Logo
FastMereja
የኢትዮጵያ የባህል አምባሳደርና የ"እስክስታው ንጉሥ" መላኩ በላይ 50ኛ ዓመት ልደት ተከበረ
#fastmereja I የኢትዮጵያን ባህላዊ ውዝዋዜና ሙዚቃ በዓለም መድረክ ያስተዋወቀው የጥበብ ሰው ክቡር ሎሬት መላኩ በላይ፣ በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ያበረከተውን የዘለቀ አሻራ የሚዘክር የክብር መርሃ-ግብር 50ኛ ዓመት የልደቱ በዓል በማስመልከት ተካሄደ። "የእስክስታው ንጉሥ" በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው መላኩ፣ የሀገርን ባህል ከዘመናዊነት ጋር በማቀናጀትና ለወጣቱ ትውልድ የጥበብ ዕድል በመፍጠር ረገድ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ታላቅ ምስጋና ቀርቦለታል።

ይህ የ50ኛ ዓመት ልደት የምስጋና ስነ-ሥርዓት እሁድ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም በሀያት ሬጄንሲ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን
ክቡር ሎሬት መላኩ በላይ በኢትዮጵያ የጥበብ ታሪክ ውስጥ በተለይም "ኢትዮ-ከለር" የተሰኘውን የባህል ሙዚቃ ቡድን በማቋቋም፣ አንጋፋና ወጣት አርቲስቶችን በአንድ መድረክ በማገናኘት ረገድ የሚጠቀስ ስም አለው።

ከግል ስኬቱ ባለፈ፣ በካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘውን የ"ፈንድቃ" የባህል ማእከልን ከትንሽ አዝማሪ ቤትነት ወደ ዓለም አቀፍ የኪነ-ጥበብ መገኛነት በመለወጥ፣ የኢትዮጵያን ባህልና ማንነት በዓለም አቀፍ ደረጃ (እንደ TED እና Lincoln Center ባሉ መድረኮች) እንዲታወቅ አድርጓል።

ከዚህም በተጨማሪ ከታዋቂው የማካሌስተር ኮሌጅ እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የውዝዋዜ ጥበብ በምርምርና በትምህርት እንዲደገፍ የላቀ ሚና ተጫውቷል።

እ.አ.አ በ2020 በCommunity Cultural Development ዘርፍ የክብር "Prince Claus Award" ተሸላሚ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ የባህል ዘርፍ ያለውን ዓለም አቀፋዊ ተጽዕኖ ማረጋገጫ ተደርጎ ይወሰዳል።

ይህ በክብር እንግዶችና በጥበብ ወዳጆች ታጅቦ የተከናወነው የምስጋና ምሽት፣ ለሀገር ባለውለታው መላኩ በላይ የሚገባውን ክብር ለመስጠትና የጀመረውን የጥበብ ጉዞ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ያለመ መሆኑ ተነግሯል።

26 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.