የ8 ዓመታት ምጥ በምስጋና ሊደመደም ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት ስምንት ዓመታት በፍርድ ቤት ስትከራከርበት የቆየችውን መሬት በሕጋዊ መንገድ ሙሉ በሙሉ መረከቧንና በአዲስ አበባ 7ኛዋን፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ 780ኛዋን አዲስ አጥቢያ (የአምልኮ ስፍራ) በይፋ እንደምትጀምር አስታወቀች። ቤተ ክርስቲያኗ ይህንን ያስታወቀችው በለቡ አጥቢያ በሚገኘው አዲሱ ስፍራ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጠችው መግለጫ ነው።
የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያ ፕሬዚዳንት መጋቢ ዶ/ር ጌታሁን ነሲቡ
እንደገለጹት ፣ ይህ አዲሱ መሬት ከነሐሴ 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የተሰጣት ቢሆንም፣ ባጋጠሙ የተለያዩ ተግዳሮቶችና ክርክሮች ምክንያት ላለፉት 8 ዓመታት ጉዳዩ በሕግ ጥላ ሥር ቆይቷል። አሁን ላይ ግን ሁሉንም ፈተናዎች በጽናትና በሕጋዊ መንገድ አልፋ መሬቱን በይፋ ለመረከብ መቻሏን ገልጸዋል።
በለቡ ከሆፕ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ በሚገኘው በዚህ አዲስ ስፍራ ላይ ቤተ ክርስቲያኗ የሚከተሉትን ሦስት ዘመናዊ የልማት ዕቅዶች ይዛ መነሳቷን አስታውቃለች። በመሆኑም
-ለምዕመናን ምቹ የሆነ ዘመናዊ የማምለኪያ አዳራሽ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ሁለንተናዊ ሥራዎች የሚያሳልጡ የቢሮዎች ግንባታ ይከናወናል።
-በአሁኑ ወቅት አገልግሎት እየሰጠ ለሚገኘው የስነ-መለኮት ኮሌጅ ተማሪዎችና አገልጋዮች የሚውሉ ዘመናዊ የማደሪያ ክፍሎች (Dormitories) ይገነባሉ።
-ግንባታው የአካባቢን ውበትና ስነ-ምህዳር ባገናዘበ መልኩ የሚከናወን ሲሆን፣ የወንዝ ዳርቻውን ልማት፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችንና መንገዶችን ያካተተ ይሆናል። ይህም ለአካባቢው ማኅበረሰብ ጭምር ምቾትና ውበት የሚሰጥ ሥራ እንደሆነ ተገልጿል።
ቤተ ክርስቲያኗ ከዚህ ቀደምም በቦሌ አራብሳ ተመሳሳይ ዘመናዊ የዋና ፅህፈት ቤት እና የአጥቢያ አገልግሎት ሕንጻ በመገንባት ማኅበራዊ ፋይዳ ያላቸውን ሥራዎች ስታከናውን መቆየቷ ይታወሳል።
እነዚህን ታላላቅ የልማት ሥራዎች ከመጀመሯ በፊት፣ ያለፉትን 8 ዓመታት ፈታኝ የፍርድ ቤት ጉዞዎችን በድል እንድትወጣ የረዳትን እግዚአብሔርን ለማመስገን ልዩ የምስጋና መርሃ-ግብር ማዘጋጀቷን ቤተ ክርስቲያኗ አስታውቃለች።
በዚህም መሠረት የፊታችን ሰኔ 7 በአዲስ አበባ ያሉ የቤተ እምነቱ አጥቢያዎች በሙሉ በጋራ በመሆን ሙሉ ቀን የሚቆይ ታላቅ ታሪካዊ የጸሎት እና የአምልኮ ፕሮግራም ያካሂዳሉ።
የቤተ እምነቱ መሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና መላው ምዕመናን በተገኙበት ልዩ የምስጋና ፕሮግራም ይኖራል።
በየሳምንቱ እሁድ ከሰዓት በኋላ በዚህ በአዲሱ የለቡ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መደበኛ የአምልኮ አገልግሎት በይፋ መቀጠል ይጀምራል።
የኢትዮጵያ ምስጋና ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 45 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ በወንጌል አገልግሎት እንዲሁም በልማትና ማኅበራዊ ሥራዎች ላይ በስፋት ስትሳተፍ የቆየች ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ሁሉም ክልሎች ውስጥ ከ780 በላይ አጥቢያዎች እንዳሏት በመግለጫው ወቅት ተነግሯል። ቤተ ክርስቲያኗ ለዚህ ስኬት መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ የፍትሕ አካላት እና ለሚዲያ ተቋማት ምስጋናዋን አቅርባለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

3 days ago