Logo
YeneTube
ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈቼ የሚወስደው መንገድ ለሁለት ቀናት ይዘጋል ተባለ

በአዲስ አበባ ከጎሮ አደባባይ በኮዬ ፈቼ በኩል ወደ ቱሉ ድምቱ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለሁለት ቀናት ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።

በመንገዱ ላይ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር መሠረተ ልማት ሥራ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የመሬት ውስጥ የሚቀበሩ መሠረተ ልማቶችን ለመዘርጋት የዋናው አስፋልት መንገድ ክፍል ተቋርጧል።

በመሆኑም ከዛሬ መስከረም 28 እስከ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ከጎሮ አደባባይ ወደ ኮዬ ፈቼ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች በጎሮ–ቦሌ ኤርፖርት መንገድ አቅጣጫ በመጓዝ በቡልቡላ በኩል ወደ ኮዬ ፈቼና አካባቢው ሊጓዙ ይገባል ተብሏል።

እንዲሁም ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ አደባባይ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች ከኮዬ ፈቼ አደባባይ በቡልቡላ በኩል ወደ ጎሮ አደባባይ የሚወስደውን የቦሌ ኤርፖርት–ጎሮ አዲስ መንገድን ጨምሮ ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ባለሥልጣኑ አሳስቧል።

አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ የተመላላሽ መንገዶችን ሊጠቀሙ ይገባል ሲሉየባለሥልጣኑ ምክትል ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@Yenetube Fikerassefa
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.