እንኳን_አደረሰህ_አሉ?
#ethiopia | "የጥበብ ፈጣሪ፣ ልጁን ልኮ በሰው ልጆች ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ጥበብ ለወደቀው የፍጡራን ነፍስ ሰጣቸው፡፡ በቃላትና በግጥም ተደርገው የማይታወቁ ተአምራቶች ታዩ፡፡ በግጥም ሰዎች ከሙታን ሲነሱ፣ የታመሙ ሲፈወሱ… ነፍሳቸውን ከስጋቸው ማስጣል ያልቻሉ… ነፃ ሲወጡ ታዩ...!"
#እንኳን_አደረሰህ_አሉ ?
==============
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
_____
ቅድም ሰዎች ምን አሉኝ?
የአዲስ ዘመን ብስራት ሲነግሩኝ
መልካም ስሜት ሲገልፁልኝ
እውን ምን ነበር ቅድም ያሉኝ?
/
“እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ አደረሰህ፣
እንኳን ከዘመን ዘመን፣ ከዓመት ዓመት
አሻገረህ
የብልፅግና የሠላም፣ የደስታ የጤና
ይሁንልህ፡፡”
ነው መሰለኝ ያሉት፣ ቅድም
ባልሰማቸውም በቅጡ የልቦናዬን
ሳስታምም፡፡
/
ግን ክራሞቴን ሳስበው
መጪውን ደግሞ ሳልመው
የራሴን እዝነ-ልቦና
የነገረኝ ድምፅ ቃና
እንኳን ከሙት ዘመን፣ ሙት ዘመን
ከዘመን ሙት፣ ዘመን ሙት
ከብኩን ሕይወት፣ ብኩን ሕይወት
ከከንቱ ዓመት፣ እከንቱ ዓመት
ገፍቶ ጣለህ
አኝኮ አላምጦ ተፋህ
የሚል መሰለኝ ፊደሉ
የልቦናዬ ትርጉም ቃሉ፡፡
/
“እንኳን አደረሰን” አልኳቸው እኔም ላፌ
የተሰማኝን ደብቄ ከእውነት መፋጠጥ ሰንፌ
“አሜን” አልኩኝ ለምናልባት
ምኞት ሰምሮ ቢሆን እውነት፡፡
/
መግለጫው እንደሁ ከዓመት ዓመት፣ ከዘመን
ዘመን ያው ነው
ግን፣ እንደህይወታችን ፈርጀን፣ እንደአሳለፍነው
ስናየው
አይደል የብስራቱ መልዕክት፣ ትርጉሙ
የሚለያየው?
ዘንድሮ እንዲህ ተረዳሁት፣ የከርሞ ሰው ካለኝ
አንድዬ
ደሞ ላመት ካደረሰኝ፣ ለዚህ ብስራት ፈጣሪዬ
እንዴት እንደሚገባኝ፣ የቃሉ ትርጉም የፊደሉ
እሱ ያውቃል ዲበ-ኩሉ፡፡
/
“እንኳን አደረሰህ” አሉ፣ እኔ መች ደረስኩና
እንዲያውስ አልተንቀሳቀስኩ፣ ከቶ መች
ተላወስኩና
ሳልሄድ አልደርስ የትስ ቢሆን፣ እንኳንስ ዘመን
ይቅርና፡፡
እካችምናው ቦታው አምናው እንደተወኝ
እዚያው እንዲያው አለሁ፣ እሱ እንዳስቀመጠኝ
ለጉድ የጎለተኝ፡፡
/
እኔ ባለሁበት ስፍገመገም፣ ስረግጥ
ሲገሰግስ መጥቶ ዘመን ሲፈረጥጥ
አሁንም እንደአምናው እሱ ደረሰና
ዘመንም ታድሶ መጣና
አይችለው የለ መአት
እኔ ላይ አራግፎ ጥሎት
አለፈ ደግሞ ለመምጣት፡፡
እንጂ እኔማ መች ደረስኩ
ከቶስ መቼ ተለወጥኩ
እንዳለሁ አለሁ እንዳከኩ፡፡
/
“እንኳን ከዘመን ዘመን፣ ከዓመት ዓመት
አሻገረህ”
ተባልኩ ከንቱው እንደሰው፣ ስንፏቀቅ ከርሜ
ስድህ፡፡
እኔስ እንዳለሁ አለሁ የካቻምናዋ ሳትዛባ
አምናም አሁንም ሳትለወጥ ሳትወልቀ
የመከራ ካባ፡፡
ይልቅ ዘመን መጣና ደረሰና እየሰገረ
ሸክሙን አራግፎብኝ ንግርት እያስነገረ
እንኳን አደረሰህ ሲሉ ወደኋላ እያስቀረ
እርስ በርሳችን በእንኳን እንኳን መልሶ
እያናቆረ
አምና ካቻምና ያለንን እንደገና እየነገረ
ውድቀታችንን እያስተጋባ በየዓመቱ እየዘከረ
እሱ አይደል እንዴ አበቅቴውን ቀመሩን
የተሻገረ?!
እንጂ እኛማ እዚሁ አለን ከድልድዩ ወዲህ ማዶ
እንዳከበርን እንደገበርን ለየዓመቱ በዓል
ዘንዶ፡፡
/
ይኽን የችግር ኑሮ የእከክ የሰቆቃ ቅርስ
እኛም በተራ ሳናፍር ለትውልድ ትውልጅ
ስናወርስ
ከበፊቱ እየባሰ የዘመን ባቡር ሦስት ሺ ዓመት
ቁም ስቅላችንን እያየን ያራገፈብንን መአት
አምልጠን ልንወጣ ስንል ደሞ ባመቱ
ሲጭንብን
ቀና ማለት እያቃተን ሸክሙ መልሶ
ሲያጎብጠን
የትም ላንደርስ ሳንሻገር ከድልድዩ ወዲህ ማዶ
የአርባ ቀናችን ችካል ከእትብታችን ጋር ተዋዶ
ውሉ ጠፍቶ ተተብትቦ እንዳሰረን ነን ቀፍድዶ፡፡
/
ይልቅስ እንነሳ በጠዋት ነው የሚያምር
መንገድ
ጀምበርን አስቀድሞ ነው መናጆ አርጎ ሩቅ
መሄድ
ሸክማችንን እንጣልና ጠፍራችንን በጣጥሰን
ዘመንን ቆመን አንጠብቅ እኛም እንሂድ
ገስግሰን፡፡
ይኽን የአሳር በርሃ ይኽን የእንባ ሸለቆ
ያው ባለቤቱ ነውና ማለፍ ያለበት ሰንጥቆ
ያለ እኛ በቀር ሌላ ማንም አያሻግረን
ተጨንቆ፡፡
ያሰብንበት ስንደርስ መከራችንን ሁሉ አልፈን
ተስፋችንም ሲፈቃ ኑሯችንም ሲሰምርልን
የዚያኔ ነው እንኳን ማለት አደረሰህ አሻገረህ
ከዘመን ጋር ስንለወጥ ሕይወታችን ሲሆን
ብሩህ፡፡
# ፀጋዬ_ገ /መድህን
ምንጭ ጦቢያ መጽሔት ነሐሴ 1989
#ethiopia | "የጥበብ ፈጣሪ፣ ልጁን ልኮ በሰው ልጆች ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ጥበብ ለወደቀው የፍጡራን ነፍስ ሰጣቸው፡፡ በቃላትና በግጥም ተደርገው የማይታወቁ ተአምራቶች ታዩ፡፡ በግጥም ሰዎች ከሙታን ሲነሱ፣ የታመሙ ሲፈወሱ… ነፍሳቸውን ከስጋቸው ማስጣል ያልቻሉ… ነፃ ሲወጡ ታዩ...!"
#እንኳን_አደረሰህ_አሉ ?
==============
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
_____
ቅድም ሰዎች ምን አሉኝ?
የአዲስ ዘመን ብስራት ሲነግሩኝ
መልካም ስሜት ሲገልፁልኝ
እውን ምን ነበር ቅድም ያሉኝ?
/
“እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ አደረሰህ፣
እንኳን ከዘመን ዘመን፣ ከዓመት ዓመት
አሻገረህ
የብልፅግና የሠላም፣ የደስታ የጤና
ይሁንልህ፡፡”
ነው መሰለኝ ያሉት፣ ቅድም
ባልሰማቸውም በቅጡ የልቦናዬን
ሳስታምም፡፡
/
ግን ክራሞቴን ሳስበው
መጪውን ደግሞ ሳልመው
የራሴን እዝነ-ልቦና
የነገረኝ ድምፅ ቃና
እንኳን ከሙት ዘመን፣ ሙት ዘመን
ከዘመን ሙት፣ ዘመን ሙት
ከብኩን ሕይወት፣ ብኩን ሕይወት
ከከንቱ ዓመት፣ እከንቱ ዓመት
ገፍቶ ጣለህ
አኝኮ አላምጦ ተፋህ
የሚል መሰለኝ ፊደሉ
የልቦናዬ ትርጉም ቃሉ፡፡
/
“እንኳን አደረሰን” አልኳቸው እኔም ላፌ
የተሰማኝን ደብቄ ከእውነት መፋጠጥ ሰንፌ
“አሜን” አልኩኝ ለምናልባት
ምኞት ሰምሮ ቢሆን እውነት፡፡
/
መግለጫው እንደሁ ከዓመት ዓመት፣ ከዘመን
ዘመን ያው ነው
ግን፣ እንደህይወታችን ፈርጀን፣ እንደአሳለፍነው
ስናየው
አይደል የብስራቱ መልዕክት፣ ትርጉሙ
የሚለያየው?
ዘንድሮ እንዲህ ተረዳሁት፣ የከርሞ ሰው ካለኝ
አንድዬ
ደሞ ላመት ካደረሰኝ፣ ለዚህ ብስራት ፈጣሪዬ
እንዴት እንደሚገባኝ፣ የቃሉ ትርጉም የፊደሉ
እሱ ያውቃል ዲበ-ኩሉ፡፡
/
“እንኳን አደረሰህ” አሉ፣ እኔ መች ደረስኩና
እንዲያውስ አልተንቀሳቀስኩ፣ ከቶ መች
ተላወስኩና
ሳልሄድ አልደርስ የትስ ቢሆን፣ እንኳንስ ዘመን
ይቅርና፡፡
እካችምናው ቦታው አምናው እንደተወኝ
እዚያው እንዲያው አለሁ፣ እሱ እንዳስቀመጠኝ
ለጉድ የጎለተኝ፡፡
/
እኔ ባለሁበት ስፍገመገም፣ ስረግጥ
ሲገሰግስ መጥቶ ዘመን ሲፈረጥጥ
አሁንም እንደአምናው እሱ ደረሰና
ዘመንም ታድሶ መጣና
አይችለው የለ መአት
እኔ ላይ አራግፎ ጥሎት
አለፈ ደግሞ ለመምጣት፡፡
እንጂ እኔማ መች ደረስኩ
ከቶስ መቼ ተለወጥኩ
እንዳለሁ አለሁ እንዳከኩ፡፡
/
“እንኳን ከዘመን ዘመን፣ ከዓመት ዓመት
አሻገረህ”
ተባልኩ ከንቱው እንደሰው፣ ስንፏቀቅ ከርሜ
ስድህ፡፡
እኔስ እንዳለሁ አለሁ የካቻምናዋ ሳትዛባ
አምናም አሁንም ሳትለወጥ ሳትወልቀ
የመከራ ካባ፡፡
ይልቅ ዘመን መጣና ደረሰና እየሰገረ
ሸክሙን አራግፎብኝ ንግርት እያስነገረ
እንኳን አደረሰህ ሲሉ ወደኋላ እያስቀረ
እርስ በርሳችን በእንኳን እንኳን መልሶ
እያናቆረ
አምና ካቻምና ያለንን እንደገና እየነገረ
ውድቀታችንን እያስተጋባ በየዓመቱ እየዘከረ
እሱ አይደል እንዴ አበቅቴውን ቀመሩን
የተሻገረ?!
እንጂ እኛማ እዚሁ አለን ከድልድዩ ወዲህ ማዶ
እንዳከበርን እንደገበርን ለየዓመቱ በዓል
ዘንዶ፡፡
/
ይኽን የችግር ኑሮ የእከክ የሰቆቃ ቅርስ
እኛም በተራ ሳናፍር ለትውልድ ትውልጅ
ስናወርስ
ከበፊቱ እየባሰ የዘመን ባቡር ሦስት ሺ ዓመት
ቁም ስቅላችንን እያየን ያራገፈብንን መአት
አምልጠን ልንወጣ ስንል ደሞ ባመቱ
ሲጭንብን
ቀና ማለት እያቃተን ሸክሙ መልሶ
ሲያጎብጠን
የትም ላንደርስ ሳንሻገር ከድልድዩ ወዲህ ማዶ
የአርባ ቀናችን ችካል ከእትብታችን ጋር ተዋዶ
ውሉ ጠፍቶ ተተብትቦ እንዳሰረን ነን ቀፍድዶ፡፡
/
ይልቅስ እንነሳ በጠዋት ነው የሚያምር
መንገድ
ጀምበርን አስቀድሞ ነው መናጆ አርጎ ሩቅ
መሄድ
ሸክማችንን እንጣልና ጠፍራችንን በጣጥሰን
ዘመንን ቆመን አንጠብቅ እኛም እንሂድ
ገስግሰን፡፡
ይኽን የአሳር በርሃ ይኽን የእንባ ሸለቆ
ያው ባለቤቱ ነውና ማለፍ ያለበት ሰንጥቆ
ያለ እኛ በቀር ሌላ ማንም አያሻግረን
ተጨንቆ፡፡
ያሰብንበት ስንደርስ መከራችንን ሁሉ አልፈን
ተስፋችንም ሲፈቃ ኑሯችንም ሲሰምርልን
የዚያኔ ነው እንኳን ማለት አደረሰህ አሻገረህ
ከዘመን ጋር ስንለወጥ ሕይወታችን ሲሆን
ብሩህ፡፡
# ፀጋዬ_ገ /መድህን
ምንጭ ጦቢያ መጽሔት ነሐሴ 1989
11 months ago