Logo
YeneTube
ትግራይ ክልል አሁናዊ ትክክለኛ መረጃ‼️
በትግራይ ክልል በተለይ በሶስት አቅጣጫ ወጊያው ቀጥሏል።

📌ከመቀሌ-ሀገረ ሰላም-አብዪ አዲ(ተንቤን-አድዋ መስመር አንዱ የውጊያ መስመር ሲሆን በዚህ መስመር መከላከያ ሰራዊት የተንቤን ዋና ከተማ የሆነችውን አብዪ አዲን ተቆጣጥሯል፣አድዋ ከተማ ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴ ቆሟል ብለዋል።

📌ከመቀሌ-ውቅሮ-ነጋሽ-አዲግራት-ዛላንበሳ---- ሌላኛው ውጊያ እየተደረገበት ያለ መስመር ሲሆን በዚህ የውጊያ መስመር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ መስከረም 28 ከሰዓት በኋላ ውቅሮን አልፎ ነጋሽ የምትባል ከተማን ተቆጣጥሯል።

በውቅሮ መከላከያ ሰራዊት ፓትሮል መጀመሩን የአዩዘሀበሻ ምንጮች በምስል አጋርተዋል።

📌ከማይፀብሪ-አዲ ገብሩ-እንዳ ባጉና-ሽሬ-አክሱም ---ሌላኛው የውጊያ መስመር ሲሆን የህወሓት ተዋጊዎች ከእንዳባጉና እና ሽሬ ለቀው ቢወጡም መከላከያ ሠራዊት ገና እንዳልገባ የአካባቢው ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።

📌አዲግራት በዛሬው ዕለት ተደጋጋሚ የጀት ድብደባ ተፈፅሟል፣ የደረሰው ጉዳት አልታወቀም።

@Yenetube Fikerassefa
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.