(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሱዳኑ አልሂላል ክለብ ወደኢትዮጵያ ለሚያደርገው ጉዞ ‹‹የደህንነት ዋስትና›› ጠየቀ፡፡ የሱዳኑ አል ሂላል ኦምድሩማን ክለብ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ግጥሚያ ከሲዳማ ቡና ጋር የሚጫወት መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይህ ግጥሚያ አንድ ሳምንት የቀረው መሆኑን ተከትሎ ክለቡ ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) አስቸኳይ ደብዳቤ ፅፏል፡፡ ‹‹ይድረስ ለካፍ የደህንነትና ፀጥታ ሀላፊ›› በሚል የተፃፈው ይህ ደብዳቤ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ስላለው የፀጥታ ችግር ቀጥተኛና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ከሚገኙ መረጃዎች ለማወቅ እንደተቻለ ጠቅሶ ጉዳዩ እንዳሳሰበው ይገልፃል፡፡ በክለቡ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዋና ፀሀፊ ዶክተር ሀሰን አሊ ኢሳ አማካኝነት የተፃፈው ይህ ደብዳቤ ሲቀጥልም ‹‹የአል ሂላል ቡድን አባላት ወደኢትዮጵያ ለመጓዝ ዝግጅት እያደረጉ በመሆኑ ለአባሎቻችን ደህንነትና ጥበቃ ቅድሚያ የምንሰጥ መሆኑን ለማስታወቅ እንወዳለን›› ካለ በኋላ ካፍ ከደህንነትና ሎጅስቲክስ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ለሚከተሉት ነጥቦች አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ ከእነዚህ ነጥቦች የመጀመሪያው የክለቡ አባላት ወደኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የአውሮፕላን ጉዞ ደህንነት ምን አይነት ዋስትና ተዘጋጅቷል? የሚል ነው፡፡
ይህ ጥያቄም የቡድኑን አዲስ አበባ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መድረስንና ከዚያም ጨዋታው ወደሚካሄድበት ድሬደዋ ከተማ የሚካሄደውን የአገር ውስጥ በረራ እንደሚያካትት አስረድቷል፡፡ ሁለተኛው ጥያቄ የአል ሂላል ቡድን አባላት አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ ድሬዳዋ እስከሚሄዱ ድረስ ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ምን አይነት ዝግጅት ተደርጓል? የሚል ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ ልኡካን ቡድኑ በድሬዳዋ ቆይታው በማረፊያውና ልምምድ በሚያደርግበት ቦታ ምን አይነት የደህንነት ጥበቃ ይደረጋል? የሚል ነው፡፡ በአራተኛነት ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የክለቡ ተጨዋቾች፣ የቴክኒክና የአስተዳደር ቡድን አባላቱ በሰላም ወደኪጋሊ እንዲመለሱ ለማስቻል የተደረገው ዝግጅት እንዲገለፅለት ጠይቋል፡፡

1 day ago