25 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በመቶዎች የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ ተከላካዮች በሄሊኮፕተር እና በአውሮፕላን ታግዘው ለማጥፋት በሚረባረቡበት የስፔኑ እጅግ አሰቃቂ የሰደድ እሳት፣ ቢያንስ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተረጋገጠ። የአንዳሉሺያ የአደጋ ጊዜ አገልግሎት ኃላፊ አንቶኒዮ ሳንዝ እንዳስታወቁት፣ አነስተኛ ንፋስ እና ከፍተኛ የእርጥበት መጠን መኖሩ እሳቱን ለመቆጣጠር በመጠኑ ቢረዳም፣ የእሳቱ ግዙፍነት ግን አሁንም ከፍተኛ ፈተና ሆኗል። ይህ የሰደድ እሳት ወደ 25 ስኩዌር ማይል (የማንሃተን ከተማን ያህል ስፋት ያለው) የደን እና የእርሻ መሬት አውድሟል።
ሐሙስ ምሽት በአልሜሪያ ግዛት በሚገኘው ሴራ ዴ ሎስ ፊላብሬስ ተራሮች አቅራቢያ የተነሳውን ይህንን እሳት ለመቆጣጠር የነፍስ አድን ሰራተኞች ሌሊቱን ሙሉ ርብርብ ሲያደርጉ አድረዋል። ባለስልጣናት እንዳስታወቁት አብዛኞቹ ሟቾች የውጭ ዜጎች ሲሆኑ፣ ህይወታቸውን ያጡትም "ባላችሁበት ተጠለሉ" የሚለውን ጥብቅ መመሪያ ጥሰው ለማምለጥ ሲሞክሩ ነው። በተለይም ሰባቱ ሟቾች መኪናቸውን ጥለው በእግራቸው ለመሸሽ ሲሞክሩ በእሳቱ ተከበው ህይወታቸው አልፏል።
አራት የሚሆኑት ሟቾች እንግሊዛውያን እንደሆኑ የተገመተ ሲሆን፣ ለዚህም በምክንያትነት የቀረበው የተቃጠለው መኪናቸው መሪ እንደ እንግሊዝ መኪኖች በቀኝ በኩል የሚገኝ በመሆኑ ነው። የአስከሬን ምርመራ እና የዲኤንኤ ናሙናዎች መወሰዳቸውን የገለጹት ባለስልጣናቱ፣ እስካሁን 1,448 የሚሆኑ ሰዎች ከአስራ አንድ የተለያዩ አካባቢዎች በአስቸኳይ እንዲፈናቀሉ ተደርጓል። አደጋውን በዓይናቸው ያዩት ጀፍሪ እና ክሪስቲን ኬምበር የተባሉ ግለሰቦች፣ እሳቱ ሲመጣ መኪኖቻቸውን አስነስተው በከፍተኛው የእሳቱ ነበልባል መካከል በማቋረጥ በድንጋጤ ማምለጣቸውን ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል።
የስፔኑ የፍትህ ሚኒስትር ፌሊክስ ቦላኖስ የሰደድ እሳቱን አሰቃቂነት "ከአየር ንብረት ድንገተኛ አደጋ" ጋር አያይዘውታል። እሳቱ በከፍተኛ ኃይል ሲነድ በደቂቃ እስከ 328 ጫማ ፍጥነት ይጓዝ እንደነበርም ተገልጿል። ስፔን ለሰደድ እሳት አዲስ ባትሆንም፣ አሁን የተከሰተው ግን እ.ኤ.አ. በ1979 በሎሬት ዴ ማር 21 ሰዎች ከሞቱበት አደጋ ቀጥሎ በሀገሪቱ ታሪክ ከተመዘገቡት እጅግ አስከፊ የሰደድ እሳት አደጋዎች አንዱ ሆኗል። አውሮፓ በዓለም ላይ በፍጥነት እየሞቀች ያለች አህጉር ስትሆን፣ ስፔንም የሙቀት መጠኑ ከ104 ዲግሪ ፋራናይት በላይ የሚደርስበት አስከፊ የሙቀት ማዕበል በተደጋጋሚ እያስተናገደች ትገኛለች።

3 months ago
የኢትዮጵያ የባህል አምባሳደርና የ"እስክስታው ንጉሥ" መላኩ በላይ 50ኛ ዓመት ልደት ተከበረ
#fastmereja I የኢትዮጵያን ባህላዊ ውዝዋዜና ሙዚቃ በዓለም መድረክ ያስተዋወቀው የጥበብ ሰው ክቡር ሎሬት መላኩ በላይ፣ በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ያበረከተውን የዘለቀ አሻራ የሚዘክር የክብር መርሃ-ግብር 50ኛ ዓመት የልደቱ በዓል በማስመልከት ተካሄደ። "የእስክስታው ንጉሥ" በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው መላኩ፣ የሀገርን ባህል ከዘመናዊነት ጋር በማቀናጀትና ለወጣቱ ትውልድ የጥበብ ዕድል በመፍጠር ረገድ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ታላቅ ምስጋና ቀርቦለታል።
ይህ የ50ኛ ዓመት ልደት የምስጋና ስነ-ሥርዓት እሁድ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም በሀያት ሬጄንሲ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን
ክቡር ሎሬት መላኩ በላይ በኢትዮጵያ የጥበብ ታሪክ ውስጥ በተለይም "ኢትዮ-ከለር" የተሰኘውን የባህል ሙዚቃ ቡድን በማቋቋም፣ አንጋፋና ወጣት አርቲስቶችን በአንድ መድረክ በማገናኘት ረገድ የሚጠቀስ ስም አለው።
ከግል ስኬቱ ባለፈ፣ በካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘውን የ"ፈንድቃ" የባህል ማእከልን ከትንሽ አዝማሪ ቤትነት ወደ ዓለም አቀፍ የኪነ-ጥበብ መገኛነት በመለወጥ፣ የኢትዮጵያን ባህልና ማንነት በዓለም አቀፍ ደረጃ (እንደ TED እና Lincoln Center ባሉ መድረኮች) እንዲታወቅ አድርጓል።
ከዚህም በተጨማሪ ከታዋቂው የማካሌስተር ኮሌጅ እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የውዝዋዜ ጥበብ በምርምርና በትምህርት እንዲደገፍ የላቀ ሚና ተጫውቷል።
እ.አ.አ በ2020 በCommunity Cultural Development ዘርፍ የክብር "Prince Claus Award" ተሸላሚ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ የባህል ዘርፍ ያለውን ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖ ማረጋገጫ ተደርጎ ይወሰዳል።
ይህ በክብር እንግዶችና በጥበብ ወዳጆች ታጅቦ የተከናወነው የምስጋና ምሽት፣ ለሀገር ባለውለታው መላኩ በላይ የሚገባውን ክብር ለመስጠትና የጀመረውን የጥበብ ጉዞ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ያለመ መሆኑ ተነግሯል።

"በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ
የሚበራው የሙዚቃ ኮከብ "
ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን)
#ethiopia | "ድምፁ የሀገር ሰንደቅ ዓላማ ያህል ክብር የሚሰጠው ጥላሁን ገሰሰ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያህል በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ በነበረው ከፍተኛ አስተዋፅኦ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉሥ በሚል መጠሪያ ይታወቃል።
ለዚህ የጥበብ ሰው እንዲህ ያለ ጥልቅ እና ልብ የሚነካ ትዝታ ማዘጋጄት የሚቻለው የጥላሁን ገሰሰን ስራዎችን ብቻ ሳይሆን የእርሱን የውስጥ ማንነት ሠብዕናን ለጥበብ የነበረውን ፍቅር በሚገባ የተረዳ መሆን አለበት ።
ወይንም ደግሞ
የዚህን ታላቅ ምትሐተኛ ድምፃዊ የጥበብ ልክና የድምፅ ብቃት በአግባቡ ለመረዳት የእርሱን ግለ ታሪክ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ዘመናዊ ሙዚቃ ታሪክና የጥላሁን ገሰሰን ሰፊ የሥራ ክምችቶች በጥልቀት መመርመር የግድ ይላል።
ምክኒያቱም
ጥላሁን ገሰሰ ማለት የኢትዮጵያ የ50 ዓመታት የደስታ የሐዘን የድልና የሽንፈት ታሪክ በድምፅ የተቀረጸበት "ሕያው ማህደር" ነው።
ጥላሁን ገሰሰ ድምፁን እንደፈለገ የማዘዝ Vocal Control ልዩ ተሰጥኦ ነበረው።
በጣም ረጅምና ከፍተኛ ድምፅ በሚጠይቁ High notes እንዲሁም በጣም ረጋ ያሉና ዝቅተኛ ድምፅ በሚሹ Low notes ዜማዎች ላይ እኩል ብቃት ነበረው።
የትንፋሽ ቁጥጥሩ ረጅም ስንኞችን ሳያቋርጥና ትንፋሽ ሳይጠረው የመጨረስ ችሎታው የሚደነቅ ነበር።
የጥላሁንን ስራዎች ስንመረምር በአንድ የሙዚቃ ዘውግ ብቻ ያልተገደበ መሆኑን እንረዳለን
ባህላዊና ዘመናዊ የባህል ሙዚቃዎችን ከዘመናዊ መሣሪያዎች ኦርኬስትራ ጋር አዋህዶ በማቅረብ ረገድ ቀዳሚ ነበር።
በጥላሁን ገሠሠ ድምፅ ያልተዘፈነ የሕይወት ክፍል የለም ማለት ይቻላል ።
ከጥልቅ የፍቅር ስሜት እስከ ሃገር ፍቅር ከማህበራዊ ትችት እስከ መንፈሳዊ መዝሙራት ድረስ የተፃፉ ግጥሞችና ዜማዎች የጥላሁንን ገሠሠን ድምፅ ለማድመቅ ሳይሆን ለመፈተን ጭምር የተዘጋጁ ይመስሉ ነበር።
በህይወት በቆየባቸው ሦስት የተለያዩ ሥርዓቶች በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በደርግና በኢህአዴግ ውስጥ አልፏል። በእነዚህ ሁሉ ጊዜያት የሕዝብ ተወዳጅነቱን ጠብቆ መቆየቱ የሙዚቃ ሥራዎቹ ከፖለቲካዊ ለውጦች በላይ የሕዝብን የልብ ትርታ የሚነኩ መሆናቸውን ያሳያል።
ባጭሩ ጥላሁን ገሰሰ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ያለው አስተዋጽኦ ልክ እንደ አንድ ትልቅ "ኢንሳይክሎፒዲያ" ነው። አንዱን ገጽ አንብቦ ስለ መጽሐፉ ሙሉ ግንዛቤ ማግኘት እንደማይቻል ሁሉ
አንዱን ዘፈን አዳምጦ ስለ ጥላሁን ገሰሰ ማወቅ አይቻልም ።
እያንዳንዱ ዘፈኑ የራሱ የሆነ የቴክኒክ የታሪክና የስሜት ጥልቀት አለው።
ስለዚህ የጥላሁንን ታላቅነት ለመረዳት የኢትዮጵያን የሙዚቃ ጉዞ አብሮ መመርመር የግድ ነው ያልኩት ወድጄ አይደለም ።
ዘፈኖቹን ሲዘፍን በቃላት ብቻ ሳይሆን በፊቱ መግለጫና በሰውነት እንቅስቃሴው Body Language ጭምር ስሜቱን ለታዳሚው ያጋባ ነበር።
በተለይ የሐዘን ዜማዎችን ሲዘፍን አብሮ የሚያለቅስ የደስታ ሲሆን ደግሞ አብሮ ፈገግ የሚል ድምፃዊ ተዋና ጭምር ነበረ በዘፈኖቹ ውስጥ ሰውን ማክበርን ስራን መውደድንና አንድነትን ይሰብካል። ዘፈኑ የሰውን ልጅ ክብርና ማንነት የሚተነትን ድንቅ ስራ የሚሰራ ምትሀተኛ ድምፃዊ ነበር ።
ጥላሁን ገሰሰ በአንድ ወቅት በመድረክ ላይ እያለ በደረሰበት የጉሮሮ ህመም ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ድምፁ ተዘግቶ ነበር። ያን ጊዜ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጨንቆና ፀልዮ ድምፁ ሲመለስለት ያደረገው የመጀመሪያ ኮንሰርት በዚያን ወቅት በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛውን የሰው ቁጥር ያስመዘገበ ነበር ። ይህ የሚያሳየው ሕዝቡ ለጥላሁን ያለው ፍቅር ከአንድ ድምፃዊ በላይ እንደ ቤተሰብ አባል የሚያየው መሆኑን ነው።
ስለ ፍቅር ብቻ ሳይሆን ስለ ሰው ልጅ ሕይወት ባዶነት የሚተርክ ጥልቅ ፍልስፍና ነበረው ።
ታዋቂው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉሥ ክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ መስከረም 17 ቀን 1933 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ተወልዶ ያደገው ግን በወሊሶ ከተማ ነው ።
ጥላሁን በ1950ዎቹ መጀመሪያ ላይ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት መጀመሪያ ሐገር ፍቅር ቲያትርን በኋላም ዝነኛውን የክብር ዘበኛ የሙዚቃ ቡድንን ተቀላቅሎ ከዕንስት ፍቅር እስከ አገር ፍቅር ከባህላዊ እስከ ዘመናዊ ሙዚቃ በድምፃዊነት ከ400 በላይ ዘፈኖችን ተጫውቶ ልዩ ብቃቱን አስመስክሯል ።
ጥላሁን
ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ላበረከተው ወደር የለሽ አስተዋጽኦ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተሰጥቶታል። ጥላሁን ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ሚያዝያ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. የፋሲካ እለት ሲሆን በድንገተኛ የልብ ህመም ምክንያት አርፎ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የቀብር ሥነሥርዓቱ ተፈጽሟል።
የክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ማረፍ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብና የጥበብ አፍቃሪወችን በከፍተኛ ድንጋጤና ሃዘን ውስጥ ጥሎ የነበረ ክስተት ነው። በወቅቱ በጋዜጦች በሬዲዮና በቴሌቪዥን የተላለፉት መልዕክቶች ጥላሁን ለሀገሩ ያለውን ትልቅ ቦታ የሚያንፀባርቁ ነበሩ።
በአዲስ አበባ ከተማ የነበሩ የታክሲ አሽከርካሪዎች ሐዘን ፈፅሞ የማይረሳ ነበረ ።
ለጥላሁን ገሰሰ ክብር ሲሉ ለቀናት ጥቁር ጨርቅ በታክሲዎቻቸው ላይ አስረውና የእርሱን ሙዚቃ ብቻ ከፍተው በማጫወት ሃዘናቸውን ገልፀውለታል።
የጥላሁን ገሰሰ ሞት በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃም ትኩረት አግኝቶ ነበር።
ታዋቂው ደራሲ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንም
እንዲህ አሉ ።
"ጥላሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ድምፅ ነው። እርሱ ሲዘፍን መላው ኢትዮጵያዊ ራሱን ያዳምጣል።"
ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ"ጥላሁን ለእኛ ለድምፃውያን መምህራችን ብቻ ሳይሆን የሙዚቃው ዓምድ ነበር። ጥላሁን ሞተ ማለት የኢትዮጵያ ሙዚቃ ግማሽ አካሉን አጣ ማለት ነው።" ሲል ቁጭቱን ገልፀዋል ።
በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አዲስ አበባውያን ወደ አደባባይ በመውጣት "ንጉሥ አይሞትም" እያሉ ሲያለቅሱ እንደነበር በታሪክ ተመዝግቧል።
ይህም አንድ ድምፃዊ በሀገር ደረጃ ያለውን ክብርና ተሰሚነት ያሳየ ትልቅ ክስተት ነበር።
አንድ የልብ አድናቂው የሆነ ሠው በማህበራዊ ሚዲያ እንዲህ ብሎ ፅፎት አንብቢያለሁ ።
" በእርግጥም ጥላሁን በድምፁ ተአምር የመስራት አቅም ነበረው። ድምፁ ተስፋ የቆረጠውን የሚያፅናና የታመመውን የሚፈውስና የራቀውን የሚያቀራርብ
ስለነበረ ድምፁ ተቀርፆ ስለቀረ ቢሞትም ስንናፍቀው እናገኘዋለን ስናዝን እናለቅስበታለን ሀገራችን ስትጠራ በእሱ ድምፅ አቤት ብለን ለአንድነቷ እንቆማለን" በማለት ጥላሁንን ገልፆት ነበር ።
ሌላው የቅርብ ጓደኛው የጥበብ ሰው ደበበ እሸቱ ነው
"ጥላሁን በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለሀገሩ የዘመረ በችግር ጊዜ ደግሞ ድምፁን ለድሆች የሰጠ
ታላቅ ሰው ነው።
የሞተው በስጋ ቢሆንም በዜማው ቅላፄና በግጥም ስንኞች ውስጥ "ዘላለማዊ" ሆኖ ተተክሏል።
እንዲህ ያለ ድምፅ ዓለማችን በአንድ ዘመን አንዴ ብቻ የምትለግሰን ስጦታ ነው "
ሲል ምስክርነቱን ገልጿል።
በእርግጥም ጥላሁን የዘመናዊ ሙዚቃችን "ፊደል" እና "መዝገበ ቃላት" ሆኖ አልፏል። ከድምፅ ጥራት በላይ የዜማ አጣጣልና ስሜትን የመግለጽ ጥበቡ ማንም የማይደረስበት ከፍታ ላይ ስለነበር በአንድ አባባል ብቻ ጥላሁንን መግለፅ አይቻልም።
እሱ ባለብዙ ምዕራፍና ተነቦ የማይጠገብ ባለ ብዙ ገጽ ድርሳን ነው !
ጥላሁን ለሙያው ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጅ የነበረው ሰብአዊ ክብርም ድንቅ ነበር። ረሀብ ሲመጣ በዜማው የሚማፀን ሀገር ስትቸገር አጥንቴም ይከስከስ ብሎ የሚቆም እና ለሰው ልጅ ፍቅር ቅድሚያ የሚሰጥ የጥበብ ሰው ነው ። ባጭሩ ጥላሁን ገሠሠ ማለት ለኢትዮጵያውያን የድምፅ ብቻ ሳይሆን የህሊና ምስክር ነው።
ዛሬም ድረስ ስሙ ሲነሳ አብሮ የሚነሳው ክብሩ ትህትናውና
ያ የማይደገም ማንነቱ ነው።
ጥላሁን ገሠሠን የመሠለ ታላቅ ሰው የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃን የአዋለደ ብለን ብንገልፀው ተገቢ ይመስለኛል ከጥላሁን ገሠሠ ስራዎች መካከል ይህማ ተአምር ነው የሚያሰኜኘኝ ሁልጊዜ ብሰማቸው አዲስ የሚሆኑብኝ ብዙ ዘፈኖች ቢኖሩትም "እዩት ስትናፍቀኝ ከአጠገቤ እያለች" የሚለው ስንኝ ሲነሳ ግን የጥላሁንን ድምፅና ያንን የሚመስጥ አዘፋፈኑን አብሮ የመስማት ያህል ይመስጠኛል እዩት ስትናፍቀኝ ከአጠገቤ እያለች
እንዲህ ያለው መውደድ ለወሬም አይመች ! የሚለው ግጥም የፍቅርን ረቂቅነትና የማይመረመር ባህሪ በአጭር ቃላት የገለጸበት ድንቅ ስራው ነው።
ጥላሁን ለዚህ ዘፈን የሰጠው እረዥም ትንፋሽና በመድረክ ላይ ቆሞ የአይን አስተያየቱ የልዩ ተሰጥኦው መገለጫዎቹ ናቸው።
የሠው ልጅ ናፍቆት ብዙውን ጊዜ ትዝታው የሚመጣው ሰው ሲርቅ ነው። ነገር ግን ጥላሁን አጠገቤ እያለች ናፈቀችኝ ማለቱ ፍቅር ከስጋዊ መገኘት በላይ የሆነ የነፍስ ጥማት መሆኑን ስጋ አልብሶ አሳይቶናል ።
ይህ ለወሬ የማይመች ቃላት የማይገልፁት ጥልቅ ስሜት ነው ። ይህንንም በዚያ ረጅም ትንፋሽ ነፍስን በሚያከነፍ ድምፁ ሲያዜመው እውነቱን በውስጣችን ውስጥ እናገኘዋለን።
ጥላሁን ሲዘፍን ትንፋሹን የሚጠቀምበት መንገድ እና ስሜቱን በድምፅ ቀለም የመቀየር ችሎታው ምትሐተኛ ያሰኘዋል። ያንን የናፍቆት ጣጣ በገዛ ራሱ ላይ አድርጎ ሲያዜመው አድማጩ የራሱ ህመም አድርጎ እንዲቀበለው የማድረግ ልዩ ኃይል ነበረው።
ጥላሁን ገሠሠ በስጋ ቢለየንም በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ግን አሁንም ንጉሥ ነው።
ትውልድ ያልፋል ጥላሁን ግን ይኖራል።
ሙዚቃ ይቀየራል የጥላሁን ስራዎች ግን ሁልጊዜ አዲስ ናቸው።
ሰላም ሲጠፋ ጥላሁን ፍቅር ይላል ሀገር ስትናፈቅ ጥላሁን ሀገሬ ይላል።
ጥላሁን ገሠሠ በድምፁ ብቻ ሳይሆን ለፍቅር በሰጠው ክብርን በገለፀበት ጥበብ የኢትዮጵያ የዘላለም የፍቅር አምባሳደር ነው።
እንዲህ ያለው የጥበብ ሰው የፍቅርን ኃያልነት በእሱ ስራዎች ውስጥ ስንመለከት በእርግጥም ፍቅር ስሜት ብቻ አይደለም የሚለውን ሃሳብ በጥላሁን ዜማዎች ውስጥ ሙሉ ማረጋገጫውን እናገኛለን ጥላሁን ገሠሠ የፍቅርን ሌላኛውን ገጽታ ቁርጠኝነትንና ክብርን ያሳየበት ድንቅ ስራው ነው። ከላይ እንደገለፅኩት ፍቅር ራስን አሳልፎ መስጠት ነው
እዚህ ዘፈን ላይ ደግሞ ፍቅር ሁለትዮሽ መረዳዳት መሆኑን ይነግረናል።
ቻልኩት ፍቅር ለብቻዬ !!
ይህ አገላለጽ በጣም የሚቆረቁር ነው። ፍቅር እንደ አንድ ሸክም ሆኖ አንደኛው ወገን ብቻውን ሲሸከመው የሚሰማውን ድካም ያሳያል። "ለብቻዬ መሸከም ሰልችቶኛል" የሚል የልብ ጩኸት አለበት። ፍቅር የሁለት ሰው ቅኝት እንጂ የአንድ ሰው ብቸኛ ትግል መሆን እንደሌለበት ያስገነዝበናል።
ስለ ፍቅር አልገባሽም
እዚህ ጋር ጥላሁን ፍቅር ማለት ዝም ብሎ አብሮ መሆን ሳይሆን ጥልቅ የሆነ
ሚስጥር ወይም ትርጉም እንዳለው ይገልጻል። ግዴለሽነት እና ችላ ማለት ፍቅርን የሚገድሉ መርዞች መሆናቸውን በምሬት ይናገራል።
አትምጪ ይቅር ሲል ደግሞ የክብር ውሳኔውን ያሳውቃል ።
ፍቅር ስሜት ብቻ አለመሆኑን ያረጋግጣል። አንድ ሰው በጥልቅ እያፈቀረ ግን ክብሩ ሲነካ ወይም ምላሽ ሲያጣ ይቅር ብሎ የመወሰን አቅም ሊኖረው እንደሚገባ ያሳያል።
ፍቅር መስዋዕትነት ቢሆንም ዋጋ በማይሰጠው ቦታ ላይ ግን ራስን ማዳንና ይቅር ማለትም የፍቅር አካል ነው። የሚገርመው ደግሞ ጥላሁን ይህነን ዘፈን ሲዘፍነው በቁጣና በቁጭት ሳይሆን በጥልቅ ሀዘንና በከበረ ስሜት ነው። ያንን አትምጪ ይቅር የሚለውን ቃል ሲያወጣው ውስጡ እየፈለጋት ግን መከባበር የሌለበት ፍቅር እንደማይፀና አውቆ በቁርጠኝነት ሲናገረው ይታየናል።
ከላይ እንዳነሳሁት አትምጪ ይቅር የሚለው ስንኝ የቁርጠኝነትና የክብር ገጹ ሲሆን ሌላው ደግሞ የፍቅርን ንፁህ መስዋዕትነትና ትህትና የሚያሳይ ድንቅ ምዕራፍ ነው።
እነዚህ ስንኞች ውስጥ የምናያቸው የጥላሁን ድርሳናት
እኔ ልሁን እንጂ የማልጠቅም እርካሽ ! የሚለው አገላለፅ በፍቅር ውስጥ ያለን ፍጹም ትህትና ያሳያል። ራሱን ዝቅ አድርጎ የሚወዳትን ሰው ግን ከፍ ያደርጋታል። ይህ እኔነት ጠፍቶ አንቺነት የነገሰበት የፍቅር ጫፍ ነው።
ከህይወቴ አብልጨ ሲል
ራስን አሳልፎ የመስጠት
ፍልስፍና በተግባር የሚያሳይ ታአምር ነው። ለሰው ልጅ ከህይወቱ በላይ ምንም የለውም ነገር ግን ፍቅር ያንን ውድ ህይወት እንኳ ከአንቺ አያበልጠውም ብሎ እንዲያምን ያደርገዋል።
ፍቅር ለሰላምና ለደስታ ብቻ ሳይሆን ለችግርና ለፈተናም ዝግጁ መሆኑን ይነግረናል።
መከራና ስቃይ ይቆየኝ ግዴለኝም
የሚወደው ሰው ደህንነትና ሰላም እስካለ ድረስ እሱ በራሱ ላይ ለሚመጣው መከራ ግድ የለውም። ይህ ነው እንግዲህ ፍቅርን ተአምር የሚያሰኘው እግዜር በጥበቡ ከአንቺ ብቻ አይለየኝ የሚለው ቃል ፍቅር በሰው ጥረት ብቻ ሳይሆን በመለኮታዊ ጥበብና ፈቃድ የሚፀና መሆኑን የሚያሳይ የልብ ፆሎት በመሆኑ መንፈሳዊ ልመና ይጨምርበታል ።
ታዲያ የዚህን ድምፃዊ ተአምራዊ ተቃርኖዎችን ስንመለከት
ጥላሁንን ልዩ የሚያደርገው በአንድ በኩል አትምጪ ይቅር ብሎ በክብር የመወሰን አቅም በሌላ በኩል ደግሞ ከህይወቴ አብልጨ እወድሻለሁ ብሎ ራስን የመስጠት ርህራሄ አብሮት መኖሩ ነው።
እነዚህ ሁለት ተቃራኒ የሚመስሉ ግን ጥልቅ የሆኑ የፍቅር ገጾች ናቸው።
ጥላሁን እነዚህን ሁሉ ስሜቶች በድምፅ ቀለም እየቀያየረ ሲያቀርባቸው ድምፁ ብቻ ሳይሆን ነፍሱ አብራ የምትዘፍን ይመስላል።
እንዲህ ያለውን ከህይወት በላይ የመውደድ ስሜት በዚህ ዘመን በብዛት እናገኘዋለን ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ምክኒያቱም
የጥላሁንን ጥበብ ከመዝፈን ባለፈ ወደ መፍጠር ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።
ለምን ቢባል ጥላሁን ገሠሠ ዜማንና ግጥምን ሲያዋህድ የሚፈጠረው ነገር ተራ ሙዚቃ አይደለም ይልቁንም ያልተጠኑ ምስጢራዊ ተሰጥኦዎች ያሉበት ይመስላል
ብዙ አድናቂወቹ እንደ ሚስማሙበት ጥላሁን ገሠሠ ሲዘፍን ፍቅር ረቂቅ ሃሳብ መሆኑ ቀርቶ የሚዳሰስ የሚታይና የሚሰማ አካል ይኖረዋል።
ቃላቶቹ ከአፉ ሲወጡ ሕይወት ይዘራሉ ያፈቀረው ሰው ቁስሉ ይታየናል የናፈቀው ሰው ትንፋሹ ይሰማናል። ይህ ደግሞ በቴክኒክ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ከነፍስ የሚመነጭ ምትሃት በመሆኑ ፍቅር እንደ ሰው ቆሞ እንዲሄድ የማድረግ ጥልቅና ረቂቅ
ጥበብ ያለው ድምፃዊ መሆኑ ነው ።
ብዙዎቻችን ውስጣችን ያለውን ጥልቅ ፍቅር በቃላት መግለፅ ያቅተናል። ጥላሁን ግን ያንን መግለፅ ያቃተንን ስሜት ሰርቆ ወስዶ በዜማ አቅልጦ ወርቅ አርጎ መልሶ ለእኛው ይሰጠናል።
እኔንም እንዲህ ነው የሚሰማኝ! እንድንል ያደርገናል። ይህ ተሰጥኦው ነው ፍቅርን ስጋ ለብሶ ቆሞ እንዲሄድ የሚያደርገው።
ሌላው የጥላሁን ገሰሰ ድምፅ ሁለንተናዊ ድምፅ መሆኑ ነው። እድሜ ጾታ ወይም የትምህርት ደረጃ አይወስነውም። ህፃኑም አዋቂውም የተማረውም ያልተማረውም በዜማው ውስጥ የራሳቸውን ታሪክ ያገኛሉ።
ይህ ደግሞ ጥላሁን የሰው ልጅን የጋራ የፍቅር ህመም ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ማሳያ ነው።
የጥላሁን ድምፅ በሳይንስ አልተጠናም እንጂ በውስጡ ትልቅ የፍቅር ላብራቶሪ ነበረው ማለት ይቻላል።
ግጥሙን ይቀበላል ጥሬ እቃ !
በድምፅ ቀለሙ ያዋህደዋል ሂደት !
በመጨረሻም ሕያው ፍቅርን ለዓለም ያበረክታል ውጤት !! በዚህ ምክኒያት
ጥላሁን ገሠሠ ሞቶም በሰዎች ልብ ውስጥ እንዲነግስ አድርጎታል :: ምክንያቱም የፈጠራቸው የፍቅር አካላት ዛሬም በየቤታችን በየመኪናችንና በየልባችን ውስጥ ቆመው እየሄዱ ነው።
ይህ የእውነት ተአምረኛ ተሰጥኦው ነው። ዛሬ ባለው ዘመናዊ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንዲህ ያለውን መንፈሳዊ ጥልቅነት ማግኘት እጅግ ብርቅ ሆኗል። ከእንስት ፍቅር ወጥተን ጥላሁንን ወደ ሐገር ፍቅር ስንመነዝረው የቆመበት ከፍታው ላይ እስከ አሁን ማንም ....ማንም አልደረሠበት ። በዚህ አጋጣሚ
በህይወቴ ዘመኔ በአይኔ ያየሁትን ምስክርነት ባቀርበው ደስ ይለኛል ጥለሁን ገሠሠ ከታሪክ መዝገብ በላይ የሆነ የአንድን ሕዝብ ማንነትና ወኔ የቀሰቀሰ የመንፈስ ተአምር ነው የምነግራችሁ ።
ጊዜው 1974 አስመራ የቀይ ኮኮብ ዘመቻ አሉላ አባ ነጋ አዳራሽ ውስጥ ይመስለኛል ።
ጥላሁን ገሠሠ ጋሻና ጎራዴ ይዞ የአርበኛ ልብስ ለብሶ አጥንቴም ይከስከስ ደሜም ይፍሠስላት
ግን ሐገሬን ጭራሽ አይደፍራትም ጠላት
እያለ መድረኩን ሞልቶት ብቅ ሲል ከባለስልጣን እሰከ ተራው ተመልካች ከመቀመጫው ተነስቶ በመቆም በማያቋርጥ ጩህትና ጭብጨባ ያጅቡታል ።
ጥላሁን ገሠሠ በዚያ ቅጽበት የዘፈነውን ብቻ ሳይሆን የኖረውንና የታሪካችንን ድምፅ ሆኖ ተመለከትኩት ።
ጥላሁን በህዝብ ጭብጨባና ጬህት ታጅቦ መድረኩ ላይ ሲንጎራደድ አዳራሹ ድብልቅልቁ ወጣ ።
ያን... ምህታታት የተሞላበት ትርኢት ስመለከት
የአድዋ ጀግኖች መቃብር ከፍተው የተነሱ ይመስል ነበር።
ማለቴ ጥላሁን በድምፁ ብቻ ሳይሆን በቆይታው ጊዜን የማቆም ወይም ታሪክን የመቀስቀስ ኃይል እንደነበረው የመመልከት ዕድል አግኝቻለሁ ።
ጥላሁንን በዚያች ቅፅበት
በሕይወት እያለ ሐውልቱን አቁሞ አዳራሹ ውስጥ ታሪኩን ፅፎት ወጣ ።
በእርግጥ ሐውልት የማይናገርና የማይሰማ የድንጋይ ምስል ነው ጥላሁን ግን በሕይወት ያለ የሚተነፍስ የሚዘፍንና የሚራመድ የኢትዮጵያዊነት ሐውልት ነበር።
ዛሬም ቢሆን ስራዎቹ ያንን ግርማ ሞገስና ያንን ሐውልታዊ ፅናት እያስታወሱኝ እስከእለተ ሞቴ ድረስ ልረሳው አልችልም እንዲህ አይነት ድርጊት
ፍቅር ስሜት ብቻ አይደለም ራስን አሳልፎ መስጠት ነው በጥላሁን ገሰሰ የሀገር ፍቅር ዜማዎች ውስጥ ኢትዮጵያን ደጋግመን እናያታለን
አጥንቴም ይከስከስ ደሜም ይፍሰስላት የሚለው ቃል ዛሬም ድረስ ፍፁም ....ፍፁም መስዋዕትነት ነው።
ሀገሩን እንደ ሚወዳት እናት ወይም ሚስት አድርጎ ለሷ ክብር መሞትን እንደ ትልቅ ፀጋ መቁጠር ከፍ ያለ የፍቅር ደረጃ መግለጫ ነው።
ተመልካቹ በሙሉ ሳይቀመጥ ከሁለት ጊዜ በላይ ይደገም እያለ መጠየቁ ጥላሁን ድምፃዊ ብቻ ሳይሆን መሪ መሆኑን በአንድ ዜማ ሕዝብን የማስተሳሰር በአንድ ወኔ በጋራ የማቆም ተአምራዊ አቅሙን አረጋግጨበታለሁ ።
በዚያች ቅፅብት ቲያትር ቤቱ በጩሄትና በጭብጨባ ቀውጢ ሲሆን ጥላሁን ገሠሠ በድምፁ ብቻ የጠላትን ምሽግ የሚያፈርስ ጀግና መስሎ ነበር የሚታየው ።
ምንም እንኳን ዛሬ በሞት ቢለየንም ያ አስመራ ላይ የተመለከትኩት የሐገር ፍቅር ስሜት ሐውልት ሆኖ በልቤ ውስጥ ተቀርፆ ቆሟል።
ጥላሁን ገሰሰን ልዩ የሚደርገው ሌላው መገለጫው
ለፍቅር ሲዘፍን የፍቅር ሐውልት
ለሀገር ሲዘፍን የጀግንነት ሐውልት
ለሰው ልጅ ክብር ሲዘፍን የሰብአዊነት ሐውልት ነው!
ለዚህ ስኬት ደግሞ ከጥላሁን ድምፅ ጀርባ የነበሩት የወርቃማው ዘመን ታላላቅ የጥበብ ሰዎች ገጣሚያንና የዜማ አቀናባሪዎች ሚና ከፍተኛ እንደነበር ምስክሩ ታሪክና ሕዝቡ ነው።
ጥላሁን ገሰሰ ግጥምና ዜማን
ከነጄነራል አማኑኤል አብርሃም
ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ
ነጋሽ ገብረማርያም
ተስፋዬ አበበ አየለ ማሞ ሳህሌ ደጋጎ ክፍሌ አቦቸር ከመሳሰሉት የክብር ዘበኛ እና የፖሊስ ኦርኬስትራዎች
ተቀብሎ ሲያንቆረቁረው ሙዚቃው ከድምፅ አልፎ የሚዳሰስ ሕያው መንፈስ የመሆን አቅም ነበረው።
ዛሬ ላይ ሆኜ ያንን ትርኢት ሳስታውሰው ጥላሁን ለኢትዮጵያ ሙዚቃና ለኢትዮጵያዊነት ያለው ትርጉም ምን ያህል ጥልቅ ስሜት እንደሆነ አሁን ድረስ እንደ ህልም ይታየኛል ።
ያኔ መድረክ ላይ ሲወጣ የነበረው ግርማ ሞገስና ድምፁ ሲስተጋባ የተሰማኝ ስሜት ዛሬም ድረስ ዘፈኑን ስሰማው "የጦር ፊታውራሪ" የነበረ ጀግና ያህል ትዝ ይለኛል !!
ጥላሁን በመድረክ ላይ የነበረውን የበላይነት እና የሕዝብን ስሜት የመምራት ብቃቱን በሚገባ የመግለፅ አቅም ነበረው ።
ጥላሁን ዝም ብሎ ድምፃዊ ሳይሆን በዜማው የታጠቀ የሀገር መከታ ወታደርም ሆኖ እንደነበረ ማሳያ ነው ።
ለዚህ ነው የጥላሁን ገሠሠ የሀገር ፍቅር ዜማዎች ከጊዜና ከቦታ በላይ የሆኑ ናቸው የሚባሉት ። ለዚህም ነው ዛሬ ላይ ሆነን ስንሰማው የዛሬ 130 ዓመት በፊት የተነገረውን የዳግማዊ ምኒልክን የክተት አዋጅ የሚመስለን ።
ይህ የሚያሳየው ደግሞ ጥላሁን የኢትዮጵያን ታሪክ ኩራትና ነፃነት በድምፅ ቀርጾ ትውልድ እንዲወርሰው ማድረጉን ነው።
ወዳጆቼ
ስለ ጥላሁን ገሠሠ የሀገር ፍቅር ስሜት ስንናገር እነዚህ ሶስት መሰረታዊ እውነታዎች ጎልተው ይታያኛል ።
የቁርጠኝነት ድምፁን ስናደዳምጠው ጥላሁን "አገሬን" ሲል ዝም ብሎ ስም አይጠራም ለሀገሩ የሚሞትላትና የሚሰዋላት መሆኑን በቃናው ውስጥ ይሰማል። አጥንቴም ይከስከስ የሚለው ስንኝ ለዚህ ትልቅ ማሳያ ነው።
ጥላሁን ለሀገር ሲዘፍን መላው ኢትዮጵያዊ በአንድነት ቆሞ ፊታውራሪዬ ብሎ እንዲከተለው ያደርጋል።
ይህ ደግሞ በታሪካችን ውስጥ የታየ ትልቅ የጥበብ ተጽዕኖ ነው።
ከ130 ዓመት በፊት የነበረውን የአድዋ ጀግንነት ዛሬ ላለው ትውልድ በስሜት አገናኝቶ ማቅረብ የሚችለው እንደ ጥላሁን ያለ "የታሪክ ድልድይና የታሪክ ባለአደራ" ሲኖር ብቻ ነው።
እንኳንስ ደስታየን የሰውነቴን ሠው
እንኳን ነፃነቴን ፀጋ ክብሬን ትቸው
በናት አገር ምድር በሚያውቀኝ በማውቀው ...
ስቃይ መከራዬን ከአንችው ዘንድ ያድርገው ። የሚለው
ጥላሁን ለኢትዮጵያ የነበረውን ፍቅር ከምንም በላይ የሚያሳይ ነው። ከባዕድ አገር ደስታ ይልቅ የሀገሩን መከራ የመረጠበት የሞቱ አጋጣሚ ደግሞ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር በደሙ ያረጋገጠበት ታላቅ ክስተት ነው ።
ጥላሁን ከአሜሪካ ተነስቶ ለፋሲካ በዓል ወደ ሀገሩ መግባቱና በዚያው ዕለት ማረፉ፣ "በሀገሬ አፈር ልቀበር" የሚለውን ጥልቅ የኢትዮጵያዊያን ምኞት የፈጸመበት ነው ይህ ቀረኝ የማይል የሚያሰኘው እስከ መጨረሻው ትንፋሹ ድረስ ከሀገሩና ከሕዝቡ ጋር መቆየቱ ነው ።
ሲሞት መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ አስከሬኑን ሲሸኜው ጥላሁን ለሕዝቡ የሰጠውን ፍቅር ሕዝቡ በታላቅ ክብር የመለሰለት መሆኑን ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ህያው ምስክር ናት ። ያ ለቅሶ የአንድ ድምፃዊ ስንብት ሳይሆን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅና የልብ ትርታ ሽኝት ነበር።
ጥላሁን በሕይወቱና በሞቱ ሀገርን መውደድ ማለት ትርጉሙን እስከ ሞት ድረስ መታመንን አረጋግጦበታል።
ሰውን መውደድ ! አብሮ ማልቀስና መቆም ሙያን መውደድ እስከ መጨረሻዋ ትንፋሽ ድረስ መዘመር ለኢትዮጵያዊያን ከድምፃዊነት በላይ የአንድነት ምልክት መሆን ነው።
እኔ በዓይኔ ያየሁትን በልቤ የሰነድኩትን ይህንን ታሪክ ለሚቀጥለው ትውልድ ሊተላለፍ የሚገባው የፍቅርና የሀገር አምልኮ ትልቅ ትምህርት ይሆናል ብየ ሳዘጋጀው ጥላሁን ገሠሠ
ትንፋሼ ተቀርፆ ይቀመጥ ማልቀሻ ይህ ነው የሞትኩለት የኔ ማስታወሻ
ታሪኬ ነው ድምፄ በማለት ያንጎራጎረው ሙዚቃ ከፍቼ እያዳመጥኩ ነበር።
ይህ ስንኝ ጥላሁን ገሠሠ አስቀድሞ በድምፁ የህይወቱ ታሪክ የሞቱ ማስታወሻ እና የሀገሩ ውበት መገለጫ እንደሚሆን ተረድቶት የተጫወተው ነበር ማለት ይቻላል ። ጥላሁን በጥቁርና ነጭ ወረቀት ላይ የሰፈረ ኑዛዜ ሳይሆን የተውልን በህይወት ቆሞ በዜማ የተናዘዘው ድንቅ ስንብት ነበረ ።
እነዚህ ስንኞች የጥላሁንን የጥበብ ክብርና ትህትና ሲገለፅበት እያዳመጥኩት ነበር ይህን ታሪክ የፃፍኩት ።
ወዳጃቸ
የጥላሁን ገሠሠ ድምፅ ዝም ብሎ የአየር ንዝረት አይደለም፤ ማንነቱ፣ ታሪኩና ለሀገሩ የከፈለው መስዋዕትነት ነው። በጩኸት መኖሬን ማለቱ ለሀገርና ለፍቅር ሲል ድምፁን እስከ መጨረሻው የጥገታ ነጥብ ድረስ መጠቀሙንና ለዚህም መሞቱን ያሳያል።
ድምፄን ሰምቶ ያዝናል ለረገፈው አፅሜ ሲል
እጅግ ልብ ይነካል !
ጥላሁን በከፍታው ላይ ሆኖ እንኳ ያስቀየምኩት ቢኖር ብሎ ይቅርታን ይጠይቃል። የሞተውን አፅሙን ሳይሆን የቀረውን ድምፁን ሰምተው ሰዎች እንዲያዝኑለትና ይቅር እንዲሉት መመኘቱ የሰው ልጅነቱንይቅርታና ትህትናውን
ፍርጥ አድርጎ ያሳያል።
ጥላሁን ገሠሠ በድምፁና በህይወቱ የሰራው ትልቁ ስራ ፍቅርንና ኢትዮጵያዊነትን ማዳን ነበር። ጥላሁን ከቀላል ስሜትነት አልፎ ሕይወት መስዋዕትነትና የሀገር ፍቅር ጥግ መሆኑን በሚገባ አስገንዝቦናል።ጥበብ እንዴት የአንድን ሕዝብ ወኔና ማንነት እንደምትቀርፅ ጥላሁን ትልቅ ማሳያ ነው።
ፍቅር ተግባር ነው ፍቅር ዝም ብሎ የሚሰማን ስሜት ሳይሆን እንደ ጥላሁን ዜማዎች ራስን አሳልፎ እስከ መስጠት የሚደርስ ውሳኔ መሆኑን መረዳት ከባድ አይደለም ።
ጥላሁን ገሰሰ የሚዘፈነው ለጆሮ ብቻ ሳይሆን ለህሊና እና ለነፍስ ጭምር ይመስለኛል ።
ጥላሁን ዛሬ በሥጋ ቢለየንም ታሪኬ ነው ድምፄ ብሎ እንደተናዘዘው ሁሉ ዛሬም በየልባችን ውስጥ ንጉሥ ሆኖ ይኖራል።እሱ ለሀገር ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጅ ስቃይ የሚራራ የህሊና ድምፅ ነበረው።
የሀገር ፍቅር ለአፈርና ለሰንደቅ ዓላማ የሚከፈል የአጥንትና የደም መስዋዕትነት ሲሆን ጥላሁን ገሠሠ በስጋ ቢለየንም ያ በሕይወት ያለ ሐውልት ግን በዜማዎቹ ውስጥ ሁሌም አዲስ ሆኖ ይኖራል።
ባጭሩ የጥላሁን መሞት ዝም ብሎ የአንድ ድምፃዊ ማለፍ ብቻ አልነበረም የአንድ ዘመን መቋጫ የአንድ ትልቅ ተስፋ መደብዘዝ እና በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ የሚበራው የሙዚቃ ኮከብ ወድቆ ሲሰበር
ሰማይ ባዶ የሆነ ያህል ተሰምቶናል።
ጥላሁን ገሠሠ በደስታ ጊዜ አብሮን የሚጨፍር በጦርነት ጊዜ ፊታውራሪ ሆኖ የሚያዘምት በረሃብና በችግር ጊዜ ደግሞ አብሮን የሚላቀስ የሕዝብ ልብ ነበር ።
ጥላሁንን ከአቅም በላይ ያደረገው ይሄው ሁለንተናዊነቱ ነው። ለፍቅር ለሀገርና ለሰብአዊነት የነበረው ጽናት እሱ ሞቶም እንዲኖር አድርጎታል።
የጥላሁን ገሠሠ ዘፈኖች "ኢትዮጵያዊ ስነ-ሰብዕና" የሚባል የፍልስፍና ዘርፍ ቢኖር የዛ ዘርፍ ዋና መማሪያ መፅሐፍ ይሆኑ ነበር ።ብቻ
የጥላሁንገሰሰ ሕይወት ልክ እንደ አንድ የተቀደሰ መፅሐፍ በመሆኑ እራሡ ከፍቶ እራሱ ዘግቶት አልፏል ።
ለዚህ ታላቅ ድምፃዊ በተወለደበት ከተማ አዲስ አበባ ላይ ዘላለማዊ ምልክት ሆኖ እንዲቀመጥ ሐውልቱ ስለቆመለት ደስታዬ ወደር የለውም ።
ነፍስ ይማር !!

ተፈሪ መኮንን
የመቶ ዓመቱ የጥቁር ህዝቦች የዕውቀት ፋና
#ethiopia | "ኢትዮጵያን በዕውቀት መገንባት!" በሚል መሪ ቃል ሚያዝያ 19 ቀን 1917 ዓ.ም. በልዑል ተፈሪ መኮንን (በኋላ አፄ ኃይለ ሥላሴ) የተመረቀው ታሪካዊው ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ዛሬ መቶኛ ዓመቱን (Centenary) ያከብራል።
ይህ ተቋም ለኢትዮጵያ ዘመናዊነት መሠረት የጣለ፣ "የአፍሪካው ሃርቫርድ" ተብሎ የሚጠራ የዕውቀት ማማ ነው።
በታሪክ ቅጥር ግቢው ውስጥ ያለፉ ታላላቅ ኢትዮጵያውያን፦
ተፈሪ መኮንን ለሀገርና ለዓለም የተረፉ ብሩህ አእምሮዎችን አፍርቷል። ጥቂቶቹን ለመጥቀስ፦
ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተ-ወልድ፦
ታዋቂው ዲፕሎማትና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር።
ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ፦
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁት ታላቁ ሰዓሊ።
ክቡር ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ፦
የ"ፍቅር እስከ መቃብር" ደራሲና ዲፕሎማት።
ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ፦
አንጋፋው የቀዶ ጥገና ሐኪም የሀገር ባለውለታ።
🔍 ተፈሪ መኮንን ለምን ይለያል?
የዘመናዊነት መነሻ፦
የመጀመሪያው አዳሪ ትምህርት ቤትና ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ዲፕሎማሲ መሠረት የሆኑ ምሁራን መፍለቂያ ነው።
የዩኒቨርሲቲው እናት፦
በ1943 ዓ.ም. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲመሰረት፣ የመጀመሪያዎቹ ተማሪዎችና መምህራን የተገኙት ከዚሁ ተቋም ነበር።
ዛሬም በታሪክ ስሙ
ዛሬ "ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ" በሚል ስያሜው የነገዎቹን የቴክኒክና የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች እያፈራ ይገኛል።
ይህ ተቋም ትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ፅናትና የብልህነት መታወቂያ ነው። ጣሊያን ንብረቱን ቢዘርፈውም፣ ኢትዮጵያውያን ግን በዕውቀት ተመልሰው ገነቡት። ዛሬ ላይ ተቋሙ ታሪካዊ ስሙን መልሶ መቶ ዓመቱን ሲያከብር ለሁላችንም ኩራት ነው።
ተፈሪ መኮንን - የመቶ ዓመት የብርሃን ጉዞ!
#getu #teferimekonnen #centenary #ethiopianhistory #moderneducation #addisababa #teferimekonnenpolytechnic #historybuilders #ተፈሪመኮንን #መቶዓመት #ታሪክ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Sponsored by
Surafel
4 months ago
ኦሮሞ ምርምር ማኅከልና የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን የበህል ጥናትና ምርምር ማዕከል በጥምረት የተዘጋጀውሁለተኛ ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ Ethiopian SkylightHotel እየተካሄደ ነው።
የኦሮሞ ምርምር ማኅከል እአአ በ2022 በተለያዩ ዘርፎች ላይበኦሮሞ ዙሪያ ምርምር ለማካሄድ ተመሰረተ፡፡በዚሁ መሰረትባለፉት አራት ዓመታት የኦሮሞ ባህል፣ ታሪክ፣ፍልስፍና፣ምጣኔሃብት፣ቋንቀቋ እና በመሳሰሉት ዘርፎች ላይ ምርምር በማድረግበመጵሐፍ መልክ ማሳተም ችሏል።
ይህ ማኅበር የተመሰረተው ከሌሎች ተመሳሳይ ዘርፍ ላይበተሰማሩት ተቋማት ለምሳሌ ያህል እንደ Oromo StudiesAssociation (OSA) እና በለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትውስጥ (የግልና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች) በተቋቋሙት ጋርለመወዳደር ሳይሆን በሉት ክፍተቶችን በመሙላትና በትብብርአብሮ ለመስራት ነው። ስለዚህ አብረን በመሆን የሰፊውን ኦሮሞህዝብ ተሪክና ዘርፈ-ብዙ ምርምሮች አድርገን ወደፊትእንራመዳለን።
እንደሚታወቀው የኦሮሞ ህዝብ በሚንኖርበት የመሬት በቆዳስፋትና ብዛት ግዙፍ ህዝብ ነው። ከመሬት ቆዳ ስፋትና ብዛትባሻገር፣ ኦሮሞ የብዝሃ-በህል፣ ፍልስፍና፣ታሪክ፣ፖለቲካ፣እሴት፣የአከባቢ ጥበቃ፣ህክምናና የመሳሰሉትባለቤት ነው። ይሁን እንጂ እነዚህን ዘርፈ-ብዙ ታርኮችን በቂምርምሮችን በማድረግ ለማውጣትና ለትውልድ ለማስተላለፍበተለያዩ ምክንያቶች እድል ሳያገኝ ቀርቷል። አሁን ግን አነዚህንሀገር በቀል እውቀቶችን ወደ ጎን የማግፋት ጊዜ ለይመለስአብቅቷል። በዓለም-አቀፍ ደረጃም ብሆን በተለያዩ አሳማኝምክንያቶች ሀገራትና ህዝቦች ወደ ቀደምት ማንነታቸው ለመመለስ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸው ይታወቃል። ስለዚህይህንን የዓለም ለውጥ ውስጥ የኦሮሞን ታሪክና ዘርፈ-ብዙ ሀገርበቀል እውቀቶችን ከተደበቁበት ለማውጣና ትውልድንለማስተማር የኦሮሞ ምርምር ማኅከል መመስረት በጣም ወሳኝናአስፈላጊ ነው።
ይህንኑ ዓላማ በመያዝ የተመሠረተው ማኅከላችንየመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ በማድረግናየተለያዩ መጵሐፍትን በእንግሊዘኛ፣ በአፋን ኦሮሞና አማርኛቋንቋ አሳትሞ በራሱ መጵሐፍት መሸጫ አቋቋሞ ለአንባብያንአድርሷል። አሁን ደግሞ ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን የበህል ጥናትና ምርምር ማዕከል ጋር በመተባበርበጥምረት ሁለተኛ ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ "ስር-መሠረታችንን ማክበር፣ ነገያችንን መቅረፅ: የኦሮሞታሪክ፣እውቀት፣በህልና አስተዳደር፣ ድሮ፣ዘንድሮና ወደፊት"በሚል መሪ ርዕስ አዘጋጅቷል። የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሎሬት ፀጋዬገ/መድህን የበህል ጥናትና ምርምር ማዕከልየበህል፣ወግ፣ትውፊት፣ስነ-ፅሑፍና ስነ-ጥበብ ላይ ምርምርበማድረግና በትያትር መልክ ለማህበረሰብ በመድረስ ላይ ይገኛል።
በEthiopian Skylight Hotel በመካሄድ ላይ በሚገኘው ሁለተኛዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ላይ 25 የተመረጡ ኦሮሞ ላይየሚያጠነጥኑ የምርምር ፅሑፎች ይቀርባሉ። እነዚህ የጥናትፅሑፎች አዳዲስና ጠቃሚ መረጃዎችንና እውቀትእንደሚያመነጩ ተስፋ እናደርጋለን።

ኮንፈረንሱ ላይ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) እና ብርሃኑ መገርሳ ሌንጂሶ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታን ጨምሮ ከመላው ኢትዮጵያ የተወጣጡ ምሁራን፣የታሪክ ጸሐፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

"ሶምሶማ" በቃላት ረሃብ ለከሳች፣ በሃሳብ ድርቅ ለጠወለች ነፍስ... ገጣሚና ደራሲ ሲራክ ወንድሙ በ "ሶምሶማ" አዲስ ስራው ድንቅ የጥበብ ማዕድ ከትቦ ይዞ ከች ብሏል።
ይህ መፅሐፍ በኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ ሰማይ ስር የተሰቀለ አዲስ የብርሃን ኮከብ ነው!
ይህ ስራ የዓለም አቀፍ ጠቢባንን ረቂቅነት ከሀገራችን የብዕር አርበኞች ጥልቀት ጋር ያዋሃደ "ወጥ" ጥበብ ነው፦
እንደ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንና ሐዲስ ዓለማየሁ ሲራክ የሀገሩን ጠረን፣ የማህበረሰቡን ስነ-ልቦና እና የታሪክን ፍሰት እንደ "ፍቅር እስከ መቃብር" ባለ ረቂቅ ስፌት ይዘግባል። የቃላት አጠቃቀሙ የሀገራችንን ስነ-ጽሁፍ ክብርና ሞገስ የሚመልስ "ጠጠር" ያለ ብቃት አለው።
እንደ ፓውሎ ኮይሎ (Paulo Coelho) እና ጋብርኤል ጋርሲያ ማርኬዝ በ "ሶምሶማ" ውስጥ የሰው ልጅ የውስጥ ፍለጋና የህልም ጉዞ እንደ "The Alchemist" ይተነተናል፤ ማህበራዊ እውነታው ደግሞ በማርኬዝ "Magic Realism" ስልት የታጀበ ይመስል በውበት ይፈሳል።
እንደ ሚላን ኩንደራ (Milan Kundera) እና በዓሉ ግርማ የህይወትን ፍልስፍናዊ "ክብደትና ቀላልነት" በድፍረትና በጥልቀት ይፈትሻል።
በሩጫ በናወዘው ዘመናችን ውስጥ "ዝግታን" እንደ መድሃኒት እየጋተ፣ በቃላት ውበት ውስጥ እንድንሰምጥና ቆም ብለን ራሳችንን እንድንመረምር ያደርገናል።
"ሶምሶማ" ትላንትን ከዛሬ፣ ዝምታን ከጩኸት፣ ጥልቀትን ከዝግታ ጋር አቆላልፎ የሰፋ ድንቅ የጥበብ ካባ ነው።
ለራስዎ የሚሰጡት የክብር አክሊል፣ ለወዳጅዎ ደግሞ ትርጉም ያለው የህይወት ገፀ-በረከት ነው!
ወንድማችን ሲራክ በለጋ እድሜህ በስለህ የበሰለ መፅሃፍ በሚያምረው ቃላትህና ቀለምን ከማይሰስተው ብዕርህ ቀንጭበህ ከትበህ ስላስነበብከን እድሜህን ያርዝምልንና የቀረውን እየደባበልክ ከትበህ እንድታስነብበን የዘውትር ፀሎታችን ነው።
ሙባረክ አበበ
ሚዛን አማን - ኢትዮጵያ

5 months ago
ከ30 አመት በኃላ ሊደገም ነው ከ30 አመት በኃላ ህዝብ ለህዝብ ድንቅ ነሽ ኢትዯጵያ ሉሲን ለመስራት ዝግጅታቸውን አጠናቀው የበላይ ኮሚቴዎች ተፈራረሙ በተላያየ ምክንያት ተቋርጦ
የነበረውን የህዝብ ለህዝብ ድንቅነሽ ኢትዯጵያ (ሉሲ) እነደሚታወቀው የዛሬ ሰላሳ አመት በፊት በመላው አለም የሀገሪቱ ክፍል እነደታየ ይታወቃል አሁን ደግሞ ከሰላሳ አመት በኌላ በአሜሪካ የተለያዩ ስቴቶች እንዲሁም በካናዳ በአውስትራልያ በ እንግሊዝ በፈረንሳይ በ ጣልያን በመሳሰሉት የአለም ክፈሎች የሚታይ ሲሆን ይሄን ስራ በ አጭር ግዜ ውስጥ አጠናቀው ለህዝቡ ለማድረስ የበላይ ኮሚቴዎች የስምምነት ፊራማቸውን አስቀምጠዋል ።
የ ህዝብ ለህዝብ የበላይ ኮሚቴዎች
1 ኛ ሎሬት አያልነህ ሙላቱ የድርሰቱ ባለቤት
2 ኛ ዶክተር ሙላቱ አስታጥቄ የሙዚቃው አቀናባሪ
3 ኛ ርቲስት ተስፋየ ታየ የኪነ ጥበብ አስተባባሪ
4 ኛ አርቲስት ቴዎድሮስ ዘዋለ (ቴዲ ማቲ) የፕሮጀክቱ ዋና አሰረተባባሪ (ማናጀር ) ፕሮጀክቱ በጥበብ አደቨርታይዚንግ እና አኢቨንት የሚዘጋጅ ሲሆን ዝግጅቱ አጠናቆ ለመጨረስ ከ 4 ወር- 5 ግዜ የሚዎስድ ሲሆን በውስጡ የሚሳተፉ የኪነ ጥብበ ሰዎች (አርቲሰረቶች ከ 55-60 ሰዎች የሚሳተፉ ይሆናል
በቅርቡም ከ አጋር ድርጅቶቻቸው ጋር በመሆን ይፋዊ ጋዜጣዊይ መግልጫ የሚሰጡ ይሆናል::

🎭 የታሪካዊው "ሕዝብ ለሕዝብ" ዳግም ትንሳኤ
"ድንቅ ነሽ ኢትዮጵያ (ሉሲ)" ሊጀመር ነው! 🇪🇹✨
#ethiopia | ከ30 ዓመታት በላይ ተቋርጦ የነበረውና በዓለም መድረክ የኢትዮጵያ የጥበብ አምባሳደር የነበረው "ሕዝብ ለሕዝብ" የኪነ-ጥበብ ጉዞ፣ አሁን በታላላቅ የጥበብ ሰዎች መሪነት ዳግም ለዓለም ሊቀርብ ስምምነት ተፈርሟል።
ፕሮጀክቱን በኃላፊነት የሚመሩት የዘርፉ አንጋፋና ስመ-ጥሩ ባለሙያዎች ናቸው፡-
ሎሬት አያልነህ ሙላቱ፦ የድርሰቱ ባለቤት
ዶክተር ሙላቱ አስታጥቄ፦ የሙዚቃው አቀናባሪ
አርቲስት ተስፋዬ ታዬ፦ የኪነ-ጥበብ አስተባባሪ
አርቲስት ቴዎድሮስ ዘዋለ (ቴዲ ማቲ)፦ የፕሮጀክቱ ዋና አስተባባሪ (ማናጀር)
ይህ ታላቅ የጥበብ ስራ በቅርብ ወራት ተጠናቆ ለተመልካች የሚደርስ ሲሆን የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ይዟል በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች፣ በካናዳ፣ በአውስትራሊያ፣ በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይ እና በጣሊያን የሚታይ ይሆናል።
ከ55 እስከ 60 የሚደርሱ የኪነ-ጥበብ ሰዎች (አርቲስቶች) በዝግጅቱ ላይ ይሳተፋሉ።
የዝግጅቱን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ለመጨረስ ከ4 እስከ 5 ወራት የሚወስድ ሲሆን፣ ስራው በ"ጥበብ አድቨርታይዚንግ እና ኢቨንት" አማካኝነት የሚዘጋጅ ነው።
የቀድሞው "ሕዝብ ለሕዝብ" የኢትዮጵያን ባህል፣ ሙዚቃና ውዝዋዜ ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ የማይተካ ሚና ነበረው። አሁን ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት የተዘጋጀው ይህ አዲሱ ፕሮጀክት፣ የጥንታዊቷን "ሉሲ" ታሪክና የሀገራችንን ድንቅ ጥበብ ዳግም ለዓለም አደባባይ ለማውጣት አልሟል።
#ሕዝብለሕዝብ #ድንቅነሽኢትዮጵያ #ሉሲ #አያልነህሙላቱ #ሙላቱአስታጥቄ #ኢትዮጵያ #ኪነጥበብ #ethiopia #peopletopeople #lucy #mulatuastatke #art #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

#ፈራን_
ፀጋዬ ገብረመድህን(ሎሬት)
#ethiopia | "ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን...።
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን
"ናቅን"
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን
"ናቅን"
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን
"ጠላን"
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ
"ራቅን"
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን።
ባለቅኔው ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ያረፉት ከዛሬ 20 ዓመት በፊት በ1998 ዓ.ም ነበር።
ነፍስ ይማር 🕯
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

6 months ago
🎭 "ምጥቀት በቅኔ አክናፍ"
የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን 20ኛ ዓመት መታሰቢያ በደመቀ ሁኔታ ተከበረ! 🖋️📜
#ethiopia | የኢትዮጵያ የሥነ-ጥበብ ቁንጮ፣ የቃላት ጠቢቡ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ 20 ዓመታት ተቆጠሩ።
ይህንን ታላቅ የጥበብ ሰው ለማሰብ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የሥነ-ጥበባት ማዕከል ያዘጋጀው መርሃ-ግብር በታዋቂ ከያንያንና ምሁራን ታጅቦ ተከናውኗል።
✨ ከመርሃ-ግብሩ ዋና ዋና ነጥቦች
📚 ጥልቅ ዳሰሳ፦ አቶ ነብዩ ባዬ የጸጋዬን የቴአትር ድርሰቶች፣ መምህር ወንድወሰን አዳነ የሥነ-ግጥም ሥራዎቹን እንዲሁም አቶ ቴዎድሮስ አጥላው በፋሲል ይትባረክ የተጻፈውን “ምጥቀት በቅኔ አክናፍ” መጽሐፍ ላይ ትንታኔ አቅርበዋል።
🎙️ የከያንያን ድምፅ፦ አንጋፋዎቹ ከያንያን አበበ ባልቻ እና ተፈሪ ዓለሙ የሎሬቱን ነባርና እስካሁን ያልታተሙ ግጥሞች በድንቅ ንባብ አቅርበው ታዳሚውን ወደ ጸጋዬ የቃላት ዓለም ወስደውታል።
🎁 አዲስ የምስራች፦ የሎሬት ጸጋዬ ያልታተሙ ግጥሞች በመጪው ነሐሴ 2018 ዓ.ም ለሚከበረው 90ኛ ዓመት የልደት መታሰቢያው ታትመው ለንባብ እንደሚበቁ ተገልጿል።
📅 የፊታችን ቅዳሜ ግብዣ (የካቲት 21/2018)፦
ጥበብ አያልቅባትም! የፊታችን ቅዳሜ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በዶ/ር ኢንጂኒየር ብርሃኑ ግዛው “ወርቃማው የፔዞ ቡሩሌያዊው በገና” የተሰኘ የምርምር እና የበገና ደርዳሪዎች ዝግጅት ስለሚቀርብ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
"ጸጋዬን በምን ያስታውሱታል?"
የሎሬቱ የትኛው ስራ (ግጥም ወይስ ቴአትር) በልብዎ ታትሞ ቀርቷል? ለጥበብ ሰው ያለዎትን ክብር በኮሜንት ይግለጹ። 👇
#tsegayegebremedhin #ethiopianliterature #poetry #art #ethiopia #memorial #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

ቤት አልባው ባለቤት፦ የነገ ጭንቀት የዛሬን ፀሐይ ሲጋርድ
በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የሚታየው እልህ አስጨራሽ ሩጫ አንድ ግብ አለው— "ነገ የተሻለ ቦታ መገኘት"። በዚህ ሩጫ ውስጥ ግን ብዙዎቻችን "ዛሬን" እንደ ትርፍ አንጀት ቆርጠን ጥለናታል። በአንድ ወቅት በአዲስ አበባ በመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ አንድ ሰው ታሪክ የዚህ እውነት ህያውና ረመጥ የሆነ ምስክር ነው።
ይህ ሰው የራሱ መጠለያ ቤት ባለመኖሩ ዘወትር ይሰበሳጭ፣ የኑሮው ትርጉም አልባነትም በኪራይ ቤት መኖሩ ይመስለው ነበር። በትርፍ ሰዓቱ እየሰራ፣ ያማረውን ሳይበላ፣ ወቅቱ የጠየቀውን ሳይለብስ፣ የልጆቹን ሳቅ ሳያደምጥ ሳንቲም በአንቲም አጠራቅሞ ያቺን የናፈቃትን ቤት ገዛ። ነገር ግን እጣ ፈንታ ሌላ ስውር እጅ ነበራት። አዲሱ ቤቱ በገባ በወሩ፣ እንጨት ወድቆበት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
የደከመበትን ቤት ሳይኖርበት፣ በላቡ ያመጣውን ውጤት ሳይጠቀምበት፣ የገዛው እንጨቱ መቃብሩ ሆኖ አለፈ።
ይህ ታሪክ የግለሰብ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ የከንቱነት ጉዞ ማሳያ ነው።
"የማይጠግበው የሰው ልጅ ስልጣኔ"
የታሪክ ምሁራን የሰውን ልጅ ጉዞ ሲመረምሩ አንድ የሚገርም ተቃርኖ (Paradox) ያገኛሉ።
የሰው ልጅ ኑሮውን ለማቅለል የፈለሰፋቸው ነገሮች ሁሉ መልሰው የጭንቀቱ ምንጭ ሲሆኑ ይታያሉ። የታሪክ ተመራማሪው ዩቫል ኖህ ሀራሪ "Sapiens" በሚለው መጽሐፉ እንደገለጸው፣ የሰው ልጅ ግብርናን የጀመረው ለነገ የሚሆን ምግብ አከማችቶ በሰላም ለመኖር ነበር። ነገር ግን ግብርናው ለበለጠ ስራ፣ ለንብረት ጥበቃ ስጋትና ለጦርነት ዳረገው።
የኢትዮጵያ ታሪካዊ አውድ፦ በአጼዎች ዘመን የነበሩ መኳንንት "ፎቅ" ለመስራትና ርስት ለማስፋፋት እድሜያቸውን በጦርነት ሲያሳልፉ፣ በመጨረሻ ግን ያከማቹት መሬት ሳይሆን የገዛ አፈራቸው በላያቸው ላይ ሲመለስ ታይቷል።
ታሪክ የሚነግረን "ነገን" ለመገንባት ዛሬን የጨረሱ ሰዎች፣ ታሪክ ሲፃፍ ስማቸው ቢኖርም ነፍሳቸው ግን በሰላም አልኖረችም።
የስነ-ልቦና ጥናትና ምርምር፦ "የደስታ ወጥመድ" (Hedonic Adaptation)
በስነ-ልቦና ሳይንስ ውስጥ "Hedonic Adaptation" የሚባል ጽንሰ-ሃሳብ አለ። ይህ ጥናት እንደሚያመለክተው የሰው ልጅ አንድን ትልቅ ስኬት (ቤት፣ መኪና፣ ሀብት) ሲያገኝ የሚሰማው ከፍተኛ ደስታ በአማካይ ከ 3 እስከ 6 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ይጠፋል። ከዚያ በኋላ ግለሰቡ ወደ ቀድሞው የጭንቀትና የጎደለኝ ስሜት ይመለሳል።
የምርምር ውጤት፦ እ.ኤ.አ በ 1978 የተደረገው ታዋቂው የሎተሪ አሸናፊዎች ጥናት እንደሚያሳየው፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያሸነፉ ሰዎች ከአንድ ዓመት በኋላ ያላቸው የደስታ መጠን፣ ምንም ካላሸነፉ ተራ ሰዎች ጋር እኩል ሆኖ ተገኝቷል።
ትርጉሙ፦ ያ በአዲስ አበባ ቤቱን ለመግዛት ሲጥር የነበረው ሰው፣ ቤቱን ከገዛ በኋላም ጭንቀቱ እንደማይለቀው ሳይንሱ ያረጋግጣል። ምክንያቱም ደስታን በቁስ ላይ "ነገ" በሚባል የቀጠሮ ቀን ላይ ሰቅሎት ነበር። ዛሬ ባለው ጥቂት ነገር ማረፍ ያልቻለ አእምሮ፣ ነገ ቢሊዮን ብር ቢኖረውም "ሀብቴን ማን ይወስድብኛል?" በሚል ስጋት መጠቃቱ አይቀሬ ነው።
ከድንበር ባሻገር ያለ እውነተኛ ሰቆቃ፦ የቪቻይ ታሪክ
ይህ የሰው ልጅ እጣ ፈንታ በአዲስ አበባ ብቻ የተገደበ አይደለም። በታይላንድ ይኖር የነበረውና በሪል ስቴት ንግድ እጅግ ስኬታማ የነበረው ቪቻይ ስሪቫዳናፕራባ ታሪክም ተመሳሳይ የልብ ስብርባሪ አለው። ቪቻይ በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብት አከማችቶ፣ የእግር ኳስ ክለብ ገዝቶ፣ በዓለም ዙሪያ ታዋቂ ሆነ።
በፈረንጆቹ ጥቅምት 2018 ላይ በገዛው ስታዲየም ውስጥ ጨዋታውን ተመልክቶ፣ በገዛው የግል ሄሊኮፕተር ወደ ቤቱ ሊሄድ ሲነሳ፣ ያቺ በሚሊዮን ዶላር የገዛት ሄሊኮፕተር ስታዲየሙ አጥር ላይ ተከስክሳ በእሳት ነደደች።
ያን ሁሉ ሰፊ መሬትና ሰማይ ጠቅላይ ህንፃ የገዛው ሰው፣ መጨረሻው በገዛው ብረት ውስጥ አመድ ሆኖ መቅረት ሆነ። የገነባው ሀብት፣ የገዛው ቅንጦት መጨረሻው መጥፊያው ሆነ። ይህ የሚያስተምረን የምንለፋለት ነገር ሁሉ የጥፋታችንም በር ሊሆን እንደሚችል ነው።
"የህይወት ግጥምና ምሬት"
ደራሲያን ህይወትን ልክ እንደ ሸክላ ሰሪ ውጤት ያዩታል። ሸክላው ተሰርቶ ሳያልቅ ሊሰበር ይችላል። ኢትዮጵያውያን ደራሲያን በስራዎቻቸው ውስጥ በተደጋጋሚ የሚያነሱት ጭብጥ የሰው ልጅን ምኞትና የሞትን ቀጠሮ አልባነት ነው።
ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን በአንድ ግጥሙ "ሰው መሆን" ያለውን ከባድ ሸክም ሲገልጽ፣ የሰው ልጅ ለምድር ባይሆንም ለምድር እንደሚጨነቅ ያሳያል።
የደራሲያን ትዝብት፦ "ሰው ለራሱ ቤት ሲሰራ፣ ለሞቱ ጉድጓድ እየቆፈረ እንደሆነ ይዘነጋል"። ያ የቤት ባለቤት የገደለው እንጨት፣ እሱ ራሱ የቤቱ ጣራ እንዲሆን የመረጠውና የገዛው ነው። ይህ የሚያሳየው ብዙዎቻችን ተጨንቀን የምናመጣው ሀብት፣ ዝና ወይም ስልጣን በውስጡ የጥፋታችንን ዘር ሊይዝ እንደሚችል ነው።
"የእለት እንጀራ" ፍልስፍና
እንደ ሃይማኖትም ሆነ እንደ ስነ-ልቦና፣ ትልቁ ጥበብ "የእለት እንጀራችንን ስጠን" ብሎ መኖር ነው። "የአመት እንጀራችንን አከማችልን" አንልም። ምክንያቱም የአመት እንጀራ አመትን ሙሉ የመጨነቅ ዋስትና እንጂ የአመቱን ህይወት የመኖር ዋስትና አይሰጥም።
ሀብትና ሰላም፦
ብዙዎቻችን ተጨንቀን የምናመጣው ነገር ምን አልባት መጥፌያችን ሊሆን ይችላል።
ሀብት መጥቶ ጤና ሊታጣ ይችላል።
ዝና መጥቶ ጭንቀት ሊነግስ ይችላል።
ብር ተገኝቶ ሰላማዊ እንቅልፍ ሊጠፋ ይችላል።
የዛሬን ፀሐይ አትጋርዱ
የተሻለ መመኘትና መስራት ክፋት የለውም። ነገር ግን "ዛሬን" ለነገ መረገጫ ማድረግ ማስተዋልን ይጠይቃል። ዛሬ ያለህን ጤና፣ ዛሬ አጠገብህ ያሉትን ቤተሰቦችህ፣ ዛሬ የምትበላትን የዕለት እንጀራ በደስታ ተቀበል።
ምን አልባት የዛሬው "ምንም የለኝም" የምትልበት ሁኔታህ፣ ነገ ላይ ሆነህ ደግመህ ለማግኘት የምትጸልይበት ብርቅዬ ቀን ሊሆን ይችላል። ዛሬ የምትረግጠው መሬት፣ ዛሬ የምትተነፍሰው አየርና ዛሬ የምትጠጣው ውሃ ከነገው ትልቅ ህንፃ በላይ ዋጋ አላቸው።
የመጨረሻው እውነት፦ የገነባኸው ቤት ሳይሆን፣ የኖርክበት ሰላማዊ ቅጽበት ነው ትክክለኛ ቤትህ። ያ በአዲስ አበባ እንጨት ወድቆበት የሞተው ሰው፣ ለቤቱ ሲል ራሱን ባይቀጣና ዛሬውን ባይበድል ኖሮ ቢያንስ ያለፉትን አመታት በደስታ ይኖር ነበር።
ዛሬን ኑር፤ ምክንያቱም ነገ ለማን እንደምትሆን አታውቅም!

🦁 "ምን እንደማስብ ታውቃላችሁ?" ሲል የክረመው አንበሳ ባንክ አዲሱን ማንነቱን ይፋ አደረገ! 🏦✨
#ethiopia | "አንበሳ ፕላስ (Anbessa Plus) የተሰኘ አዲስ የሞባይል መተግበሪያም ተመርቋል"
ለ18 ዓመታት በኢትዮጵያ ፋይናንስ ዘርፍ ሲያገለግል የቆየው አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ፤ አርማውን እና መለያ ቀለሙን በመቀየር ዘመናዊነትን የተላበሰ አዲስ የብራንድ መለያ (Rebranding) በይፋ ተግብሯል።
የለውጡ ዋና ዓላማ ምንድን ነው?
የባንኩ አመራሮች እንደገለጹት፤ ይህ ለውጥ የምስል ቅያሬ ብቻ አይደለም። ባንኩን ለዲጂታል ዘመን በሚመጥን መልኩ ለማዘመን፣ የቴክኖሎጂ አቅምን ለማሳደግ እና በኢንዱስትሪው ያለውን ተወዳዳሪነት ለማጎልበት የተደረገ ስትራቴጂካዊ ሽግግር ነው።
በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ ምን ተከናወነ?
✅ አዲስ አርማ: የባንኩን የ18 ዓመታት ጉዞ የሚገልጽ እና ለዲጂታል ባንኪንግ ምቹ የሆነ አዲስ ሎጎ ይፋ ሆኗል።
✅ አዲስ መተግበሪያ: "አንበሳ ፕላስ" የተሰኘ ዘመናዊ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ተዋውቋል።
✅ ክብር ለባለሙያ: የቀድሞውን የባንኩን አርማ ለሰሩት ሎሬት ደስታ ሐጎስ ልዩ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
ባንኩ በአሁኑ ወቅት 365 ቅርንጫፎች እና ከ44 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ያለው ሲሆን፤ ይህ አዲስ ምዕራፍ ለደንበኞች ቀልጣፋ አገልግሎት ይዞ እንደሚመጣ ተገልጿል።
#lioninternationalbank #anbessabank #rebranding #newera #anbessaplus #digitalbanking #ethiopia #getutemesgen

👏 የዓለም ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ በ60 ሚሊዮን ብር ታሪክ ሰሩ! 🇪🇹
#ethiopia | "ሀገሩ ሳይኖራት አስተምራው፤ እውቀቱን ለምዕራቡ ዓለም የሚገብር ትውልድ በሞላበት... የመጣበትን ዞሮ ያየ ወርቅ ሰው!"
በግብርና ሳይንስ ምርምር ዓለምን ያደነቁት ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ፤ አሁን ደግሞ በትውልድ ቀያቸው የማይረሳ የታሪክ አሻራ አሳርፈዋል።
ስለ ፕሮጀክቱ አስደናቂ እውነታዎች፡
📍 ቦታ:
በትውልድ ቦታቸው ኦሎንኮሚ (ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ ሆለታ እና ጊንጪ መካከል)።
💰 ወጪ:
ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ።
🏫 ስያሜ:
ለዚህ ክብር ያበቋቸውን ውድ እናታቸውን ለመዘከር "ሞቱ አያኖ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት" ሲሉ ሰይመውታል።
ፀሐፊ፣ ተመራማሪ እና የዓለም ሎሬት የሆኑት ፕሮፌሰሩ፤ እውቀታቸው ለዓለም ቢተርፍም ልባቸው ግን ሀገራቸው እና ወገናቸው ጋር መሆኑን በተግባር አስመስክረዋል። የነገ ሀገር ተረካቢዎች የሚፈሩበትን የዕውቀት ማዕከል ለትውልድ አበርክተዋል።
ክብር እና ምስጋና ለፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ!
ፈጣሪ እድሜ እና ጤና ይስጥዎ! 🙏❤️
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#profgebisaejeta #rolemodel #ethiopia #olonkomi #motuayanoschool #education #givingback #hero

7 months ago
🎭 አበበ ባልቻ፡ የህግ እና የኪነ-ጥበብ ሰው
#ethiopia | "በጥበብ መድረክ ላይ የነገሠ፣ በህግ አደባባይ የሞገተ የዘመናችን ድንቅ ባለሙያ!"
📌 የግል መረጃ በአጭሩ
ልደት፦ ታህሳስ 23 ቀን 1948 ዓ.ም
የትውልድ ቦታ፦ አዲስ አበባ (ኦሜድላ ሆስፒታል)
ትምህርት፦ ኮከበ ፅባህ (1ኛ-12ኛ) እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት (LLB)
ትዳር፦ ከጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ ጋር (3 ልጆች አፍርተዋል)
🏛️ የህግ ባለሙያው አበበ ባልቻ
አበበ ባልቻ በህግ ሙያው ጉልህ አሻራ ያሳረፈ ሰው ነው።
የመጀመሪያ ስራ፦ በአውራ ጎዳና ባለስልጣን በጥብቅና ተቀጥሮ በመስራት ሰፊ ልምድ አግኝቷል።
ሙያዊ ተጽዕኖ፦ ለተለያዩ መንግስታዊና የግል ተቋማት በከፍተኛ የህግ አማካሪነት እና ጥብቅና የቆመ "ጉምቱ" የህግ ሰው ነው።
አድናቆት፦ ለታዋቂው የህግ ባለሙያ አቶ ተሾመ ገብረማሪያም ትልቅ አክብሮት አለው።
🎬 የጥበብ ጉዞና ስኬቶች
ለአበበ ባልቻ ጥበብ የህይወቱ ግማሽ አካል ናት። በተለይ ከጋሽ አባተ መኩሪያ እና ከሎሬት ጸጋዬ ገብረመድን ጋር የነበረው ቆይታ ማንነቱን ቀርጾታል።
ታዋቂ የቲያትር ስራዎቹ፦
ኦቴሎ፦ የመሪ ገፀ-ባህሪውን በመወከል 384 ጊዜ መድረክ ላይ ቀርቧል።
ቴዎድሮስ፦ በታሪክ ገፅታው ተመልካችን ያስደመመበት ስራው።
የከርሞ ሰው፦ በአሜሪካ መድረኮች የተወነበት የሎሬት ጸጋዬ ስራ።
አሉላ፦ በብሔራዊ ቲያትር የቀረበ።
የፊልም እና የድራማ ስራዎቹ፦
ተከታታይ ድራማዎች፦ ሰው ለሰው (አስናቀ)፣ ባለጉዳይ፣ ዘመን፣ ግራና ቀኝ፣ በሕግ አምላክ።
ፊልሞች፦ አስከሬኑ፣ ሔሮሽማ፣ 3 ማዕዘን፣ አቡጊዳ።
🎙️ የሚድያ እና የስራ አመራር ብቃቱ
አበበ ባልቻ ከተዋናይነት ባሻገር በትልቅ የአመራር ደረጃ ሀገሩን አገልግሏል፡-
ሸገር ኤፍ ኤም 102.1፦ የሬድዮ ጣቢያው መስራች እና በአሁኑ ሰዓት ስራ አስፈፃሚ።
ሸራተን አዲስ፦ ሆቴሉ ሲከፈት የዝግጅቶች ዋና አስተባባሪ።
ሚሊኒየም አከባበር፦ የኪነ-ጥበብ ዝግጅት ኃላፊ ሆኖ ሰርቷል።
ሪፖርተር ጋዜጣ፦ የቀድሞ ባለድርሻ።
✨ የአርቲስቱ ሰብዕና
በሙያ ባልደረቦቹ ዘንድ "ለዲስፕሊን እና ለትወና ትልቅ ፍቅር ያለው" ተብሎ ይገለጻል። በተለይ በ "ሰው ለሰው" ድራማ ላይ የተጫወተው "አስናቀ" የተባለው ገፀ-ባህሪይ በአሁኑ ትውልድ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን አትርፎለታል።
"ለትወና፣ ለቲያትር ዕውቀት፣ ባጠቃላይ ለሥነጥበብ አይኔን የከፈተልኝ አባተ መኩሪያ ነው።" — አበበ ባልቻ

ፈራን
"ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን...።
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን
"ናቅን"
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን
"ናቅን"
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን
"ጠላን"
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ
"ራቅን"
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን።
ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን
"ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን...።
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን
"ናቅን"
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን
"ናቅን"
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን
"ጠላን"
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ
"ራቅን"
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን።
ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን
8 months ago
የቀይ ባህር እንቁ አሥመራ ሽኮሪና
የአለማችን የመጀመርያዋ የቅርስ ከተማ!
( በታዴ የማመይ ልጅ )
#ethiopia | በእርግጥም በምስራቅ በፅሎትና ቤተ ጊዮርጊስ ፣ በምዕራብ በፀራራት ፣በሰሜን በአክሪያና ባዕታ አስመራ፣ በደቡብ አዲ ጓእዳ ኮረብታዎች ደጀን የሆኗት በፅዳቷ ፣ በእርጋታዋ ፣ እንደሚፈርጥ እንቁላል በጥንቃቄ በተደረደሩት እፁብ ህንፃዎቿ በተንዠረገጉት ዘንባባዎቿ፣ የአፍሪካ ዘመናዊ ከተማ ፣የቀይ ባህር እንቁ ትመስላለች ።
በዛሬዉ የአፍታ ቱሪዝም ጉብኝታችን ባለፉት ሦስት አስርት አመታት ክፉ ክፉዉን አግዝፈው የሚነግሩን ቤኒቶ ሙሶሊኒም “ፒኮላ ሮማ” ወይም “ትንሿ ሮም” ሲል ያሞካሻት የኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ገብተናል ።
በቆይታችን ደግነትና ባህል አክባሪነት መገለጫው ሰዉን ያለልዩነት የሚወደው ቸርነት ከባህሪዉ የሆነው የአስመራ ህዝብ አለና ወደኋላም ከመነሻዋ ወደፊትም ከገፅታዋ መለስ ቀለስ እያልን በጎዳናዎቿ ሸር ብትን እንላለንና አብራችሁን ዝለቁ ።
ጥንት ከሁለት ሺህ ዓመት በላይ ታሪክ ያለዉ አዶሊስ በዝያን ጊዜ ከነበሩ ከታወቁ የተለያዩ ሃገሮች ጋር ትልቅ የንግድ ግንኙነት የነበረዉ፤ አዶላዉያን በዝያን ጊዜ እስከ ሕንድ አልፈዉ እስከ ቻይና ግንኙነት ያደርጉባት የነበረዉ የወደብ ከተማ ናት የሰሜን ፈርጧ አስመራ።
በአሥመራ በሠምበል አካባቢ የተገኘው የአርኪዮሎጂ ማስረጃ ከተማዋ ስያሜ በ 800 ዓ.ዓ. ይወስደናል ።
የኦና ባህል ተብሎ የሚጠራውን የአሥመራ ታሪክ በ 800 ዓ.ዓ. እና በኤርትራ ትግሪኛ ቃል ባሕላዊ ታሪክ መሠረት፣ በቀበሳ አምባ ላይ በአስመራ አካባቢ አራት ጎሳዎች ይኖሩ ነበር።
በዘመኑ ተበታትነው የነበሩት ገዛ ጉርቶም። ገዛ ሽሌሌ፣ ገዛ ሴሬንሰር እና ገዛ አስመኤ የተባሉ ግዛቶች ጎሳዎች በአንድነት በመሆን ከተማ በመመስረት "አርባተ አስመራ" የሚል ስም ሰጧት ይባላል ይህም አርባተ አስመራ ማለት በትግርኛ ቋንቋ 'አራቱ ጎሳዎች' ማለት ነው።
ከባህር ጠለል በላይ ከ2,300 ሜትር በላይ ከፍታ ላይ የምትገኝ ሲሆን ከአካባቢው ዝቅተኛ ቦታዎች ሙቀት ጋር የሚቃረን መለስተኛ የአየር ንብረት ያላት አስመራ ግብፆች፤ ቱርኮች፤ጣልያኖች እንጊሊዞች ተዋግተዉባታል። ከተማዋን የጎዳ ማንም ኃይል ግን አልነበረም ወዘናዋ ዛሬም በእርጋታ ተዉቦ ይገኛል ።
ከተማዋና ዙርያዋ ታሪክ ከ 2000 ዓመት ወደኋላ ይወስደናል 2000 አመታት በላይ ስልጣኔ የነበረዉ ታሪካዉ" መጠራ በለዉ ከለዉ" የተባለ በአፍሪቃዉ ቀንድ ላይ ለሚገኙ ሁለቱም ሃገሮች የሥነ-ጽሑፍ የተከሰተበት ታሪካዊ ቦታ ሲሆን በሃዉልቱ ላይ አናባቢ የሌለዉ የግዕዝ ጽሑፍ ሰፍሮ ይገኛል ።
ሰፊ ከተማ የነበረችዉ 17 ኪሎሜትር ስፋት የነበራት ቆሃይቶ እስከ ትልቅ የአፍሪቃ ከተማ ያደርጋታል። ከዚህም ባሻገር በአፍሪቃ እስልምናን ከተቀበሉት አካባቢዎች የመጀመርያዉ የሆነው ዳህላክኬሪስ
ጥንታዊ መቃብሮች ጥንታዊ የዉኃ ማጠራቀምያ ገንዳዎች መገልገያዎች አስመራና ዙርያዋ የረጂም ታሪክ እንዳላት ህያው እማኝ ይሆናሉ ።
ይሁንና የዛሬውን ገፅታ የያዘችው በጎርጎረሳዉያኑ 1930ዎቹ በቅኝ ግዛት ኤርትራን የያዘዉ ኢጣልያዊዉ ፋሺስት ሞሶሎኒ በምስራቅ አፍሪቃ ለሚያካሂደዉ የቅኝ ግዛት ዘመቻ ማዕከል እና መነሻ እንድትሆነዉ ዓይኑን ከጣለባት በኋላ ነበር ።
የጣልያንን መምጣት ተከትሎም አስመራ የምትባለዉ ትንሽ መንደር ሞቅ ደምቅ ማለት ጀመረች ። በአፍሪካ የመጀመሪያው የቴሌቪዥን ስርጭት ፣ የመጀመሪያው Am FM አጭር መካከለኛ ረጂም ሞገድ ራዲዮ ፣
የኤርትራ የባቡር መስመር በጊንዳ ከተማ በኩል በካርሎ ካቫና መሪነት ወደ ምጽዋ የባህር ዳርቻ የሚያመራ ሀዲድ ፣ ሲኒማ
ፋብሪካዎች በብዛት ተገንብተው በአፍሪካ ምድር ላይ የአውሮፓ ዘመናዊነት እውነተኛ ማሳያ ያደርጋታል ።
ሲኒማ ኢምፔሮ፣ የፊያት ታግሊየሮ አገልግሎት ጣቢያ እና የቅዱስ ጆሴፍ ካቴድራል ያሉ ታዋቂ ሕንፃዎች ለዚህ የፈጠራ ኃይል ምስክር ናቸው። ፊያት ታግሊየሮ፣ እንደ አውሮፕላን ለመነሳት ዝግጁ የሆነ አውሮፕላን ቅርጽ ያላቸው የተጠናከረ የኮንክሪት ክንፎቹ ያሉት፣ የዘመኑን የቴክኖሎጂ፣ የእድገት እና የፍጥነት ውበት ያለውን ማራኪነት መገለጫዎች ናቸው ።
ጋዜጠኛ ጆን ጉንተር እ.ኤ.አ. በ 1955 እንደገለጸው "ጣሊያኖች [አስመራን] እንደ ትሪፖሊ በጥሩ ሁኔታ እንደገነቧት ጽፏል።
በሚያማምሩ ሰፊ ጎዳናዎች ፣ ያጌጡ የህዝብ መገልገያ ሕንፃዎች እና የሥልጣኔ ምልክት የሆነው በከተማዋ የተገነባው ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት ... የጣልያኖች የስራ ውጤት መሆኑን ጽፏል።
የኢጣሊያ መንግሥት በአስመራ እና በአስመራ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች በኢንዱስትሪ ልማት ላይ ኢንቨስት አድርጓል ።
ከሥነ ሕንፃዋ ባሻገር፣የጂኦሜትሪክ ዲሲፕሊን እና የሜዲትራኒያን ጸጋ ድብልቅ አሰራሯ አስመራን ልዩ ውበት ይሰጣታል ።
አስመራ ሙሉ በሙሉ በዘመናዊነት ሀሳብ ዙሪያ ለተቀረፀ የከተማ ፕላን ትታወቃለች፤ ሰፊ አውራ ጎዳናዎች፣ ሥርዓታማ ሰፈሮች፣ ለጋስ የሕዝብ ቦታዎች እና ቀልጣፋ መሠረተ ልማቶች የጣልያኖች የስራ ዉጤት የተመለከተው ፋሽስት ሞሶሎኒም በዝያን ጊዜ አስመራን አፍሪቃዊትዋ ትንሽዋ የሮም ከተማ ሲል አንቆለጳጽሷታል።
ሲኒማ ቤቶቹ ራሳቸዉ ድንቅ ናቸዉ ሲኒማ ኤንፔሮ፤ ሲኒማ ዳንቴ፤ ሲኒማ ካፒቶል፤ ሲኒማ ሮማ፤ ሲኒማ ኦዲዎን የሚባሉ ሲኒማ ቤቶች አሉ።ሁሉም ሲኒማ ቤቶች የተሰሩት በአዉሮጳ ደረጃ ነዉ። ሌሎቹ ሕንጻዎች ቡናማ ሰማያዊ አረንጓዴ ቀለም ያላቸዉ ሲሆኑ የአስመራ ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርስትያን ዉብ ቪላ ቤቶች ፤ ፋብሪካዎች አስመራ የሚገኘዉ ትልቁ መስጊድ የመሳሰሉት ሁሉ የሚያማልሉ ናቸዉ።
ከተማዋ እድለኛ ከተማም ናት 30 እና 40 ዓመት ጦርነት ተካሂዶ ከተማዋ ምንም አልተጎዳችም ከተማዋን የጎዳ ኃይል የለም። በመጀመርያ ከተማ አስመራን በኦቶማን ኤምፓየር በሚባለዉ ዘመን ቱርኩች ያዙ፤ ከዝያ በኋላ ግብጾች ያዙ ከዝያ በኋላ ጣልያኖች ያዙ ከዝያ በኋላ እንጊሊዞች ያዙ። ይህ ሁሉ ትርምስ ሲካሄድ ግን ከተማዋ አልተጎዳችም ።
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ድርጅት አስመራ የዓለም ቅርስ ሆና እንድትመዘገብ በፖላንድ ዋርሶ ባካሔደው ጉባዔ ላይ የአለማችን የመጀመርያዋ የቅርስ ከተማ ክብር መዝገብ አስፍሯታል ።
በአስመራ የሚገኙትና ቅኝ ግዛቱ ዘመን የተሰሩት ከ 50 በላይ ሕንፃዎች በሙሉ በዓለሙ መንግሥታት የቅርስ መዝገብ በመስፈራቸዉ ኤርትራ ጥንታዊና የባህል ቅሪቶች በሙሉ የተመዘገበላት ቀዳሚዋ የዓለም ሀገር ያደርጋታል ።
UNESCO ስለ ከተማዋ ሲገልፅ
«አስመራ በጣም ዉብ የሆነች ከተማ ናት። ከሁሉ ደግሞ ሕዝብዋ በዉስጥዋ እየኖረ ባህሉን እየጠበቀ ሥነ ሕንጻዉን እየጠበቀ በመሆኑ ነዉ። የአስመራ ሕንጻዎች ለየት ያለ ንድፍና ቅርስ የያዙ ናቸዉ። ጣልያኖቹ በቅኝ ግዛት ወቅት ሃገራቸዉ ዉስጥ የሌለ ነጻነት አስመራ ዉስጥ፤ ቅኝ ሃገር ዉስጥ ነጻነት ተሰምቶአቸዉ ፤ በምህንድስናዉ ረገድ አብዮት ያካሄዱ ይመስላል። ምክንያቱም ኢጣልያ ዉስጥ የማይገኘዉ ሕንጻ አስመራ ዉስጥ አለ።» ሲል ገልጿል ።
አስመራ ከተማ በኪነ ሕንጻ ብቻ ሳይሆን በጽዳትዋ ፤ በአየር ፀባይዋና በተለያዩ ሁኔታዎች ከአፍሪቃ የታወቁ ከተማ በመሆንዋ አስመራ በዓለሙ የቅርስ መዝገብ መመዝገብዋ ለኛ ለኢትዮጵያዉያን ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ኩራት ነዉ ሲሉ የወቅቱ የበኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ገልጿል ።
አስመራ ሕያው ሙዚየም እና ሕያው የስልጣኔ ከተማ የአፍሪካን ዘመናዊነት ማሳያ የተረጋጋች እጅግ ማራኪ ብትሆንም ከተማዋ ከቱሪዝም ዘርፉ ተጠቃሚ አልሆነችም።
ሜሳረጊያዉን የባለቅኔዉን የሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ግጥም እንገባበዝና ለዛሬው ይብቃን ።
አስመራ
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
እንደ ከተሞች መዲና አቀያየሱ ቢጠራ
ያውራ ጎዳናሽ ጠለላ ፡
ሁሉን በአክናፉ እየጠራ
አስር ሰዓት ላይ ሲደራ
ለመንገደኛሽ መዝናኛ ፣ሲያጠላ ሲያብብ ሲያፈራ
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
አደባባይ ሲያነጥፉ
አድባራትና መስኪዱን ፣ ካቴድራሉን በየረድፉ
ገበያውን በየመልኩ ፣ እንደ አውታር እያሰለፉ
በወግ እየደረደሩ ፣በስምረት እያሰመሩ
በውበት እያዳበሩ ፣እያሳመሩ ቢያደሩ
በየክፍሉ በየበሩ በየመልኩ በየተራ
ፋኖሱን እንደ ደመራ
ቡና ቤቱን እንደ ሦራ
ምነው ሁሉ እንደ አንቺ አስመራ
እንደ ከተሞች መዲና አቀያየሱ ቢጠራ፡፡
እሳት ወይ አበባ (ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን )

11 months ago
የግብረ ሰናዩ ላየንስ ክለብ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ እና ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነብርሃን
#ethiopia | COVID 19 - ኮሮና ከነጠቀን ባለአበርክቶዎች ኢትዮጵያውያን የጤና ዘርፉ ሻምፒዮኖች መካከል የላየንስ ክለብ አለም አቀፍ ማህበር ዐብይ ተልዕኮ ፈፃሚው ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነብርሃን አይዘነጉም።
እኔ ሳውቃቸው ትኩረት በሚሹ የሃሩራማ በሽታዎች በተለይም የዓይን ማዝ (Trachoma) እና ጊኒ ዎርምን ጨምሮ በወባ መከላከል፥ቁጥጥር እና በሕክምና ከነበራቸው ጉልህ አስተዋጽኦ ጋር በተያያዘ ነው።
በተለይም በአማራ ክልል የትራኮማ (Trachoma) ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ ወባም (Malaria) እንዲሁ የሕብረተሰብ ጤና ስጋት ስለነበር ሁለቱን በሽታዎች ባቀናጀ በካርተር ሴንተር የሕብረተሰብ አቀፍ የጤና ቁጥጥር ፕሮጄክት (Mal-Tra)ጉልህ ድርሻ ነበራቸው።
በዚህ ረገድ ሎሬቱ ከቲ.ኤፍ. ግሎባል ሄልዝ (Taskforce for Global Health) የአፍሪካ ተጠሪ ከዶ/ር ተሾመ ገብሬ እና ከካርተር ሴንተር የኢትዮጵያ ተጠሪ ከዶ/ር ዘሪሁን ታደሰ ጋር በአጋርነት የከወኑትን አካትቼ በሰፊው እመለስበታለሁ።
ዛሬ ላይ ይህ የላየንስ ክለብ እንቅስቃሴ እንዴት ነው?
"እናገለግላለን" (We Serve) የሚል መሪ ቃልን አንግቦ ነው የተነሳው።
በሕብረተሰብ አገልግሎት ልቆ ለመገኘት ሰውን በጥልቅ የልብ ፍቅር መውደድ ይሻል።
በኢትዮጵያ ላየንስ ክለብ የግብረ ሰናይ ስራ ከጀመረ ከስድስት አስርት አመት በላይ ሆኖታል።
የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ነፍስኄር ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ከላየንስ ክለብ ኢትዮጵያ አምስት የቻርተር አባላት አንዱ ነበሩ።
ለዓይነ ስውርነት የሚዳርጉ በሽታዎችን ለምሳሌ በዓይን ማዝ (Trachoma)፥ በዓይን ሞራ ግርዶሽ Cataract)፥ በውሃ ወለድ መዘዝ የዓይነ ስውርነት (River blindness) በሽታዎች ለሚሰቃዩ ቅድሚያ በመስጠት በሕክምና ጥበብ እይታቸው እንዲመለስና ወደ አዲስ የተሻለ ሕይወት እንዲሸጋገሩ ማድረግ የግብረሰናይ ተልዕኮው ቀዳሚ ትኩረት ሆኖ ነው የቆየው።
እነኚህን በሽታዎች በዘላቂነት ለመከላከል ከእህት የላየንስ ክለቦች፥ ከካርተር ሴንተር፥ ከኢንተርናሽናል ትራኮማ ኢኒሺዪቲቭ፥ ከክሪስቶፌል ብላየንድነስ ሚሽን እና ከሌሎችም አጋሮች ጋር በመሆን የ2ኛ ደረጃ የዓይን ሕክምና አገልግሎትን በማስፋፋት የጤና ዘርፉን ሲደግፍ ቆይቷል።
በቀዶ ሕክምና ዜጎች በተለይ አቅመ ደካሞች የዓይን ብርሃንቸው ተነጥቀው እንዳይቀሩ ብሎም 2ኛ ደረጃ የዓይን ማዕከላት በባህርዳር፥ ደብረ ብርሃን፥ አርባምንጭና ጅግጅጋ መቋቋማቸውን የድርጅቱ ሰነድ ያመለክታል።
የመንግስት ሆስፒታሎችን አቅም በማሳደግ ረገድ ራስ ደስታ፥ ልዕልት ዘነበወርቅ ሆስፒታል፥ ራስ ደስታና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎች ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው።
60 አመታትን ያስቆጠረው ላየንስ ክለብ በተጨማሪም በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ግቢ የስኳር ሕሙማን ማዕከል እንዲቋቋምም አድርጓል።
ላየንስ ክለብ በኢትዮጵያ ሕብረተሰባዊ ምግባረ ሰናይ ተግባሩ እንዲጠናከር አባላት በማፍራት ያለበትን ውሱንነት በመቅረፍ የአባላት ማቀፍ እድሎችን ማስፋፋት እንደሚያሻ የክለቡ የኢትዮጵያ አመራሮች በአፅንኦት የሚያነሱት ነው።
ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው የቆዳ ሕክምና ስፔሻሊስቶች (Dermatologists) መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
የቆዳ፣ የስጋ ደዌ፣ የአባላዘር፣ የትራኮማ እና ሌሎች ችግሮች የት የሃሩራማ በሽታዎች ቁጥጥር ላይ በተለይም በአለም አቀፍ ዲፕሎማሲ የሕብረተሰብ ጤና ትኩረት እንዲያገኝ ወሳኝ አካላትን በማግባባት (በ-advocacy) ሚናቸው ታላቅ እንደነበር ለዘርፉ ባለኝ ቅርበት ምስክር ነኝ።
ከሐኪምነታቸው በተጨማሪ የሀገር ሽማግሌ፣ እርዳታ አስተባባሪ፣ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አባል፣ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባል እና በብዙ የበጎ ፈቃደኝነት ስራ ሀገራቸውን አገልግለዋል።
ጥቅምት 22 ቀን በ1941 ዓ.ም በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት፣ ሐረር ከተማ የተወለዱት ዶ/ር ጥበበ ትምህርት የተከታተሉት በአዲስ አበባ ሽመልስ ሀብቴ ት/ቤት ነው።
አባታቸው ሻለቃ የማነብርሃን ወ/ሥላሴ በጦር ሰራዊቱ መኮንን ስለነበሩና የሚታየው ዲሲፕሊንና አለባበስ ከስካውት (Scout) ዲስፕሊንና አለባበስ ጋር የሚቀራረብ ስለነበር ጥበበ በዚያ ተማርከው የስካውት ክበብ አባል ሆነዋል።
ጥበበ 8ኛ ክፍልን ሳሉ የተቸገሩ ልጆችን በት/ቤቱ አካባቢ አይተው ከጓደኞቻቸው ጋር ተማከሩና ከድርሻ የኪስ ገንዘባቸው ቀንሰው በማጠራቀም ሞከሩና፤ ኋላም ‹‹የ10 ወንድማማቾች ማኅበር›› የተባለ ማኅበር መሰረቱ።
የጦር ሰራዊት እና የክብር ዘበኛ የሙዚቃ ቡድኖችን ጋብዘው ስራዎቻቸውን ለተማሪዎች እንዲያሳዩ በማድረግ ከዚያ የሚገኘውን ገንዘብ ለችግረኛ ተማሪዎቹ እንዲሰጥ መላ ዘየዱ።
ከዝግጅቶቹ ያገኙት ገንዘብ የተማሪዎቹን የምግብና የደንብ ልብስ ወጪ ለመሸፈን አስቻላቸው።
ይህ የበጎ ፈቃደኝነት ጥረት ተጠናክሮ ከተደገፉት ተማሪዎች ውስጥ እስከ ዩኒቨርሲቲ ተምረውና ትልቅ ደረጃ ደርሰው በምዕራባውያኑ ባህር ማዶ ሀገራት የሚኖሩም አሉ።
ጥበበ በልጅነታቸው ዲፕሎማት የመሆን ምኞት የነበራቸው ቢሆንም እናታቸው ታመው ሆስፒታል የገቡበት አጋጣሚ ግን የጥበበን ፍላጎትና የሕይወት መንገድ ቀየረው።
እናታቸው ታመው አሁን ጦ/ኃይሎች ሆስፒታል ከሚባለው የልዕልት ፀሐይ መታሰቢያ ሆስፒታል ገቡ።
የእናታቸውን ቀዶ ሕክምና በስኬት ያከናወኑትን ኢትዮጵያውያን ዶክተሮችን (ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን፣ ፕሮፌሰር ታዬ መኩሪያንና ሌሎች ሐኪሞችን) ሲመለከቱ ሐኪም የመሆን ምኞት አሸነፋቸውና ሃሳብ ቀየሩ።
ከዚያም የሩስያ ወዳጅነት ማኅበር የትምህርት እድል ሲሰጥ ጥበበ እድሉን አግኝተው ወደ ሩሲያ ሄደው ለ6 አመታትየሩስያ ቋንቋና የሕክምና ትምህርትን ተምረው በማዕረግ አጠናቀዋል።
በቆዳ ሕክምና የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪያቸውንም አገኙ፤ የአለም አቀፍ የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርትን ማከላቸው ለኋላው ዲፕሎማሲን ለሚሻው የጤና ልማት የማግባባት አድቮኬሲ ስራ ብዙ እንዳገዛቸው መገመት ይቻላል።
ዶ/ር ጥበበ ከ1972 እስከ 1985 ዓ.ም ድረስ በሉቮቭ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ በአማካሪ ስፔሻሊስትነትና ተባባሪ ፕሮፌሰርነትም አገልግለዋል።
ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው የመላው አፍሪካ የሥጋ ደዌ ማገገሚያና ስልጠና ማዕከል (All Africa Leprosy Rehabilitation & Training Center - ALeRT) ዋና የቆዳ ሐኪምና የክፍሉም ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል።
የዶ/ር ጥበበ ከተሳተፉባቸው ዋነኛ ጉዳዮች አንዱ የላየንስ ክለብ ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን (Lions Clubs International) ነው።
በዚህ ክለብ ተሳትፏቸው በተለይ አፍለኛ የዓይን ማዝ ቁጥጥር (control of active trachoma) እና የዓይን ሞራ ግርዶሽ (cataracts) ሕክምና እንዲሁም የዓይን ቆብ ቀዶ ሕክምና (trachomatus trichiasis) ላይ ሳይጠቀሱ አይታለፍም።
ትኩረት ከሚሹ የሃሩራማ በሽታዎች አንዱ የጊኒ ወርም በሽታ ሲሆን ከጊኒ በመወገዱ የኢትዮጵያ ዎርም ተብሎ ስም ለውጥ እንዳይደረግ ያሰጋል።
እናም ይህን በሽታ ለማጥፋት በተያዘ ፕሮግራም የበጎ ፈቃድ አምባሳደርም ሆነው አገልግለዋል።
ሎሬት ዶክተር ጥበበ የሎሬትነት ማዕረግን ያገኙት ከሰሜን አሜሪካ ነው።
የዓለም ሎሬቱ ዶ/ር ጥበበ በርካታ ሽልማቶችን አግኝተዋል። እንደውም በአንድ የሽልማት ሁነት ላይ እንዲህ እል:-
"… ማንም ሰው የትም አገር ሄዶ ሽልማት ሊሸለም ይችላል፤ በአገሩ የተሸለመው ሽልማት ግን ታላቁ ነው ብዬ አምናለሁ። ለእኔ ትልቁ ሽልማቴ በ2002 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሰጠኝ የክብር ዶክትሬት ነው"።
በዓለም የጤና ድርጅት፣ በዓለም ባንክ፣ በብሪታኒያና አሜሪካ የቆዳ ሕክምና ማህበርና አካዳሚ፣በዓለም አቀፍ የቆዳ ሕክምና ማኅበር፣ በአፍሪካ የኤድስ (AIDS) መከላከል መርሃ ግብር፣ በዊልያም ዱ ቦይስ የአፍሮ-አሜሪካ የምርምር ተቋም እንዲሁም በሌሎች ተቋማትም አገልግለዋል።
ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቩላድሚር ፑቲን ዘንድ ለሩሲያም ሆነ ለቀሪው ዓለም መልካም ተግባር ላከናወኑ ሰዎች የሚሰጠውን ከፍተኛ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ከ39ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር ጋር በ-Carter Center እና ሎሬቱ ከፍተኛ አመራር በነበሩበት የላየንስ ክለብ ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ጥምረት አማካይነት ሰፊ የጤና ልማት ስራ ስለመከናወኑ በብዙ የመስክ ስራዎች ራሴም ተገኝቼ መሬት የነካ ሃቅ መሆኑን ታዝቤያለሁ።
‹‹ገና ላሳካው ፈልጌ ያልፈጸምኩት ብዙ ቀሪ ክንውኖች አሉኝ›› ሲሉ የነበሩት ሎሬት ዶ/ር ጥበበ ዓለምን ባርበደበደው ኮሮና በሽታ የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም በ72 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
በቺካጎ ከተማ የዛሬ110 አመት ገደማ ላየንስ ክለብ የተመሰረተው ሲሆን 1.4 ሚሊዮን አባላትን በማቀፍ በ183 ሀገራት ውስጥ ከ43,300 ክለቦች በላይ በ714 የአገልግሎት ማስተባበሪያ አውራጃዎች ተቀናጅቶ እየተመራ ነው።
ክለቦቹ ከመደበኛ ማህበራዊ ስብስብነት በላይ አባላቱ ተልኳቸው ጊዜያቸውን፥ እውቀታቸውንና ሃብታቸውን አቀናጅተው ለበጎ ምግባር በማዋል እርዳታናድጋፍ የሚሹትን የሕብረተሰብ ክፍሎች መታደግ ነው።
........
(Composed by:- Eshetu Geletu - Public health advocate & Champion of NTDs Control)

እንኳን_አደረሰህ_አሉ?
#ethiopia | "የጥበብ ፈጣሪ፣ ልጁን ልኮ በሰው ልጆች ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ጥበብ ለወደቀው የፍጡራን ነፍስ ሰጣቸው፡፡ በቃላትና በግጥም ተደርገው የማይታወቁ ተአምራቶች ታዩ፡፡ በግጥም ሰዎች ከሙታን ሲነሱ፣ የታመሙ ሲፈወሱ… ነፍሳቸውን ከስጋቸው ማስጣል ያልቻሉ… ነፃ ሲወጡ ታዩ...!"
#እንኳን_አደረሰህ_አሉ ?
==============
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
_____
ቅድም ሰዎች ምን አሉኝ?
የአዲስ ዘመን ብስራት ሲነግሩኝ
መልካም ስሜት ሲገልፁልኝ
እውን ምን ነበር ቅድም ያሉኝ?
/
“እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ አደረሰህ፣
እንኳን ከዘመን ዘመን፣ ከዓመት ዓመት
አሻገረህ
የብልፅግና የሠላም፣ የደስታ የጤና
ይሁንልህ፡፡”
ነው መሰለኝ ያሉት፣ ቅድም
ባልሰማቸውም በቅጡ የልቦናዬን
ሳስታምም፡፡
/
ግን ክራሞቴን ሳስበው
መጪውን ደግሞ ሳልመው
የራሴን እዝነ-ልቦና
የነገረኝ ድምፅ ቃና
እንኳን ከሙት ዘመን፣ ሙት ዘመን
ከዘመን ሙት፣ ዘመን ሙት
ከብኩን ሕይወት፣ ብኩን ሕይወት
ከከንቱ ዓመት፣ እከንቱ ዓመት
ገፍቶ ጣለህ
አኝኮ አላምጦ ተፋህ
የሚል መሰለኝ ፊደሉ
የልቦናዬ ትርጉም ቃሉ፡፡
/
“እንኳን አደረሰን” አልኳቸው እኔም ላፌ
የተሰማኝን ደብቄ ከእውነት መፋጠጥ ሰንፌ
“አሜን” አልኩኝ ለምናልባት
ምኞት ሰምሮ ቢሆን እውነት፡፡
/
መግለጫው እንደሁ ከዓመት ዓመት፣ ከዘመን
ዘመን ያው ነው
ግን፣ እንደህይወታችን ፈርጀን፣ እንደአሳለፍነው
ስናየው
አይደል የብስራቱ መልዕክት፣ ትርጉሙ
የሚለያየው?
ዘንድሮ እንዲህ ተረዳሁት፣ የከርሞ ሰው ካለኝ
አንድዬ
ደሞ ላመት ካደረሰኝ፣ ለዚህ ብስራት ፈጣሪዬ
እንዴት እንደሚገባኝ፣ የቃሉ ትርጉም የፊደሉ
እሱ ያውቃል ዲበ-ኩሉ፡፡
/
“እንኳን አደረሰህ” አሉ፣ እኔ መች ደረስኩና
እንዲያውስ አልተንቀሳቀስኩ፣ ከቶ መች
ተላወስኩና
ሳልሄድ አልደርስ የትስ ቢሆን፣ እንኳንስ ዘመን
ይቅርና፡፡
እካችምናው ቦታው አምናው እንደተወኝ
እዚያው እንዲያው አለሁ፣ እሱ እንዳስቀመጠኝ
ለጉድ የጎለተኝ፡፡
/
እኔ ባለሁበት ስፍገመገም፣ ስረግጥ
ሲገሰግስ መጥቶ ዘመን ሲፈረጥጥ
አሁንም እንደአምናው እሱ ደረሰና
ዘመንም ታድሶ መጣና
አይችለው የለ መአት
እኔ ላይ አራግፎ ጥሎት
አለፈ ደግሞ ለመምጣት፡፡
እንጂ እኔማ መች ደረስኩ
ከቶስ መቼ ተለወጥኩ
እንዳለሁ አለሁ እንዳከኩ፡፡
/
“እንኳን ከዘመን ዘመን፣ ከዓመት ዓመት
አሻገረህ”
ተባልኩ ከንቱው እንደሰው፣ ስንፏቀቅ ከርሜ
ስድህ፡፡
እኔስ እንዳለሁ አለሁ የካቻምናዋ ሳትዛባ
አምናም አሁንም ሳትለወጥ ሳትወልቀ
የመከራ ካባ፡፡
ይልቅ ዘመን መጣና ደረሰና እየሰገረ
ሸክሙን አራግፎብኝ ንግርት እያስነገረ
እንኳን አደረሰህ ሲሉ ወደኋላ እያስቀረ
እርስ በርሳችን በእንኳን እንኳን መልሶ
እያናቆረ
አምና ካቻምና ያለንን እንደገና እየነገረ
ውድቀታችንን እያስተጋባ በየዓመቱ እየዘከረ
እሱ አይደል እንዴ አበቅቴውን ቀመሩን
የተሻገረ?!
እንጂ እኛማ እዚሁ አለን ከድልድዩ ወዲህ ማዶ
እንዳከበርን እንደገበርን ለየዓመቱ በዓል
ዘንዶ፡፡
/
ይኽን የችግር ኑሮ የእከክ የሰቆቃ ቅርስ
እኛም በተራ ሳናፍር ለትውልድ ትውልጅ
ስናወርስ
ከበፊቱ እየባሰ የዘመን ባቡር ሦስት ሺ ዓመት
ቁም ስቅላችንን እያየን ያራገፈብንን መአት
አምልጠን ልንወጣ ስንል ደሞ ባመቱ
ሲጭንብን
ቀና ማለት እያቃተን ሸክሙ መልሶ
ሲያጎብጠን
የትም ላንደርስ ሳንሻገር ከድልድዩ ወዲህ ማዶ
የአርባ ቀናችን ችካል ከእትብታችን ጋር ተዋዶ
ውሉ ጠፍቶ ተተብትቦ እንዳሰረን ነን ቀፍድዶ፡፡
/
ይልቅስ እንነሳ በጠዋት ነው የሚያምር
መንገድ
ጀምበርን አስቀድሞ ነው መናጆ አርጎ ሩቅ
መሄድ
ሸክማችንን እንጣልና ጠፍራችንን በጣጥሰን
ዘመንን ቆመን አንጠብቅ እኛም እንሂድ
ገስግሰን፡፡
ይኽን የአሳር በርሃ ይኽን የእንባ ሸለቆ
ያው ባለቤቱ ነውና ማለፍ ያለበት ሰንጥቆ
ያለ እኛ በቀር ሌላ ማንም አያሻግረን
ተጨንቆ፡፡
ያሰብንበት ስንደርስ መከራችንን ሁሉ አልፈን
ተስፋችንም ሲፈቃ ኑሯችንም ሲሰምርልን
የዚያኔ ነው እንኳን ማለት አደረሰህ አሻገረህ
ከዘመን ጋር ስንለወጥ ሕይወታችን ሲሆን
ብሩህ፡፡
# ፀጋዬ_ገ /መድህን
ምንጭ ጦቢያ መጽሔት ነሐሴ 1989

ስታር ዋይድ አዋርድ ሀገርን በቅንነትና በትጋት ያገለገሉ ኢትዮጵያዊያን በማለት የእውቅና ሰርተክፌት ሰጠ
ፕሮግራሙ የቀድሞ የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት አቶ ሙላቶ ተሾመ በክብር እኝግድነት ጋብዞ ነበር የእለቱን ሁነት የጀመረው።
ከዚህ ቀድም በአገር አቀፍ ደረጃ ሲዘጋጅ የቆየው ይህ የሽልማት መርሐ ግብር፣ ዘንድሮ አድማሱን በማስፋት የምስራቅ አፍሪካ አገራትን አካትቷል።
ስታር ዋይድ አዋርድ ለሕዝብ እና ለአገር በጎ ነገር ያበረከቱ ግለሰቦችና ስኬታማ የኢካኖሚ ጀግኖች, በትጋት በቅንናት እና በአገር ፍቅር መስራት ተምሰሌት የሆኑ አመረሮች,ዕውቅና እና ሽልማት የሚያበረክት ሲሆን፣ በመጀመሪያው ዙር የሽልማት መርሐ ግብር በተለያዩ የሞያ ዘርፎች አስተዋጽዖ ላበረከቱ ግለሰቦች እና ተቋማት ዕውቅና እና ሽልማት መስጠቱ ይታወሳል።
ስታር ዋይድ አዋርድ ካከናወነው የሽልማት መርሀግብር አንደኛው ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ታለቅ ስራ የሰሩ ሰዎች የሚመሰገኑበት በህይወት ለሌሉ ሰዎች የሚሰጠው እውቅና ሲሆን በዚህም ሎሬት ዶ/ር ጌታቸው ትኩበት ልዩ እውቅና ተሰጥቶቸዋል።
ሎሬት ጌታቸው ትኩበት በ2015 አመተ ምህረት ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው የሚታወስ ሲሆን ባለቤታቸው በፕሮግራሙ በመገኘት የእውቅና ሽልማቱን ተቀብለዋል።
በዘንድሮው የእውቅና መርሀግብር የእድሜ ዘመን ተሸላሚ በመሆን ጋዜጠኛ ኢሳያስ ሆርዶፋ ሽልማትና እውቅና ተሰጥቶታል።
በዘንድሮ የስታር ዋይድ አዋርድ ላይ በአመራርነት እውቅና ከተሰጣቸው አመራሮች መካከል የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ እንዲሁም የሶማሊያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ መስጠፌ መሀመድ ልዩ እውቅና ሰጥቶቸዋል።
እንደዚሁም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ማርያም በአመራር ዘርፍ እውቅና እንደዚሁም ሽልማት ከተሰጣቸው አመራሮች መካከል ይገኙበታል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩም በስራ ብቃት አመራር ዘርፍ ልዩ እውቅና ከተሰጣቸው አመራሮች መካከል ይገኙበታል።
የዘንድሮ የስታር ዋይድ ሽልማት እውቅና ከሰጣቸው ግለሰቦች መካከል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ይገኙበታል።
ጊፍት ሪል ስቴት በስታር ዋይድ አዋርድ ልዩ እውቅናና ሽልማት ከተሰጣቸው የቤት አልሚዎች መካከል ይገኙበታል።
በስራ ፈጠራ ዘርፍ እውቅናና ሽልማት ከተሰጣቸው ዜጎች መካከል አቶ በላይነህ ክንዴ ይገኙበታል።
እንደዚሁም የቶቶት ምግብ ቤት መስራች አቶ ጠንክር ቴኒም ሌላኛው ናቸው።
በዛሬ የሽልማት መርሀግብር አቶ ገምሹ በሶስት ዘርፎች ሽልማት የተበረከተላቸው ሌላኛው ግለሰብ ናቸው።
እንደዚሁም የሀይብሪድ ዲዛይን መስራች የሆነችው ወ/ሮ ሳምራዊትም ሽልማት ካገኙ እውቅ ሰዎች መካከል ትገኝበታለች።
በአመቱ ምርጥ የሚዲያ ፕሮግራም ዘርፍ ጋዜጠኛ አስካለች በውሎ አዳር ፕሮግራሟ ሽልማት ወስዳለች።

🏆ስታር ዋይድ አዋርድ
ሀገርን በቅንነትና በትጋት ያገለገሉ ኢትዮጵያዊያን እውቅና የሰጠው ፕሮግራም።

በዘንድሮው የእውቅና መርሀግብር የእድሜ ዘመን ተሸላሚ በመሆን ጋዜጠኛ
ኢሳያስ ሆርዶፋ ሽልማትና እውቅና ተሰጥቶታል።

የዘንድሮ የስታር ዋይድ ሽልማት እውቅና ከሸጣቸው ግለሰቦች መካከል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ይገኙበታል።

12 months ago
ሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ ሕንጻ
#ethiopia | የጎንደር ዩንቨርሲቲ ሴኔት ሐምሌ 24 ቀን 2017ዓ.ም ባካሄደው ጉባዔ ሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ ላበረከተው ፈርጀ ብዙና ፈር ቀዳጅ የሙያ አስተዋጽዖ የሙዚቃ ትምህርት ቤቱን ሕንጻ "ሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ ሕንጻ" ብሎ ሰይሞታል።
◾️ሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ
#በሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ካሳረፉ ባለውለታዎች መካከል ኢትዮጵያዊው ሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። በ1936 ዓ.ም በጅማ ከተማ የተወለደው አንጋፋው አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከጃዝ እና ላቲን ሙዚቃ ጋር በማስተጋበር ልዩ የሆነ የሙዚቃ ቀለም በመፍጠር የኢትዮጵያ ሙዚቃን ከፍ ያለ እውቅና እንዲያገኝ እና ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ ያስተዋወቀ የአገር ባለውለታ ነው። በዚህም ምክንያት "የኢትዮ-ጃዝ አባት" ተብሎ ይጠራል።
#ለንደን፣ ኒውዮርክ እና ቦስተን በሚገኙ ስመጥር የሙዚቃ ትምህርት ቤቶች ተምሯል። በሙያው ብቁ በሆኑ ባለሙያዎች ሰልጥኗል። ጥበብና ክህሎቱን በትምህርት ካዳበረ በኃላ “Broken Flowers“ ለተሰኘው የእንግሊዝኛ ፊልም ማጀቢያ ሙዚቃ መሥራት ጨምሮ ታላላቅ አገራዊና ዓለም ዓቀፋዊ መድረኮች ላይ ሥራውን አቅርቧል።
#በዘመን ተሻጋሪ የጥበብ ሥራዎቹ የሀገራችንን ውብ የብሔር ብሔረሰቦች ሙዚቃ መሳሪያዎችና ውዝዋዜዎች የዓለም ትኩረት እንዲያገኙ ከማድረግ ባለፈ በታዋቂ አርቲስቶች ሥራዎች ላይ ጭምር እንዲካተቱ ከፍተኛ ተጽእኖ ማሳደር ችሏል። በዓለም ላይ ያሉ ብዙ የጥበብ ሰዎች እርሱ መድረክ ሥራ ላይ ይዟቸው ከቀረቡ የብሔረሰቦቻችን ሙዚቃ፣ ሙዚቃ መሳሪያ እና ውዝዋዜ አያሌ ትምህርቶችን እንደቀሰሙ ይነገራል።
#ይህ ጉምቱ የጥበብ ሰው የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ዜማ እና መሳሪያዎችን ለትውልድ ለማስተማርና ለማሳደግ ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዜማ መሣሪያዎች ታሪካዊ ሚና እና በሀገሪቱ የሙዚቃ ቅርስ ላይ ያላቸውን ተፅእኖ የሚዳስስ መጽሐፍም አዘጋጅቷል።
#ሎሬት ሙላቱ ለዓለም ሙዚቃ ላበረከተው ታላቅ አስተዋጽኦ በኢትዮጵያ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ሽልማቶች ተበርክቶለታል። ከጅማ ዩንቨርስቲ የክብር ዶክትሬት እንዲሁም የህይወት ዘመን የክብር ሽልማት ተሸላሚ፤ ከበርክሌይ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ያገኙ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ፤ በጀርመን አገር በስሙ መንገድ የተሰየመለት፤ በፈረንሳይ መንግሥት የአገሪቱ ከፍተኛ የክብር ኒሻን "Ordre des Arts et des Lettres" ተሸላሚ፤ እንዲሁም ከኢጣልያ መንግሥትም 'Ordine della Stella d’Italia' ኒሻን ከተበረከቱለት እውቅናዎችና ሽልማቶች ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ።
#በጎንደር ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ ጊዚያት በተጋባዥነት እየተገኘ የሙዚቃ ትምህርት ክፍሉ እንዲጠናከር ልምድና እውቀቱን ለመምህራንና ተማሪዎች አካፍሏል።
#ስለሆነም የጎንደር ዩንቨርሲቲ ሴኔት ሐምሌ 24 ቀን 2017ዓ.ም ባካሄደው ጉባዔ ሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ ላበረከተው ፈርጀ ብዙና ፈር ቀዳጅ የሙያ አስተዋጽዖ እውቅና ለመስጠትና ትውልዱ እንዲማሩበት በማሰብ የሙዚቃ ትምህርት ቤቱን ሕንጻ "ሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ ሕንጻ" ብሎ ሰይሞታል።
©AsratAtsedeweyn
#ethiopianhisoryandtourism #ethiopianhistoryandtourism #enkssm

አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
ተዋናይ ፣ኮሜዲያን፣ አዘጋጅ ሆኖ ለረዥም ዓመታት አገልግሏል፡፡ በመድረክ ፣ በሬዲዩ፣ በቴሌቪዥን፣ በፊልም ስራ እና በጋዜጠኝነት ሙያ ሠርቷል ። በአፍሪካ የመድረክ ሙያተኞች ማህበር በሊቀመንበርነት መርቷል ፣ በአትላንታ ጆርጂያ በበረከተው የሙያው ሥራ ኖቬምበር 24 ቀን በስሙ ተሰይሞለታል። (ጋሽ ደቤ) በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በህይወት ካሉት አርቲስቶች ግንባር ቀደሙና አንጋፋው ነው።
መጀመሪያ በቴያትር የታዩት በመንግስቱ ለማ በተጻፈው ያላቻ ጋብቻ ሲሆን ከዚያ በአንዳንድ እንግሊዝኛ ትርኢት (The game of chess, ‘Waiting for Godot’) እንዲሁም በራዲዮም ሆነ በቴሌቪዥን ተጫወቱ።
አርቲስት ደበበ እሸቱ (ጋሽ ደቤ) ለታሪክ የሚተላለፉ ህያው ስራዎች ሰርቷል እስቲ ጋሽ ደቤ ከሰራቸው ስራዎች ውስጥ በጥቂቱ እንያቸው፤ በሃገር ውስጥ ካለው ታዋቂነትና ለሙያው ካደረገው አስተዋጽኦ ለመጠቀስ ያህል ፡-
በቤተኪነጥበባት ወቴአትር፡-
ያላቻ ጋብቻ ተዋናይ
ሮሚዎባ ዡልየት ተዋናይ
ጠልፎ በኪሴ ተዋናይም አዘጋጂም
ዳንዴው ጨቡዴ ››
ዘ ጌም ኦፍ ቼዝ (በእንግሊዝኛ) ተዋናይ
ኦቴሎ (በአንግሊዝኛ) ተዋናይም አዘጋጂም
አዳ ኦክ አራክል (በእንግሊዝኛ)ከሎ.ጸ.ገ.መ ተዋናይ
በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ(ብሔራዊ) ቴአትር፡-
የበጋ ሌሊት ራዕይ ተዋናይ
አንድ ዓመት ከአንድ ቀን ተዋናይ
እናት ዓለም ጠኑ ተዋናይ
ኪንግ ሊር ተዋናይ
ዋናው ተቆጣጣሪ ተዋናይ
ጠያቂ ተዋናይ አዘጋጅ
በቀይካባ ስውር ደባ አዘጋጅ
ተሓድሶ አዘጋጅ
የአዘውንቶች ክበብ አዘጋጅ ተዋናይ
በሃገር ፍቅር ቴአትር፡-
ጠልፎ በኪሴ አዘጋጅ/ተዋናይ
የወፍ ጎጆ ተዋናይ
ኪንግ ሊር ተዋናይ
የቬኒሱ ነጋዴ ተዋናይ
ናትናኤል ጠቢቡ ተዋናይ
ድብልቅልቅ ተርጓሚ/ ተዋናይ
ማዕበል ተርጓሚ አዘጋጅ
በፊልም በሃገርና በዓለም አቀፍ፡-
ዘ ሴይለር ፍሮም ጂብራልታር
ሻፍት ኢን አፍሪካ
ጉማ
ዚ አፍሪካን ስፓይ
ዜልዳ
አፍሪካ
ዘግሬቭ ዲገር
ዘ ግሬት ሪቤሊየን
እነዚህ ለምሳሌ ያህል የቀረቡ እንጂ የደበበ ስራዎች በርካቶች ናቸው፡፡ ከመድረክና ፊልም ስራዎቹ ባሻገር ተማሪዎችም አሰልጥኗል፡፡ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን በብሔራዊ ቴአትር የተዋንያን ስልጠና ማዕከል ሲያቋቁሙ ከመምሃራኖቹ መሃልና በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው መምህር ደበበ ሲሆን ለተማሪዎቹም መማርያ እንዲሆን የተረጎመው የስታንስላቭስኪ የተዋናይ ሀሁ ለበርካታዎች የሙያ ተማሪዎች የሙያቸው ፊደል መቁጠርያ ሆኖ ይገ ኛል፡፡
በትርጉም በኩልም ደበበ ከቴአትር፡-
ያልታመመው በሽተኛ
ድብልቅልቅ
ጎርፉ
ከመጽሐፍ ደሞ
የዳዊት ወልደጊዮርጊስን
የደም እንባ
የራሱን ወጥ ሥራ በተመለከተ
የእምነቴ ፈተና
ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው
ደበበ ለአፍሪካ ጥበብ ያለውን አመለካከትና ግንዛቤ ከቅኝ ገዢዎች ትርጓሜ ለማውጣትና ሶስተኛው ዓለም ኋላ ቀር ሲባልም በኤኮኖሚና በቴክኒዮሎጂ እንደሆነ፤ ይህም የሆነው ነጩ የአፍሪካን የዋህነት፤ እንግዳ ተቀባይነትና ሩህሩህነት መንጠላጠያ በማድረግ ቅኝ አድርገው ህሊናውን ስለዘጉበትና ስላሰሩት መሆኑን፤በባህል በኩል ግን ጨርሶ ሊደርሱበት የማይችሉትና ሊያጠፉትም ያደረጉት ሙከራ ዋጋ ቢስ ሆኖ እንደቀረ የሚያስረዳ ጥናታዊ ጽሁፍ በማቅረብ ተቀባይነትን አግኝቶ ድል ያደረገና፤ ቀደም ሲል የጀመረውን ትግል አጠናክሮ በመቀጠል በ1985 ዓ/ም እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በርሊን ላይ በተካሄደው የዩኔስኮ የባህል(አይ ቲ አይ) ኢንተርናሽናል ቴአትር ኢትዮጵያን ወክሎ በመገኘት በአፍሪካ ውስጥ የመጀመርያው ፕሮፌሽናል ቴአትር ቤት የሃገር ፍቅር ቴአትር መሆኑን በማስረጃ አስደግፎ ተቀባይነትን አገኘ፡፡
በዚሁ ዓመት የዩኔስኮ የባሕል ክፍል አይ ቲ አይ የአፍሪካ ተጠሪ ሆኖ በመመረጥ፤ በዚያው ዘመን ዝምባብዌ ላይ በሚካሄደው ቴአትር ለልማትና ዕድገት ወርክሾፕ ላይ በመሪነት እንዲገኝ በዩኔስኮ ተወክሎ በመሄድ ወርክሾፑን በአጥጋቢ ችሎታውና የአመራር ብቃቱ ከመፈጸሙም ባሻገር ለብዙ ጊዜ ተሞክሮ ሲወድቅ ሲነሳ የነበረውን የአፍሪካ የመድረክ ባለሙያዎች ማሕበርን አስተባብሮ በማቋቋም የማሕበሩም መስራች ፕሬዜዳንት ሆኖ ለ12 ዓመታት መርቷል፡፡ አሁንም መስራች ፕሬዛዳንት በመባል ይጠራል፡:
ደበበ በችሎታውና በብቃቱ በማስተባበር ችሎታው ዩኔስኮ ዓለም አቀፍ የቴአትር ኢንሳይክሎፒዲያን ለማዘጋጀት ሲወስን ደበበንም አፍሪካን በመወከል የኤዲቶርያል ቦርድ አባል አድርጎ መድቦት ሥራውን በሚገባ ተወጥቷል፡፡
ደበበ ቴአትር ለልማትና ለእድገት በሚል የሚታወቀውን የቴአትር ዲሲፕሊን ስልጠና ለበርካታ ሃገራት ባለሙያዎች ያስተማረ ሲሆን በርካታ ወርክሾፖችም በየሃገራቱ እየተጋበዘ መርቷል፡፡ ይሀን ዘዴ ካዋቀሩትም አምስት አፍሪካዊ ባለሙያዎች አንዱ ደበበ ነው፡፡
ወርክሾፕ የሰጠባቸው ቦታዎች፤ ታንዛኒያ፤ኡጋንዳ፤ኬንያ፤ማላዊ፤ኮንጎ ብራዛቪል፤አይቮሪ ኮስት፤ ካሜሩን፤ ናይጄርያ፤አይርላንድ፤ብራዚል፤ሰሜን አሜሪካ፤እንግሊዝ፤ ኩባ፤ በርሊን፤ካናዳ ይገኙበታል፡፡
ደበበ ላለፉት ከ40 በላይ ዓመታት በቴአትር ጥበብ ውስጥ ኖሮ በ1995 በተካሄደው ሃገራዊ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ‹‹ቀስተደመና›› የፖለቲካ ፓርቲን ተቀላቅሎ፤ በኋላም ቅንጅት ሲፈጠር የምክር ቤት አባልና የሕዝብ ግንኙነት በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ ቅንጅትን ለድል ያበቃ፤ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዝግጅቶቹ ገዢውን ፓርቲ ያንበረከኩና ቅንጅትና ያገዘፉ ነበሩ፡፡በዚህም ከሌሎች አመራሮች ጋር ለአንድ ዓመት ከአስር ወራት ለእስር ተዳርጓል፡፡ እንዲሁም በ2002 በድጋሚ ለአንድ አመት ታስሮ ተፈቷል፡፡
ደበበ በሃገሩ ለመሸለም ባይበቃም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግን ለሽልማቶች የበቃ ባለሙያ ነው፡፡ ለዚሁ የሙያ አስተዋጽኦ ክፍተኛው ክብሩ በአትላንታ ጆርጂያ ኖቬምበር 24 የደበበ እሸቱ ቀን ተብሎ እንዲሰየም የከተማው ምክር ቤት ማጽደቁ ነው፡፡
ጋሽ ደቤ ጋደኛም ሚስትም ከሆነችው ከአልማዝ ደጀኔ ጋር 4 ልጆች እና 6 የልጅ ልጆች አሉት።
ነፍስ ይማር
viaጌጡ ተመስገን

የኪነ ጥበቡ ዋርካ አርፈዋል
#ethiopia | አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
በሕክምና በተለያዩ ሆስፒታሎች ይከታተሉ ነበር።
***
ጋሽ ደቤ !

እነዚህ ለምሳሌ ያህል የቀረቡ እንጂ የደበበ ስራዎች በርካቶች ናቸው፡፡ ከመድረክና ፊልም ስራዎቹ ባሻገር ተማሪዎችም አሰልጥኗል፡፡ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የተዋንያን ስልጠና ማዕከል ሲያቋቁሙ ከመምህራኖቹ መሃልና በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው መምህር ደበበ ሲሆን ለተማሪዎቹም መማርያ እንዲሆን የተረጎመው የስታንስላቭስኪ የተዋናይ ሀሁ ለበርካታዎች የሙያ ተማሪዎች የሙያቸው ፊደል መቁጠርያ ሆኖ ይገኛል፡፡
በትርጉም በኩልም ደበበ ከቴአትር፡-
ያልታመመው በሽተኛ
ድብልቅልቅ
ጎርፉ
ከመጽሐፍ ደሞ
የዳዊት ወልደጊዮርጊስን
የደም እንባ
የራሱን ወጥ ሥራ በተመለከተ
የእምነቴ ፈተና
ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው
ደበበ ለአፍሪካ ጥበብ ያለውን አመለካከትና ግንዛቤ ከቅኝ ገዢዎች ትርጓሜ ለማውጣትና ሦስተኛው ዓለም ኋላ ቀር ሲባልም በኤኮኖሚና በቴክኒዮሎጂ እንደሆነ፤ ይህም የሆነው ነጩ የአፍሪካን የዋህነት፤ እንግዳ ተቀባይነትና ሩህሩህነት መንጠላጠያ በማድረግ ቅኝ አድርገው ህሊናውን ስለዘጉበትና ስላሰሩት መሆኑን፤ በባህል በኩል ግን ጨርሶ ሊደርሱበት የማይችሉትና ሊያጠፉትም ያደረጉት ሙከራ ዋጋ ቢስ ሆኖ እንደቀረ የሚያስረዳ ጥናታዊ ጽሁፍ በማቅረብ ተቀባይነትን አግኝቶ ድል ያደረገና፤ ቀደም ሲል የጀመረውን ትግል አጠናክሮ በመቀጠል በ1985 ዓ.ም እንደ አውሮፓውያን ቆጣጠር በርሊን ላይ በተካሄደው የዩኔስኮ የባህል(አይ ቲ አይ) ኢንተርናሽናል ቴአትር ኢትዮጵያን ወክሎ በመገኘት በአፍሪካ ውስጥ የመጀመርያው ፕሮፌሽናል ቴአትር ቤት የሃገር ፍቅር ቴአትር መሆኑን በማስረጃ አስደግፎ ተቀባይነትን አገኝቷል፡፡
በዚሁ ዓመት የዩኔስኮ የባሕል ክፍል አይ ቲ አይ የአፍሪካ ተጠሪ ሆኖ በመመረጥ፤ በዚያው ዘመን ዝምባብዌ ላይ በሚካሄደው ቴአትር ለልማትና ዕድገት ወርክሾፕ ላይ በመሪነት እንዲገኝ በዩኔስኮ ተወክሎ በመሄድ ወርክሾፑን በአጥጋቢ ችሎታውና የአመራር ብቃቱ ከመፈጸሙም ባሻገር ለብዙ ጊዜ ተሞክሮ ሲወድቅ ሲነሳ የነበረውን የአፍሪካ የመድረክ ባለሙያዎች ማሕበርን አስተባብሮ በማቋቋም የማሕበሩም መስራች ፕሬዜዳንት ሆኖ ለ12 ዓመታት መርቷል፡፡ አሁንም መሥራች ፕሬዚዳንት በመባል ይጠራል፡:
ደበበ በችሎታውና በብቃቱ በማስተባበር ችሎታው ዩኔስኮ ዓለም አቀፍ የቴአትር ኢንሳይክሎፒዲያን ለማዘጋጀት ሲወስን ደበበንም አፍሪካን በመወከል የኤዲቶርያል ቦርድ አባል አድርጎ መድቦት ሥራውን በሚገባ ተወጥቷል፡፡
ደበበ ቴአትር ለልማትና ለእድገት በሚል የሚታወቀውን የቴአትር ዲሲፕሊን ስልጠና ለበርካታ ሃገራት ባለሙያዎች ያስተማረ ሲሆን በርካታ ወርክሾፖችም በየሃገራቱ እየተጋበዘ መርቷል፡፡ ይህን ዘዴ ካዋቀሩትም አምስት አፍሪካዊ ባለሙያዎች አንዱ ደበበ ነው፡፡
ወርክሾፕ የሰጠባቸው ቦታዎች፤ ታንዛኒያ፤ ኡጋንዳ፤ ኬንያ፤ማላዊ፤ ኮንጎ ብራዛቪል፤ አይቮሪ ኮስት፤ ካሜሩን፤ ናይጄርያ፤ አይርላንድ፤ ብራዚል፤ ሰሜን አሜሪካ፤ እንግሊዝ፤ ኩባ፤ በርሊን፤ ካናዳ ይገኙበታል፡፡
ደበበ ላለፉት ከ40 በላይ ዓመታት በቴአትር ጥበብ ውስጥ ኖሮ በ1995 በተካሄደው ሃገራዊ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ‹‹ቀስተደመና›› የፖለቲካ ፓርቲን ተቀላቅሎ፤ በኋላም ቅንጅት ሲፈጠር የምክር ቤት አባልና የሕዝብ ግንኙነት በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ ቅንጅትን ለድል ያበቃ፤ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዝግጅቶቹ ቅንጅትን ያገዘፉ ነበሩ፡፡በዚህም ከሌሎች አመራሮች ጋር ለአንድ ዓመት ከአስር ወራት ለእስር ተዳርጓል፡፡ እንዲሁም በ2002 በድጋሚ ለአንድ አመት ታስሮ ተፈቷል፡፡
ደበበ በሃገሩ ለመሸለም ባይበቃም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግን ለሽልማቶች የበቃ ባለሙያ ነው፡፡ ለዚሁ የሙያ አስተዋጽኦ ክፍተኛው ክብሩ በአትላንታ ጆርጂያ ኖቬምበር 24 የደበበ እሸቱ ቀን ተብሎ እንዲሰየም የከተማው ምክር ቤት ማጽደቁ ነው፡፡
ጋሽ ደቤ ጋደኛም፤ ሚስትም ከሆነችው ከአልማዝ ደጀኔ ጋር 4 ልጆች እና 6 የልጅ ልጆች አሉት።

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተለያዩ ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅና ሰጠ
#ethiopia | የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ እና የማስተማሪያ ሆስፒታሉ 100ኛ ዓመት ምሥረታ ማጠቃለያ መርሐግብር በዛሬው እለት በልዮ ልዩ መርሐግብሮች በማክበር ተጠናቋል።
በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ለተቋሙ እና ለሀገር አሰተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት እና ግለሰቦች የተለያዩ እውቅና ተሰጥቷል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሥራት አጸደወይን የጎንደር ዩኒቨርሲቲን 70ኛ እና የማስተማሪያ ሆስፒታሉ 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በድምቀት ተጀምሮ በስኬት ለፍጻሜው መብቃቱን ገልጸው በዚህ የደመቀ ክብረበዓል ከማኅበረሰቡ ጋር ያለንን ታሪካዊ ግንኙነት በልማት ፕሮጀክቶች ርክክብ የበለጠ ያጠናከርንበት፣ የቀድሞ ምሩቃን፣ የሀገር ውስጥና ዓለም ዓቀፍ ባለድርሻ አካላት ከተቋማችን ጋር እንዲተሳሰሩ እድል የፈጠረንበት፣ ታሪካዊ ጉዟችንን አስተዋውቀን ዛሬ የደረስንበትን በማሳየት የነገ ህልማችንን በማጋራታችን በመንግሥትና በተለያዩ ባለድርሻ አካላት ዘንድ የነበረንን ተአማኒነት ከፍ ያደረግንበት ነበር ብለዋል።
ከዚህ ባሻገር መልካም ተሞክሮዎችን ያጋራንበት፣ መሪዎችንና ባለውለታዎችን ያከበርንበት፣ እንዲሁም ማኅበረሰብ ተኮር ችግሮችን ለመቅረፍ ጥልቅ ውይይት ያደረግንበትና ችግር ፈቺ የተግባር አቅጣጫዎች እንደተቀመጠ ዶክተር አስራት ገልጸዋል።
በዚህ ዓመት ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ 22 ፕሮጄክቶችን ማስመረቃቸውን ያስታወሱት ዶክተር አስራት በቀጣይ አምስት አመታት ውስጥ የሚጠናቀቁ 26 ኘሮጀክቶች በዛሬው እለት የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጣቸውን ገልጸዋል።
በዛሬው የማጠናቀቂያ መርሐግብር ላይ እውቅና ከተሰጣቸው ግለሰቦች እና ተቋማት ባሻገር ከዚህ በታች ለሚገኙ ግለሰቦች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚገኙ ሕንጻዎች በስማቸው ተሰይሞላቸዋል።
👉 ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ
👉 ዶክተር በርናንድ አንደርሰን
👉 ፕሮፌሰር መንገሻ አድማሱ
👉 ዶክተር ደሳለኝ መንገሻ
👉 ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ
👉 ጋዜጠኛ እና ደራሲ ብርሃኑ ዘርሁን
👉 ለፕሮፌሰር ማለደ ማሩ፣
👉 ለዶክተር ያሬድ አሰፋ፣
👉 ለዶክተር ነብዩ መስፍን፣
👉 ለቤተር ራይዝሽ፣
👉 ለፕሮፌሰር ደኒዝ ዲ ካርልሰን፣
👉 ለፕሮፌሰር ያሬድ ወንድምኩን
👉 ለሎሬት ሙላቱ አስታጥቄ
👉 በ1963 ዓ.ም መሬታቸውን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ በፈቃደኝነት ለሰጡ 59 አርሶ አደሮችም በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የተለያዩ ሕንጻዎች በስማቸው እንዲሰየም ተደርጓል።

1 year ago
ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት
/ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን/
------------
አዬ፣ ምነው እመ ብርሃን? ኢትዮጵያን ጨከንሽባት?
ምነው ቀኝሽን ረሳሻት?
እስከመቼ ድረስ እንዲህ፣ መቀነትሽን ታጠብቂባት?
ልቦናሽን ታዞሪባት?
ፈተናዋን፣ ሰቀቀኗን፣ ጣሯን ይበቃል ሳትያት?
አላንቺእኮ ማንም የላት….
አውሮጳ እንዲሁ ትናጋዋን፣ በፋሽስታዊ ነቀርሳ
ታርሳ፣ ተምሳ፣ በስብሳ
ሂትለራዊ እባጭ ጫንቃዋን፣ እንደኮረብታ ተጭኗት
ቀና ብላ እውነት እንዳታይ፣ አንገቷን ቁልቁል ጠምዝዟት
ነፍሷን ድጦ ያስበረከካት
ሥልጡን፣ ብኩን፣ መፃጉዕ ናት፤ ….
እና ፈርቼ እንዳልባክን፣ ሲርቀኝ የኃይልሽ ውጋገን
አንቺ ካጠገቤ አትራቂ፣ በርታ በይኝ እመ ብርሃን
ቃል ኪዳኔን እንዳልረሳት፣ እንዳልዘነጋት ኢትዮጵያን፡፡
አዎን፣ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ፣ ተፈትቶ እንዳይከዳት ሠጋሁ …
አዋጅ፣ የምሥራች ብዬ፣ የትብት ምግቤን ገድፌ
ከእናቴ ማኅፀን አርፌ
ከአፈርዋ አጥንቴን ቀፍፌ
ደሜን ከደሟ አጠንፍፌ
ከወዟ ወዜን ቀፍፌ
በሕፃ እግሬ ድሄባት፣ በህልም አክናፌ ከንፌ
እረኝነቴን በሰብሏ፣ በምድሯ ላብ አሳልፌ
ከጫጩት እና ከጥጃ፣ ከግልገል ጋር ተቃቅፌ፤
በጋው የእረኛ አደባባይ፣ ክረምት እንደወንዙ ፍሳሽ
በገጠር የደመና ዳስ፣ በገደል ሸለቆ አዳራሽ
ከቆቅ እና ከሚዳቋ፣ ከዥግራ ጠረን ስተሸሽ
በወንዝ አፋፍ ሐረግ ዝላይ፣ መወርወር መንጠልጠል ጢሎሽ
ከፍልፈል ጋር ሩጫ ስገጥም፣ ከቀበሮ ድብብቆሽ
ከናዳ ጫፍ ሣር አጨዳ፣ ለግት ላሜ ትንሽ ግጦሽ
ለጥጃዬ የሌት ግርዶሽ
ለጥማድ በሬዎች ራት፣ ለማታቸው ትንሽ ድርቆሽ
ለግልገሌ ካውሬ ከለል
እማሳው ሥር ጎጆ መትከል
ለፀሐይ የሾላ ጠለል፣ ለዝናብ የገሳ ጠለል
ውሎ የንብ ቀፎ ማሰስ፣ ያበባ እምቡጥ ሲፈነዳ
የግጦሽ ሣር ሲለመልም፣ ሲሰማሩ ሰደድ ሜዳ
አዝመራው ጣል ከንበል ሲል፣ ከብቱ ለሆራ ሲነዳ
ፈረስ ግልቢያ ስሸመጥጥ፣ ከወፎች ዜማ ስቀዳ
ልቤ በንፋስ ተንሳፎ፣ በዋሽንት ዋይታ ሲከዳ …..
ያቺን ነው ኢትዮጵያ የምላት
እመ ብርሃን እረሳሻት?
ያቺን የልጅነት የምሥራች? የሕፃንነት ብሥራት
የሣቅ የፍንደቃ ዘመን፣ የምኞት የተስፋ ብፅአት
ያቺን የልጅነት እናት?
አዛኚቱ እንዴት ብለሽ፣ ጥርሶችሽን ትነክሺባት?
ሥሜን በሥምሽ ሰይሜ፣ ባገልግሎትሽ ስዋትት
ከዜማ ቤት እቅኔ ቤት፣ ከድጓ ቤት እመጻሕፍት
ካንቺ ተቆራኝታ ዕድሌ፣ ካንቺ ተቆራኝታ ነፍሴ
ከቀፈፋ ደጀሰላም፣ ከቤተልሔም ቅዳሴ
እኰ፣ ቀፎ ዳባ ለብሶ
ቅኔ ዘርፎ ግስ ገሦ
መቅደስ አጥኖ ማኅሌት ቆሞ
በልብስ ተክህኖ አጊጦ፣ በብር አክሊል ተሸልሞ
እመ ብርሃን ያንች ጽላት፣ ነፍስ ላይ በእሳት ታትሞ
የመናኒው ያባ ተድላ፣ ረድ ሆኜ፣ አብሮኝ ታድሞ
ሕይወቴ እምነትሽን ጸንሶ
ሥጋ ፈቃዴ ተድሶ
ለሕንፃሽ መዲና ቆሞ፣ ለክብርሽ ድባብ ምሰሶ
ሥሜን በሥምሽ ሰይሜ፣ ሆነሺኝ የእምነቴ ፋኖስ
ለዋዜማሽ ግሸን ማርያም፣ ለክብርሽ ደብረ ሊባኖስ
ስሮጥ፣ በወንበሩ አኖርሺኝ፣ በአንበሳው በቅዱስ ማርቆስ
ታዲያ ዛሬ ኢትዮጵያ ስትወድቅ፣ ከምትሰጪኝ የፍርሃት ጦስ
ምነው በረኝነት እድሜ፣ ዓይኔን በጓጎጣት የሎስ
የጋኔል ጥንብ አንሳ ከንፎ፣ ወርዶ በጨለማ በርኖስ
ባክሽ እመ ብርሃን ይብቃሽ፣ ባክሽ ምስለ ፍቁር ወልዳ
ጽናት ስጪኝ እንድካፈል፣ የእናቴን የኢትዮጵያን ፍዳ፣
ከነከሳት መርዝ እንድቀምስ፣ ከነደደችበት እቶን
የሷን ሞት እኔ እንድሞታት፣ ገላዋ ገላዬ እንዲሆን፡፡ …..
አዎን፣ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ፡፡ …..
""""""""""""
በዋይታ ጣር
"""""""""""
ሕፃን ሆኜ የእርግብ ጫጩት፣ አንዳንዴ ራብ ሲያዳክማት
ችጋር ከጎጆዋ ገብቶ፣ እዛፍ ግርጌ ሲጥላት
እናቷ በርራ ደርሳላት
በአክናፏ ሙቀት ታቅፋት
እፍ እያለች ግንባሯ ላይ፣ ሕይወት ስትተነፍስባት
ወዲያው ነፍስ ትዘራለች
ሽር- ትር- ትር እያለች፡፡
ባክሽ አንቺም አትራቂብኝ
እመ ብርሃን እናቴ፣ ትንፋሽሽን እፍ በይብኝ
ፅናትሽን እፍ በይብኝ፣
ወይም ይቺን የሞት ጽዋ፣ ጥላዋ ነፍሴን ካፈናት
እንዳልጠጣት አሳልፊያት
መራራ ክንፏን ገንጥለሽ፣ ቀጠሮ፣ ቃልዋን ግደፊያት፤ ….
አለዚያም ጽናትሽን ስጪኝ፣ ልጠጣው ኪዳነ-ውሉን
የኔ ፍቃድ እምነትሽ ነው፣ ያንች ፍቃድ ብቻ ይሁን
እንደውሎስ እንድጸና፣ በፍርሃት እንዳልታሰር
በውስጤ ከሚታገለኝ፣ በሥጋ አውሬ እንዳልታወር
ለየዕለቱ ሞት እንዳልሰንፍ
የኪዳኔ ቃል እንዳይነጥፍ
ቃልሽ በሕሊናዬ ዲብ፣ ኃይልሽ በሕዋሴ ይረፍ
ፍርሃት ቢያረብብብኝም፣ አንቺ ካለሺኝ አልሰጋም
ኩርምትም ብዬ እችልበት፣ እሸሸግበት አይጠፋም
የግማደ መስቀሌን ጉጥ፣ እታገስበት አላጣም
አለዚያማ ብቻዬን ነኝ፣ ኢትዮጵያም ያላንች የላት
አንቺ አፅኚኝ እንድፀናላት፣
አሥርጪብኝ የእምነት ቀንጃ፣ ለሥጋቴ አጣማጅ አቻ
ለጭንቀቴ-መቀነቻ፡፡ . . .
ባክሽ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ ….
--------
,,,,,,,,,,,,,,,, /ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን/
ምንጭ፤ “ታሪካዊ ተውኔቶች” ጸጋዬ ገብረ መድኅን
አሳታሚ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ፤ 2003ዓ.ም

Comments