8 months ago
🦁 "ምን እንደማስብ ታውቃላችሁ?" ሲል የክረመው አንበሳ ባንክ አዲሱን ማንነቱን ይፋ አደረገ! 🏦✨
#ethiopia | "አንበሳ ፕላስ (Anbessa Plus) የተሰኘ አዲስ የሞባይል መተግበሪያም ተመርቋል"
ለ18 ዓመታት በኢትዮጵያ ፋይናንስ ዘርፍ ሲያገለግል የቆየው አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ፤ አርማውን እና መለያ ቀለሙን በመቀየር ዘመናዊነትን የተላበሰ አዲስ የብራንድ መለያ (Rebranding) በይፋ ተግብሯል።
የለውጡ ዋና ዓላማ ምንድን ነው?
የባንኩ አመራሮች እንደገለጹት፤ ይህ ለውጥ የምስል ቅያሬ ብቻ አይደለም። ባንኩን ለዲጂታል ዘመን በሚመጥን መልኩ ለማዘመን፣ የቴክኖሎጂ አቅምን ለማሳደግ እና በኢንዱስትሪው ያለውን ተወዳዳሪነት ለማጎልበት የተደረገ ስትራቴጂካዊ ሽግግር ነው።
በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ ምን ተከናወነ?
✅ አዲስ አርማ: የባንኩን የ18 ዓመታት ጉዞ የሚገልጽ እና ለዲጂታል ባንኪንግ ምቹ የሆነ አዲስ ሎጎ ይፋ ሆኗል።
✅ አዲስ መተግበሪያ: "አንበሳ ፕላስ" የተሰኘ ዘመናዊ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ተዋውቋል።
✅ ክብር ለባለሙያ: የቀድሞውን የባንኩን አርማ ለሰሩት ሎሬት ደስታ ሐጎስ ልዩ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
ባንኩ በአሁኑ ወቅት 365 ቅርንጫፎች እና ከ44 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ያለው ሲሆን፤ ይህ አዲስ ምዕራፍ ለደንበኞች ቀልጣፋ አገልግሎት ይዞ እንደሚመጣ ተገልጿል።
#lioninternationalbank #anbessabank #rebranding #newera #anbessaplus #digitalbanking #ethiopia #getutemesgen

1 year ago
የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል ብር 5.6 ቢሊዮን ደረሰ
#ethiopia | አዲስ ባንክ አ.ማ. እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2025 ዓ.ም. በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በሁሉም ዋና ዋና የሥራ የአፈጻጸም መለኪያዎች ታሪካዊ እድገት ማስመዝገብ ቻለ።
የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል ብር 5.6 ቢሊዮን እንዲሁም የተከፈለ ካፒታል ብር 2.5 ቢሊዮን መድረስ ችሏል።
ከዚህም በላይ ባንኩ በተያዘው ሂሳብ ዓመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት ውስጥ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ አክስዮኖች መሸጥ የቻለ ሲሆን በዚህም የተከፈለ ካፒታሉን ወደ ብር 3.1 ቢሊዮን ማሳደግ ችሏል፡፡
ይህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የብር አምስት ቢሊዮን ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሟላት በትክክለኛው መንገድ ላይ እንደሚገኝ ማሳያ ነው፡፡
ባንኩ በጠንካራ የገቢ እድገትና ጥንቃቄ የተሞላበት የወጪ አጠቃቀም ከታክስ በፊት የተገኘውን ትርፍ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ397 በመቶ በማሳደግ ብር 2.9 ቢሊዮን እንዲሁም ከታክስ በኋላ የተገኘው የተጣራ ትርፍ ብር 2.2 ቢሊዮን ሆኗል።
በዚህም ባንኩ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ የአክስዮን ትርፋ ድርሻ ማለትም 92.43 በመቶ እንዲሁም 57.37 በመቶ የትርፍ ክፍፍል መስጠት ችሏል፡፡
በሌላ በኩል ባንኩ የእይታ ገጽታውን ለማዘመንና የደንበኞችን አገልግሎት ለማሻሻል የገጽታ ስም ለውጥ (rebranding) ያደረገበት ታሪካዊ ወቅት ነበር።
የዚህ ጥረት አካል የሆነው እና የባንኩን የወደፊት ማንነቱን የሚያንጸባርቁ አዲስ አርማ፣ የታደሰ መፈክር እና የሥም ማሻሻያዎችን አስተዋውቋል።

Comments