"ዋናው ሀገራዊ ጉባዔ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምር ይካሄዳል" - መስፍን ዓርዓያ (ፕ/ር)
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚካሄድ በይፋ አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ዛሬ ምሽት በሸራተን አዲስ ሆቴል ለሚዲያዎች መግለጫ እየሰጠ ይገኛል። በዚህም የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕ/ር)፣ "ዋናው ሀገራዊ ጉባዔ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምር ይካሄዳል" ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ የመጨረሻው ዋና ጉባዔ በአዲስ አበባ ከተማ ከሦስት ሳምንታት ባልበለጠ ጊዜ እንደሚካሄድም አስታውቀዋል።
በትግራይ ክልል በሚስተዋለው የፖለቲካ አለመረጋጋት መግባት ባለመቻሉ የክልሉን አጀንዳ በአዲስ አበባ ከተማ መቀበሉን፣ በሌሎች ሁሉም ክልሎች በአካል በመንቀሳቀስ መቀበሉን ሲያስታውቅ ቆይቷል። በተያያዘ የቀረቡለት አጀንዳዎቹን ለባለድርሻ አካላት በማቅረብ ሀሳብ እየተቀበለ መሆኑን መሆኑን ከሰሞኑ ጭምር ገልጿል።
በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ዳያስፖራዎችም ከጀንዳ መቀበሉን ገልጿል።
ይሁን እንጅ የተወሰኑ የፖለቲካ ፖርቲዎች መጀመሪያ ጦርነት፣ የጸጥታ ችግር እንዲቆም፣ እስረኞች እንዲፈቱ ካልተደረገ በምክክሩ አንሳተፍም እንዳሉ ናቸው።
ኮሚሽኑ መጀመሪያ በተሰጠው ሦስት አመታት ስራው ባለመጠናቀቁ ፓርላማው ለአንድ ዓመት ተጨማሪ ጊዜ ከሰጠው በኋላ፣ ያም ባለመብቃቱ ለሁለተኛ ጊቡ የስምንት ወራት ጊዜ ተጨምሮለት እየሰራ ይገኛል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #tikvahethiopiafamilyaa

17 hours ago