2 months ago
ስንጀምር የደረሰብን ተቃውሞና ትችት ፈታኝ ነበር፦ሙላቱ አስታጥቄ
አለም ለስራዎቻችን የሚገባቸውን ክብር አልሰጠም፦ ሙላቱ አስታጥቄ
#ethiopia | የኢትዮ ጃዝ አባት ሙላቱ አስታጥቄ ለአፍሪካ ባህላዊና ሀገር በቀል የጥበብ ስራዎች በአለም መድረክ ላይ ተገቢው ክብርና እውቅና አልተሰጣቸውም ሲል ተናግሯል።
የኢትዮ ጃዝ ሙዚቃ ስልት መሥራችና ባለቤት የሆነው አንጋፋው ባለብዙ መሣሪያ ተጫዋቹ ሙላቱ አስታጥቄ የአፍሪካ ሀገር በቀል የጥበብ ስራዎች እና ባህላዊ ሙዚቃዎች የሚገባቸው ዓለም አቀፋዊ እውቅና እና ክብር እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርቧል።
የኢትዮ ጃዝ የሙዚቃ አባት ሙላቱ አስታጥቄ ከ ዘጋርዲያን ጋር ባደረገው ቆይታ ስለ ኢትዮጵያና አፍሪካ ባህላዊና ሀገር በቀል የሙዚቃ ስራዎች ሰፊ ማብራርያ ሰጥቷል።
የኢትዮ ጃዝን አዲስ የሙዚቃ ስልት በ1960ዎቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ ሲያስተዋውቅ ከፍተኛ ተቃውሞና ፈታኝ ሁኔታዎች ገጥመውት እንደነበር አስታውሷል።
ሙላቱ አስታጥቄ ባለፉት ሁለት አሥርት አመታት ይህ ድንቅ ስልት በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ የተወደደና የብዙዎችን ቀልብ መሳብ መቻሉን ገልጿል።
በመሆኑም የአፍሪካን የሙዚቃ ሀብትና ባህላዊ እሴቶች ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ የቀደሙትም ሆነ የዛሬዎቹ ሀገር በቀል የጥበብ ስራዎች የሚጫወቱት ሚና ትልቅ በመሆኑ ተገቢውን ክብር ማግኘት እንዳለባቸው አሳስቧል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #ethiojazz #music #theguadian #mulatuastatke

7 months ago
🎭 የታሪካዊው "ሕዝብ ለሕዝብ" ዳግም ትንሳኤ
"ድንቅ ነሽ ኢትዮጵያ (ሉሲ)" ሊጀመር ነው!
✨
#ethiopia | ከ30 ዓመታት በላይ ተቋርጦ የነበረውና በዓለም መድረክ የኢትዮጵያ የጥበብ አምባሳደር የነበረው "ሕዝብ ለሕዝብ" የኪነ-ጥበብ ጉዞ፣ አሁን በታላላቅ የጥበብ ሰዎች መሪነት ዳግም ለዓለም ሊቀርብ ስምምነት ተፈርሟል።
ፕሮጀክቱን በኃላፊነት የሚመሩት የዘርፉ አንጋፋና ስመ-ጥሩ ባለሙያዎች ናቸው፡-
ሎሬት አያልነህ ሙላቱ፦ የድርሰቱ ባለቤት
ዶክተር ሙላቱ አስታጥቄ፦ የሙዚቃው አቀናባሪ
አርቲስት ተስፋዬ ታዬ፦ የኪነ-ጥበብ አስተባባሪ
አርቲስት ቴዎድሮስ ዘዋለ (ቴዲ ማቲ)፦ የፕሮጀክቱ ዋና አስተባባሪ (ማናጀር)
ይህ ታላቅ የጥበብ ስራ በቅርብ ወራት ተጠናቆ ለተመልካች የሚደርስ ሲሆን የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ይዟል በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች፣ በካናዳ፣ በአውስትራሊያ፣ በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይ እና በጣሊያን የሚታይ ይሆናል።
ከ55 እስከ 60 የሚደርሱ የኪነ-ጥበብ ሰዎች (አርቲስቶች) በዝግጅቱ ላይ ይሳተፋሉ።
የዝግጅቱን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ለመጨረስ ከ4 እስከ 5 ወራት የሚወስድ ሲሆን፣ ስራው በ"ጥበብ አድቨርታይዚንግ እና ኢቨንት" አማካኝነት የሚዘጋጅ ነው።
የቀድሞው "ሕዝብ ለሕዝብ" የኢትዮጵያን ባህል፣ ሙዚቃና ውዝዋዜ ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ የማይተካ ሚና ነበረው። አሁን ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት የተዘጋጀው ይህ አዲሱ ፕሮጀክት፣ የጥንታዊቷን "ሉሲ" ታሪክና የሀገራችንን ድንቅ ጥበብ ዳግም ለዓለም አደባባይ ለማውጣት አልሟል።
#ሕዝብለሕዝብ #ድንቅነሽኢትዮጵያ #ሉሲ #አያልነህሙላቱ #ሙላቱአስታጥቄ #ኢትዮጵያ #ኪነጥበብ #ethiopia #peopletopeople #lucy #mulatuastatke #art #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

9 months ago
🏰 "የአፄዎቹ ሽልማት" ለኢትዮጵያ ባለውለታዎች በፋሲል ግቢ ተበረከተ!
🏅
"በታሪካዊቷ ጎንደር የክብር ምሽት!"
#ethiopia | በታሪክ፣ በኪነ-ጥበብ፣ በስፖርት እና በሕክምና ዘርፎች ሀገራቸውን ላገለገሉ 9 ታላላቅ የኢትዮጵያ ባለውለታዎች፤ በጎንደር አብያተ-መንግሥት (ፋሲል ግቢ) "የአፄዎቹ ሽልማት" እና የክብር እውቅና ተሰጥቷል።
የክብር ተሸላሚዎች ዝርዝር፡-
1️⃣ ዶክተር ማለደ ማሩ
2️⃣ ፕሮፌሰር ዕደማርያም ጸጋ
3️⃣ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ (የታሪክ ተመራማሪ)
4️⃣ ሰዓሊ ወርቁ ማሞ
5️⃣ ዶክተር ሙላቱ አስታጥቄ (የኢትዮ-ጃዝ አባት)
6️⃣ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ (ፊልም ሰሪ)
7️⃣ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ
8️⃣ አቶ ኃብተሥላሴ ታፈሰ (የቱሪዝም አባት)
9️⃣ አቶ ካሳሁን ምስጋናው
በመርሃ-ግብሩ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበልን ጨምሮ የክልል እና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ህያው ምስክሮቻችንን በህይወት እያሉ ማክበር ትልቅነት ነው! እንኳን ደስ አላችሁ! 👏
#ጌትነት ተመስገን
#gondar #fasilghebbi #ethiopianheroes #awards #hailegebrselassie #mulatuastatke #hailegerima #history #getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

Comments