Logo
Getu Temesgen
👏 የዓለም ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ በ60 ሚሊዮን ብር ታሪክ ሰሩ! 🇪🇹
#ethiopia | ​"ሀገሩ ሳይኖራት አስተምራው፤ እውቀቱን ለምዕራቡ ዓለም የሚገብር ትውልድ በሞላበት... የመጣበትን ዞሮ ያየ ወርቅ ሰው!"

​በግብርና ሳይንስ ምርምር ዓለምን ያደነቁት ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ፤ አሁን ደግሞ በትውልድ ቀያቸው የማይረሳ የታሪክ አሻራ አሳርፈዋል።

​ስለ ፕሮጀክቱ አስደናቂ እውነታዎች፡
📍 ቦታ:
በትውልድ ቦታቸው ኦሎንኮሚ (ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ ሆለታ እና ጊንጪ መካከል)።

💰 ወጪ:
ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ።

🏫 ስያሜ:
ለዚህ ክብር ያበቋቸውን ውድ እናታቸውን ለመዘከር "ሞቱ አያኖ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት" ሲሉ ሰይመውታል።

​ፀሐፊ፣ ተመራማሪ እና የዓለም ሎሬት የሆኑት ፕሮፌሰሩ፤ እውቀታቸው ለዓለም ቢተርፍም ልባቸው ግን ሀገራቸው እና ወገናቸው ጋር መሆኑን በተግባር አስመስክረዋል። የነገ ሀገር ተረካቢዎች የሚፈሩበትን የዕውቀት ማዕከል ለትውልድ አበርክተዋል።

​ክብር እና ምስጋና ለፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ!
ፈጣሪ እድሜ እና ጤና ይስጥዎ! 🙏❤️

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

​#profgebisaejeta #rolemodel #ethiopia #olonkomi #motuayanoschool #education #givingback #hero

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.