Logo
AHADU RADIO FM 94.3
ሴንቸሪ ሪልስቴት ድምፃዊ ዳዊት ጽጌን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሰየመ

መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሪል እስቴትና በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ያከናወናቸውን ሥራዎችና ዕቅዶች ይፋ አድርጓል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ አዲስ የብራንድ አምባሳደር ስምምነት ከድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ጋር ተፈራርሟል ።

የሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተፈራ ለማ ሴንቸሪ በሪል እስቴትና በኮንስትራክሽን ግብዓት፣ ብረታ ብረት፣ ኬሚካልና ማዕድን ዘርፎች ላይ በመስራት ለሀገራዊ ልማት አስተዋፅዖ ማድረጉን ገልጸዋል።

የሴንቸሪ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከፍተኛ አማካሪና የቦርድ አባል ፕሮፌሰር አበበ ድንቁ በበኩላቸው፣ ተቋሙ ላለፉት 70 ዓመታት በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች መስራቱን ገልጸዋል።

የሴንቸሪ ሪል እስቴት ዋና ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር አቶ ፈለቀ ሹሜ፣ ድርጅቱ ላለፉት 10 ዓመታት በአዲስ አበባ ለመኖሪያ፣ ለንግድና ለቢሮ የሚውሉ ሕንፃዎችን መገንባቱን ገልጸዋል። የግንባታ ግብዓቶችን በራሱ ማምረቱ የተለየ ጥቅም እንደሚሰጠው ጠቁመዋል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ ሴንቸሪ ሪል እስቴት የድምፃዊ ዳዊት ጽጌን ብራንድ አምባሳደር በማድረግ “ደግሞ በዚህ ላይ... ሥራዎቻችን ምስክሮቻችን!” በሚል አዲስ ዘመቻ መጀመሩ ተገልጿል።

ድምፃዊ ዳዊት ጽጌ በበኩሉ፣ ድርጅቱ በሪል እስቴት ዘርፍ ከሚያከናውነው ሥራ ባሻገር በማህበራዊ ኃላፊነትና በበጎ አድራጎት ሥራዎች የሚያደርገውን ተሳትፎ በመመልከት ከሴንቸሪ ሪል እስቴት ጋር ለመስራት መስማማቱን ገልጿል።

በቃልኪዳን ኃይሌ

#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.