የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊሆን አይችልም!
*******************
ከጥንታዊቷ እስከ ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ቀይ ባህር የግዛቷ አካል ሆኖ መርከቦቿ ሲጠቀሙበት የኖሩ ሲሆን ጥንታዊት ኢትዮጵያን በአለም ላይ ከነበሩት ታላላቅ ሀይሎች አንዷ እንድትሆን ያደረጓት በወቅቱ ታስተዳድራቸው የነበሩት ወደቦቿ፣ የንግድ ትስስሮቿ እና "ባህረ ነጋሽ" የሚለው የማእረግ መጠሪያ ስያሜ እንደነበሩ ይታወቃል።
ሆኖም ሀገራችን በታሪክ አጋጣሚዎች እና በተደረጉባት እኩይ ሴራዎች ምክንያት ከሶስት አስርት አመታት በላይ የባህር በር አልባ ሆና በመቆየቷ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ የጂኦ ፖለቲካ እና የብሄራዊ ደህንነት ማነቆዎች ተዳርጋ ኖራለች።
በተባበሩት መንግስታት የንግድና ልማት ጉባኤ መረጃ መሰረትም የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከአለም አማካይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ወጪ በላይ ተጨማሪ ክፍያ ለማውጣት የሚገደዱ በመሆኑ ይህ ተፅእኖ በዜጎች እለታዊ የሸመታ አቅም፣ በሀገራችን የኢንቨስትመንት እድሎች እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዲጂታል መረጃ በሚያስተላልፉት ከባህር በታች ያሉ የፋይበር ኦፕቲክስ መስመሮች ተጠቃሚነት ላይ ከፍተኛ ጫና ሲፈጥር ቆይቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግስት ምስረታ ወቅት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደገለፁት የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን ሊሆን አይችልም፡፡
በመሆኑም በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት አጥብቀን እንሰራለን ያሉም ሲሆን፤ ይህንን ታሪካዊ ስህተት እና የትውልድ ቁጭት ለመቅረፍ "የመደመር መንግስት" የባህር በር ጥያቄን ከወቅታዊ ፖለቲካ እና ከፓርቲ ወገንተኝነት በላይ በሆነ ትውልድ ተሻጋሪ ብሄራዊ አጀንዳ አድርጎ እንደሚሰራበት ተናግረዋል።
የመደመር መንግስት በያዘዉ ጠንካራ አቋም የኢትዮጵያ ስልጣኔና እድገት ያለ ባህር በር እውን ሊሆን ስለማይችል ሀገራችን በሰጥቶ መቀበል በጋራ ተጠቃሚነት እና በሰላማዊ ዲፕሎማሲ መርህ ወደ አለም የምትወጣበትን መስመር የማረጋገጥ ጉዞዋ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
እውነተኛ ብሄራዊ ደህንነትና ሉአላዊነት የሚረጋገጠው ስትራቴጂካዊ ቁሳቁሶች ያለ ምንም የውጭ ጫና እገዳ ወይም የጎረቤት ሀገራት በጎ ፈቃድ በቀጥታ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ሲችሉ እንደመሆኑ መጠን ቀጥተኛ የባህር በር ማግኘት የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት እድሎችን በመክፈት የወጣቶችን ስራ አጥነት ከመቅረፉ ባሻገር ኢትዮጵያ በቀይ ባህር እና በስትራቴጂካዊ የውሃ አካላት ቀጠናዊ ውሳኔዎች ላይ ያላትን የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ተሰሚነት ከፍ ያደርገዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ አካል እንጂ ከሩቅ የመጣች እንግዳ እንዳልሆነችና በጂኦ ፖለቲካዊ ሴራዎች የባህር በር አልባ እንድትሆን መደረጓን ለአለም እያስረዳች ትገኛለች።
ኢትዮጵያ ቀይ ባህር ላይ እግሯን እንዳትተክል የሚደረጉ የተለያዩ የፖለቲካ የዲፕሎማሲ እና የፕሮፓጋንዳ ሸፍጦች አልቆሙም እነዚህን ሸፍጦች ሲጠነስሱ እንቅልፍ አጥተው የሚያድሩ አካላት መፍጨርጨራቸው ባይገታም ኢትዮጵያን በዘላቂነት ሊያግዷት አይችሉም።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም እና የአካባቢያዊ ትስስር ዋና ምሰሶ እንደመሆኗ የባህር በር ማግኘቷ ለአካባቢው ሀገራትም ቢሆን ትልቅ የኢኮኖሚ ጥቅም የሚያስገኝ በመሆኑ በቅርብም በሩቅም ያሉ ሀገራት ለኢትዮጵያ ቀና ምላሽ በመስጠት በጋራ መስራትን ተመራጭ ያደርጋሉ።
ፈጣን እድገት እያስመዘገበ ያለው ኢኮኖሚና ትልቅ ህዝብ ያላት ሀገር መሆኗም ይህን ግስጋሴ የሚያስተናግድ የባህር በር የማግኘት ትልሟን እውን ለማድረግ ትልቅ አቅም ይሆናታል።
በአጠቃላይ የታሪክ እውነታ የህግ መብት እና የህልውና ጥያቄ የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ አይቀሬ ያደርጉታል።
ይህንን አገራዊና ታሪካዊ ሀላፊነት ከግብ ለማድረስ የውስጥ አንድነትን ማፅናትና ደህንነትን ማረጋገጥ የሃሳብ ፖለቲካን ማጠናከር እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር ወሳኝ መፍትሄ ነው።
በአለም አቀፍ የባህር ህግጋት እና በዲፕሎማሲያዊ አማራጮች የታገዘው ይህ ጥረት የመጪውን ትውልድ መብትና እድል የማስከበር የታሪክ ጥሪም ሲሆን ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ ገንብቶ ለዘላቂ ብልፅግና የሚያሸጋግር ጨዋታ ቀያሪ ምእራፍ ነው።
ዛሬ ብርቱዋ ኢትዮጵያ ለሶስት አስርት አመታት ካቀረቀረችበት ቀና ብላለች የቀይ ባህር ተጋሪነቷን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ማናቸውም ሸፍጦች ጊዜያዊ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ እንጂ የህዝቧን የታሪክ እና የተፈጥሮ መብት ሊያጠፉ አይችሉም።
ኢትዮጵያ አትቆምም የጂኦ-ፖለቲካ ሴራዎችን ሁሉ በጣጥሳ ከባህሩ ትደርሳለች ባህር ሀይሏና መርከቦቿም በቀይ ባህር ዳግም ይጓዛሉ።
በብሌን ደምበሎ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #seaaccess #redsea #diplomacy

22 hours ago