3 hours ago
u12a8u1260u1300u1271 u1300u122du1263u1363 u12a8u1349u12adu12adu122d u12c8u12f0 u121du12adu12adu122d u1363 u12e8u1355u122cu12ddu12f3u1295u1271 u12e8u12abu12edu122e u121du120du120du1235 #u1226u1235u1275 u1290u1325u1265","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ከበጀቱ ጀርባ፣ ከፉክክር ወደ ምክክር ፣ የፕሬዝዳንቱ የካይሮ ምልልስ #ሦስት ነጥብ
6 hours ago
መረጃ‼️
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ ቅድመ-ምረቃ በረራዎችን ከዛሬ ሰኔ 6 ጀምሮ እንደሚያደርግ አስታወቀ።
አየር መንገዱ፣ ወደ ደብረ ማርቆስ መጓዝ የሚፈልጉ መንገደኞች የበረራ ቲኬቶችን በሁሉም የቲኬት መሸጫ ቢሮዎች ማግኘት እንደሚችሉ ዛሬ ባሠራጨው መረጃ ላይ ገልጧል።
ኾኖም አየር መንገዱ ወደ ደብረ ማርቆስ በሳምንት ስንት በረራዎችን ለማድረግ እንዳሰበ አልገለጠም።
አዲሱ የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ከሦስት ሳምንት በፊት አንድ የሙከራ በረራ ማስተናገዱ ይታወሳል።
Seledadotio

16 hours ago
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) የኮሚሽኑ ሥራ የደረሰበትን ታሪካዊ ምዕራፍ አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ያነሷቸው ነጥቦች፡-
👉 ኢትዮጵያ አሳታፊና አካታች ሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ከገባች አራት ዓመታት ተቆጥረዋል
👉 በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ወደ ምክክር ጉባኤ የሚያደርሱ መሰረታዊ ተግባራት ተከናውነዋል
👉 በመላው ሀገሪቱ 1ሺህ 234 ወረዳዎችን ማሳተፍ ተችሏል
👉 ይህም በሀገሪቱ ካሉ አካባቢዎች 93 በመቶውን የሚሸፍን ነው
👉 በ12 ክልሎች፣ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከፌደራል ባለድርሻ አካላት ስኬታማ የአጀንዳ ማሰባሰብ ተግባር ተከናውኗል
👉 በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንዲሳተፉ ተደርጓል
👉 አጀንዳ የተሰባሰበባቸው አካባቢዎች ለዋናው ጉባኤ የሚወክላቸውን መርጠዋል
👉 የምክር ሂደቱ ከጅምሩ አንስቶ ግልጽ፣ ገለልተኛና አሳታፊ በሆነ አሰራር እንዲመራ ተደርጓል
👉 የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሂደቱ የሰጠው ትኩረትና ያሳየው የባለቤትነት መንፈስ እጅግ የሚያበረታታ ነው
👉 የኢትዮጵያ ሕዝብ በምክክር ሂደቱ ታሪክ የማይረሳው ሀገራዊ ኃላፊነት ተወጥቷል
👉 ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በመጪው ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀመራል
👉 ጉባኤው በአዲስ አበባ ከተማ ለሦስት ተከታታይ ሳምንታት ይካሄዳል

17 hours ago
በሀገራዊ ጉባኤው ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ጽኑ መሰረት እንጥላለን - ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በመሰረታዊ አጀንዳዎች ላይ በሰለጠነ መንገድ በመነጋገር ለዘላቂ ሰላም ጽኑ መሰረት የሚጣልበት ነው አሉ ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ከሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ሳምንታት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የምክክር ሒደቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በጽናት በማለፍ ወደ ዋናውና ወሳኙ የምክክር ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል፡፡
የሀገራዊ ምክክሩ ቀጣይ ተግባራት በጉባኤው ላይ በኢትዮጵያ መሰረታዊ አጀንዳዎች ላይ በሰለጠነ መንገድ መነጋገርና ዘላቂ መግባባት ላይ መድረስ እንደሆነ አንስተዋል።
ውጤቱም በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም በሕዝብና በመንግሥት መካከል ያለው ግንኙነት እንዲሻሻልና መተማመን የሰፈነበት አዲስ የፖለቲካ ሥርዓት እንዲገነባ ያደርጋል ነው ያሉት።
ጉባኤው ለዘመናት ሲንከባለሉ የነበሩ ውስጣዊ ችግሮች ተፈተው ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥና ጠንካራ ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግሥት ለመገንባት ጽኑ መሰረት የሚጣልበት እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝቦች ተከባብረው፣ ተነጋግረውና ተደማምጠው በመግባባት የሚያቀርቧቸው ምክረ ሃሳቦች በተግባር ተተርጉመው ሀገራችን ወደ አዲስ የሰላምና የእድገት ምዕራፍ እንድትሸጋገር የጋራ ቁርጠኝነትና ጥረት ይጠበቃል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
በመሆኑም ለጉባኤው ስኬታማነት አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ምክክር ተግባራትን ለማከናወን እንዲቻል የጉባኤው ተሳታፊዎች ጉባኤው ከመጀመሩ አንድ ሳምንት ቀደም ብለው ተጠቃልለው እንዲገቡ እንደሚደረግ ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።
በብርሃኑ አበራ

Sponsored by
Surafel
17 hours ago
"ዋናው ሀገራዊ ጉባዔ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምር ይካሄዳል" - መስፍን ዓርዓያ (ፕ/ር)
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚካሄድ በይፋ አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ዛሬ ምሽት በሸራተን አዲስ ሆቴል ለሚዲያዎች መግለጫ እየሰጠ ይገኛል። በዚህም የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕ/ር)፣ "ዋናው ሀገራዊ ጉባዔ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምር ይካሄዳል" ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ የመጨረሻው ዋና ጉባዔ በአዲስ አበባ ከተማ ከሦስት ሳምንታት ባልበለጠ ጊዜ እንደሚካሄድም አስታውቀዋል።
በትግራይ ክልል በሚስተዋለው የፖለቲካ አለመረጋጋት መግባት ባለመቻሉ የክልሉን አጀንዳ በአዲስ አበባ ከተማ መቀበሉን፣ በሌሎች ሁሉም ክልሎች በአካል በመንቀሳቀስ መቀበሉን ሲያስታውቅ ቆይቷል። በተያያዘ የቀረቡለት አጀንዳዎቹን ለባለድርሻ አካላት በማቅረብ ሀሳብ እየተቀበለ መሆኑን መሆኑን ከሰሞኑ ጭምር ገልጿል።
በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ዳያስፖራዎችም ከጀንዳ መቀበሉን ገልጿል።
ይሁን እንጅ የተወሰኑ የፖለቲካ ፖርቲዎች መጀመሪያ ጦርነት፣ የጸጥታ ችግር እንዲቆም፣ እስረኞች እንዲፈቱ ካልተደረገ በምክክሩ አንሳተፍም እንዳሉ ናቸው።
ኮሚሽኑ መጀመሪያ በተሰጠው ሦስት አመታት ስራው ባለመጠናቀቁ ፓርላማው ለአንድ ዓመት ተጨማሪ ጊዜ ከሰጠው በኋላ፣ ያም ባለመብቃቱ ለሁለተኛ ጊቡ የስምንት ወራት ጊዜ ተጨምሮለት እየሰራ ይገኛል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #tikvahethiopiafamilyaa

19 hours ago
የ8 ዓመታት ምጥ በምስጋና ሊደመደም ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት ስምንት ዓመታት በፍርድ ቤት ስትከራከርበት የቆየችውን መሬት በሕጋዊ መንገድ ሙሉ በሙሉ መረከቧንና በአዲስ አበባ 7ኛዋን፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ 780ኛዋን አዲስ አጥቢያ (የአምልኮ ስፍራ) በይፋ እንደምትጀምር አስታወቀች። ቤተ ክርስቲያኗ ይህንን ያስታወቀችው በለቡ አጥቢያ በሚገኘው አዲሱ ስፍራ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጠችው መግለጫ ነው።
የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያ ፕሬዚዳንት መጋቢ ዶ/ር ጌታሁን ነሲቡ
እንደገለጹት ፣ ይህ አዲሱ መሬት ከነሐሴ 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የተሰጣት ቢሆንም፣ ባጋጠሙ የተለያዩ ተግዳሮቶችና ክርክሮች ምክንያት ላለፉት 8 ዓመታት ጉዳዩ በሕግ ጥላ ሥር ቆይቷል። አሁን ላይ ግን ሁሉንም ፈተናዎች በጽናትና በሕጋዊ መንገድ አልፋ መሬቱን በይፋ ለመረከብ መቻሏን ገልጸዋል።
በለቡ ከሆፕ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ በሚገኘው በዚህ አዲስ ስፍራ ላይ ቤተ ክርስቲያኗ የሚከተሉትን ሦስት ዘመናዊ የልማት ዕቅዶች ይዛ መነሳቷን አስታውቃለች። በመሆኑም
-ለምዕመናን ምቹ የሆነ ዘመናዊ የማምለኪያ አዳራሽ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ሁለንተናዊ ሥራዎች የሚያሳልጡ የቢሮዎች ግንባታ ይከናወናል።
-በአሁኑ ወቅት አገልግሎት እየሰጠ ለሚገኘው የስነ-መለኮት ኮሌጅ ተማሪዎችና አገልጋዮች የሚውሉ ዘመናዊ የማደሪያ ክፍሎች (Dormitories) ይገነባሉ።
-ግንባታው የአካባቢን ውበትና ስነ-ምህዳር ባገናዘበ መልኩ የሚከናወን ሲሆን፣ የወንዝ ዳርቻውን ልማት፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችንና መንገዶችን ያካተተ ይሆናል። ይህም ለአካባቢው ማኅበረሰብ ጭምር ምቾትና ውበት የሚሰጥ ሥራ እንደሆነ ተገልጿል።
ቤተ ክርስቲያኗ ከዚህ ቀደምም በቦሌ አራብሳ ተመሳሳይ ዘመናዊ የዋና ፅህፈት ቤት እና የአጥቢያ አገልግሎት ሕንጻ በመገንባት ማኅበራዊ ፋይዳ ያላቸውን ሥራዎች ስታከናውን መቆየቷ ይታወሳል።
እነዚህን ታላላቅ የልማት ሥራዎች ከመጀመሯ በፊት፣ ያለፉትን 8 ዓመታት ፈታኝ የፍርድ ቤት ጉዞዎችን በድል እንድትወጣ የረዳትን እግዚአብሔርን ለማመስገን ልዩ የምስጋና መርሃ-ግብር ማዘጋጀቷን ቤተ ክርስቲያኗ አስታውቃለች።
በዚህም መሠረት የፊታችን ሰኔ 7 በአዲስ አበባ ያሉ የቤተ እምነቱ አጥቢያዎች በሙሉ በጋራ በመሆን ሙሉ ቀን የሚቆይ ታላቅ ታሪካዊ የጸሎት እና የአምልኮ ፕሮግራም ያካሂዳሉ።
የቤተ እምነቱ መሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና መላው ምዕመናን በተገኙበት ልዩ የምስጋና ፕሮግራም ይኖራል።
በየሳምንቱ እሁድ ከሰዓት በኋላ በዚህ በአዲሱ የለቡ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መደበኛ የአምልኮ አገልግሎት በይፋ መቀጠል ይጀምራል።
የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 45 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ በወንጌል አገልግሎት እንዲሁም በልማትና ማኅበራዊ ሥራዎች ላይ በስፋት ስትሳተፍ የቆየች ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ሁሉም ክልሎች ውስጥ ከ780 በላይ አጥቢያዎች እንዳሏት በመግለጫው ወቅት ተነግሯል። ቤተ ክርስቲያኗ ለዚህ ስኬት መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ የፍትሕ አካላት እና ለሚዲያ ተቋማት ምስጋናዋን አቅርባለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

23 hours ago
የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን የ3 ሳምንታት ታላቅ የምስጋና እና የጸሎት መርሃ-ግብር አዘጋጀች!
#fastmereja I የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ከተማ ለቡ አካባቢ ከመንግስት የተሰጣትንና ላለፉት ስምንት ዓመታት በፍርድ ቤት ክርክር ውስጥ የነበረውን 10 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው መሬት በሕጋዊ መንገድ በይፋ መረከቧን አስታወቀች።
ቤተ ክርስቲያኒቱ በዚህ አዲስ ይዞታ ላይ በአገር አቀፍ ደረጃ 78ዐኛውን፣ በአዲስ አበባ ደግሞ 7ኛውን አዲስ አጥቢያ በይፋ እንደምትጀምር በዛሬዉ እለት በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጻለች።
የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተክርስትያን ፕሬዝዳንት መጋቢ ዶ/ር ጌታሁን ነሲቡ በለቡ አጥቢያ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳመለከቱት፤ አዲሱ ይዞታ (ለቡ 01 ሆፕ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ) በ2010 ዓ.ም ከመንግስት የተሰጠ ቢሆንም፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት ባጋጠሙ የተለያዩ ይዞታ ነክ ተግዳሮቶችና ክርክሮች ምክንያት ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ መቆየቱን ገልፀዉ በአሁኑ ወቅት ግን ተቋሙ ሁሉንም ፈተናዎች በሕጋዊ መንገድ በማለፍ መሬቱን በይፋ ለመረከብ መቻሉን አስታውቀዋል።
በይፋ በተረከቡት አዲሱ ስፍራ ላይ በቀጣይ ታላላቅ የልማት ዕቅዶች እንደሚከናወኑ የተገለፀ ሲሆን ከታቀዱት ዋና ዋና ፕሮጀክቶች መካከል የዘመናዊ አምልኮ እና የቢሮ ሕንጻ ግንባታ፣ ለስነ-መለኮት ኮሌጅ አገልግሎት የሚውሉ ዘመናዊ የተማሪዎችና የአገልጋዮች ማደሪያ ክፍሎች (Dormitories) ግንባታ፣ እና ከአካባቢው ወንዝ ተያያዥነት ያለው የ10 ሺህ ካሬ የወንዝ ዳርቻ ልማትና የአረንጓዴ ስፍራ ጥበቃ እንደሚገኙበት ጠቁመዋል።
ቤተ ክርስቲያኒቱ እነዚህን ታላላቅ የልማትና የህንጻ ግንባታ ዕቅዶች ከመጀመሯ በፊት፣ ባለፉት 8 ዓመታት የነበሩትን ፈታኝ የፍርድ ቤት ጉዞዎች በድል እንድትወጣ የረዳትን አምላክ ማመስገን ቀዳሚ ተግባሯ መሆኑን ገልጻ የሦስት ሳምንት ተከታታይ መርሃ-ግብር ማዉጣቷን አስታዉቃለች።
የፊታችን እሁድ ሰኔ 07 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያሉ የቤተ እምነቱ አጥቢያዎች በሙሉ በጋራ በመሆን ሙሉ ቀን የሚቆይ ታላቅ ታሪካዊ የጸሎት እና የአምልኮ ፕሮግራም ያካሂዳሉ።
እሁድ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ደግሞ የቤተ እምነት መሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ልዩ የምስጋና ፕሮግራም ይደረጋል።
ከእሁድ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በየሳምንቱ እሁድ ከሰዓት በኋላ በዚህ በአዲሱ 7ኛ ለቡ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መደበኛ የአምልኮ አገልግሎት በይፋ እንደሚቀጥል ታውቋል።
የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 45 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ በወንጌል አገልግሎት እንዲሁም በልማትና ማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ በስፋት ስትሳተፍ የቆየች ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ሁሉም ክልሎች ላይ ከ780 በላይ አጥቢያዎች እንዳሏት ከመግለጫው ለመረዳት ተችሏል።
ዶ/ር ጌታሁን ነሲቡ ለዚህ ታሪካዊ ስኬት መሳካት አምላካቸውን እያመሰገኑ፣ ክርስቲያኒቱ ጎን ለቆሙ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

1 day ago
12ኛ ዙር የደም ልገሳ መርሃ ግብር
የዓለም የደም ለጋሾች ቀን እና
የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች 3ኛ ዓመት በዓል ማክበር
📅 ሰኔ 6 እና 7, 2018 ዓ.ም.
📍 በኢትዮጵያ 20 + ከተሞች
አንድ የደም ልገሳ እስከ ሦስት ሰዎች ሕይወት ሊያድን ይችላል። በየቀኑ በሆስፒታሎቻችን ውስጥ ለቀዶ ሕክምና፣ ለአደጋ ተጎጂዎች፣ ለካንሰር ታማሚዎች፣ ለእናቶች እና ለሌሎች በርካታ ሕሙማን ደም በአስቸኳይ ያስፈልጋል።
ይህ 12ኛው ዙር የደም ልገሳ መርሃ ግብር የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች ለ3 ዓመታት ሲያከናውኑት የቆየውን የሰብዓዊነት ጉዞ የሚያከብር ሲሆን፣ በዓለም የደም ለጋሾች ቀን ላይም ለሕይወት አዳኝ ለጋሾች የምስጋና መልዕክት ያስተላልፋል።
እርስዎ የሚለግሱት ደም ለአንድ ቤተሰብ ተስፋ፣
ለአንድ ታማሚ ሕይወት፣
ለአንድ እናት ፈገግታ፣
ለአንድ ልጅ ነገን ሊሰጥ ይችላል።
🤝 ሁላችንም በጎ ፈቃደኞች፣ ወጣቶች፣ ቤተሰቦች፣ ተቋማት እና ማኅበረሰቡ በአጠቃላይ በዚህ ታላቅ የሕይወት ማዳን ተግባር እንዲሳተፉ በክብር እንጋብዛለን።
🩸 ደም መለገስ ሕይወት መስጠት ነው!
ኑ! በደማችን አዲስ ታሪክ እንፃፍ! ❤️🩸
#worldblooddonorday #የደም_ልገሳ #ተስፋ_አዲስ_ቤተሰቦች #donatebloodsavelives #20ከተሞች_አንድ_ዓላማ #ሕይወትን_እናድን

የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ከወዲሁ ታወቀ? የጀርመናዊው ሊቅ አስገራሚ ግምት
#ethiopia | ባለፉት ሦስት ተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች የጀርመንን፣ የፈረንሳይን እንዲሁም የአርጀንቲናን ድል አስቀድሞ በትክክል በመተንበይ ስሙ ናኝቶ የቆየው ምጣኔ ሀብት አዋቂና የሂሳብ ሊቅ ዮአኪም ክሌመንት ለዘንድሮው የዓለም ዋንጫ አዲስ መላምት ይዞ ብቅ ብሏል።
ባለሙያው የስፖርታዊ ብቃትን መለኪያዎች ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ-ህዝባዊ መረጃዎችን ያካተተ ሳይንሳዊ የስሌት ቀመር በመጠቀም በ2026ቱ ታላቅ የኳስ መድረክ ኔዘርላንድስ ባለድል እንደምትሆን አስታውቋል።
ይህ የክሌመንት አዲስ መግለጫ እንደ አርጀንቲና፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ እና ስፔን ላሉት ግዙፍ የኳስ ሀገራት የተሰጠውን ቅድሚያ ግምት ወደ ጎን በመግፋት ለሆላንድ እውቅና በመስጠቱ በስፖርቱ ማህበረሰብ ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ፈጥሯል።
በሊቁ ሳይንሳዊ ቀመር ትንተና መሰረት በሮናልድ ኪውማን የሚመራው የኔዘርላንድስ ብሔራዊ ቡድን ለፍጻሜ ደርሶ የፖርቹጋልን አቻ በመርታት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ሻምፒዮንነትን ክብር ይቀዳጃል።
እግር ኳስ ሁልጊዜም ባልተጠበቁ ክስተቶችና በአጋጣሚዎች የተሞላ በመሆኑ ስሌቱ መቶ በመቶ ፍጹም ሊሆን እንደማይችል ባለሙያው ቢያስገነዝብም፣ ከዚህ ቀደም በ1974፣ 1978 እና 2010 ለፍጻሜ ደርሰው ለጥቂት ዋንጫው ያመለጣቸው ብርቱካናማዎቹ ከአንድ ወር በኋላ በሚጠናቀቀው በዚህ ውድድር ታሪክ ሰርተው ግምቱን እውን ካደረጉት፣ የጀርመናዊው ምሁር የማይሳሳት የትንበያ ስም በዓለም መድረክ ላይ በድጋሚ ደምቆ የሚመዘገብ ይሆናል።#አዲስ አድማስ
#worldcup2026 #netherlands #joachimklement #footballprediction #worldcupwinners #football #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የ5ቱ ዓመታት ገፆች፦ የኢትዮጵያ ዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እመርታ እና የኢኮኖሚው አዲስ ምዕራፍ
*********************
ባለፉት አምስት ዓመታት በሀገራችን የተከናወኑ መጠነ ሰፊ የዲጂታል መሠረተ ልማት ግንባታዎችና የፖሊሲ ማሻሻያዎች በኢትዮጵያ የክፍያ ሥርዓት ላይ ታላቅ አብዮት ፈጥረዋል።
"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" እና "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂዎች ይፋ ከሆኑ ወዲህ፣ በኢትዮጵያ ከባህላዊው የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ወደ ዘመናዊው የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ያደረገችው ሽግግር አስገራሚ ዕድገት አስመዝግቧል።
ቀደም ሲል በኦፕሬተር የሚመራ የሞባይል ገንዘብ ሥርዓት ባለመኖሩ የጥሬ ገንዘብ ጥገኝነት መላቀቅ ተስኖ የነበረ ቢሆንም፣ የፖሊሲ ማሻሻያ ተደርጎ የኢትዮ ቴሌኮም "ቴሌብር" ወደ ሥራ መግባቱ ሁኔታዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀይሮታል።
ቴሌብር በሦስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ45 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን ማፍራቱ የሀገራችንን የዲጂታል አቅም ለዓለም ያሳየ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የሞባይል ዋሌት አካውንቶች ቁጥር 161 ሚሊዮን በላይ ደርሷል።
ይህም ከአጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር በላይ መሆኑ የአገልግሎቱን ተደራሽነት የሚያሳይ ሲሆን፣ በፕላትፎርሙ የሚከናወነው የገንዘብ ዝውውርም ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 82 በመቶ ደርሷል።
ይህ የዲጂታል ክፍያ አብዮት ለሀገራዊ ኢኮኖሚው በርካታ ጥቅሞችን እያስገኘ ይገኛል።
የመጀመሪያው የፋይናንስ አካታችነት ሲሆን፣ የባንክ አገልግሎት ባልደረሰባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ዜጎች በስልካቸው ብቻ ገንዘብ መቆጠብ፣ መላክ እና መቀበል በመቻላቸው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ወደ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው እንዲገቡ አድርጓል።
በሌላ በኩል፣ መንግሥት እንደ ነዳጅ ግብይት፣ የትራፊክ ቅጣት፣ የግብር ክፍያ እና የውኃና መብራት አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ በማድረጉ ብክነትን በመቀነስ ገቢው በቀጥታ ወደ ካዝናው እንዲገባ አስችሏል፤ ለምሳሌ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል ብቻ መሆኑ ሕገ-ወጥ ዝውውርን በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።
በተጨማሪም ብሔራዊ ባንክ ለገንዘብ ሕትመትና ጥገና የሚያወጣውን በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ ለማዳን የተቻለ ሲሆን፣ የገንዘብ ምንጭና መድረሻው ስለሚታወቅ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመከላከልና የጥቁር ገበያን ለመቆጣጠር የተሻለ አቅም ተፈጥሯል።
ባጠቃላይ ይህ ዕድገት ወደ ዘመናዊ ኢኮኖሚ ለምናደርገው ጉዞ ትልቅ ሞተር እየሆነ ሲሆን፣ ዘርፉ በፖሊሲ መደገፉን መቀጠሉ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ ከሆኑት የዲጂታል ምጣኔ ሀብት ተጠቃሚ ሀገራት ተርታ እንደሚያሰልፋት ይጠበቃል።
በላሉ ኢታላ
#digitalethiopia #telebirr #cashlesssociety #digitaleconomy #ethiopianbroadcastingcorporation Ethiopian Broadcasting Corporation

የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት እና ምልጃቸው አይለየን🙏
እናታቸው አላቀፈቻችውም፤ ጡትም አልጠቡም
ወላጆቻቸው ልጅ አጥተው ሠላሳ ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ታላቅ ክብር ያለው ልጅ እንደምትወልድ የሚናገር ድምጽ ሰማች፡፡ በመጋቢት 29 ቀን ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ቀን ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ ግብጽ ንሂሳ በምትባል ቦታ ወለደች፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ “የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን” አላት፡፡ ሕፃኑ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገደ፡፡ “ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን” አለ፡፡ ከዚህ በኋላ እናታቸው አላቀፈቻችውም፤ ጡትም አልጠቡም፡፡
ሦስት ዓመት ሲሞላቸውም ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ ሕፃኑን ከእናቱ ክንድ ወስዶ እስከ ሰባቱ ሰማይ አውጥቶ በሥሉስ ቅዱስ ፊት አቅርቦት አስባረከው፡፡ እመቤታችን፣ ቅዱሳንም ሁሉ ባረኩት፡፡ አምላካችን እግዚአብሔርም አጸናው አበረታው፡፡ ከዚህም በኋላ መልአኩ አባ ዘመደ ብርሃን ወዳለበት ገዳም አወረደው እርሱም አስተምሮ ካሳደገው በኋላ ዲቁና በኋላም ምንኩስናና ቅስና ሰጠው፡፡ ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በጾም በጸሎት ተጠምደው በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ የተአምራትና የፈውስ ሀብት ተሰጣቸው፡፡ ከሰው ተለይተው ከአናብስትና ከአናብርት ጋር እንዲኖሩ፣ እንስሳቱም የእግራቸውን ትቢያ እየላሱ እንደሚኖሩ ነገራቸው፡፡
ሰውነታቸውም ሁሉ በጠጉር ተሸፈነ፡፡ በፍጹም ተጋድሎም ከኖሩ በኋላ በቀንና በሌሊት የክርስቶስን መከራ እያሰቡ ስለኃጥአንም ጥፋት እንባቸውን እያፈሰሱ ይጸልዩ ነበር፡፡ ሦስት መቶ ዓመት ሲሆናቸውም ቅዱስ ገብርኤል በነፋስ ሠረገላ ጭኖ ከ60 አንበሶችና ከ60 ነብሮች ጋር ወደ ኢትዮጵያ አምጥቶ ምድረ ከብድ አደረሳቸው፡፡ ደብር ቅዱስ ወደሚባለው ዝቋላም ሔደው የኢትዮጵያን ሕዝብ ማርልኝ ብለው ለአንድ መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው ስጋቸው እስኪያልቅ ጸልየዋል፡፡ ጌታችንም መጥቶ ኢትዮጵያን ምሬልሀለሁ ብሎ ታላቅ ቃል ኪዳን ሰጣቸው፡፡ አባታችን በሀገራችን 262 ዓመታት ኖረው በተወለዱ በ562 ዓመታቸው በዕለተ እሁድ አርፈዋል፡፡ በቅዱሳኑ ምልጃ ያመንን ገዳማውያንን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) በ97ኛው ደቂቃ (90+7) ላይ ኮሪያውያን ቼኮች የጎል ዕድል ሊያደርጓት የሚችሉትን ኳሷን ከግብ ክልላቸው አጽድተው በማራቅ የድል አፋፋቸው ላይ ሲደርሱ፣ ዋናው ዳኛ የጨዋታውን ማጠናቀቂያ ፊሽካ ነፍተዋል!
በእውነትም እጅግ ማራኪ እና ፉክክር የታከለበት ጨዋታ የነበረ ሲሆን፣ በተለይም በሁለተኛው አጋማሽ ልዩ ድምቀት አግኝቶ ነበር። ቼክ ሪፐብሊኮች በሁለተኛው አጋማሽ ከመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ እጅግ የተሻለ ብቃት አሳይተዋል፤ ይሁን እንጂ በአጠቃላይ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ደቡብ ኮሪያ የተሻለች ቡድን ነበረች። ኮሪያውያኑ ወደ ፊት በማጥቃት ሂደታቸው ባሳዩት ጥራት፣ እንዲሁም ጨዋታን በአንዴ መቀየር የሚችሉ ተጠባባቂ ተጫዋቾችን ወደ ሜዳ በማስገባት ብልጫውን ወስደው ጨዋታውን በበላይነት አጠናቀዋል።
መጀመሪያ ግብ ተቆጥሮባቸው ቼክ ሪፐብሊኮች መሪ ቢሆኑም... ኮሪያውያኑ ተስፋ ባለመቁረጥ ከኋላ ተነስተው (Comeback) 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ጣፋጭ ድል ተቀዳጅተዋል።
ይህ ድል ለደቡብ ኮሪያ ምን ያህል ትልቅ ትርጉም እንዳለው በግልጽ ማየት ይቻላል። በውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታ ላይ እነዚህን ወሳኝ ሦስት ነጥቦች ማሳካት፣ ቡድኑ ወደ ቀጣዩ ዙር (ጥሎ ማለፍ) ለማለፍ የሚያደርገውን ጉዞ እጅግ ብሩህ እና ሰፊ እድል የሚሰጠው ይሆናል።

2 days ago
23ኛው የዓለም ዋንጫ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ ያዘጋጁት የ2026 የዓለም ዋንጫ ውድድር መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በሜክሲኮ አዝቴካ ስታዲየም መካሄድ ጀምሯል፡፡
የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት ሀገራት የሚያዘጋጁት ሲሆን ÷ በመርሐ ግብሩ 48 ሀገራት ይሳተፋሉ፡፡
በአጠቃላይ 1 ሺህ 248 ተጫዋቾች የሚሳተፉበት ውድድሩ÷ በርካታ ከዋክብትም የመጨረሻ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እስካሁን ድረስ 8 ሀገራት ብቻ የዓለም ዋንጫ ያሸነፉ ሲሆን ÷ ብራዚል፣ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ አርጀንቲና፣ ፈረንሳይ፣ ኡራጓይ፣ እንግሊዝ እና ስፔን በመድረኩ ሻምፒዮን መሆን የቻሉ ሀገራት ናቸው፡፡
በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ከአዘጋጆቹ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነቸው ሜክሲኮ ምሽት 4 ሰዓት ከደቡብ አፍሪካ ትገናኛለች፡፡
ሜክሲኮ ለ18ኛ ጊዜ ተጋጣሚዋ ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ለ4ኛ ጊዜ በመድረኩ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡
ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በፈረንጆቹ 2010 ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ ውድድር የመክፈቻ ጨዋታ ላይ መገናኘታቸውም ይታወሳል፡፡

የ«በዓለ ኃምሳ» በዓል በአድዋ ሙዚየም ሊከበር ነው
📌''እኔ ባልሄድ አጽናኙ(ጰራቅሊጦስ) ወደ እናንተ አይመጣምና'' ጌታ ኢየሱስ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል እና አርሞኒየም ተሃድሶ ቤተክርስቲያን በጋራ በመተባበር “ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ” በሚል ርዕስ በሚከበረው የበዓለ ኃምሳ በዓልን በማስመልከት በመጪው ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ ሙዚየም አዳራሽ በልዩ ሁኔታ እንደሚያከብሩ አስታወቁ። በዓሉን አስመልክቶ የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ቅዱስ ጴጥሮስ የነቢዩ ኢዩኤልን ትንቢት በመጥቀስ (ኢዩኤል 2፡28-32)፣ በዛው ክፍል የሆነው ድንቅና ተዓምራቱ የሆነው በመንፈስ ቅዱስ መውረድ እንደሆነ ገልጾ እና ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ በመመስከር የመጀመሪያውን ስብከት ሰብኮ በዚያች ቀን ወደ ሦስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መጠመቃቸውን ይናገራል።
የአርሞኒየም ተሃድሶ ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ የሆኑት ፓስተር ሄኖክ መንግስቱ(ሲንገሌ) በሰጡት መግለጫ፣ ይህ በዓል ከዚህ ቀደም በየአጥቢያ ቤተክርስቲያኑ በተናጠል ይከበር እንደነበር አስታውሰው፣ የዘንድሮው ግን አማኞች በአንድነት ሆነው መንፈስ ቅዱስን የሚያመሰግኑበት እና ግንዛቤ የሚያገኙበት የጋራ መድረክ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን አብራርተዋል። አክለውም በዓሉ በመጽሐፍ ቅዱስ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ላይ እንደተጻፈው ቤተክርስቲያን የተወለደችበት፣ ከ3,000 በላይ ነፍሳት ወደ ጌታ የመጡበት እና አማኞች ወንጌልን በድፍረት ለመስበክ ኃይል ን የተቀበሉበት ታሪካዊ ዕለት መሆኑን አውስተዋል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስልን በመወከል ንግግር ያደረጉት ፓስተር አሸብር ከተማ፣ በዓለ ኃምሳ የአንድ ቀን የስነ-ስርዓት ክንውን ብቻ ሳይሆን ከወንጌል ሥራ ጋር ተያይዞ ዓመቱን ሙሉ ሊታሰብ የሚገባው ትልቅ በዓል መሆኑን ገልጸዋል። በሐዋርያት ዘመን የነበረችው ቤተክርስቲያን በ24 ዓመታት ውስጥ ዓለምን በወንጌል መድረስ የቻለችው በመንፈስ ቅዱስ መውረድ ባገኘችው ሃይል መሆኑን ያነሱት ፓስተር አሸብር፣ ይህ በዓል የዶክትሪን ጉዳይ ሳይሆን አብያተ ክርስቲያናት በቅድስና እና በአንድነት የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋት የሚተጉበት መድረክ መሆኑን አስምረውበታል።
በመጨረሻም አማኞች የተሰጣቸውን ዕድል በመጠቀም በበጎ ፈቃድ እና በቅን ልቦና ተባባሪ በመሆን የበኩላቸውን እንዲወጡ ወቅታዊ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በዕለቱ ከሚከናወኑት አበይት መርሃ ግብሮች መካከል ቃለ እግዚአብሔር ፣የዝማሬ እና የአምልኮ ጊዜ እንዲሁም ስለ በዓለ ኃምሳ ታሪካዊና መንፈሳዊ ፋይዳ ሰፋ ያለ ውይይት የሚካሄድበት ድንቅ ጊዜ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
📌''እኔ ባልሄድ አጽናኙ(ጰራቅሊጦስ) ወደ እናንተ አይመጣምና'' ጌታ ኢየሱስ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል እና አርሞኒየም ተሃድሶ ቤተክርስቲያን በጋራ በመተባበር “ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ” በሚል ርዕስ በሚከበረው የበዓለ ኃምሳ በዓልን በማስመልከት በመጪው ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ ሙዚየም አዳራሽ በልዩ ሁኔታ እንደሚያከብሩ አስታወቁ። በዓሉን አስመልክቶ የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ቅዱስ ጴጥሮስ የነቢዩ ኢዩኤልን ትንቢት በመጥቀስ (ኢዩኤል 2፡28-32)፣ በዛው ክፍል የሆነው ድንቅና ተዓምራቱ የሆነው በመንፈስ ቅዱስ መውረድ እንደሆነ ገልጾ እና ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ በመመስከር የመጀመሪያውን ስብከት ሰብኮ በዚያች ቀን ወደ ሦስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መጠመቃቸውን ይናገራል።
የአርሞኒየም ተሃድሶ ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ የሆኑት ፓስተር ሄኖክ መንግስቱ(ሲንገሌ) በሰጡት መግለጫ፣ ይህ በዓል ከዚህ ቀደም በየአጥቢያ ቤተክርስቲያኑ በተናጠል ይከበር እንደነበር አስታውሰው፣ የዘንድሮው ግን አማኞች በአንድነት ሆነው መንፈስ ቅዱስን የሚያመሰግኑበት እና ግንዛቤ የሚያገኙበት የጋራ መድረክ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን አብራርተዋል። አክለውም በዓሉ በመጽሐፍ ቅዱስ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ላይ እንደተጻፈው ቤተክርስቲያን የተወለደችበት፣ ከ3,000 በላይ ነፍሳት ወደ ጌታ የመጡበት እና አማኞች ወንጌልን በድፍረት ለመስበክ ኃይል ን የተቀበሉበት ታሪካዊ ዕለት መሆኑን አውስተዋል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስልን በመወከል ንግግር ያደረጉት ፓስተር አሸብር ከተማ፣ በዓለ ኃምሳ የአንድ ቀን የስነ-ስርዓት ክንውን ብቻ ሳይሆን ከወንጌል ሥራ ጋር ተያይዞ ዓመቱን ሙሉ ሊታሰብ የሚገባው ትልቅ በዓል መሆኑን ገልጸዋል። በሐዋርያት ዘመን የነበረችው ቤተክርስቲያን በ24 ዓመታት ውስጥ ዓለምን በወንጌል መድረስ የቻለችው በመንፈስ ቅዱስ መውረድ ባገኘችው ሃይል መሆኑን ያነሱት ፓስተር አሸብር፣ ይህ በዓል የዶክትሪን ጉዳይ ሳይሆን አብያተ ክርስቲያናት በቅድስና እና በአንድነት የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋት የሚተጉበት መድረክ መሆኑን አስምረውበታል።
በመጨረሻም አማኞች የተሰጣቸውን ዕድል በመጠቀም በበጎ ፈቃድ እና በቅን ልቦና ተባባሪ በመሆን የበኩላቸውን እንዲወጡ ወቅታዊ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በዕለቱ ከሚከናወኑት አበይት መርሃ ግብሮች መካከል ቃለ እግዚአብሔር ፣የዝማሬ እና የአምልኮ ጊዜ እንዲሁም ስለ በዓለ ኃምሳ ታሪካዊና መንፈሳዊ ፋይዳ ሰፋ ያለ ውይይት የሚካሄድበት ድንቅ ጊዜ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
2 days ago
12ኛ ዙር የደም ልገሳ መርሃ ግብር
የዓለም የደም ለጋሾች ቀን እና
የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች 3ኛ ዓመት በዓል ማክበር
📅 ሰኔ 6 እና 7, 2018 ዓ.ም.
📍 በኢትዮጵያ 20 + ከተሞች
አንድ የደም ልገሳ እስከ ሦስት ሰዎች ሕይወት ሊያድን ይችላል። በየቀኑ በሆስፒታሎቻችን ውስጥ ለቀዶ ሕክምና፣ ለአደጋ ተጎጂዎች፣ ለካንሰር ታማሚዎች፣ ለእናቶች እና ለሌሎች በርካታ ሕሙማን ደም በአስቸኳይ ያስፈልጋል።
ይህ 12ኛው ዙር የደም ልገሳ መርሃ ግብር የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች ለ3 ዓመታት ሲያከናውኑት የቆየውን የሰብዓዊነት ጉዞ የሚያከብር ሲሆን፣ በዓለም የደም ለጋሾች ቀን ላይም ለሕይወት አዳኝ ለጋሾች የምስጋና መልዕክት ያስተላልፋል።
እርስዎ የሚለግሱት ደም ለአንድ ቤተሰብ ተስፋ፣
ለአንድ ታማሚ ሕይወት፣
ለአንድ እናት ፈገግታ፣
ለአንድ ልጅ ነገን ሊሰጥ ይችላል።
🤝 ሁላችንም በጎ ፈቃደኞች፣ ወጣቶች፣ ቤተሰቦች፣ ተቋማት እና ማኅበረሰቡ በአጠቃላይ በዚህ ታላቅ የሕይወት ማዳን ተግባር እንዲሳተፉ በክብር እንጋብዛለን።
🩸 ደም መለገስ ሕይወት መስጠት ነው!
ኑ! በደማችን አዲስ ታሪክ እንፃፍ! ❤️🩸
#worldblooddonorday #የደም_ልገሳ #ተስፋ_አዲስ_ቤተሰቦች #donatebloodsavelives #20ከተሞች_አንድ_ዓላማ #ሕይወትን_እናድን
የዓለም የደም ለጋሾች ቀን እና
የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች 3ኛ ዓመት በዓል ማክበር
📅 ሰኔ 6 እና 7, 2018 ዓ.ም.
📍 በኢትዮጵያ 20 + ከተሞች
አንድ የደም ልገሳ እስከ ሦስት ሰዎች ሕይወት ሊያድን ይችላል። በየቀኑ በሆስፒታሎቻችን ውስጥ ለቀዶ ሕክምና፣ ለአደጋ ተጎጂዎች፣ ለካንሰር ታማሚዎች፣ ለእናቶች እና ለሌሎች በርካታ ሕሙማን ደም በአስቸኳይ ያስፈልጋል።
ይህ 12ኛው ዙር የደም ልገሳ መርሃ ግብር የተስፋ አዲስ ቤተሰቦች ለ3 ዓመታት ሲያከናውኑት የቆየውን የሰብዓዊነት ጉዞ የሚያከብር ሲሆን፣ በዓለም የደም ለጋሾች ቀን ላይም ለሕይወት አዳኝ ለጋሾች የምስጋና መልዕክት ያስተላልፋል።
እርስዎ የሚለግሱት ደም ለአንድ ቤተሰብ ተስፋ፣
ለአንድ ታማሚ ሕይወት፣
ለአንድ እናት ፈገግታ፣
ለአንድ ልጅ ነገን ሊሰጥ ይችላል።
🤝 ሁላችንም በጎ ፈቃደኞች፣ ወጣቶች፣ ቤተሰቦች፣ ተቋማት እና ማኅበረሰቡ በአጠቃላይ በዚህ ታላቅ የሕይወት ማዳን ተግባር እንዲሳተፉ በክብር እንጋብዛለን።
🩸 ደም መለገስ ሕይወት መስጠት ነው!
ኑ! በደማችን አዲስ ታሪክ እንፃፍ! ❤️🩸
#worldblooddonorday #የደም_ልገሳ #ተስፋ_አዲስ_ቤተሰቦች #donatebloodsavelives #20ከተሞች_አንድ_ዓላማ #ሕይወትን_እናድን
2 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ሐሙስ ዕለት ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት፣ በግጭት ወይም በጭቆና ምክንያት በግዴታ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር በአስር ዓመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2025 መቀነሱን አስታወቀ። ይሁን እንጂ፣ 118 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች አሁንም ከመኖሪያ ቀያቸው እና ከሀገራቸው ተፈናቅለው እንደሚገኙ በመግለጽ፣ ቁጥሩ አሁንም እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ተቋሙ አስጠንቅቋል።
የኮሚሽኑ የ2025 ዓለም አቀፍ አዝማሚያዎች ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ በዓመቱ መጨረሻ በግጭት፣ በዓመጽ ወይም በጭቆና ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 117.8 ሚሊዮን ደርሷል። ይህ አሃዝ ስደተኞችን፣ ጥገኝነት ጠያቂዎችን፣ በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎችን እና ዓለም አቀፍ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውን ሌሎች ቡድኖችን ያጠቃልላል። የኮሚሽኑ ዋና የስታስቲክስ ባለሙያ ታሬክ አቡ ቻባክ፣ ይህ ቁጥር ሊቀንስ የቻለው በርካታ ሰዎች ወደ ሀገራቸው በመመለሳቸው እና ብዙ ስደተኞች በተጠለሉበት ሀገር ዜግነት በማግኘታቸው መሆኑን አብራርተዋል። የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ባርሃም ሳሊህ በበኩላቸው፣ በአብዛኛው በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉት ሰዎች አሃዝ አሁንም ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አስገንዝበዋል።
ምንም እንኳን ከቀዳሚው ዓመት የሦስት በመቶ ቅናሽ ቢታይም በ2025 ብቻ 5.4 ሚሊዮን ሰዎች ጥገኝነት ፍለጋ ዓለም አቀፍ ድንበሮችን አቋርጠዋል። ባለፈው ዓመት ከተመዘገቡት 41.6 ሚሊዮን ስደተኞች መካከል ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዙት ሕፃናት ሲሆኑ፣ አብዛኞቹ ስደተኞች ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ ይኖራሉ። በተለይም ኮሎምቢያ፣ ጀርመን እና ቱርክ እያንዳንዳቸው ከሁለት ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን ተቀብለው አስተናግደዋል። ከአስር ስደተኞች መካከል ሰባቱ ከአምስት ዓመታት በላይ በስደት የኖሩ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ በድሃ ሀገራት በሚገኙ ሰፋፊ ካምፖች ውስጥ ተወስነው ይገኛሉ። ኮሚሽነር ሳሊህ፣ የሰብአዊ ዕርዳታ የሰዎችን ሕይወት ማትረፍ ቢችልም፣ ትውልዶችን ላልተወሰነ ጊዜ ለመደገፍ የታሰበ አለመሆኑን ገልጸው፣ ተቋማቸው በሰብአዊ ዕርዳታ ላይ ጥገኛ የሆኑ የረጅም ጊዜ ስደተኞችን ቁጥር እ.ኤ.አ. በ2035 በግማሽ ለመቀነስ ማቀዱን ተናግረዋል።
ሪፖርቱ አክሎም ባለፈው ዓመት በሀገራቸው ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 68.7 ሚሊዮን መድረሱን ያሳያል። በሱዳን ያለው ቀጣይነት ያለው ጦርነት 9.1 ሚሊዮን ሰዎችን በማፈናቀል በዓለም ትልቁን የውስጥ መፈናቀል አስከትሏል። ኮሎምቢያ፣ ሶሪያ፣ የመን እና አፍጋኒስታንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ይገኙባቸዋል። የ2026 የትንበያ መረጃዎችም ከዚህ የተሻለ ተስፋ አላሳዩም። በየካቲት ወር የተቀሰቀሰውን የኢራን ጦርነት ተከትሎ፣ እስከ መጋቢት ወር ድረስ በኢራን ውስጥ 3.2 ሚሊዮን ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን፣ በግንቦት ወር አጋማሽ ደግሞ አንድ ሚሊዮን ሰዎች በሊባኖስ ውስጥ ተፈናቅለዋል። ይህ ሁኔታ ተቀባይነት የሌለው እና አዲስ የተለመደ ክስተት እንዳይሆን መከላከል እንደሚያስፈልግ ኃላፊው አሳስበዋል።
በ2025 ወደ ሀገራቸው ከተመለሱት 4.4 ሚሊዮን ስደተኞች ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት ወደ ሶሪያ፣ አፍጋኒስታን እና ሱዳን ያቀኑ ናቸው። ይህ ቁጥር ተቋሙ መረጃ መሰብሰብ ከጀመረበት ባለፉት ስድስት አሥርት ዓመታት ውስጥ ሁለተኛው ከፍተኛ ቁጥር ነው። በተመሳሳይ፣ 10.3 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል። ነገር ግን ኃላፊው፣ ብዙዎቹ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት በጫና እና ክብር ያለው ሕይወት ለመምራት የሚያስችል መሠረተ ልማት በሌለበት ሁኔታ መሆኑን አስጠንቅቀዋል። በተጨማሪም፣ ዜግነት የሌላቸው ሰዎች (በተለይም የሚየንማሩ ሮሂንጋዎች) በባንግላዲሽ፣ አይቮሪኮስት፣ ታይላንድ እና ምያንማር በብዛት የሚገኙ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ዜግነት ማግኘት የቻሉት 46 ሺህ ብቻ ናቸው።
በ2024 ከነበረው 188 ሺህ የስደተኞች ሰፈራ አሃዝ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን የገለጹት ሳሊህ፣ መንግሥታት ህጋዊ የሰፈራ መንገዶችን እንዲያስፋፉ ጠይቀዋል። አክለውም፣ "እያንዳንዱ አደገኛ የባህር ጉዞ እና በበረሃ ውስጥ የሚከሰት ሞት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ውድቀት ማሳያ ነው፤ የዚህ ውድቀት ሰብአዊ ዋጋ የሚለካው በስታትስቲክስ ሳይሆን በሰዎች ሕይወት ነው" ብለዋል።

በዲጂታሉ ዓለም የጀመርነው ታሪካዊ ምዕራፍ ብሔራዊ ርዕያችንን የምናፋጥንበት መነሻ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዲጂታሉ ዓለም በልኩ ለመዘጋጀት የጀመርነው ታሪካዊ ምዕራፍ የጉዟችን ማብቂያ ሳይሆን ብሔራዊ ርዕያችንን ይበልጥ የምናፋጥንበት መነሻ ነው አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ በሦስት ዓመታት ውስጥ ለማሳካት የታቀደውን የ5 ሚሊየን ኮደሮች ግብ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።
የ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደሮች ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም መጀመሩን አስታውሰው፥ በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣ በመረጃ ትንተና፣ በአንድሮይድ ሶፍትዌር ልማትና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡
በዚህም 5 ሚሊየን 5ሺህ 146 ሰልጣኞች መመዝገባቸውን ገልጸው፥ ከእነዚህም ውስጥ ከ3 ሚሊየን በላይ ሰልጣኞች ስልጠናውን አጠናቅቀዋል ነው ያሉት።
ይህ ስኬት የሕዝባችንን ቁርጠኝነት እና ወሰን የሌለው አቅም ማረጋገጫ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም. ድረስ የሰልጣኞችን ቁጥር 7 ሚሊየን ለማድረስ የተሰነቀውን ግብ ለማሳካት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዚህ ብሔራዊ ተልዕኮ አካል እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ለወጣት ተማሪዎቻችን መጭው የክረምት ወቅት ትልቅ ዕድላችሁ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በዚህ የክረምት ወቅት ስልጠናውን በመውሰድ ተማሪዎች ብቻ ሳትሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላችሁ የዲጂታል መሪዎች እንድትሆኑ አሳስባለሁ ነው ያሉት።
ሥልጠናዎቹ ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጡ ሲሆን የምስክር ወረቀቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ:
ethiocoders.et/

የኢትዮጵያ ቱሪዝም፦ ከአቧራ የተነሱ ጸጋዎች፣ ለዕለት ጉርስ የሆኑ ዐሻራዎች!
**************
የዕለቱ መልዕክት
ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ የታየው አዲስ ተነሳሽነትና ስር ነቀል መዋቅራዊ ሽግግር፣ ሀገራችን ለዘመናት በአቧራ ተሸፍነው የቆዩ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ጸጋዎቿን ለሕዝብ ጥቅምና ለሀገር ግንባታ የምታውልበትን አዲስ ምዕራፍ ፈጥሯል።
ይህ ለውጥ ቱሪዝምን ከተራ የኢኮኖሚ ዘርፍነት ባሻገር የብሔራዊ አንድነት፣ የሰላም፣ የብዝኃነት መገናኛና የሀገር ገጽታ ግንባታ ታላቅ መሣሪያ አድርጎታል።
ለ16 ዓመታት ሳይሻሻል የቆየውን የቱርዝም ፖሊሲ በአዲስ በመተካት ዘርፉን በሚኒስቴር ደረጃ ማደራጀት፣ የዲጂታል አሰራርንና የኢ-ቪዛ ቴክኖሎጂን መተግበር እንዲሁም የስብሰባና ኤግዚቢሽን ስትራቴጂን መቅረጽ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ አድርጓታል።
እንደ “ገበታ ለሸገር”፣ “ገበታ ለሀገር” እና “ገበታ ለትውልድ” ያሉ ታላላቅ ፅንሰ-ሀሳቦች በተግባር ተተርጉመው በአጭር ጊዜ ውስጥ አዳዲስ የመስህብ ስፍራዎችን መፍጠር ችለዋል።
በአዲስ አበባ የተከናወነው ሰፊ የኮሪደር ልማትም የሀገራችን ዋና መግቢያ በር ውበትና ምቾት በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል። ፈታኝ በሆኑ ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ሁኔታዎች ውስጥም ቢሆን እነዚህ ስልታዊ የልማት ፕሮጀክቶች የኢኮኖሚውን ትንሳኤ የሚያፋጥኑ ትልልቅ በረከቶችን ይዘውልን መጥተዋል።
የዚህ ሁሉን አቀፍ ጥረት ውጤትም ተጨባጭ ስኬት አስገኝቷል። ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የውጭ ቱሪስቶች ቁጥር ከ781 ሺህ ወደ 1.3 ሚሊዮን ማደጉ፣ የውጭ ምንዛሪ ገቢን ከማሳደጉም በላይ ለሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል ፈጥሯል።
እንጦጦ ፓርክ፣ ሳይንስ ሙዚየም፣ ታላቁ ብሔራዊ ቤተመንግስት፣ ደንቢና ጎሪጎራ ኢኮ ሪዞርቶች፣ የሃላላ ኬላ እና የኮይሻ ፓርክ "ከቅርሱ ወደ ቁርሱ" የሚለውን መርህ በተግባር ያሳዩ ናቸው። ኢትዮጵያ በዓለም ቱሪዝም ድርጅት ልዩ ዕውቅና ማግኘቷና በአንድ ዓመት ውስጥ ሦስት አዳዲስ ቅርሶችን በዩኔስኮ ማስመዝገቧም የዚሁ ታሪካዊ ስኬት አካል ነው።
ይሁን እንጂ የተመዘገቡት ስኬቶች የዛሬ ጥንካሬዎቻችን ማሳያ እንጂ የነገው ስልታዊ ጉዟችን ማዘናጊያ አይደሉም። ሀገራችን በቀጣይ ዓመታት የውጭ ቱሪስት ፍሰቱን እስከ 7.3 ሚሊዮን ለማድረስ የሰነቀችው ግዙፍ ብሔራዊ ራዕይ ትልቅና የተቀናጀ ሥራን ይጠይቃል።
ይህንን ታላቅ ግብ ለማሳካት የመንግሥት፣ የግል ዘርፍና የኅብረተሰቡ የተቀናጀ አጋርነት ወሳኝ ነው። የመሠረተ ልማት አውታሮችን በተለይም መንገዶችን፣ አስተማማኝ ኤሌክትሪክን፣ ንጹህ ውሃንና የቴሌኮም ኔትወርኮችን በመዳረሻዎች አካባቢ ማሻሻልና ደህንነቱ የተጠበቀ ምቹ ሁኔታን መፍጠር የቀዳሚነት ደረጃ ሊሰጠው ይገባል።
በተጨማሪም የዲጂታል ቴክኖሎጂን፣ ዘመናዊ የዳታ አያያዝንና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) በመጠቀም አገልግሎቶችን ማዘመን፤የጎብኚዎችን ልምድ መጠቀምና የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን መደገፍና ማበረታታት ይኖርብናል።
ቱሪዝም ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዜጎች ኑሮ መሻሻል ያለውን የማይተካ ሚና በመገንዘብ፣ የተጀመረው አገራዊ የልማት ዐሻራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የሀገራችን ራዕይ እውን እንዲሆን ሁላችንም በጋራ ልንረባረብ ይገባል።
በብሔራዊ ዕድገታችንና በትውልድ ገጽታ ግንባታችን ላይ የሚጋረጡ ማናቸውንም ተግዳሮቶች የምንሻገረው በጀመርነው የልማት መስመር ላይ በጽናትና በአንድነት ስንቆም ብቻ ነው።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

3 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ ትልቁ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነት የሆነው የደቡብ ባፕቲስት ጉባኤ (ሳውዘርን ባፕቲስት ኮንቬንሽን)፣ ሴቶች በፓስተርነት እንዳያገለግሉ በይፋ የሚከለክለውን ሕገ-ደንብ ለማጽደቅ ረቡዕ ዕለት በከፍተኛ ድምፅ ወስኗል። ይህ ውሳኔ በቤተክርስቲያኒቱ ወግ አጥባቂ ምዕመናን ዘንድ ስብከት የወንዶች ብቻ መብትና ኃላፊነት መሆኑን ግልጽ መልእክት ያስተላለፈ ነው።
በፍሎሪዳ ግዛት ኦርላንዶ ከተማ በተካሄደው ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ከተገኙት ተወካዮች መካከል 6,028ቱ ማሻሻያውን ሲደግፉ፣ 2,026ቱ ብቻ ተቃውመዋል። ይህ ከሦስት እጅ አንድ የሆነው የድምፅ ልዩነት፣ ሕጉን ለማሳለፍ ከሚጠየቀው የሁለት ሦስተኛ አብላጫ ድምፅ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል። ይሁን እንጂ ማሻሻያው በቤተክርስቲያኒቱ ሕገ-መንግሥት ውስጥ በቋሚነት እንዲካተት፣ በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው ተመሳሳይ ጉባኤ ላይ የሁለት ሦስተኛ ድምፅ ማግኘት ይኖርበታል።
የሕግ ማሻሻያውን ያቀረቡት በኬንታኪ የሚገኘው የነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ፕሬዝዳንት አልበርት ሞህለር፣ ውሳኔው ቤተ እምነቱ ያለውን አቋም በእውነት፣ በአንድነት እና በጽኑ እምነት በግልጽ ለማሳየት የተፈጠረ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ብለዋል። "በለዘብተኛ (ሊበራል) እና በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ወንጌላውያን መካከል ትልቅ የልዩነት መስመር አለ፤ ይህንንም በዚህ ጉዳይ ላይ በግልጽ ማየት ይቻላል። የለዘብተኛ ቤተ እምነቶች አቅጣጫ ግልጽ ነው" በማለት ተናግረዋል።
በጉባኤው ላይ ለማሻሻያው የተሰማው ብቸኛ የተቃውሞ ድምፅ ከሳውዝ ካሮላይናው ፓስተር ዳግ ማይዝ የመጣ ነበር። ይሁን እንጂ የእሳቸውም ተቃውሞ ሴት ፓስተሮችን ከመደገፍ የመነጨ ሳይሆን፣ ቤተ እምነቱ አስቀድሞ ሴት ፓስተሮችን የሚሾሙ አጥቢያዎችን ከማኅበሩ የሚያስወጣበት አሰራር ስላለው ይህ አዲስ ሕገ-መንግስታዊ ማሻሻያ አያስፈልግም በሚል ነው። ቤተ እምነቱ ከዚህ ቀደም በካሊፎርኒያ የሚገኘውን ታዋቂውን የሳድልባክ ቤተክርስቲያንን ጨምሮ፣ ሴቶች በዋና ፓስተርነት የሚያገለግሉባቸውን አጥቢያዎች ከአባልነት ማገዱ ይታወሳል።
አዲሱ የማሻሻያ ቃል፣ ማንኛውም የጉባኤው አባል የሆነ አጥቢያ አንዲትን ሴት በፓስተርነት፣ በሽማግሌነት ወይም በተለይም ለተሰበሰበው ምዕመን ቃሉን እንድትሰብክ መሾም ወይም ማጽደቅ እንደሌለበት በጥብቅ ያስገድዳል። የቤተ እምነቱ መሪዎች ይህንን ውሳኔያቸውን የፓስተርነትን አገልግሎት ለወንዶች ብቻ ከሚገድቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር ያያይዙታል።
በሌላ በኩል ከተለያዩ የባፕቲስት አጥቢያዎች ጋር የሚሠራው የባፕቲስት ሴት አገልጋዮች ማኅበር በውሳኔው በእጅጉ ማዘኑን ገልጿል። ማኅበሩ ባወጣው መግለጫ፣ "በዚህ ድምፅ አሰጣጥ፣ ከውሳኔው ጀርባ ባለው የጥላቻ ቅስቀሳ እና ውሳኔው በሚወክለው ጎጂ የነገረ መለኮት ትርጓሜ ለተጎዱ ሴት አገልጋዮች አጋርነታችንን እንገልጻለን። ሴት አገልጋዮች መከበር እና የእግዚአብሔርን ጥሪ የመከተል ዕድል ሊሰጣቸው ይገባል፤ በዚህ ውሳኔ መሰረታዊ ነጻነታቸውን በመነጠቃቸው ልባችን ተሰብሯል" ብሏል።
ከዚህ ታሪካዊ ውሳኔ ጎን ለጎን፣ ማክሰኞ ዕለት በተካሄደው ምርጫ የፍሎሪዳው ፓስተር ዊሊ ራይስ 58 በመቶ ድምፅ በማግኘት የቤተ እምነቱ አዲሱ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል። ራይስ ይህንን ሴት ፓስተሮችን የሚከለክለውን የሕግ ማሻሻያ በጽኑ ከሚደግፉ እና ቤተ እምነቱ በዘር፣ በጾታ እና በስደተኞች ዙሪያ ከመጠን ያለፈ የነጻነት አመለካከት እያራመደ ነው ብለው ከሚሞግቱ ወግ አጥባቂ መሪዎች መካከል አንዱ መሆናቸው ውሳኔውን ይበልጥ አጠናክሮታል።

በሶሻል ሚዲያ ታዋቂ በሆኑ ሦስት ግለሰቦች ላይ የስም ማጥፋት ክስ ተመሠረተ፤ የባንክ አካውንታቸውም እንዲታገድ ተወሰነ
በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በስፋት የሚታወቁት ወገነ አበበ ፀጋዬ፣ ሌዊ አጎናፍር ወዳጆ እና ገዛኸኝ ተረሳ ቤኛ (አዎንታ በርሲሳ) በስም ማጥፋት ወንጀል የተመሠረተባቸው የፍትሐብሔር ክስ ለሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ተቀጠረ።
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ የሆኑት ደጉ ታደለ ኮይራ ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሚ ኩራ ምድብ 8ኛ የፍትሐብሔር ችሎት ባቀረቡት ክስ፤ ከተከሳሾቹ ጋር ምንም ዓይነት የግልም ሆነ የሥራ ግንኙነት እንደሌላቸው ገልጸው፣ ላለፉት አራት ዓመታት በቲክቶክ ማኅበራዊ ሚዲያ በነፃ የሕግ ትምህርት በመስጠት የገነቡትን መልካም ስም ለማጥፋት ተከሳሾቹ ፎቶአቸውን በመጠቀም የሐሰት መረጃዎችን በየግል ገጻቸው ማሰራጨታቸውንና በሥራቸው ላይ ቀጥተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን አስረድተዋል።
ከሳሽ ከውል ውጪ በሚደርስ ኃላፊነት በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2044 መሠረት ለደረሰባቸው የስም ማጥፋት ጉዳት 150 ሺህ ብር የገንዘብ ካሳ እንዲከፈላቸው፣ ተከሳሾቹ ይፋዊ ይቅርታ ጠይቀው ማስተባበያ እንዲሠሩ፣ አስቀድሞ በገጻቸው ላይ የለቀቁትን መረጃ እንዲያጠፉ እና የሞራል ካሳ እንዲከፍሏቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱ የከሳሽን አቤቱታ መሠረት በማድረግ፣ ተለዋጭ ትዕዛዝ እስኪሰጥ ድረስ የተከሳሾች የባንክ ሒሳብ እስከ 50 ሺህ ብር ድረስ ታግዶ እንዲቆይ ለባንኮች እንዲጻፍ ባለፈው ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፣ የግራ ቀኙን ክርክር ለመስማትም ለሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏
መልአኩ ፋኑኤል ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መገባት🙏
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ገና በቅድስት ሐና ማሕጸን ከነበረችበት ወቅት ጀምሮ ተአምራት ታደርግ ነበር፡፡ አንድ አይኗን ያጣች ቤርሳቤህ የተባለች ሴት የሀናን መጽነስ ስትሰማ በደስታ ልትጎበኛት መጣች፡፡ ቅድስት ሐናን እንኳን ደስ አለሽ ብላ ሆዷን ከዳሰሰቻት በኋላ በዚያው እጇ ዓይኗን ብትነካው ዐይኗ በርቶላታል፡፡ ይህን ምሳሌ አደርገው ድውያን እየመጡ ሆዷን ዳሰው ይፈወሱ ነበር፡፡ በመካንነት የነበሩት ወላጆቿ ልጅ ከሰጣቸው ለቤተ እግዚአብሔር ሊሰጡ ስዕለት ገብተው በቅድስት ድንግል ማርያም መወለድ ፍሬ ሲያገኙ ዓለም ደግሞ የመድኃኒቱን እናት አጊኝቷል፡፡ እናታችን ቅድስት ሐና ጸንሳ ሳለች የአጓቷ ልጅ አርፎ እጅግ የአልጋውን ሸንኮር እየዞረች ስታለቅስ ከሞተበት ተነስቶ “የሰማይና የምድር ፈጣሪ አያት ሆይ ላንቺ ክብር ይገባሻል” ብሎ መስክሮ ተመልሶ አርፏል፡፡
አይሁድም “ቀድሞ የእነዚህ ዘር የነበሩ ዳዊትና ሰሎሞን አርባ፣ አርባ ዘመን ገዙን አሁን ከዚህች የሚወለድ ምን ሊያደርገን ነው?” ብለው በድንጋይ ሊወግሯት ተነሱ፡፡ የራማው ልዑል ቅዱሰ ገብርኤል ወደ ሊባኖስ ተራራ ወሰዳቸው፤ በእዚያም በጨለማ ውስጥ የነበረው ዓለም ብርሃን የሚያይባት፣ የእውነተኛው ጸሐይ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡ ኢያቄምና ሐና የተሳሉትን ስእለታቸው አስታውሰው በሦስት ዓመቷ ወስደው ለቤተ እግዚአብሔር ሲሰጧትም ካህኑ ዘካርያስ ስለምግቧ ተጨንቆ፤ ሕዝቡን ሰብስቦ ሳለ መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፤ ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ሊቀበል ሲቀርብ ወደ ላይ ራቀበት፡፡ በዚያ በተሰበሰቡትም ቢሞክሩ አልሆነም፡፡
ዘካርያስም ሐናን “እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ” አላት፤ በዚያም ጊዜ ቅድስት ማርያም እናቷን ስትከተል መልአኩ ፋኑኤል ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መግቧት፤ በክብር ዐረገ፡፡ ሊቀ ካህናቱና ሕዝቡም “የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር” ብለው ታህሣስ 3 ቀን ወደ ቤተ መቅደስ አስገቧት፡፡ ለ12 ዓመታትም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች በቤተ መቅደስ ኖረች፡፡ ይህችን ብርሃን፣ የብርሃን እናት ገዳማውያን አባቶችና እናቶች ዘወትር በጸሎታቸው ያስቧታል፡፡ ገዳማቸውን እናግዝ፣ በዓታቸውን እናጽና፡፡

4 days ago
ዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት የጉዞ ማዕረጉን በሽልማት እና በበጎ አድራጎት ተግባራት ደመደመ
#ethiopia | ለግማሽ ዓመት ያህል በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር የሰነበተው የዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በሸራተን አዲስ ሆቴል በተከናወነ ታላቅ የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ፍጻሜውን አግኝቷል።
በዕለቱ የክብር እንግዳ በመሆን የተገኙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ባንኩ ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በሀገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እና የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ላበረከተው ጉልህ ሚና ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ገዥው አክለውም ባንኩ የተጀመረውን ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርም በመደገፍ በመጪው የለውጥ ምዕራፍ ተወዳዳሪነቱን ይበልጥ እንዲያጠናክር አሳስበዋል።
የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በበኩላቸው የባንኩ የ30 ዓመታት የስኬት ጉዞ የደንበኞች፣ የባለድርሻ አካላትና የሠራተኞች የጋራ ጥረት ውጤት መሆኑን ገልጸው፣ ወደፊትም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ለሀገር እድገት የሚጠበቅበትን ሚና መወጣቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ባንኩ ከጥር 2018 ዓ.ም ጀምሮ የ30ኛ ዓመት ኤክስፖ፣ የኢኖቬሽን ወር እና የሴቶች አቅም ማጎልበቻ መርኃ ግብሮችን ጨምሮ በርካታ ዝግጅቶችን ሲያካሂድ መቆየቱ ተጠቅሷል።
በመዝጊያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባንኩ ለአሁኑ የስኬት ደረጃው እንዲበቃ ስያሜ ከመስጠት ጀምሮ ከፍተኛ ድጋፍ ላደረጉት ለክቡር ሸኽ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አላሙዲን ልዩ የዕውቅና ሽልማት ተበርክቷል።
ከተገቢው ክብር ጋር ለ11 የባንኩ መስራቾች፣ ለቀድሞ የቦርድ አመራሮች፣ ለቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች፣ ለአጋር ተቋማት፣ ለረጅም ዘመን ደንበኞች እና የረጅም ጊዜ አገልግሎት ላላቸው ሠራተኞችም ዕውቅና ተሰጥቷል።
የማህበራዊ ኃላፊነቱን የመወጣት ተግባሩ አካል አድርጎም ባንኩ በአዕምሮ እድገት ውስንነት ላላቸው ወገኖች ድጋፍ ለሚያደርገው ለዲቦራ ፋውንዴሽን የ30 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ስጦታ አበርክቷል።
በሌላ በኩል በዳሸን ሱፐር አፕ መተግበሪያ በተካሄደው የዕድል ጨዋታ አሸናፊ ለሆነው ደንበኛ የዘመናዊ ቢዋይዲ ሴጉል የኤሌክትሪክ መኪና ሽልማት ተላልፏል።
በዚህ ታላቅ መርሃ ግብር ላይ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ኢዮብ ተካልኝን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#dashenbank #banking #ethiopianeconomy #finance #deborahfoundation #byd #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ለፌደራል መንግሥት የ2019 በጀት ከ2.3 ትሪሊየን ብር በላይ ቀረበ!
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለፌደራል መንግሥት ለቀጣዩ 2019 ዓ.ም. በጀት ከ2.3 ትሪሊየን ብር በላይ አጸደቀ።ዛሬ ሰኔ 2/2018 ዓ.ም. በተካሄደው 56ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በቀረበው የፌደራል መንግሥት የ2019 ረቂቅ በጀት ላይ "በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል" ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ተገልጿል።
ለመደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልል መንግሥታት ድጋፍ እንዲሁም ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ የሚውል 2,339,268,126,738 (ሁለት ትሪሊዮን፣ ሦስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ቢሊዮን፣ ሁለት መቶ ስድሳ ስምንት ሚሊዮን፣ አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺ፣ ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር) በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቦ መጽደቁ ተገልጿል።የፌደራል መንግሥት ለ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት የመደበው 1.93 ትሪሊዮን ብር ነበር።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ባወጣው መግለጫ የ2019 ዓ.ም. የፌደራል መንግሥት በጀት የ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት "የፕሮግራም በጀት አፈጻጸምን መነሻ በማድረግ" መዘጋጀቱን ይገልጻል።በቀጣይ ሊኖር የሚችለው "የማኅበራዊና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎችና ዓላማዎች" እንዲሁም በመንግሥት የተቀመጡ "ግቦችን ለማሳካት የመንግሥትን የፋይናንስ አቅም እና አስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች ከተሰጣቸው ተልዕኮ እና ኃላፊነት አንጻር የሚያስፈልገውን ወጪ በመገምገም" ተዘጋጅቶ መቅረቡ ተመልክቷል።
ምክር ቤቱ ከ2019-2023 ዓ.ም. በሚኖረው የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ላይ እንደተወያየ ጠቅሶ፤ "የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ካሉበት ተግዳሮቶች እየተላቀቀ እና የኢኮኖሚው መሠረቶችም እየተጠናከሩ መጥተዋል" ብሏል።"በኢኮኖሚ ሪፎርሙ የተገኙ አበረታች ውጤቶችን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል" እንዲሁም "ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ታሳቢዎች ላይ በመመሥረት" የ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት በጀት መነሻ መሆኑም ተጠቅሷል።

ከአቅም በላይ የሆነው የትራንስፖርት ዋጋ
አብዛኛው የመንግሥትም ሆነ የግል ሠራተኞች ነጋዴዎችም ሆኑ የቀን ሠራተኞች የዕለት ሥራቸውን የሚጀምሩትና የሚያጠናቅቁት በትራንስፖርት ነው። ይሁን እንጂ በየወቅቱ የሚወጡት አዳዲስ የታሪፍ ማሻሻያዎች በትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን ላይ ተገማች ያልሆነ ጫና እያሳደረ ይገኛል፡፡ የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መናጋትን ተገን በማድረግ በአገር ውስጥ የሚደረጉ የዋጋ ማስተካከያዎች፣ ዛሬ ላይ የዜጎችን የመንቀሳቀስና የኢኮኖሚ አቅም በእጅጉ እየፈተኑት ነው፡፡ ታሪፍ በየወቅቱ ይጨምራል፣ የተሳፋሪው ደመወዝና ገቢ ግን ባለበት እንደቀጠለ ነው፡፡
አቶ መለስ አምሳሉ ከሸገር ከተማ ኮዬ ፈጨ ተነስተው ሽሮ ሜዳ በየዕለቱ ከባለቤታቸው ጋር ለሥራ ይመላለሳሉ፡፡ ‹‹አጋጣሚ የእኔም የባለቤቴም ሥራ አንድ አካባቢ በመሆኑ ሁሌም በጧት ተነስተን ተያይዘን ነው የምንወጣው›› የሚሉት አቶ መለሰ፣ ‹‹ብዙ ጊዜ በከተማ ባስ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በታክሲ እየተመላለሰን ነው የምንሠራው፡፡ እኔም ባለቤቴም አብረን ስለምንሄድ ነው መሰል የትራንስፖርቱ ክፍያ ከሁሉም በላይ ያሰለቻል የሚዘለቅ አይመስልም›› ሲሉ ይገልጻሉ፡፡
በቀን ከባለቤታቸው ጋር ከ300 እስከ 500 ብር ለትራንስፖርት እንደሚያወጡ የተናገሩት አቶ መለስ፣ የሚከፈላቸው ደመወዝና የሚያወጡት የቀን ወጪ ሊጣጣም እንዳልቻለ ይጠቁማሉ፡፡
በተለይ የትራንስፖርት ወጪው፣ ነዳጅ በጨመረ ቁጥርትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ዋጋ መጨመር በየቀኑ የተለያየ ክፍያ መጠየቅና ተደራድሮ መጫን፣ መሸት ካለ በእጥፍ እስከመጨመር መድረስ ለሕዝቡ ሸክም መሆኑን ይጠቁሟሉ፡፡
መንግሥት አምስት ብር ወይም አሥር ብር ታሪፍ ጨመረ ሲባል እነሱ ከተባለው እጥፍ በላይ አድርገው ይጨምራሉ፣ ኅብረተሰቡ ተመጣጣኝ ክፍያን ያስከፍሉ የነበሩት የከተማ አውቶብሶች ዛሬ ላይ በተደረገ ጭማሪ ውድ መሆናቸውን ያስረዳሉ፡፡
‹‹በምግብ፣ በዕቃና በሌሎች ነገሮች ላይ የሚደረገውን የዋጋ ጭማሪ አንዳንዱን ልታልፈው ትችላለህ፡፡ አንዳንዱም ለጊዜው ላያስፈልግ ስለሚችል ልተወው ትችላለህ፡፡ ነገር ግን ትራንስፖርት ልተው ወይም ለነገ ሊባል የሚችል አይደለም፡፡ ከሥራህ ታክሲ አጣሁ ወይም ብር የለኝም ብለህ ብትቀርከደመወዝህ ይቀነሳል፤›› ሲሉም ያሉበትን ፈተና ይገልጻሉ፡፡
በተደጋጋሚ ከሥራ መቅረት እስከ መባረር ለሚያደርስ ቅጣት ይደረጋል በመሆኑም ትራንስፖርት ላይ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ በደንብ ሊታሰብበት እንደሚገባም በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
‹‹ኅብረተሰቡም ቢሆን ችግር አለበት›› የሚሉት አቶ መለስ፣ ‹‹አንዳንድ ተቆጣጣሪዎች በተለይ መነሻው ላይ ስንት ብርእንደተጠየቅን ሲጠይቁን፣ ትክክለኛውን አንናገርም፡፡ በመሆኑም ይኼ ነገር ለመንግሥት ቁጥጥርም አስቸጋሪ ይመስለኛል፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡
በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው የትራንስፖርት እጥረትና እጥረቱን ተከትሎ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ በጣም እንዳስመረራቸው የሚናገሩት ደግሞ ወ/ሮ መሠረት ኃይሉ ናቸው፡፡
ወ/ሮ መሠረት ከአራብሳ ተነስተው መስቀል አደባባይአካባቢ ወደሚገኘው የሥራ ቦታቸው ዘወትር ይመላለሳሉ ‹‹አሁን ላይ የሚታየውን የትራንስፖርት ችግር ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ችግሩ ተደራራቢ መሆኑ ነው፣ የመጀመሪያው ረዥም ሠልፍ መሠለፍ፣ ከዚያም ከታሪፍ በላይ መክፈል፣ ታሪፍ ነው ብለን ለመከራከር ስንሞክር ነዳጅ ስለጨመረ ጨምሯል እንባላለን፤›› በማለት ያስረዳሉ፡፡
‹‹ቤት እንዳልውል ከቤት ኪራይ ጀምሮ ያለው ወጪ ከአቅም በላይ ነው፡፡ ተሯሩጦ ለመሥራት ደግሞ ከሁሉም በላይየትራንስፖርት ወጪው ያሰለቻል፣ ነገር ግን ቁጭ ከማለት ይሻላል በሚል እየለፋን ለቤት ኪራይና ለትራንስፖርት እንሰጣለን፣ ለነገ ብንታመም፣ ብንሞት ብለን የምናስቀምጠው ጥሪት የለንም፤›› ሲሉ ሐሳባቸውን አጋርተዋል፡፡
እነዚህና መሰል ቅሬታዎች በተለይ በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት መቀስቀስ ጋር ተያይዞ በነዳጅ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ከተደረገ ወዲህ በስፋት ይስተዋላሉ፡፡ ጦርነት ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ከደረሰባቸው ሴክተሮች መካከልም የትራንስፖርት ዘርፉ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው፡፡
በነዳጅ እጥረት ምክንያት የሚከሰቱ ችግሮች ዞረው ዞረው ማረፊያቸው እንደ አቶ መለስና እንደ ወ/ሮ መሠረት ባሉ ተጠቃሚዎች ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ሲጨምር መንግሥት የትራንስፖርት ‹‹የታሪፍ ማሻሻያ በሚል በየወቅቱ ይጨምራል፡፡ መንግሥት ከሚጨምረው የታሪፍ ጭማሪ ባሻገር ጭማሪውን ተከትለው የሚጨምሩ አሽከርካሪዎች መበራከታቸውን አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል የሚደረገው የታሪፍ ጭማሪ የኅብረተሰቡን ገቢ ያላገናዘበ መሆኑን ተሳፋሪዎች ይናገራሉ፡፡
‹‹በሁለት ዓመትና በሦስት ዓመት ምንም ዓይነት የደመወዝ ጭማሪ ሳይደረግልኝ በትራንስፖርት ታሪፉ ላይ ግን በቀላሉ ከሦስት ጊዜ በላይ የታሪፍ ጭማሪ በሚል ቢያንስ ከ2ዐ እስከ 3ዐ ብር በቀን በአንድ ጉዞ ላይ ጭማሪ መደረጉን አውቃለሁ፤›› ሲሉ የተናገሩት የሕዝብ ትራንስፖርት ተጠቃሚ አባት ናቸው፡፡
እሳቸው እንደሚሉት፣ አዘውትረው የሚጠቀሙት የከተማ አውቶብስን ነው፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ ገቢያቸው ዝቅተኛ በመሆኑ በታክሲ መሄድ ስለማይችሉ ነው፡፡ ነገር ግን አሁን ያለው የባስ አገልግሎት ታሪፉም ቢሆን የሚቀመስ አልሆነም ይላሉ፡፡
ምንም እንኳን ኅብረተሰቡ መንግሥት ካስቀመጠው ታሪፍ በላይ የሚገደድባቸው ሁኔታዎች፣ በተለይ በምሽት ቢኖሩም፣ ተገቢው ቁጥጥር አለ ብለው እንደማያምኑም ያክላሉ፡፡
የሚኒባስ አሽከርካሪው ተስፋ ብርሃኑ፣ ተሳፋሪዎች የሚያቀርቡት ጥያቄም ሆነ አስተያየት ትክክል ነው፣ ነገር ግን ያላወቁልን ነገር ቢኖር የእኛን መቸገር ነው ሲል ተናግሯል፡፡
በአሁኑ ወቅት ነዳጅ ከማደያ እስከ 18ዐ ብር ነው እየከፈልን የምንቀዳው፡፡ ነገር ግን ነዳጅ ሲጨምር እኛ ታሪፍ አንጨምርም፡፡ ሰው በየዕለቱ ከቤት ወደ ሥራ ቦታ ከሥራ ቦታ ወደ ቤት ሲመላለስ 5ዐ ሆነ መቶ ሲያወጣ ከባድ ይሆንበታል፡፡
እኛ ደግሞ ከነዳጅ ባሻገር የምናወጣው የጥገና ወጪ እንዲሁ የሚነገር አይደለም፡፡ በዚያ ላይ የተለያዩ ሕጋዊ የሆነም ሕጋዊ ያልሆነም ምክንያቶችን በመፍጠር በየመንገዱ ለቅጣት የምናወጣው ወጪም ቀላል እንዳልሆነ ያስረዳል፡፡
እንደ አሽከርካሪው፣ አብዛኛው ሹፌር የሚሠራው በልቶ ለማደር ነው፡፡ ከሰዓት እላፊ በላይ ከሠራ ምን አልባት ጭማሪ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ከዚያ ውጪ አብዛኛው ሰው ዘይትና ሽንኩርት መጨመሩን ያውቃል፡፡ ነገር ግን ትራንስፖርት ከአምስት ወር በፊት በነበረው የሚቀጥል የሚመስላቸው ሰዎች አሉ፡፡ ብዙ ሰዎች የትራንስፖርት ማሻሻያ ተደርጓል መባሉን የሚሰሙት ቆይተው ነው፡፡
እነዚህን መሰል ከኅብረተሰቡና ከአሽከርካሪዎች የተነሱ ጥያቄዎችን በተለይ የነዳጅ አቅርቦት ተስተካክሏል ከተባለ ወዲህ ያሉ መሻሻሎች ካሉ ምላሽና ማብራሪያዎችን ለማግኘት ጉዳዩ ወደሚመለከተው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምላሽ ለማግኘት ሐሙስ ግንቦት 2ዐ ቀን 2018 ዓ.ም. ከሰዓት በቢሮው ብንገኝም፣ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ስለሚበዙ በወቅቱ መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ በቃል አሳውቀውናል፡፡
ዘገባው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

የዓለም ዋንጫ ማሸነፍ የቻሉ ሀገራት…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከፈረንጆቹ 1930 ጀምሮ መደረግ በጀመረው በዓለም ዋንጫ ውድድር ስምንት ሀገራት ብቻ ዋንጫውን ማሳካት ችለዋል፡፡
በዓለም ዋንጫ ታሪክ ብራዚል አምስት ጊዜ ሻምፒዮን በመሆን ቀዳሚዋ ሀገር ስትሆን÷ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫውን ያሳካችው በፈረንጆቹ 1958 ነበር፡፡
ከዚያ በመቀጠል በፈረንጆቹ 1962 ሻምፒዮን በመሆን በተከታታይ ዋንጫውን አሳክታለች፡፡
እንዲሁም በ1970፣ 1994 እና 2002 ሻምፒዮን በመሆን በመድረኩ አምስት ጊዜ ዋንጫውን በማሳካት ቀዳሚዋ ሀገር ናት፡፡
ከብራዚል በመቀጠል የዓለም ዋንጫን ብዙ ጊዜ ማሳካት የቻሉት ጀርመን እና ጣሊያን ናቸው፡፡
ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች በተመሳሳይ አራት ጊዜ ሻምፒዮን ሆነዋል፡፡
ጣሊያን በፈረንጆቹ 1934 ለመጀመሪያ ጊዜ ሻምፒዮን ስትሆን÷ በድጋሚ በ1938 ዋንጫውን በማሳካት በተከታታይ ሻምፒዮን ለመሆን በቅታለች፡፡
እንዲሁም በፈረንጆቹ 1982 ለሦስተኛ ጊዜ ያሸነፈች ሲሆን÷ ለመጨረሻ ጊዜ ዋንጫውን ያሳካችው በፈረንጆቹ 2006 ነበር፡፡
የአራት ጊዜ የመድረኩ አሸናፊዋ ሀገር ጣሊያን የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ ጨምሮ ለተከታታይ ሦስተኛ ጊዜ ከውድድሩ ውጪ የሆነች ሲሆን÷ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችው በፈረንጆቹ 2014 ነበር፡፡
ከዚያ በኋላ ማጣሪያውን ማለፍ ባለመቻሏ ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ ከመድረኩ ውጪ ሆናለች፡፡
ሌላኛዋ አራት ጊዜ የዓለም ዋንጫን ያሸነፈችው ሀገር ጀርመን ለመጀመሪያ ጊዜ ሻምፒዮን የሆነችው በ1954 ነበር፡፡
ከዚያ በኋላ በፈረንጆቹ 1974፣ 1990 እና 2014 ላይ በመድረኩ ሻምፒዮን መሆኗ ይታወሳል፡፡
የደቡብ አሜሪካዋ ሀገር አርጀንቲና ደግሞ ሦስት ጊዜ የዓለም ዋንጫን ማሳካት ችላለች፡፡
አርጀንቲና ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫን ማሳካት የቻለችው በፈረንጆቹ 1978 እንደነበር ይታወሳል፡፡
በፈረንጆቹ 1986 ለሁለተኛ ጊዜ ሻምፒዮን ከሆነች በኋላ ከ36 ዓመታት ጥበቃ በኋላ በ2022 ለ3ኛ ጊዜ ማሸነፏ ይታወሳል፡፡
ፈረንሳይ እና ዩራጋይ ደግሞ በተመሳሳይ ሁለት ጊዜ የዓለም ዋንጫን ማሳካት የቻሉ ብሔራዊ ቡድኖች ናቸው፡፡
ዩራጋይ የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ ውድድር ያሸነፈች ሲሆን÷ ወቅቱም በፈረንጆቹ 1930 ነበር፡፡
የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ ውድድር ያሸነፈችው ዩራጋይ በወቅቱ ውድድሩን ያዘጋጀችው ራሷ እንደነበረች ይታወሳል፡፡
ዩራጋይ ከዚያ በኋላ በፈረንጆቹ 1950 በድጋሚ ዋንጫውን ማንሳቷ አይዘነጋም፡፡
ፈረንሳይ በፈረንጆቹ 1998 እና 2018 ሻምፒዮን በመሆን በመድረኩ ሁለት ጊዜ ከዋንጫው ጋር ተገናኝታለች፡፡
እንግሊዝ እና ስፔን ደግሞ በተመሳሳይ አንድ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ማሳካት ችለዋል፡፡
እንግሊዝ በፈረንጆቹ 1966 ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ያሳካች ሲሆን÷ በወቅቱም የውድድሩ አዘጋጅ ሀገር ራሷ ነበረች፡፡
ከዚያ በኋላ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በመድረኩ ሻምፒዮን መሆን አልቻለም፡፡
ስፔን በፈረንጆቹ 2010 ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪኳ ሻምፒዮን መሆኗ ይታወሳል፡፡
የፊታችን ሐሙስ በሚጀምረው የ2026 ዓለም ዋንጫ አዲስ ሀገር ሻምፒዮን ይሆናል ወይስ ከዚህ ቀደም ካነሱ ሀገራት መካከል አንዱ ሻምፒዮን ይሆናል የሚለው ይጠበቃል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ

5 days ago
ኬብሮን አማኑኤል በ“ጣፋጭ ሕይወት” ልዩ ተመስጋኝ ሆናለች
#fastmereja I በጎ ተግባርን ማዕከል በማድረግ ለ6ኛ ዙር በተካሄደው የ“ጣፋጭ ሕይወት” የምስጋና መርሃ ግብር ላይ፣ “ልጄ ሆይ” በተሰኘው የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዋ የምትታወቀው ኬብሮን አማኑኤል የዘንድሮው የ“ልዩ ተመስጋኝ” ተሸላሚ ሆና ተመርጣለች።
ባለፉት ዓመታት በልጆች፣ በወላጆችና በችግረኛ ማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ትኩረት አድርጋ ስትሠራ የቆየችው ኬብሮን አማኑኤል፣ ማኅበረሰቡን ማገልገል ግዴታዋ እንደሆነ ብታምንም ድርጅቱ ለታናናሾች ተምሳሌት እንድትሆንና ለወደፊቱ ይበልጥ እንድትተጋ ይህንን ዕውቅና እንደሰጣት ተገልጿል። ተሸላሚዋ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ብቻ 38 ሕፃናትን በትምህርት፣ በቁሳቁስና በነፃ ሕክምና ከመርዳቷም በላይ በሚኪሊላንድ መንግሥት ትምህርት ቤት የእናት አምባሳደር በመሆን አገልግላለች። በተጨማሪም በሆለታ፣ በፋኖስ እና በጅማ ለሚገኙ ከ3,000 በላይ ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገች ሲሆን፣ በአረጋውያን፣ በተጣሉ ሕፃናት እና በካንሰር ታማሚዎች ዘንድ በመገኘት ማህበራዊ ድጋፍ ስትሰጥ መቆየቷ ተመልክቷል።
በዓመት ሦስት ጊዜ የደም ልገሳ ፕሮግራም በማዘጋጀትና ብቻቸውን ልጆቻቸውን የሚያሳድጉ እናቶችን እንዲሁም ከሱስ ለማገገም የሚጥሩ ሴቶችን በመደገፍ የምትታወቀው ኬብሮን፣ ሽልማቱን ከተቀበለች በኋላ ባስተላለፈችው መልዕክት “ውስጥ ካለኝ ሳይሆን ከሌለኝ ያካፈልኩት የኖርኩት ኑሮዬ ነው” በማለት ምስጋናዋን አቅርባለች። ወደፊትም በ“ልጄ ሆይ” ተግባሯ የተጣለባትን አደራ ለመወጣት ቃል የገባች ሲሆን፣ በገንዘብና በሃሳብ ከጎኗ ለቆሙት የ“200 ብር ቻሌንጅ” ተሳታፊዎችና የቅርብ ደጋፊዎቿ ምስጋናዋን አቅርባለች።
በርቺ ብለናል 🤝

ኢትዮ-ኮል በተጨማሪ ሦስት አገራት ጀመረ!!
ኢትዮ-ኮል:-
📞 ማንኛውንም የሞባይል ወይም የመደበኛ ስልክ ላይ መደወል ያስችላል
💰 በታላቅ ቅናሽ በደቂቃ ከ$0.1 ጀምሮ
🔄 ወደ ኢትዮጵያ መደወል ብቻ ሳይሆን፣ ጥሪዎችን በገዙት ጥቅል መነሻነት በነፃ መቀበል ይችላሉ።
🇺🇸 አሜሪካ 🇮🇱 እስራኤል
🇨🇦 ካናዳ 🇾🇪 የመን
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ 🇰🇪 ኬንያ
መተግበሪያውን ያውርዱ:
App store: https://bit.ly/42Zg6jx
Play store: https://bit.ly/4u12uPu
ከአኗኗርዎ ጋር የሚስማማውን ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ ወይም የ15 ቀናት የድምፅ ጥቅሎችን መርጠው ይጠቀሙ።
#ethiocall #ethiotelecom #telebirr #telebirrsuperapp #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

ያንጎ ጉዞ የትራንስፖርት አገልግሎቱን በሐዋሳ ከተማ በይፋ መጀመሩን አስታወቀ
#ethiopia | ዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ያንጎ ግሩፕ አካል የሆነው ያንጎ ጉዞ፣ ዘመናዊና ተመጣጣኝ የዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎቱን በሐዋሳ ከተማ በይፋ ማስጀመሩን ገልጿል።
ይህ አዲስ አሠራር በሲዳማ ክልል ዋና ከተማ የተዘረጋው ከሀገር ውስጥ ድርጅቶች ማለትም ከኤልና ትሬዲንግ እና ከኮንትራስት ትሬዲንግ ጋር በመተባበር ሲሆን፣ ዓላማውም በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ሥርዓት ማዘመንና ማቀላጠፍ ነው።
በአዲሱ መተግበሪያ ላይ ባጃጅ፣ ባለ አራት እግር ባጃጅ እና የሞተር ሳይክል አገልግሎቶች የተካተቱ ሲሆን፣ ተሳፋሪዎች በመጀመሪያዎቹ ሦስት ጉዞዎቻቸው የ30 በመቶ ቅናሽ ያገኛሉ።
አገልግሎቱ በሁለት የታሪፍ ክፍሎች የሚሰጥ ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች የጉዞ ዋጋውን አስቀድመው ማወቅ ስለሚችሉ ከመንገድ ላይ መኪና ከማስቆም የተሻለና አስተማማኝ አማራጭ ይሆንላቸዋል።
የባጃጅ ታሪፍ ባለ ሦስትና ባለ አራት እግር ተሽከርካሪዎችን የሚያካትት ሲሆን፣ የሞቶ ታሪፍ ደግሞ ፈጣን እንቅስቃሴ ለሚፈልጉ ተሳፋሪዎች የተዘጋጀ ነው።
ይህ የቴክኖሎጂ ፕላትፎርም ለአሽከርካሪዎችም ሰፊ የሥራ ዕድል ይዞ መጥቷል።
የያንጎ የጉዞ ማዛመጃ ዘዴ አሽከርካሪዎችን በአቅራቢያቸው ከሚገኙ ተሳፋሪዎች ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ በመሆኑ፣ ያለሥራ የሚቆዩበትን ጊዜ በመቀነስ ዕለታዊ ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ ይረዳቸዋል።
ከተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች መካከል ዳዊት ይድነቃቸው እንደገለጸው፣ መተግበሪያውን መጠቀም ከጀመረ ወዲህ ደንበኞችን በቀላሉ ማግኘት እንደቻለና የሥራ ሂደቱ እንደተቀየረለት ገልጿል።
ከ560 ሺህ በላይ ሕዝብ ያላትና በንግድና ቱሪዝም ዘርፍ በፍጥነት እያደገች የምትገኘው ሐዋሳ፣ ያንጎ ከአዲስ አበባ ውጪ አገልግሎቱን ያስፋፋባት የመጀመሪያዋ ከተማ ሆናለች።
የያንጎ ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ ዶክተር የቀናዓለም አበበ እንደተናገሩት፣ የኩባንያው ዋና ዓላማ እያንዳንዱን የከተማ ጉዞ ለተሳፋሪዎች ምቹ ማድረግና ለአጋር አሽከርካሪዎች ደግሞ የተሻለ ጥቅም ማስገኘት ነው።
ያንጎ ግሩፕ በትራንስፖርት፣ በማድረስ፣ በመዝናኛና በሌሎች ዲጂታል ዘርፎች በአፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ፣ በአውሮፓና በመካከለኛው ምሥራቅ ከ30 በላይ ሀገራት ውስጥ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ዓለም አቀፍ ተቋም ነው።
#yango #hawassa #sidama #transport #digital #taxi #tech #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 days ago
ኢሰመኮ ስለ አርሲው ጥቃት ምን አለ?
📌ኦሮሚያ በአርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ የደረሰውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በተመለከተ መንግሥት ተገቢውን ምርመራ በማካሄድ ተጠያቂነትን የማረጋገጥ እና ተጎጂዎችን ለመካስና ለማቋቋም የሚያስችሉ እርምጃዎችን ሊወስድ ይገባል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጋዜጣዊ መግለጫ
#ethiopia በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ ግንቦት 23 እና 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ክትትል እና ምርመራ እያከናወነ
ይገኛል፡፡ ኢሰመኮ ይህ መግለጫ ይፋ እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ በአካባቢው በአካል በመገኘት
ከዐይን እማኞች፣ ከተጎጂዎች፣ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ እና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ባሰባሰባቸው መረጃዎችና ማስረጃዎች ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው “በተለምዶ ኦነግ ሸኔ” ታጣቂ ቡድን በፈጸመው ጥቃት የመንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላትና ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን፣ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን፣ የንብረት ውድመት እና ቃጠሎ መድረሱን ለማረጋገጥ ችሏል።
ኢሰመኮ በምርመራ ሂደቱ እንዳረጋገጠው በአሰኮ ወረዳ ደለተ ጫፋ ቀበሌ አካባቢ ከግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ በመስተዋሉ የአካባቢው ሚሊሻዎችና የኦሮሚያ ጸረ ሽምቅ ውጊያ ፖሊስ አባላት በስፍራው በመሰማራታቸው “በተለምዶ ኦነግ ሸኔ” ተብሎ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን እና በተሰማሩ የጸጥታ አካላት መካከል ግጭት ተፈጥሯል።
ግጭቱን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ላይ ታጣቂ ቡድኑ ባደረሰው ጥቃት ከአካባቢው መሸሽ ባልቻሉ ኃይሉ ንጉሴ እና ሰሙ አባይነህ በተባሉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲሁም በአካባቢው ከብቶች በመጠበቅ ላይ የነበረ ባቶ ሰፈኖ የተባለ የእስልምና እምነት ተከታይ በአጠቃላይ
የሦስት ሲቪል ሰዎች ሕይወት ሊያልፍ ችሏል።
በተጨማሪም ቁጥራቸው ለጊዜው በውል ባልታወቁ ቤቶች ላይ ቃጠሎ መድረሱን፣ የጠለታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መቃጠሉን፤ ቢዮ ቡጡሌ የሼክ ሙስተፋ መስጅድ አጥር ላይ ጉዳት መድረሱን፣ በድለተ ጫፋ ጤና ጣቢያ፣ በነዋሪዎች መኖሪያ ቤቶችና የንግድ መደብሮች ላይ በመደዳ ዘረፋ መፈጸሙን እንዲሁም ከ2,650 በላይ የሚገመቱ የአካባቢው ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ኢሰመኮ አረጋግጧል።
ኢሰመኮ በአርሲ ዞን በሽርካ፣ በአሰኮ፣ በአንቆሎ ዋቤ፣ ጉና እና መርቲ ወረዳዎች ላይ በታጣቂዎቹ ሲፈጸሙ የነበሩ ጥቃቶች ዳግም እንዳይከሰቱ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ እና ጥቃት ፈጻሚዎች ላይ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ በተለያዩ ጊዜያት ማሳሰቡ ይታወሳል።
መንግሥት በአካባቢው ላይ በተደጋጋሚ መሰል ጥቃቶች እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መከሰት መቀጠላቸው አሳሳቢ መሆኑን ከግምት በማስገባት ጥቃት በተፈጸመባቸው አካባቢዎች የጀመራቸውን ጥረቶች በማጠናከር በአስቸኳይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንዲሰማሩ እና ሰላምና ደኅንነትን በማረጋገጥ ነዋሪዎችን ወደ ተረጋጋ ሕይወት የመመለስ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመንግሥትና በሌሎች አጋር አካላት በጥቃቶቹ ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች በቂ የሆነ የአስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ እንዲቀርብና ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ተመልሰው በዘላቂነት የሚቋቋሙበት ሁኔታ እንዲመቻች ኢሰመኮ ያሳስባል።
በሌላ በኩል ኢሰመኮ ጉዳዩን አስመልክቶ ዝርዝር የምርመራ ሪፖርት ይፋ የሚያደርግ መሆኑን እየገለጸ፤ የተፈጸሙ ጥቃቶችን በአግባቡ ሳያረጋግጡ የሚሰነዘሩ ፍረጃዎችና ቅስቀሳዎች ተጨማሪ ግጭት እንዲፈጠር የማነሳሳት ዕድላቸው ሰፊ በመሆኑ ማናቸውም ተቋማትም ሆኑ ግለሰቦች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥሪ ያቀርባል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ኢሰመኮ በዜጎች ላይ ለደረሰው ሞትና ጉዳት ማዘኑን ገልጸው በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸሙት የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች አሳሳቢ መሆናቸውንአስረድተዋል፡፡ አክለውም መንግሥት ሁኔታውን ለማረጋጋት እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ያከናወናቸው ተግባራት መቀጠል ያለባቸው መሆኑን ጠቅሰው፤ በማንኛውም ጊዜ የጸጥታ ሥጋት
ባለባቸው አካባቢዎች ሁሉ በቂ የጸጥታ ኃይሎች በመመደብና ተመሳሳይ ጥቃቶችን የመከላከል ሥራ በመሥራት የነዋሪዎች በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነት እና የንብረት መብቶች ለአደጋ እንዳይጋለጡ እንዲያደርግ፣ ተገቢውን ምርመራ በማካሄድ ተጠያቂነትን የማረጋገጥ እና ተጎጂዎችን ለመካስና ለማቋቋም የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንዲወስድ እንዲሁም ሁሉም አካላት የተፈጠሩ ችግሮችን ከማውገዝ ባሻገር ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ መግለጫዎች እና ድርጊቶች እንዲታቀቡ ጥሪ አቅርበዋል።
ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)

"ለሞት ተቃርቤ ነበር" ስትል አስደንጋጭ የጤና እክል እንደገጠማት የጂምናስቲክስ ኮከቧ ሲሞን ባይልስ ተናገረች
#ethiopia | ታዋቂዋ አሜሪካዊት የጂምናስቲክስ ስፖርተኛ ሲሞን ባይልስ፣ በቅርቡ ባጋጠማት ድንገተኛ እና አስደንጋጭ የጤና መታወክ ሆስፒታል ገብታ እንደነበርና ለሞት ተቃርባ እንደነበር ይፋ አድርጋለች።
ሰባት የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ የቻለችው የ29 ዓመቷ ባይልስ ምንም እንኳን የግል ሕይወቷን በሚስጥር መያዝ እንደምትመርጥ ብትገልጽም፣ የገጠማት የጤና እክል ግን በሕይወቷ ካጋጠሟት አስፈሪ ክስተቶች ሁሉ ዋነኛው እንደነበር ተናግራለች።
በተለይም የጤና እክሉ በገጠማት ወቅት የአሜሪካ እግር ኳስ (NFL) ተጫዋች የሆነው ባለቤቷ ጆናታን ኦውንስ ለልምምድ ወደ ሌላ ከተማ ሄዶ መቆየቱ ሁኔታውን ይበልጥ አስፈሪ እንዳደረገው ባይልስ ጠቅሳለች።
በአሁኑ ወቅት ዕረፍት እያደረገች የምትገኘው ይህች ስመ-ጥር አትሌት፣ በአስቸጋሪው ጊዜ ከጎኗ ለነበሩ የቅርብ ወዳጆቿ ምስጋናዋን አቅርባለች።
ሲሞን ባይልስ በታሪክ ከታዩ ስኬታማ የጂምናስቲክስ ስፖርተኞች አንዷ ስትሆን፣ በ2024ቱ የፓሪስ ኦሊምፒክ ላይ ብቻ ሦስት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 11 የኦሊምፒክ ሜዳሊያዎችን ማሸነፏ ይታወሳል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ebc #simonebiles #sport

Comments