Logo
Getu Temesgen
ዛሬ ሹመታቸውን የተቀበሉት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ ጋር ውይይት አደረጉ
#ethiopia | የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ጄን መሐመድ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸውም በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ የፀጥታ እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት ምክትል ዋና ፀሐፊዋ አሚና ጄን ሙሀመድ ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅድሚያ በሚሰጧቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ እንደሚመክሩ ተመላክቷል፡፡

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.