በሶሻል ሚዲያ ታዋቂ በሆኑ ሦስት ግለሰቦች ላይ የስም ማጥፋት ክስ ተመሠረተ፤ የባንክ አካውንታቸውም እንዲታገድ ተወሰነ
በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በስፋት የሚታወቁት ወገነ አበበ ፀጋዬ፣ ሌዊ አጎናፍር ወዳጆ እና ገዛኸኝ ተረሳ ቤኛ (አዎንታ በርሲሳ) በስም ማጥፋት ወንጀል የተመሠረተባቸው የፍትሐብሔር ክስ ለሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ተቀጠረ።
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ የሆኑት ደጉ ታደለ ኮይራ ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሚ ኩራ ምድብ 8ኛ የፍትሐብሔር ችሎት ባቀረቡት ክስ፤ ከተከሳሾቹ ጋር ምንም ዓይነት የግልም ሆነ የሥራ ግንኙነት እንደሌላቸው ገልጸው፣ ላለፉት አራት ዓመታት በቲክቶክ ማኅበራዊ ሚዲያ በነፃ የሕግ ትምህርት በመስጠት የገነቡትን መልካም ስም ለማጥፋት ተከሳሾቹ ፎቶአቸውን በመጠቀም የሐሰት መረጃዎችን በየግል ገጻቸው ማሰራጨታቸውንና በሥራቸው ላይ ቀጥተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን አስረድተዋል።
ከሳሽ ከውል ውጪ በሚደርስ ኃላፊነት በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2044 መሠረት ለደረሰባቸው የስም ማጥፋት ጉዳት 150 ሺህ ብር የገንዘብ ካሳ እንዲከፈላቸው፣ ተከሳሾቹ ይፋዊ ይቅርታ ጠይቀው ማስተባበያ እንዲሠሩ፣ አስቀድሞ በገጻቸው ላይ የለቀቁትን መረጃ እንዲያጠፉ እና የሞራል ካሳ እንዲከፍሏቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱ የከሳሽን አቤቱታ መሠረት በማድረግ፣ ተለዋጭ ትዕዛዝ እስኪሰጥ ድረስ የተከሳሾች የባንክ ሒሳብ እስከ 50 ሺህ ብር ድረስ ታግዶ እንዲቆይ ለባንኮች እንዲጻፍ ባለፈው ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፣ የግራ ቀኙን ክርክር ለመስማትም ለሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

5 days ago