10 days ago
ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ለ5 (አምስት) አንጋፋ አርቲስቶች መኖሪያ ቤታቸውን አደሰ
♦️ ለተጨማሪ 2 (ሁለት) ግለሰቦችም እንዲሁ ቤታቸው እንዲሰራላቸው ሆኗል
#ethiopia | ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ፣ ለመላው ላለፉት በርካታ ዓመታት በተለያዩ የጥበብ ዘርፎች ሀገራቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በቅንነት ሲያገለግሉ ለቆዩ 5 አንጋፋ አርቲስቶች አዲስ ያስገነባላቸውን ደረጃቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶች በዛሬው ዕለት በይፋ አስረክቧል።
አርቲስቶቹ ድምጻዊት ብርቱካን ዱባለ፣ ከ 3,000 በላይ ዜማና ግጥም የደረሰው የኔው አካሉ፣ የሙዚቃ ባለሙያና አቀናባሪ ኮማንደር ሊቀመኳስ አየለ፣ ደራሲ ግርማይ ገ/ ጻዲቅ እና ተዋናይ እና የሙዚቃ ባለሙያው ጸጋዬ ብርሃኔ ይገኙበታል፡፡
የአርቲስቶቹ ቤቶች የተገነባው የኢትዮጲያ ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በጎ አድራጎት ማህበር ለዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ነው፡፡
አንጋፋዎቹ አርቲስቶች ቀደም ሲል ለሀገር እና ለወገን ካበረከቱት አስተዋጽዖ አንጻር በማይመጥናቸው ያረጁ የጭቃ ቤቶች ይኖሩ የነበረ ሲሆን፣ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ያረጁትን የጨቃ ቤቶች ሙሉ በሙሉ በማፍረስ እና በዘመናዊ የግንባታ ዲዛይን በማስገንባት አስረክቧል፤ ቤቶቹ ለአርቲስቶቹ ምቹና የተረጋጋ ህይወት ለመምራት የሚያስችሉ ሙሉ የቤት ቁሳቁሶች ማለትም አልጋ ከፍራሽ ጋር፣ ሶፋ፣ ቲቪ ፣ ቁምሳጥን እና የኪችን ካቢኔት) እንዲሟላላቸው ተደርጓል።
ከዚህ ጎን ለጎን የግጥምና ዜማ ደራሲው የኔው አካሉ ቤት በሚፈርስበት ወቅት ግርግዳ ለሚጋሩት አቶ አብደላ ኡመር እና ወ/ሮ ሳዓዳ ናስር ለተባሉ ጎረቤቶች ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ሀላፊነቱን በመውሰድ የነሱን ሁለት ቤቶች ጎን ለጎን በመገንባት እና ዘመናዊ ሶፋ በመግዛት እንዲጠቀሙበት አስረክቧል፡፡
በተለይም ወ/ሮ ሳዳት ባለቤታቸው በሞት የተነጠቁ፣ 4 ልጆችን የሚያሳድጉ እና ልብስ በማጠብ የሚተዳደሩ በመሆኑ ድካማቸውን ለመቀነስ የልብስ ማጠቢያ ማሽንን እና ለሌሎች ጉዳዮች የሚሆን የብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ) ከዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ተበርክቶላቸዋል፡፡
ለታዋቂው የግጥምና ዜማ ደራሲ ግሩም ሀይሌ መኖሪያ ቤት እድሳት ተጠናቆ ሳለ ከግንባታ ፍቃድ እና ተያያዥ ህጋዊ ሂደቶች ጋር በገጠመው እክል ሳቢያ ዛሬ መረከብ ባይችልም፣ሂደቱ እንደተጠናቀቀ ቤቱ ወዲያውኑ ለደራሲ ግሩም ሀይሌ የሚረከብ ይሆናል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ የኮርፖሬት አፌርስ እና ኮሚኒኬሽን ማኔጀር አቶ አብርሃም ዘሪሁን እንደገለጹት፤ "ፋብሪካችን ከንግድ ስራው ጎን ለጎን ለማህበራዊ ኃላፊነት (CSR) ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል።
ፋብሪካው ከተመሰረተበት ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 26 ዓመታት ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ የትምህርት ተቋማትን በመገንባት፣ የጤና ተቋማትን በመገንባት፣ የህክምና መሳሪያዎችን በመለገስ፣ የአረጋዊያን መጠለያ በመገንባት፣ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ፈጥኖ በመድረስ፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍና በሌሎችም የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል" ብለዋል። አክለውም" የሀገር ባለ ውለታ አርቲስቶችን መደገፍና ማከበር የኩባንያው ዋና እሴት ነው " ብለዋል።
የኢትዮጲያ ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በጎ አድራጎት ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ልዑል ጌታነህ በበኩላቸው “ ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ ለኪነጥበብ ባለሙያዎች እያበረከተ ያለው በጎ አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው፡፡ ለዚህም በኢትዮጲያ ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ማህበር ስም ለማመስገን እንወዳለን” ብለዋል፡፡
ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ በ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል ላይም በተመሳሳይ ለ5 ታዋቂ አርቲስቶች ቤቶችን አድሶ ክሙሉ የቤት ቁሳቁስ ጋር ያስረከበ ሲሆን፤ አነዚህም እርቲስት ችሮታው ከልካይ፣ አርቲስት ሽመላሽ ለጋስ፣ አርቲስት ጸጋዬ ዘርፉ፣ አርቲስት ብርሃኑ በርታ እና አርቲስት ተስፋ ብርሃን ገ/ጻዲቅ ነበሩ፤
በዕለቱ በተካሄደው የቁልፍ ማስረከብ ስነ-ስርዓት ላይ አንጋፋና ወጣት አርቲስቶች፣ የዳሽን ቢራ ከፍተኛ አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የብዙሃን መገናኛ ባለሙያዎች በተገኙበት ቤቶቹ ለባለቤቶቻቸው ተረክበዋል።
ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ በቀጣይም ከህብረተሰቡ ጎን በመቆም ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣቱን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ "ጥበብን ማክበር - ታሪክን ማክበር ነው!" በሚለው መርሁ የሀገር ባለ ውለታዎችን መደገፉን እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
#dashenbeer #ethiopia #corporatesocialresponsibility #communitysupport #socialresponsibility #csr #ethiopianartists #cultureandart #givingback

2 months ago
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለመቄዶንያ ከ4.6 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አበረከተ
#ethiopia | አዲስ አበባ | ኢትዮጵያ – የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የመስሪያ ቤቱን ማኔጅመንት፣ ሰራተኞች እና ታራሚዎች በማስተባበር ለመቄዶንያ አረጋውያንና ህጻናት መረዳጃ ማህበር ከ4.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አበርክቷል።
ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በገባው ቃል መሰረት በየዓመቱ ሐምሌ 28 መቄዶንያን የመጎብኘት ልማዱን በመቀጠል፣ በዚህ ዓመትም 547 ሺህ 65 ብር ጥሬ ገንዘብ እና ከ4.1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለማህበሩ አስረክቧል።
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ዋና ኮሚሽነር የኑስ ሙሉ፣ መቄዶንያ ለሚያከናውነው ሰብዓዊ አገልግሎት በኮሚሽኑ ስም ያላቸውን አክብሮትና ምስጋና ገልጸዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የኮሚሽኑ የህክምና ልዑካን ቡድን ከ770 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና ቁሳቁሶችን በማበርከት ብቻ ሳይሆን፣ ለማህበሩ ተገልጋዮች የህክምና አገልግሎትም ሰጥቷል።
በተጨማሪም በኮሚሽኑ ስር የሚገኙ ታራሚዎች በእጃቸው ያመረቷቸውን የተለያዩ ቁሳቁሶች በስጦታ በማበርከት ከመልካም ምኞት መልዕክታቸው ጋር ለማህበሩ አስረክበዋል።
የመቄዶንያ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር ዶ/ር ቢንያም በለጠ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ የማህበሩ ተገልጋይ አረጋውያንም በተደረገላቸው ጉብኝትና ድጋፍ ያላቸውን ደስታ ገልጸዋል።
ጌጡ ተመስገን
#ethiopia #federalprisoncommission #macedonia #charitysupport #givingback #humanitarianassociation #getutemesgen #ጌጡተመስገን

7 months ago
🛑 የሰብአዊነት ጥሪን የተቀበሉት የኖርዌይ የህክምና ባለሙያዎች አዲስ አበባ ገቡ
#ethiopia | በኖርዌይ ኦስሎ ነዋሪ የሆኑት ታዋቂው የልብ ስፔሻሊስት ዶ/ር ንጉሴ ቦጋለ፣ 36 ከፍተኛ የልብ ህክምና ባለሙያዎችን ያካተተ ቡድን በመምራት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል።
ይህ የባለሙያዎች ቡድን ወደ ሀገር ቤት የመጣው በልዩ ተልዕኮ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የልብ ህክምና ለማግኘት ረጅም ቀጠሮ ተሰጥቷቸው በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን ነፃ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ነው።
📍 የጉዞው ዋና ዋና ነጥቦች፦
* ባለሙያዎች፦ በልብ ህክምና ዘርፍ የተሰማሩ 36 የኖርዌይ እና የውጭ ሀገር ደጋግ ባለሙያዎች።
* ቁሳቁስ፦ ለህክምናው የሚያስፈልጉ ዘመናዊ መድሀኒቶች እና የህክምና ቁሳቁሶችን በሙሉ በራሳቸው ይዘው መጥተዋል።
* ተቀባይ፦ ቡድኑ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በደመቀ ሁኔታ አቀባበል ተደርጎለታል።
ዶ/ር ንጉሴ ቦጋለ እና የሥራ ባልደረቦቻቸው በአካል በስደት ቢኖሩም፣ በሥራቸውና በሰብአዊነታቸው ግን ከሀገራቸውና ከወገናቸው ጋር መሆናቸውን በተግባር አሳይተዋል። እንዲህ ዓይነቱ በጎ ተግባር በጤናው ዘርፍ ያለውን ክፍተት ከመሙላቱም በላይ፣ ለሀገር ፍቅር ትልቅ ማሳያ ነው።
ለዶ/ር ንጉሴ፣ አብረዋቸው ለመጡት የህክምና ባለሙያዎች እና ይህ በጎ ተግባር እውን እንዲሆን ላገዙ አካላት በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #healthcare #humanitarianmission #drnigussiebogale #blacklionhospital #norwaytoethiopia #givingback

8 months ago
🏫 "ትምህርት ቤቴን አድሳለሁ!" — ለይርጋዓለም ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት የመልሶ ግንባታ ጥሪ! 🌳✨
#ethiopia | ይርጋዓለም ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት፤ የሀገር ዋርካ የሆኑ አንቱ የተባሉ ምሁራንን፣ ሚኒስትሮችን፣ ደራሲያንንና ጋዜጠኞችን ያፈራ የዕውቀት ማዕከል ነው።
ከታላቁ ደራሲ ደበበ ሰይፉ እስከ ስፖርት ጋዜጠኝነት ፈር ቀዳጁ ገነነ ሊብሮ፣ ከዶ/ር አብርሃም ፈለቀ እስከ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ድረስ የዚህ አንጋፋ ትምህርት ቤት ፍሬዎች ናቸው።
ለምን ጥሪ ተደረገ?
በ1963 ዓ.ም ማስተማር የጀመረውና በተፈጥሮ ውበቱ የሚታወቀው ይህ ትምህርት ቤት፤ አሁን ካለንበት ዘመን ጋር በሚመጥን መልኩ ተሻሽሎ ለአዲሱ ትውልድ ምቹ የመማሪያ ስፍራ እንዲሆን ታላቅ የመልሶ ግንባታ ዕቅድ ተይዟል።
ጥሪው ለማን ነው?
🎓 በዚህ ትምህርት ቤት የተማራችሁ የቀድሞ ተማሪዎች (Alumni)
👨🏫 ያስተማራችሁና የምታስተምሩ መምህራን
💰 የይርጋዓለም ተወላጅ የሆናችሁ ባለሀብቶችና ወጣቶች
🌍 በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትኖሩ የይርጋዓለም ወዳጆች በሙሉ
የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጅነር እምባቆም ዼጥሮስ እና የዞኑ አስተዳደር ባቀረቡት ጥሪ መሠረት፤ ትምህርት ቤቱን በቋሚነት ራሱን እንዲያስተዳድርና ዘመናዊ እንዲሆን በምናደርገው የገቢ ማሰባሰቢያ ንቁ ተሳትፎ እንድታደርጉ ተጋብዘዋል።
ትናንት የዕውቀት ብርሃን የፈነጠቀልንን ቤት፣ ዛሬ ተረክበን እናድሰው!
መላኩ ይርጋለም
#yirgalemsecondaryschool #educationethiopia #schoolrenovation #yirgalem #sidama #givingback #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

👏 የዓለም ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ በ60 ሚሊዮን ብር ታሪክ ሰሩ! 
#ethiopia | "ሀገሩ ሳይኖራት አስተምራው፤ እውቀቱን ለምዕራቡ ዓለም የሚገብር ትውልድ በሞላበት... የመጣበትን ዞሮ ያየ ወርቅ ሰው!"
በግብርና ሳይንስ ምርምር ዓለምን ያደነቁት ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ፤ አሁን ደግሞ በትውልድ ቀያቸው የማይረሳ የታሪክ አሻራ አሳርፈዋል።
ስለ ፕሮጀክቱ አስደናቂ እውነታዎች፡
📍 ቦታ:
በትውልድ ቦታቸው ኦሎንኮሚ (ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ ሆለታ እና ጊንጪ መካከል)።
💰 ወጪ:
ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ።
🏫 ስያሜ:
ለዚህ ክብር ያበቋቸውን ውድ እናታቸውን ለመዘከር "ሞቱ አያኖ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት" ሲሉ ሰይመውታል።
ፀሐፊ፣ ተመራማሪ እና የዓለም ሎሬት የሆኑት ፕሮፌሰሩ፤ እውቀታቸው ለዓለም ቢተርፍም ልባቸው ግን ሀገራቸው እና ወገናቸው ጋር መሆኑን በተግባር አስመስክረዋል። የነገ ሀገር ተረካቢዎች የሚፈሩበትን የዕውቀት ማዕከል ለትውልድ አበርክተዋል።
ክብር እና ምስጋና ለፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ!
ፈጣሪ እድሜ እና ጤና ይስጥዎ! 🙏❤️
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#profgebisaejeta #rolemodel #ethiopia #olonkomi #motuayanoschool #education #givingback #hero

Sponsored by
Surafel
9 months ago
የፍቅር እና የቤተሰብ ምሽት፦ "ስለ እናት" ልዩ የፊልም ምሽት አዘጋጅቷል
#ethiopia | "የተሻለ የልጅነት ጊዜ ለሁሉም ሕፃናት!" በሚል መሪ ቃል የሚንቀሳቀሰው ስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ የፊታችን ቅዳሜ ለየት ያለና ትርጉም ያለው የቤተሰብ የፊልም ምሽት ሊያካሂድ ነው።
📅 የመርሃ ግብሩ ዝርዝር፦
ቀን፦ ቅዳሜ ታኅሣሥ 25 ቀን 2018 ዓ.ም
ሰዓት፦ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ
ቦታ፦ ሳርቤት በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ
❤️ የፍቅር እና የአጋርነት ምሽት
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ያሬድ አብዱ እንደገለጹት፣ ይህ ምሽት ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ይዘው በመምጣት ፊልም ከማየት ባለፈ፦
ድርጅቱ ድጋፍ ከሚያደርግላቸው ሕፃናት ጋር የፍቅር ጊዜ የሚያሳልፉበት፣
ለሕፃናቱ አጋርነታቸውን በተግባር የሚያሳዩበት፣
ቃል ኪዳናቸውን የሚያድሱበት "አይረሴ ምሽት" ይሆናል።
🌟 ስለ "ስለ እናት" በጎ አድራጎት ድርጅት
ላለፉት 24 ዓመታት በሥራ ላይ የቆየው ድርጅቱ፤ ወላጆቻቸውን ያጡ፣ ተጥለው የተገኙና በከፋ ድህነት ውስጥ ያሉ ሕፃናትን በመርዳት የሚታወቅ ሲሆን፦
እስካሁን በአዲስ አበባና በሻሸመኔ ከ 11 ሺህ በላይ ሕፃናትንና እናቶችን መታደግ ችሏል።
በአሁኑ ወቅት 1 ሺህ 700 ለሚሆኑ ሕፃናትና ሴቶች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
📞 እንዴት መሳተፍ ይቻላል?
በዚህ በጎ ተግባር ላይ በመታደም ለሕፃናቱ ክንፍ ለመሆንና የደስታቸው ተካፋይ ለመሆን በሚከተሉት ስልኮች በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፦
📱 0901 66 88 22
0921 93 93 93
0940 65 65 65
#sileenat #charityevent #familymovienight #ethiopia #addisababa #childsupport #volunteerethiopia #givingback #familytime

Comments