"ሶምሶማ" በቃላት ረሃብ ለከሳች፣ በሃሳብ ድርቅ ለጠወለች ነፍስ... ገጣሚና ደራሲ ሲራክ ወንድሙ በ "ሶምሶማ" አዲስ ስራው ድንቅ የጥበብ ማዕድ ከትቦ ይዞ ከች ብሏል።
ይህ መፅሐፍ በኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ ሰማይ ስር የተሰቀለ አዲስ የብርሃን ኮከብ ነው!
ይህ ስራ የዓለም አቀፍ ጠቢባንን ረቂቅነት ከሀገራችን የብዕር አርበኞች ጥልቀት ጋር ያዋሃደ "ወጥ" ጥበብ ነው፦
እንደ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንና ሐዲስ ዓለማየሁ ሲራክ የሀገሩን ጠረን፣ የማህበረሰቡን ስነ-ልቦና እና የታሪክን ፍሰት እንደ "ፍቅር እስከ መቃብር" ባለ ረቂቅ ስፌት ይዘግባል። የቃላት አጠቃቀሙ የሀገራችንን ስነ-ጽሁፍ ክብርና ሞገስ የሚመልስ "ጠጠር" ያለ ብቃት አለው።
እንደ ፓውሎ ኮይሎ (Paulo Coelho) እና ጋብርኤል ጋርሲያ ማርኬዝ በ "ሶምሶማ" ውስጥ የሰው ልጅ የውስጥ ፍለጋና የህልም ጉዞ እንደ "The Alchemist" ይተነተናል፤ ማህበራዊ እውነታው ደግሞ በማርኬዝ "Magic Realism" ስልት የታጀበ ይመስል በውበት ይፈሳል።
እንደ ሚላን ኩንደራ (Milan Kundera) እና በዓሉ ግርማ የህይወትን ፍልስፍናዊ "ክብደትና ቀላልነት" በድፍረትና በጥልቀት ይፈትሻል።
በሩጫ በናወዘው ዘመናችን ውስጥ "ዝግታን" እንደ መድሃኒት እየጋተ፣ በቃላት ውበት ውስጥ እንድንሰምጥና ቆም ብለን ራሳችንን እንድንመረምር ያደርገናል።
"ሶምሶማ" ትላንትን ከዛሬ፣ ዝምታን ከጩኸት፣ ጥልቀትን ከዝግታ ጋር አቆላልፎ የሰፋ ድንቅ የጥበብ ካባ ነው።
ለራስዎ የሚሰጡት የክብር አክሊል፣ ለወዳጅዎ ደግሞ ትርጉም ያለው የህይወት ገፀ-በረከት ነው!
ወንድማችን ሲራክ በለጋ እድሜህ በስለህ የበሰለ መፅሃፍ በሚያምረው ቃላትህና ቀለምን ከማይሰስተው ብዕርህ ቀንጭበህ ከትበህ ስላስነበብከን እድሜህን ያርዝምልንና የቀረውን እየደባበልክ ከትበህ እንድታስነብበን የዘውትር ፀሎታችን ነው።
ሙባረክ አበበ
ሚዛን አማን - ኢትዮጵያ

4 months ago