በኖቬምበር 2019 መጨረሻ ላይ ከስራቸው ተባረሩ።
በዚህ ወቅት የአርሰናል ቦርድ በተለይ ስታን እና ጆሽ ክሮንኬ ከዚህ ቀደም የተደረገውን ስህተት ላለመድገም እና የክለቡን መርህ የሚረዳ አሰልጣኝ ለማግኘት ቆርጠው ተነሱ።
ዒላማቸውም በቀጥታ ሚካኤል አርቴታ ሆነ .....
@Bisrat_Sport_433et

Comments