3 months ago
🎭 የታሪካዊው "ሕዝብ ለሕዝብ" ዳግም ትንሳኤ
"ድንቅ ነሽ ኢትዮጵያ (ሉሲ)" ሊጀመር ነው! 🇪🇹✨
#ethiopia | ከ30 ዓመታት በላይ ተቋርጦ የነበረውና በዓለም መድረክ የኢትዮጵያ የጥበብ አምባሳደር የነበረው "ሕዝብ ለሕዝብ" የኪነ-ጥበብ ጉዞ፣ አሁን በታላላቅ የጥበብ ሰዎች መሪነት ዳግም ለዓለም ሊቀርብ ስምምነት ተፈርሟል።
ፕሮጀክቱን በኃላፊነት የሚመሩት የዘርፉ አንጋፋና ስመ-ጥሩ ባለሙያዎች ናቸው፡-
ሎሬት አያልነህ ሙላቱ፦ የድርሰቱ ባለቤት
ዶክተር ሙላቱ አስታጥቄ፦ የሙዚቃው አቀናባሪ
አርቲስት ተስፋዬ ታዬ፦ የኪነ-ጥበብ አስተባባሪ
አርቲስት ቴዎድሮስ ዘዋለ (ቴዲ ማቲ)፦ የፕሮጀክቱ ዋና አስተባባሪ (ማናጀር)
ይህ ታላቅ የጥበብ ስራ በቅርብ ወራት ተጠናቆ ለተመልካች የሚደርስ ሲሆን የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ይዟል በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች፣ በካናዳ፣ በአውስትራሊያ፣ በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይ እና በጣሊያን የሚታይ ይሆናል።
ከ55 እስከ 60 የሚደርሱ የኪነ-ጥበብ ሰዎች (አርቲስቶች) በዝግጅቱ ላይ ይሳተፋሉ።
የዝግጅቱን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ለመጨረስ ከ4 እስከ 5 ወራት የሚወስድ ሲሆን፣ ስራው በ"ጥበብ አድቨርታይዚንግ እና ኢቨንት" አማካኝነት የሚዘጋጅ ነው።
የቀድሞው "ሕዝብ ለሕዝብ" የኢትዮጵያን ባህል፣ ሙዚቃና ውዝዋዜ ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ የማይተካ ሚና ነበረው። አሁን ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት የተዘጋጀው ይህ አዲሱ ፕሮጀክት፣ የጥንታዊቷን "ሉሲ" ታሪክና የሀገራችንን ድንቅ ጥበብ ዳግም ለዓለም አደባባይ ለማውጣት አልሟል።
#ሕዝብለሕዝብ #ድንቅነሽኢትዮጵያ #ሉሲ #አያልነህሙላቱ #ሙላቱአስታጥቄ #ኢትዮጵያ #ኪነጥበብ #ethiopia #peopletopeople #lucy #mulatuastatke #art #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን