ኬብሮን አማኑኤል በ“ጣፋጭ ሕይወት” ልዩ ተመስጋኝ ሆናለች
#fastmereja I በጎ ተግባርን ማዕከል በማድረግ ለ6ኛ ዙር በተካሄደው የ“ጣፋጭ ሕይወት” የምስጋና መርሃ ግብር ላይ፣ “ልጄ ሆይ” በተሰኘው የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዋ የምትታወቀው ኬብሮን አማኑኤል የዘንድሮው የ“ልዩ ተመስጋኝ” ተሸላሚ ሆና ተመርጣለች።
ባለፉት ዓመታት በልጆች፣ በወላጆችና በችግረኛ ማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ትኩረት አድርጋ ስትሠራ የቆየችው ኬብሮን አማኑኤል፣ ማኅበረሰቡን ማገልገል ግዴታዋ እንደሆነ ብታምንም ድርጅቱ ለታናናሾች ተምሳሌት እንድትሆንና ለወደፊቱ ይበልጥ እንድትተጋ ይህንን ዕውቅና እንደሰጣት ተገልጿል። ተሸላሚዋ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ብቻ 38 ሕፃናትን በትምህርት፣ በቁሳቁስና በነፃ ሕክምና ከመርዳቷም በላይ በሚኪሊላንድ መንግሥት ትምህርት ቤት የእናት አምባሳደር በመሆን አገልግላለች። በተጨማሪም በሆለታ፣ በፋኖስ እና በጅማ ለሚገኙ ከ3,000 በላይ ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገች ሲሆን፣ በአረጋውያን፣ በተጣሉ ሕፃናት እና በካንሰር ታማሚዎች ዘንድ በመገኘት ማህበራዊ ድጋፍ ስትሰጥ መቆየቷ ተመልክቷል።
በዓመት ሦስት ጊዜ የደም ልገሳ ፕሮግራም በማዘጋጀትና ብቻቸውን ልጆቻቸውን የሚያሳድጉ እናቶችን እንዲሁም ከሱስ ለማገገም የሚጥሩ ሴቶችን በመደገፍ የምትታወቀው ኬብሮን፣ ሽልማቱን ከተቀበለች በኋላ ባስተላለፈችው መልዕክት “ውስጥ ካለኝ ሳይሆን ከሌለኝ ያካፈልኩት የኖርኩት ኑሮዬ ነው” በማለት ምስጋናዋን አቅርባለች። ወደፊትም በ“ልጄ ሆይ” ተግባሯ የተጣለባትን አደራ ለመወጣት ቃል የገባች ሲሆን፣ በገንዘብና በሃሳብ ከጎኗ ለቆሙት የ“200 ብር ቻሌንጅ” ተሳታፊዎችና የቅርብ ደጋፊዎቿ ምስጋናዋን አቅርባለች።
በርቺ ብለናል 🤝

7 days ago