2 months ago
ጥቂት ስለ ግጥምና ገጣምያን!
ደረጀ በላይነህ
ገጣሚና ሐያሲ
#ethiopia | ግጥም እንደ ቋንቋ ጥንታዊና ሁለንታዊና መግባቢያ ስለሆነ፣ጥንታውያኑ ተጠቅመውበታል፤ዘመናውያኑ ደግሞ ኮትኩተውታል ይላሉ-ፕሮፌሰር ሎረነስ ፐሪኔ።
ግጥም ከሥነ ጽሑፍ ዘውጎች ተወዳጅና አክሊል የሚባለውም እንደ ጥንቅሽ እየተላጠ ተበልቶ ትዝታው ስለማይጠፋ፣የዋሽንቱ ዜማ ከልብ ስለማይገሠሥ ነው።
ዜማዊነቱ ለአይረሴነቱ ሰበብ ሲሆን፣ እምቅነቱ፣ምናባዊነቱ፣ተውኔታዊነት፣ቁጥብነት ወዘተ መለያ ባህርያቱ ናቸው።
ሌላው ብርቅ ከሚያሰኙት አንዱ ደግሞ አተያዩና ፍካሬው ነው። እንደ አልማዝ የተለያዩ ነጸብራቆች ስላሉት የዚያ ብርቅርቅታና ቀለም የገጣሚውን ምናብ ይለካዋል።
ግጥም ይፈላሰፋል፤ግን ፍልስፍና አይደለም። ገጠመኝን አሳምሮ፣በምናብ ወልውሎ ያመጣል እንጂ!
Its primary concern is not with beauty,not philosophical truth,not eith percuation,but with experience. ይላሉ።
ፊትን በመስታወት እንደማየት ይመስላል፤ ጥሬ ምስል አይደለም። ብዙ ቀለም በርካታ ቅርጾች አሉት። ምናልባትም በተሰባበረ መስተዋት እንደማየት ሊሆን ይችላል።.
በቅርጹም ወይ ተራኪ፣ተውኔታዊ፣አሊያም ሌሪክ ይሆንና እንደገና በየፈርጁ ይሸነሸናል።...በተለይ ስሜት ንክር፣ሙዚቃዊ የሆነው ሌሪክ የስሜት ዳንሶች ይዞ በሙሾ ሊያላዝን፣በፍቅር እስክስታ ሊመታ፣በትዝታ ቆርፍዶ እንባው በረዶ ሊሆን ይችላል።...እንጉርጉሮ ቢሆን፣ ጸሎትና ምሕላ፣ሽለላና ቀረርቶም እንደዚሁ።
ቃላት ለግጥም አንዱ መታበያው፣የቁመናው ጌጥ፣የመጋረጃው ዘርፍ ነው።...በተለይ ዘይቤያዊ ቃላት ደመና ላይ ሰቅለው ቼ! በለው የሚሉበት የከፍታው ጉልላት ነው።
ቃላቱንም እማሬያዊና ፍካሬያዊ ብለን ብንለያቸው፣በአብዛኛው ከዘወትራዊው ይልቅ በተምሳሌታዊና አምሳያዊ ትዕምርቶች በወደድነው ሥፍራ ብንዶላቸው ጣማቸው ይጨምራል።
ወይም ስሜት የነሸጠውን ያየንበት ትዝብት ውል ሲልብን፣እንደ መንግሥቱ ለማ፦
በጠራ ጨረቃ በእኩለ ሌሊት
ዓይኖቿ እያበሩ እንደክዋክብት
"ሳማት ሳማት"አሉት"ዕቀፍ ዕቀፋት"
አላወላወለም፤ወጣቱ ታዘዘ፤
ወገቧን አንገቷን፤በእጅና እጁ ያዘ፤
ከንፈሩ በረአድ ወዳፏ ተጠጋ።
-ምንም እንኳ ጡቷ እንደሾህ ቢዋጋ
ጣቷ በመሆኑ የበረዶ አለንጋ፤
ጆሮግንዱን ሰማው በጥፊ ሲናጋ።
በጠራው ጨረቃ በእኩለ ሌሊት
ዋ ጀማሪ መሆን ፤ዋ ተማሪነት፣
ዋ ትዕዛዝ መፈጸም፣ዋ ምክር መስማት።
እንግዲህ ተራኪው ግጥም እንዲህ ያለ መልዕክት፣ሲያስላልፍ ሥዕሉ ደምቋል። ጣቶቿ አለንጋ፤ጡቶቿ ሹል፣ሲል የልጅቷ ዕድሜ ከውስጥ ፤ቁመናው ከላይ ይታዩናል። ከዚህም አልፎ ደግሞ የምንበረብረው ሳጥን አለ። ከንፈሩ ለምን ቀዘቀዘ?...ፈርቷል። የፈራው ለምንድነው?...ልጅቷ እንዳትቆጣ!...ያኔ በዘመኑ ዐውድ ልጃገረ በእጅ መንካት ሽጉጥ ያስመዝዛል። ግን ተማሪ ጓደኞቹ አሳሳቱትና ጥፊ ቀመሰ።ቅምሻ ብቻ አይደለም ተናጋ። ሲናጋ ድምፅ አለው።
እዚህ ጋ ምሰላ ይመጣል- ድምፅ፣እላይ አጎጠጎጤ- ምስል፤ዐይኖችዋ መጉላት-ዕይታ።
ግጥም እንዲህና እንዲያ ነው። ሙዚቃው ያግባባል፤ሐሳቡ ሆድ ይገባል።
ግጥም የየዘመኑን ዳና ያስቀራል ስንል፥ ፖለቲካው፣ሥነ ልቦናው፣ፍልስፍናው ባሕሉ ወዘተ ቀለሙ ውስጥ ታትሞ ይኖራል። የረሃብ ይሆን ጥጋብ፤የጸብ ይሁን ፍቅር የትውልዱን ትዝብት፣ የነውጡን ንፋስ ፈትል ሰማይ ላይ ረጭቶ፣ የትካዜው ፉጨት፣የሳቁን ዜማ፣የትዝታውን ጥላ፤ ሻካራና እሾሁን፣ ሕመምና ጥዝጣዜውን፣ሳቅና ፍካቱን፣...
የአማርኛ ግጥሞች ዕድሜ ብዙ ሩቅ አይደለም።በዚያ ላይ አዳዲስ ፈርጆችን ይዞ አላስደነቀም። ከፖለቲካው ሥርዐትና ርዕዮት ጋር የቀየረው ቅርጽ የለም።ርዕዮቶችን በአንቀልባ እያዘሉ ከማውረድ የተለየ ሚናም አልነበረው። እንደ ፈረንጆቹ፣ወይም እንደላቲኖቹ፣ካልሆነም እንደመካከለኛ ምሥራቋ እሰራኤል የቤት ዐመታት ላይ የመጣው ለውጥ አልተመዘገበም።
ዘውጉን ሳይለቅ የቁመና ለውጥ ያመጣው ባለፉት አርባ ዐመታት ይመስለኛል። ያም ከፖለቲካዊና አገዛዛዊ ሸምቀቆ ጋር ተያይዞ የመጣ መጉበጥ ይመስላል።
አጫጭር ግጥሞች መብዛታቸውም፣የመታከት፣ብዙ ለመተንተን ሰሚ በማጣት የተፈጠረ መሰልቸት ይመስላል፤ዝም ብሎ ለመተንፈስ ብቻ። ቢጨንቀውና ሰሚ ቢያጣ መሬት ቆፍሮ ለመሬት እንዳወራው ሰው ዓይነት።
በዚሁ ተመሳሳይ ዘመን ሌላም ነገር ታይቷል። በግጥሙ መዝጊያ ላይ አንድ መገረሚያ ማምጣት። ትንሽ ቆይቶም፣
የአዳራሽ ግጥሞች በሙዚቃ እየታጀቡ መቅረብ መጀመራቸው ዘለግ ያሉና መድረክ ላይ የሚያቆዩትን አመጣ። እነዚህ የተንዛዙ ግጥሞችን ወደ ኅትመት ሰፈር ሲመጡ ዘልዛላ ሆኑ።
የመጀመሪያ መጻሕፍታቸው ያማሩላቸው ገጣምያን ሳይቀሩ ግጥሞቻቸው ለዛቸውንና እምቅነታቸውን ነጠቋቸው።
ከዚህ ዘመን ገጣምያን አንዷ ሜሮን ጌትነት ነበረች። ሜሮን ነገሮችን የምታይበትና የምትፈትልበት መንገድ ግሩም ነው። "ዙረት" በሚለው የግጥም መጽሐፏ አንገት በሚያስነቀንቁ፣ልብ በሚንጡ ግጥሞቿ አስመሰከረች።
መድረኮች ላይ ስትወጣ ግን፣እንደነምሥራቅ፣እንደነ ዶክተር በድሉ፣አረዘመቻቸው። ከነርዝመቱ ለዛውን ጠብቆ የሚሄደው አሳየኸኝ ረጋሳ ይመስለኛል። ትዕግሥት ማሞም አንዳች የማይረግብ ገሞራ አላት።
በግጥም ኅትመት ዓለም ብዙዎቹ የመጀመሪያ መጽሐፋቸውና ቀጣዮቹ እኩል አይደምቁም። ስስነትና እርግበት ይታይባቸዋል። በዚህ ፈተና ያልወደቀው ጋዜጠኛ ዲበኩሉ ጌታ ነው፤የእነ ደበበ ሰይፉን ደጅ እያንኳኳ ይመስላል።እነ አበረ አያሌው ገና አልተፈተኑም። ትዕግሥት ዓለምነህም ወደፊት በመጀመሪያ ግጥሟ ልክ ከመጣች፣ተዐምር ነው።ቋንቋ፣አተያይዋና Allusion አጠቃቀሟ ድንቅ ነው።
ወደ ሜሮን አዲሱ መጽሐፍ ልምጣ ። ስሜት የሚያሞቁት ከበሮ ድብደባዎች፣በቀጭን የሚመጡት ሳቆቿ ፣አንገት የሚያወዛውዙት ግርምቶች፣በአጫጭር ግጥሞቿ የምታደርጋቸው ተዐምራት የቀነሱ ይመስላል።
ቆንጆ ግጥሞች አሏት?...አዎ። ግን እንደድሮ አይደሉም። አዳዲስ ውበቶችና የቃላት ውበት ጨምራለች።
ግጥሞቿ፣ይስበኩን አይባልም። poetry does not teach:but it inspires.ይላሉ የዘርፉ ሰዎች።...ለነገሩ በዚህ የሚያምኑት ሊቃውንት በርካታ ናቸው።
እስቲ ከሜሮን ልምዘዝ፦
መተላለፍ 2
ሐቀኛ ነጋዴ በአመድ ገበያ ላይ ዱቄት ይዟል ማልዶ፣
የታይታ ሀብታም ሰው በሥጋ ወረፋ ይሰለፋል ማዶ።
ዘመን ሰውነትን ሸቀጥ አርጎ አውጥቶ ዐየን እንደዋዛ፣
የወረቀት ገንዘብ ወርቅ ሕልም እየገዛ።
ይህ ግጥሟ ሐሳቡ ብቻ ሳይሆን የቤት መምቻው ድምፅ ደማቅ ነው። ይህን ያደረጉት አናባቢዎቿ ናቸው። ሐሳቡም ግዙፍና የነፋሱን ዘመን በእፍኝ የሰፈረ ነው። ወርቅ ሕልም ፣በወረቀት እየሸጠ፤ዕንቁ በእሪያዎች ፊት እየተጣለ።
ልበ...
የአንተም ልብ ድንጋይ...
የእኔም ልብ ድንጋይ...
(ለዚያ ነው መሰለኝ)
በተጋጨን ቁጥር በፍቅር የምንጋይ።
ግጥም ሙዚቃ፣ ሥዕልም የተካተቱበት የሥነ ጽሑፍ ዘውግ ሰለሆነ፣ነፍስ ያፍነከንካል ፤ትርዒት ያሳያል።
ጋሽ ጸጋዬ በዘይቤዎቹ መዐዛ፣ በምሰላዎቹ ምትሐት ቀልብ ሲስብ፣ ገብረክርስቶስ በሜሎዲዎቹ ብብት ይኮረኩራል። ደበበ ሐሳብ እንደሽንኩርት እየላጠ ያስደምማል። ሁሉም በየራሳቸው ድንኳን የሚሰጡን ጣ'ም አለ።
ላምቦርን("ዶ/ር)ስለዚህ ሲጽፉ፦ Since every one likes pictures and most find pleasure in music,the common indifference to poetry must be due to a failure to realize that poetry is really both.

5 months ago
ይቻላል" ምሽት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ የክብር እንግዳ ይሆናል
#ethiopia | የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል 48ኛውን የኪነጥበብ ምሽት ረቡዕ መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም. በልዩ ዝግጅት ሊያከናውን ነው።
ማዕከሉ ከዚህ ቀደም የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ብቻ ሲጋብዝ የቆየ ቢሆንም፣ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ግን አገራቸውን በተለያዩ ዘርፎች ያገለገሉ ስመጥር ባለውለታዎችንም እንግዳ ማድረግ ይጀምራል።
የብሔራዊ ኩራት ምልክት የሆነውና "ይቻላል" በሚለው መሪ ቃሉ የሚታወቀው ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በመካከላችን በመገኘት ሙያዊ ልምዱን ያካፍላል።
በዕለቱ ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ለታዳሚዎች ተሰናድቶ ይጠብቃል።
ረቡዕ መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 11:30 ጀምሮ በባህል ማዕከል አዳራሽ ይካሄዳል።
ለመግቢያ፦ የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የሥነ-ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያችሁ በ5ተኛ በር በኩል መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ምሽት ከጥበብ ባለፈ ከአገራዊ ባለውለታዎች ልምድ የሚቀሰምበት ታላቅ መድረክ በመሆኑ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
#getu #ethiopia #addisababauniversity #culturalcenter #artnight #hailegebrselassie #literature #poetry #music #አዲስአበባዩኒቨርሲቲ #የባህልማዕከል #ኪነጥበብ #ኃይሌገብረሥላሴ #ይቻላል #ጌጡተመስገን #getutemesgen

🎭 "ምጥቀት በቅኔ አክናፍ"
የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን 20ኛ ዓመት መታሰቢያ በደመቀ ሁኔታ ተከበረ! 🖋️📜
#ethiopia | የኢትዮጵያ የሥነ-ጥበብ ቁንጮ፣ የቃላት ጠቢቡ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ 20 ዓመታት ተቆጠሩ።
ይህንን ታላቅ የጥበብ ሰው ለማሰብ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ሥላሴ የሥነ-ጥበባት ማዕከል ያዘጋጀው መርሃ-ግብር በታዋቂ ከያንያንና ምሁራን ታጅቦ ተከናውኗል።
✨ ከመርሃ-ግብሩ ዋና ዋና ነጥቦች
📚 ጥልቅ ዳሰሳ፦ አቶ ነብዩ ባዬ የጸጋዬን የቴአትር ድርሰቶች፣ መምህር ወንድወሰን አዳነ የሥነ-ግጥም ሥራዎቹን እንዲሁም አቶ ቴዎድሮስ አጥላው በፋሲል ይትባረክ የተጻፈውን “ምጥቀት በቅኔ አክናፍ” መጽሐፍ ላይ ትንታኔ አቅርበዋል።
🎙️ የከያንያን ድምፅ፦ አንጋፋዎቹ ከያንያን አበበ ባልቻ እና ተፈሪ ዓለሙ የሎሬቱን ነባርና እስካሁን ያልታተሙ ግጥሞች በድንቅ ንባብ አቅርበው ታዳሚውን ወደ ጸጋዬ የቃላት ዓለም ወስደውታል።
🎁 አዲስ የምስራች፦ የሎሬት ጸጋዬ ያልታተሙ ግጥሞች በመጪው ነሐሴ 2018 ዓ.ም ለሚከበረው 90ኛ ዓመት የልደት መታሰቢያው ታትመው ለንባብ እንደሚበቁ ተገልጿል።
📅 የፊታችን ቅዳሜ ግብዣ (የካቲት 21/2018)፦
ጥበብ አያልቅባትም! የፊታችን ቅዳሜ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በዶ/ር ኢንጂኒየር ብርሃኑ ግዛው “ወርቃማው የፔዞ ቡሩሌያዊው በገና” የተሰኘ የምርምር እና የበገና ደርዳሪዎች ዝግጅት ስለሚቀርብ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
"ጸጋዬን በምን ያስታውሱታል?"
የሎሬቱ የትኛው ስራ (ግጥም ወይስ ቴአትር) በልብዎ ታትሞ ቀርቷል? ለጥበብ ሰው ያለዎትን ክብር በኮሜንት ይግለጹ። 👇
#tsegayegebremedhin #ethiopianliterature #poetry #art #ethiopia #memorial #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

6 months ago
🛑 የማይቀርበት ታሪካዊ ምሽት! 🇪🇹✊
"ዝክረ አድዋ ኢትዮጵያዊነት" - የጥቁር ህዝቦች የአሸናፊነት ምልክት!
በአብርሃም ግዛው ኢንተርቴይመንት የተዘጋጀው እና የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የሚታደስበት ልዩ የኪነ-ጥበብ ምሽት፤ አርብ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይቀርባል።
በዕለቱ የክብር እንግዶች እነማን ናቸው?
ውድ የሀገራችን እንቁዎች በአንድ መድረክ ይገናኛሉ፡-
🎙 አያልነህ ሙላቱ (ደራሲ፣ ገጣሚ እና ባለ ቅኔ)
🎙 አምባሣደር ዲና ሙፍቲ
🎙 ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ
🎙 ኡስታዝ አቡበከር አህመድ
🎙 መምህር ዲያቆን ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል
🎙 ጥበቡ በለጠ (ጋዜጠኛና ደራሲ)
🎙 አርቲስት ሙላለም ታደሠ
🎙 አርቲስት ሱራፌል ተካ
ምን ይጠብቁ?
✅ የምሁራን ጥናታዊ ፅሁፍ እና ዲስኩር
✅ ልብ የሚነካ የግጥም ምሽት እና ስታንዳፕ ኮሜዲ
✅ የጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ሽለላ እና ፉከራ (በባህል ባንድ ታጅቦ)
✅ ሰርፕራይዝ እንግዶች እና ሌሎችም...
መቼ?
አርብ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም
(ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ)
የት?
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር
🎟 ቲኬት:
መደበኛ 300 ብር | VIP 500 ብር
(በቴሌ ብር፣ በጃዕፋር መፅሐፍት እና በ2000 ሐበሻ ይሸጣል)
ኑ!
አድዋን እየዘከርን ኢትዮጵያዊነትን እናድምቅ!
#adwavictory #ethiopia #zikreadwa #nationaltheater #history #art #poetry #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

7 months ago
🎭 "ፍንጭቷ ምሽት" ከሳካው ንጉሥ ጋር! 🌟
#ethiopia | በአሁኑ ሰዓት የ41ኛው የባህል ማዕከል የኪነ-ጥበብ ምሽት በአንጋፋው ድምጻዊ ፀሐዬ ዮሐንስ የክብር እንግዳነት በድምቀት እየተካሄደ ነው!
ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመን (Golden Era) ከሚባለው ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ በልዩ ጉልበት እና ተወዳጅነት የዘለቀ አንጋፋ የሙዚቃ ንጉሥ ነው።
ስለ እሱ ማወቅ ያለብዎት ዋና ዋና ነጥቦች እነሆ፡-
1. የሙዚቃ ስልቱ እና መለያው
የ"ሳካ" ንጉሥ፡ ፀሐዬ ዮሐንስ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ "ሳካ" (Saka) የተሰኘውን የሙዚቃ ስልት (Rhythm) በማስተዋወቅ እና በስፋት በመጠቀም ይታወቃል። ዘፈኖቹ አድማጭን የማነቃነቅ እና የመደነስ ጉልበት አላቸው።
ልዩ የድምፅ ቀለም: ድምፁ በተፈጥሮው ኃይለኛ እና ልዩ የሆነ የድምፅ ርግብግብ (Vibrato) ያለው ሲሆን፤ ይህም ከሌሎች ድምጻውያን ይለየዋል።
የመድረክ እንቅስቃሴ: በመድረክ ላይ በሚያሳየው ጉልበታማ (Energetic) እንቅስቃሴ እና ልዩ አለባበስ ይታወቃል።
2. የማይረሱ ሥራዎቹ
ፀሐዬ ዮሐንስ በርካታ ተወዳጅ ዘፈኖች ያሉት ሲሆን ጥቂቶቹ፡-
"የበረሃ ሎሚ" (እጅግ ተወዳጅ ስራው)
"ሳካ"
"እምቢ አልልም"
"ወይ አዲስ አበባ"
"ትዝታ" (በራሱ ስልት የተጫወተው)
"አይዞሽ ሀገሬ"
3. የህይወት ጉዞው
ፀሐዬ በወጣትነቱ ወደ ሙዚቃ ዓለም የገባ ሲሆን፣ በቀድሞ ጊዜ በተለያዩ የሙዚቃ ባንዶች (ለምሳሌ በብሔራዊ ቲያትር እና በሌሎችም) ውስጥ አገልግሏል።
ለረጅም ዓመታት በውጭ ሀገር (በተለይም በአሜሪካ) የኖረ ሲሆን፣ በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ በሙዚቃው ዘርፍ በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል።
4. አሁን ያለው ሁኔታ
ፀሐዬ ዮሐንስ በልዩ ልዩ መድረኮች ላይ በመገኘት ልምዱን እያካፈለ ያለ የጥበብ አባት ነው።
በአጠቃላይ ፀሐዬ ዮሐንስ ባህላዊ የኢትዮጵያን ዜማ ከዘመናዊ የሙዚቃ ቅንብር (Funk/Soul elements) ጋር በማዋሃድ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ ድምጻውያን አንዱ ነው።
"የበረሃ ሎሚ"፣ "ሳካ" እና ሌሎችም ዘመን አይሽሬ ስራዎች ባለቤት የሆነው ፀሐዬ ዮሐንስ፤ በዚህ ልዩ ምሽት ተገኝቶ የሙያ ልምዱን ለታዳሚው እያካፈለ ይገኛል።
ምሽቱ በምን አሸብርቋል?
📜 ልብ የሚነኩ ግጥሞች
🗣 ማራኪ ወጎች እና ሞኖሎጎች
🎶 ጣፋጭ ሙዚቃዎች
ጥበብ ከልምድ ጋር የተዋሃደበት ልዩ ምሽት!
Photographer Rix / ረታ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#finchitwa #artnight #tsehayeyohannes #legend #ethiopianmusic #culture #addisababa #poetry

🏰 "ጎንደር ሁሌም ታምራለች -- በጥር ደግሞ ትሞሸራለች!"
ደረሰ!
#ethiopia | ለጥምቀት ወደ ጎንደር ለምትመጡ እና በከተማዋ ለምትገኙ የጥበብ ወዳጆች ልዩ የምሽት ጥሪ!
"እናት ዓለም ጎንደር -- ጥርን ካንቺ ልደር!" በሚል ርዕስ፤ ተወዳጁ ግጥም ከመሰንቆ ቅኝት ጋር ተዋህዶ የሚቀርብበት ልዩ መርሐግብር ተዘጋጅቷል።
ታሪክ፣ ጥበብ እና ባህል በውቢቷ ጎንደር ሰማይ ስር ይተሳሰረሉ።
📅 ቀን፡ ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም
⌚ ሰዓት፡ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ
📍 ቦታ፡ በታላቁ ቴዎድሮስ አደባባይ
ኑ! ጥርን በጎንደር በልዩ ድምቀት እናሳልፍ!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#gondar #tir #timket #poetry #masinko #ethiopianculture #tewodrossquare #art

📢 የምሥራች ከወደ ምሥራቅ ኢትዮጵያ!
* የመምህር መክብብ ዐሥራት (የሐረሩ) "ጌርሳም" የግጥም መጽሐፍ ሊታተም ነው 📚
#ethiopia | የአንጋፋው የሐረር ራስ መኮንን ት/ቤት ሚኒ ሚዲያ ዓርማ፣ የብዙዎቻችን የሞያ አባት እና መካሪ፣ በ"ንስር ዓይን" የሬዲዮ ዝግጅቶቹ የምናውቀው መምህር መክብብ ዐሥራት፤ ከ30 ዓመታት በላይ ያካበተውን የሥነ-ጽሑፍ ልምድ "ጌርሳም" በተሰኘ የግጥም መጽሐፍ ከትቦ ይዞልን መጥቷል።
በዶ/ር እንዳለጌታ ከበደ፣ በገጣሚ አበባው መላኩ እና በመምህር ገዛኸኝ ፀጋው (ዶ/ር) የተገመገመ ድንቅ ሥራ ነው!
ስለ መጽሐፉ ሊቃውንት ምን አሉ?
"ጌርሳም መክብቤን መመልከቻ አንዷ መነጽራችን ናት፡፡ ገጣሚው በልቡ ውስጥ የታተመውን አሻራ ነው ያስጎበኘን፡፡ አሻራዎቹ ደግሞ አገር ወዳድነቱን፣ ቀናኢ ስሜቱን፣ ማኅበራዊ ሃያሲነቱን አምነን እንድንቀበል የሚያስገድዱ ናቸው፡፡"
— ዶ/ር እንዳለጌታ ከበደ (ደራሲ)
"በግጥሞቹ ሕይወትን፣ አካባቢን፣ ሰውነትን ሞግቷል፡፡ በጥሩ የአገጣጠም ስልት ባልጠነነ የቋንቋ ለዛ አስውቦ የሰደራቸውን ስንኞች እነሆ ብሎናል።"
— ገጣሚ አበባው መላኩ
💰 የመጽሐፉ ዋጋ: 400 ብር
በኦንላይን ለሚገዙ ዋጋ 350 ብር ነው
🏦 ገቢ የሚደረግበት ሂሳብ ቁጥር:
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000302286489
ስም: Tsedey Melaku Tesfaye
(ፀደይ መላኩ ተስፋዬ)
⚠️ ማሳሰቢያ:
ገቢ ሲያደርጉ ደረሰኙን እና የመጽሐፍ ተረካቢውን ስልክ በቴሌግራም/ሜሴንጀር ለ +251-915-740291 መላክዎን አይርሱ።
መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ #ሼር ያድርጉት!
ለበለጠ መረጃ (አስተባባሪ): 0915 46 46 46 (ታሪኩ ለሜሳ)
ወዳጆች ሆይ፤ እንረባረብ!
ለጋሽ መክብብ ያለንን ክብርና ፍቅር ለመግለጽ፤ መጽሐፉን አስቀድመን በመግዛት ድጋፋችንን እናሳይ።
#gersam #mekbibasrat #harar #poetry #newbook #ethiopianliterature

Sponsored by
Surafel
Comments