Logo
TIKVAH-ETHIOPIA
" በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም " - ጌዲዮን ጤሞቲዮስ (ዶ/ር)

👉 " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም ! "

ኢትዮጵያ በኤርትራ ወረራ እንደተፈጸመባት እና ራሷን ከመከላከል ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላት በመግለጽ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) በደብዳቤ አሳወቀች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዮስ (ዶ/ር) ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት ደብዳቤ መጻፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በዚህም ደብዳቤ፤ የኤርትራ ሠራዊት ድንበር አልፎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በሁለት የተለያዩ ጊዜያት ለፀጥታው ም/ቤት አባላት በላከችው ደብዳቤ " ኤርትራ በተደጋጋሚ በፈጸመችው ጸብ አጫሪነት እና ድንበር ጥሶ የመግባት እርምጃ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ አደጋ መደቀኑን " በመጥቀስ ትኩረት እንዲሰጠው መጠየቃቸውን አስታውሰዋል።

" ኤርትራ የፀብ አጫሪነት ድርጊቷን በአሁኑ ጊዜ ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግራ ሜካናይዝድ ክፍሎችን ጨምሮ ወታደሮቿን በጥልቀት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት አሰማርታለች " ያሉት ጌዲዮን (ዶ/ር) ፥ " ይህም ሦስት የትግራይ ዞኖችን በማካተት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከ30 አስከ 60 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ርቀት ወደ ውስጥ ገብተዋል " ብለዋል።

ሚኒስትር ጌዲዮን የኤርትራ ድርጊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር ውስጥ የሰፈሩትን መሠረታዊ መርሆዎች በግልጽ የሚጥስ ነው በማለት " ይህም ኢትዮጵያ ራሷን የመከላከል ሕጋዊ መብት እንድትጠቀም የሚያስገድድ ነው " ሲሉ ጽፈዋል።

ለፀጥታው ም/ቤት የጻፉት ደብዳቤ የተፈጸመውን ወረራ ለማሳወቅ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ለምትወስደው የመከላከል እርምጃ ድጋፍ ጠይቀዋል።

" በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ የላትም " በማለት ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ የገጠማትን ሁኔታ በመረዳት ድጋፍ እንዲደያርግላት እና ከጎኗ እንዲቆም ጠይቀዋል።

ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራ በኩል ለረዥም ጊዜ ሲፈጸሙ ለነበሩ ትንኮሳዎች በትዕግሥት እና ራስን በመቆጠብ መቆየቷን አመልክተዋል።

በመሆኑም " ሁለቱን አገራት በእኩል ሚዛን ለማስቀመጥ የሚሞክር ማንኛውም አቋም ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኅንነት አይጠቅምም " ብለዋል።

" ኤርትራ ወራሪ ናት፤ ኢትዮጵያ ደግሞ የወረራ ሰለባ ናት። ኤርትራ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እየጣሰች ነው " ሲሉም አሳውቀዋል።

ኢትዮጵያ ራሷን ከመከላከል በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌላትም ገልጸዋል።

መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia 🇪🇹 ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሕግን መሠረት በማድረግ ሉዓላዊነቷ እና የግዛት አንድነቷን የመከላከልና የማስጠበቅ ሕጋዊ መብት እንዳላት አሳወቀች። የተባበሩት መንግስታት (UN) ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና ጄን ሙሀመድ አዲስ አበባ ይገኛሉ። ዛሬ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው መክረዋል። ሚኒስትሩ፥ ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ እየፈጸመች ስላለው ቀጣይነት ያለው የጠብ አጫሪነት ተግባና…
19 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.