8 days ago
"ለሞት ተቃርቤ ነበር" ስትል አስደንጋጭ የጤና እክል እንደገጠማት የጂምናስቲክስ ኮከቧ ሲሞን ባይልስ ተናገረች
#ethiopia | ታዋቂዋ አሜሪካዊት የጂምናስቲክስ ስፖርተኛ ሲሞን ባይልስ፣ በቅርቡ ባጋጠማት ድንገተኛ እና አስደንጋጭ የጤና መታወክ ሆስፒታል ገብታ እንደነበርና ለሞት ተቃርባ እንደነበር ይፋ አድርጋለች።
ሰባት የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ የቻለችው የ29 ዓመቷ ባይልስ ምንም እንኳን የግል ሕይወቷን በሚስጥር መያዝ እንደምትመርጥ ብትገልጽም፣ የገጠማት የጤና እክል ግን በሕይወቷ ካጋጠሟት አስፈሪ ክስተቶች ሁሉ ዋነኛው እንደነበር ተናግራለች።
በተለይም የጤና እክሉ በገጠማት ወቅት የአሜሪካ እግር ኳስ (NFL) ተጫዋች የሆነው ባለቤቷ ጆናታን ኦውንስ ለልምምድ ወደ ሌላ ከተማ ሄዶ መቆየቱ ሁኔታውን ይበልጥ አስፈሪ እንዳደረገው ባይልስ ጠቅሳለች።
በአሁኑ ወቅት ዕረፍት እያደረገች የምትገኘው ይህች ስመ-ጥር አትሌት፣ በአስቸጋሪው ጊዜ ከጎኗ ለነበሩ የቅርብ ወዳጆቿ ምስጋናዋን አቅርባለች።
ሲሞን ባይልስ በታሪክ ከታዩ ስኬታማ የጂምናስቲክስ ስፖርተኞች አንዷ ስትሆን፣ በ2024ቱ የፓሪስ ኦሊምፒክ ላይ ብቻ ሦስት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 11 የኦሊምፒክ ሜዳሊያዎችን ማሸነፏ ይታወሳል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ebc #simonebiles #sport

Comments