2 days ago
“ኢትዮጵያውያን ዛሬም በአንድነት በመትመም አዲስ ተዓምር ሠርተዋል” - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
*********************
ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመትመም ዛሬም አዲስ የአረንጓዴ ልማት ተዓምር ፈጽመዋል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አለን መልእክት፣ ባለፉት የአረንጓዴ ዐሻራ ዓመታት ዛሬን በማሰብ ምግብ መመረቱን እና ለነገ ኃላፊነት ደግሞ ደን መልማቱን ገልጸዋል።
“እንደ ሕዝብ የተጋነው ፍሬ አፍርቷል፤ ተራሮች አረንጓዴ ካባ ደርበዋል፣ ዉኆች እንደገና መንጭተዋል” ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የተራቆተው ለብሶ፣ የጠፋው ተመልሶ፣ የደፈረሰው ጠርቶ እንዲሁም የነጠፈው አፍርቶ የሀገር መልክ መቀየሩን እና ይሄንን ያየው ዓለምም ለትጋታችን ደጋግሞ ዕውቅና መስጠቱን አብራርተዋል።
በራዕይ ማቀድን፣ በትጋት ወዳሰቡት መራመድን፣ ጽፈው ብቻ ሳይሆን ከተናገሩት በላይ ኖረው፣ ቃላቸውን በአርአያነት ተግብረው ላሳዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአረንጓዴ ዐሻራ ለመጣው ስኬት ምስጋና እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
መሪ እና ሕዝብ ለአንድ ዓላማ በመሰለፍ አፈር ነክተው፣ ጭቃ ረግጠው ተስፋን መትከላቸውን የጠቀሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ “እነርሱ ዝቅ ብለው ሀገርን ከፍ አደረጉ” ብለዋል።
ኢትዮጵያውያንም የመሪያቸውን ጥሪ ተቀብለው፣ ከሠርቅ እስከ ሰርክ ተምመው፣ የአየር ሁኔታውን አሸንፈው ዕቅዳቸውን ማሳካታቸውን ገልጸዋል።
ዛፍ የሚተከለው ለትውልድ በመሆኑ ከጥላው ያረፉ፣ ከድርቅ የተረፉ፣ ከፍሬው የቀመሱና ከልምላሜው የተቋደሱ ሁሉ የሚያመሰግኑ መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የዘንድሮውን የአንድ ጀንበር ሕልም መሳካቱን እና ለቀሪውም በርተው በሁለመናዋ የበለጸገች አረንጓዴ ኢትዮጵያን የመገንባት ስራ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

19 days ago
በቅጠሉ ንጹህ አየርን የሚፅፍ፣ በሥሩ አፈርን የሚያፀና
ታሪክ ሁልጊዜ በብዕር ብቻ አይጻፍም፤ አንዳንዴ በእጅ የተቆፈረ ትንሽ ጉድጓድ፣ በውስጡ በተተከለ አንዲት ችግኝ እና በላዩ በተጨመረ አፈር ይጻፋል።
ዛፍ የሚተክል ሰው ለዛሬ ብቻ አይሠራም፤ ያላየውን ትውልድ እያሰበ ይተጋል። ከራሱ ዕድሜ የሚረዝም ተስፋን በምድር ውስጥ ያኖራል። ስለዚህ አንድ ችግኝ መትከል አንድ የወደፊት ምዕራፍ መጀመር ነው።
በዚህ ምክንያት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ ዘመቻ ብቻ አይደለም። አንድ ሕዝብ ከተፈጥሮው ጋር የሚያድሰው የታሪክ ውል ነው።
በዚህ ውል ላይ ፈራሚው መንግሥት ብቻ አይደለም። አርሶአደሩ፣ ተማሪው፣ መምህሩ፣ ሠራተኛው፣ ወጣቱ፣ እናት፣ አባት እና ሕፃን ጭምር ናቸው።
ምክንያቱም አካባቢን መጠበቅ የአንድ ተቋም ኃላፊነት ሳይሆን የሁሉም ዜጋ የጋራ አደራ ስለሆነ።
በዚህ ዓመት በ"ተስፋ እንትከል" መሪ ሐሳብ የወደፊት ታሪካችንን በራሳችን እጅ የምንቀርጽበት ነው። ምድር የምትለምልመው በዝናብ ብቻ አይደለም። በሰው ኃላፊነት፣ በሰው ራዕይ እና በሰው ፍቅርም ጭምር እንጂ።
ዛፍ ደግሞ ዝም ብሎ የሚቆም ፍጥረት ሳይሆን በዝምታው ብዙ ነገር ይናገራል። በቅጠሉ ንጹህ አየርን ይጽፋል፤ በሥሩ አፈርን ያጸናል፤ በጥላው ሕይወትን ያቅፋል፤ በፍሬው ተስፋን ያበቅላል። ስለዚህ አንድ ዛፍ መትከል የነገን ሕይወት መትከል ነው።
ዛሬ የዓለማችን ፈተና የአየር ንብረት ለውጥ፣ የደን መመናመን፣ የመሬት መራቆትና የውኃ እጥረት ሆኗል። እነዚህን ችግሮች በንግግር ብቻ መፍታት አይቻልም፤ በተግባር የተደገፈ ኃላፊነት ይፈልጋሉ። የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴም የዚህ ኃላፊነት ሕያው መግለጫ ነው።
የዘንድሮው "ተስፋ እንትከል" መሪ ቃል በውስጡ ጥልቅ ፍልስፍና ይዟል።
ተስፋ አይዘራም፤ ይተከላል እንጂ። ምክንያቱም ሥር ማበጀት አለበት፣ በትዕግሥት ማደግ አለበት፣ ፍሬ ማፍራት አለበት። ልክ እንደ ዛፍ።
በዛፍ የሚጀምር ልማት በሀገር ዘላቂ እድገት ላይ ያለውን እምነት በተግባር ያሳያል።
የዘንድሮው ጉዞ በቁጥርም ሲገለጽ ትልቅ ራዕይን ያሳያል። በ2018 ዓ.ም 8 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዷል።
በዚህም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ቀደም ሲል የነበረውን 48 ቢሊየን ችግኞች የመትከል ግብ ወደ 56 ቢሊየን ከፍ አድርጎታል። እነዚህ ቁጥሮች የተቆጠሩ ችግኞችን ብቻ አይወክሉም። የሕዝብ ተሳትፎን፣ የሀገር ቁርጠኝነትን እና ለቀጣይ ትውልድ የሚገነባውን አረንጓዴ ተስፋ ይወክላሉ።
ዘንድሮ የሚካሄደው ሀገር አቀፍ የተከላ መርሃ ግብርም የዚህ ጉዞ ከፍተኛ ምዕራፍ ይሆናል። በመላ ኢትዮጵያ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በአንድ ዓላማ ይሰባሰባሉ።
የመደመር መንግሥት አመራሮች፣ የልማት አጋሮች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ተማሪዎች እና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች በጋራ ይሳተፋሉ።
ይህ ለሀገር አንድ የጋራ ዓላማ ሲኖር ልዩነቶች ከአንድነት ፊት እንደሚያንሱ የሚያሳይ ተጨባጭ ምሳሌ ነው። ምክንያቱም የዛሬው ችግኝ የነገው ደን ነው፤ የዛሬው አሻራ ደግሞ የኢትዮጵያ የወደፊት ታሪክ ነው።

21 days ago
ባማኮን ሪል እስቴት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ የገነባውን ዘመናዊ አፓርታማ አስመረቀ!
#fastmereja I ባማኮን ሪል እስቴት በቦሌ አዉሮፕላን ማረፊያ አካባቢ የገነባውንና ግንባታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀውን ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርታማ ህንፃ በዛሬዉ እለት በይፋ መርቆ ለደንበኞቹ አስረከበ።
ፕሮጀክቱ በሀገሪቱ የታየውን ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና እና የህንጻ መገንቢያ ቁሳቁሶች ዋጋ ንረት ተቋቁሞ፣ በደንበኞች ላይ ምንም ዓይነት ተጨማሪ ክፍያ ሳይጠይቅ መረከቡ ተገልጿል።
የባማኮን ሪል እስቴት የሽያጭና ማርኬቲንግ ዋና ኦፊሰር አቶ ፍሬው በየነ በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደገለጹት፤ ህንፃው በአጠቃላይ 22 ሰፋፊ መኖሪያ ቤቶችን እና ተጨማሪ አንድ የፔንት ሃውስ (Penthouse) መኖሪያን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።
ህንፃው በየወለሉ (per floor) ሁለት አፓርታማዎችን ብቻ የያዘ ሲሆን፣ ይህም ቤቶቹ ሰፋፊ፣ ዘመናዊና ምቹ እንዲሆኑ ታስቦ የተገነባ መሆኑን ጠቁመዋል።
እንዲሁም በየወለሉ ላይ የሚገኙት "A" እና "B" የተሰኙት ቤቶች 206 እና 208 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ሲሆን፣ ለነዋሪዎች አስተማማኝ ፀጥታና ግላዊነትን (Privacy) የሚያጎናጽፉ የቅንጦት (Super Luxury) መኖሪያዎች መሆናቸው ተብራርቷል።
በተጨማሪም ቤቶቹ ዘመናዊ (Modern) እና የሀገር ውስጥ ባህላዊ ምግቦችን ለማዘጋጀት የሚረዳ (Traditional) ባለሁለት ኩሽናን ያካተቱ ሲሆን፣ ይህም የምግብ ሽታና ጭስ ወደ ሳሎን እንዳይሰራጭ ታስቦ የተሰራ ነው።
በሀገሪቱ የነበረው የገንዘብ ምንዛሬ ለውጥ (Devaluation)፣ የጦርነት ተፅዕኖ እና የነዳጅ ዋጋ መጨመር በህንፃ መገንቢያ ግብአቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ቢያስከትልም፤ ኩባንያው ደንበኞቹን ከተጨማሪ ክፍያ በጠበቀ መልኩ ቤቶቹን ማስረከብ መቻሉን የሥራ ኃላፊው ገልጸዋል።
በተጨማሪም ባማኮን በአጠቃላይ ስምንት እህት ኩባንያዎች ያሉት ሲሆን፣ እነዚህ ኩባንያዎች እርስ በርስ የሚደጋገፉበት ጠንካራ አቅም መኖሩ ሥራው ሳይስተጓጎል እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ እገዛ ማድረጉን ገልጸዋል።
"ህንፃው ወደ ሽያጭ ከመውጣቱ በፊት ከ80% እስከ 85% የሚሆነው ግንባታው ተጠናቆ እንደነበር የተጠቀሰ ሲሆን ይህም በደንበኞች ላይ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግ ሙሉ በሙሉ አጠናቀዉ (Fully Finished) ለማስረከብ መቻላቸዉንም ገልፀዋል።
ባማኮን ሪል እስቴት ከተቋቋመ ሰባት ዓመታት የሆነው ሲሆን፣ አሁን ያስረከበው ህንፃ አራተኛ ፕሮጀክቱ ነው። ዋናው እናት ኩባንያ የሆነው ባማኮን ኢንጂነሪንግ በአዲስ አበባ የባንክ ዲስትሪክት አካባቢ በርካታ ግዙፍ ህንፃዎችን በመገንባት የሚታወቅና በዘርፉ ከ23 ዓመታት በላይ ልምድ ያለው ታላቅ ኩባንያ መሆኑ ይታወቃል።
#ቢዝነስ

22 days ago
“ታሪካዊው ሀገራዊ ምክክር በኃይለ ቃል ጀምሮ በኃይለ እርምጃ የሚደመደመውን የኢትዮጵያን የፖለቲካ አዙሪት የሚሰብር ነው”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ መድረኩ ኢትዮጵያ በኃይለ ቃል ጀምሮ በኃይለ እርምጃ የሚደመደመውን የፖለቲካ አዙሪት በመስበር በንግግር እና በውይይት የምትተካበት ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ይህ ጉባኤ ኢትዮጵያ በገዛ እጇ አዲስ ታሪክ እንድትጽፍ የሚያስችላትን “ብዕር እና ብራና” ያገኘችበት መሆኑን ጠቅሰዋል።
መድረኩ በቀጣዮቹ ሳምንታት አራት ሺህ ተሳታፊዎችን በአንድ ጣሪያ ሥር የሚያሰባስብ መሆኑን በማንሣት፣ ሂደቱም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በማሳተፍ ከታች ወደ ላይ በዘለቀ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ ላይ የተመሠረተ እንደሆነ አስታውቀዋል።
ለዚህ ታላቅ ሀገራዊ ጉዞ መሳካት ላበረከቱት አስተዋጽኦም ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ይህ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ግዙፍ እና ታላቅ ዓላማ ያለው ጉባኤ፣ ሀገራችን የገጠሟትን ፈተናዎች ወደ መልካም አጋጣሚዎች በመቀየር ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ባህልን ለማጽናት እንደሚያስችል አስገንዝበዋል።
ዛሬ የሚዘራው መልካም ዘር ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ እና ልጆች ፍሬውን የሚቋደሱት መሆኑንም አክለዋል።
የምክክሩ ተሳታፊዎች ከሰፈር አስተሳሰብ ወጥተው ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ መጪው ትውልድ በማሰብ ፍሬያማ ውይይት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሀገራዊ ችግሮችን በውስጥ ውይይት እና በይቅርታ መፍታት ሀገርን ከውጭ ጣልቃ ገብነት እንደሚታደግም በመጠቆም፣ የምክክሩ ውጤት ለኢትዮጵያ መልካም፣ ለአፍሪካ አስተማሪ እና ለመላው ኢትዮጵያውያን እውነተኛ እረፍትን የሚያመጣ ታሪካዊ ስኬት እንዲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
#ethiopia #ebc #pmabiyahmed #nationaldialogue #nationalconsensus

27 days ago
“8 ሰዓት ተኙ’ የሚለውን ምክር በፍጹም አትቀበሉ” – አቶ ዘነበ ፍሬው
#ethiopia | «እኔ ቀደም ሲል በቀን 3 ሰዓት ብቻ ነበር የምተኛው። አሁን ግን ትንሽ ጨምሬያለሁ። 4 ወይም 5 ሰዓት እንቅልፍ በቂ ነው፤ ቢበዛም ከ6 ሰዓት በላይ መተኛት አያስፈልግም። ምክንያቱም እኛ ገና ድሆች ነን፤ ከእጅ ወደ አፍ፣ ከአፍ ወደ ሆድ የምንኖር ሰዎች ነን። በትጋት ሰርተን ሕይወታችንን ከቀየርን በኋላ ግን ያን ጊዜ የበለጠ ማረፍ ይቻላል” ብለዋል አቶ ዘነበ ፍሬው»
አቶ ዘነበ ፍሬው በኢትዮጵያ በጠንካራ የሥራ ፈጣሪነት አስተሳሰባቸው ከሚታወቁ የቢዝነስ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው። ከልጅነታቸው ጀምሮ በተለይም በመርካቶ አካባቢ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ውጤታማ የሆነ የሥራ ጉዞ አድርገዋል።
በአሁኑ ጊዜም በሪል እስቴት፣ በውሃና ፕላስቲክ ማምረት፣ በብረት ማቅለጫና በሚስማር ማምረቻ ኢንዱስትሪ የተሰማሩ ሲሆን፣ በቅርቡም ወደ አገልግሎቱ ዘርፍ [እንደገና] በመግባት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን እያስፋፉ ነው።
አቶ ዘነበ ፍሬው በሃዋሳ ከተማ መግቢያ 75 በመቶ የተጠናቀቀ ሪዞርት እየገነቡ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም በቡኢ ከተማ ሌላ የሪዞርት ፕሮጀክት ግንባታ መጀመራቸውንም ከ«መሪ ፖድካስት» ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።
ሶዶ ለማ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #zenebefirew #realestate #resort #enterpreneur #enterpreneurmindset

Sponsored by
Surafel
1 month ago
ሞሮኮ ካናዳን አሸንፋ ወደ ሩብ ፍጻሜ አለፈች
#ethiopia | የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን "የአትላንቲክ አንበሶች" ካናዳን በማሸነፍ ወደ የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ በማለፍ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።
ድሉ በአፍሪካና በዓረቡ ዓለም ትልቅ ኩራት በመሆን ከዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃንና ከስፖርት ተንታኞች ሰፊ አድናቆት አግኝቷል።
በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የሞሮኮ ቡድን ያሳየው የተደራጀ መከላከል፣ ጠንካራ የቡድን መንፈስ እና የታክቲክ ብልሃት በስፋት ተወድሷል።
በተጨማሪም በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የተወለዱና ያደጉ ተጫዋቾችን በአንድ ዓላማ በማሰባሰብ የተፈጠረው ጠንካራ ቡድን ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተምሳሌት መሆኑ ተጠቅሷል።
ታዋቂው የስፖርት ኮመንታተር ፒተር ድሩሪ የሞሮኮን የጨዋታ ስልት በማድነቅ፣ ቡድኑ በመጀመሪያው አጋማሽ ካናዳን ከባድ ጫና ውስጥ እንዳስገባ እና በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታውን በከፍተኛ ብልሃት እንደተቆጣጠረ ገልጿል።
ጋሪ ሌንከር በበኩሉ የሞሮኮ ወደ ሩብ ፍጻሜ መድረስ የአጋጣሚ ውጤት ሳይሆን የጥራትና የዝግጅት ውጤት መሆኑን ሲገልጽ፣ ይህ የአፍሪካ እግር ኳስ አዲስ ምዕራፍ መከፈቱን ያሳያል ብሏል።
አላን ሺረርም የሞሮኮን የመከላከል አደረጃጀትና የተጫዋቾቹን መረጋጋት በማድነቅ፣ ቡድኑ የታክቲክ እግር ኳስ ምሳሌ መሆኑን ገልጿል።
ተንታኞች እንደሚሉት፣ የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባለፉት ዓመታት በስልጠና ማዕከላት፣ በዘመናዊ መሠረተ ልማት እና በተሰጥኦ ልማት ላይ ያደረገው ሥራ ዛሬ ፍሬውን በማሳየት ለአፍሪካ እግር ኳስ ትልቅ ኩራት ሆኗል።
አለባቸው ደሳለኝ ( ከለንደን )

ባለውለታዋን እናት
ከ12 ዓመታት በኋላ የተገለጠ የደግነት ታሪክ
ብሩክታይት ሽመልስ ባለውለታዋን እናት አገኘች፤ የእንባና የምስጋና አፍታ
#ethiopia | አንዳንድ የሰው መልካምነት ከጊዜ ጋር አይረሳም፤ ዓመታት ቢያልፉም በሰው ልብ ውስጥ እንደ ብርሃን ይኖራል። በ"ሰይፉ በኢቢኤስ" ፕሮግራም ላይ የታየው የብሩክታይት ሽመልስ (ብርክቲ) እና የወይዘሮ አዜብ ገብረ መስቀል መገናኘት የዚህ እውነት ሕያው ማሳያ ነው።
ያልተረሳ ውለታ
ከ12 ዓመታት በፊት፣ የ15 ዓመት ታዳጊ የነበረችው ብሩክታይት ከሐዋሳ ወጥታ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ ሳለች ጭንቀትና ፍርሃት ውስጥ ገብታ ነበር። በዚያ አስቸጋሪ ወቅት ሕይወቷን የቀየረች አንዲት ሴት አገኘቻት፤ ዛሬ የምትጠራት "ባለውለታዬ" ብላ ነው።
"ማን እንደላካት አላውቅም፤ እኔ ግን እግዚአብሔር የላከልኝ ሰው ነበረች ብዬ አምናለሁ" ስትል ብሩክታይት የዚያን ቀን ትዝታ በእንባ አስታወሰች።
አንዲት እናት... አንድ የሰብአዊነት ውሳኔ
ወይዘሮ አዜብ ገብረ መስቀል በዚያ ዕለት ብሩክታይትን በአውቶቡስ ላይ አገኘቻት። የታዳጊዋ ጭንቀትና ፍርሃት በፊቷ ይነበብ ነበር።
ምሳ እንድትበላ ብትጋብዛትም እንባዋን ማቆም አልቻለችም። ወይዘሮ አዜብም ጉዳዩን በእርጋታ ለማወቅ ሞከረች፤ ከዚያም ወደ ቤቷ ወስዳ አሳረፈቻት፣ አረጋጋቻት፣ ከቤተሰቦቿም ጋር እንድትገናኝ አደረገች።
"እናትሽና አባትሽ በጣም ይጨነቃሉ፤ የምትፈልጊው ቦታ በሰላም ትደርሻለሽ" ብላ በፍቅር ያረጋጋቻትን ቀን ዛሬም በግልጽ ታስታውሳለች።
"ይህ የኢትዮጵያዊነት ባህል ነው"
ወይዘሮ አዜብ ያደረገችውን እንደ ልዩ ጀግንነት አትቆጥረውም። ይልቁንም እውነተኛ ኢትዮጵያዊነት መሆኑን ትገልጻለች።
"እኔ ልጅ ያለችኝ እናት ነኝ። ያንን ልጅ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ቢያገኛት እንደዚያው ያደርግላት ነበር። ይህ የባህላችንና የማንነታችን መገለጫ ነው" ብላለች።
የደግነት ዋጋ
በፕሮግራሙ ላይ የተፈጠረው መገናኘት የተመልካቾችን ልብ ነክቷል። ብሩክታይት ባለውለታዋን እናት አቅፋ ስታለቅስ፣ ወይዘሮ አዜብም በደስታ እንባ ታጠበች።
ይህ ታሪክ የሚያስተምረን አንድ ትልቅ እውነት አለ፤ የሰው መልካምነት አይጠፋም፣ አይረሳም። በአንድ አስቸጋሪ ወቅት የተዘራ የደግነት ዘር፣ ከዓመታት በኋላም በምስጋና፣ በክብርና በፍቅር ፍሬውን ያፈራል።
ወይዘሮ አዜብ የተናገረችው አንድ ሐረግ ደግሞ የዚህን ታሪክ ሙሉ ትርጉም ይገልጻል፦
"ለሰው ብትኖር ምንም አትጎዳም፤ በምድርም በሰማይም ዋጋውን ታገኛለህ።"

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ ገዥው ስርዓት ህዝቡን እርስ በእርስ ለማጋጨት የመጨረሻ ያለውን "የሃይማኖት ካርድ" እየተጠቀመ ነው ሲል ከባድ ክስ አቀረበ። ፓርቲው በቅርቡ በዳንግላ እና በባቲ ከተሞች የተፈጸሙትን የሃይማኖት አባቶች አሳዛኝ ግድያ በጽኑ በማውገዝ፣ ምዕመናን ራሳቸውን እና ሃይማኖታቸውን ከጥቃት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።
በኢሕአፓ መግለጫ መሰረት አገዛዙ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ ለዘመናት በወንድማማችነት እና በመከባበር አብሮ በኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ግጭት እና እልቂት እንዲፈጠር ሆን ብሎ ሲሰራ ቆይቷል። ይህ እኩይ ሴራው ባሰበው ልክ ህዝቡን ባለማጋጨቱ፣ አሁን ላይ የሃይማኖት አባቶችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችን እያባባሰ መምጣቱን ፓርቲው አስታውቋል። ለዚህም በቅርቡ በዳንግላ ከተማ የኹጥባ መስጂድ ኢማም የሆኑት ሸይኽ ሱፍያን ሙሀመድ ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ ሳሉ በጥይት ተመትተው መገደላቸውን፣ እንዲሁም ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በባቲ ከተማ የጓሀ ጽባህ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ቄስ ፍሬው ሀብታሙ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው ማለፉን በአብነት ጠቅሷል።
ከእነዚህ የቅርብ ጊዜ ክስተቶች በተጨማሪ ቀደም ሲል በወለጋ እና በአርሲ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን እና አገልጋዮች ላይ የደረሰውን ግድያ እና መፈናቀል ፓርቲው በመግለጫው አስታውሷል። በተመሳሳይ በጦርነት ስም በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናት እና መስጂዶች ላይ የደረሰውን ውድመት፣ እንዲሁም ፍትህ በጠየቁ ንጹሃን ላይ የተፈጸመውን እስራት፣ አገዛዙ የሃይማኖት ካርዱን ተግባራዊ እያደረገ ለመሆኑ በቂ ማሳያዎች ናቸው ብሏል።
በእምነት አባቶች እና በምዕመናን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቆም እና ፍትህ ለማስፈን የሚሰራ መዋቅር ባለመኖሩ፣ ህዝቡ ተደራጅቶ ራሱን እና እምነቱን ሊጠብቅ እንደሚገባ ኢሕአፓ አሳስቧል። በተለይም የተደራጀ ጥቃት ሰለባ የሆኑት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እና የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ ከተደገሰላቸው የጥፋት ሴራ እርስ በእርስ በመጠበቅ፣ ታሪካዊ የወንድማማችነት እና የመከባበር እሴታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ፓርቲው አደራ ብሏል።
ሲያጠናቅቅም ፓርቲው ለተገደሉት የሃይማኖት አባቶች (ለሸይኽ ሱፍያን ሙሀመድ እና ለቀሲስ ፍሬው ሀብታሙ) ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ተመኝቷል።

2 months ago
የሞሮኮው የዳይመንድ ሊግ ውድድር የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ስኬት ታይቶበታል
#ethiopia | በሞሮኮ ራባት በተካሄደው ሶስተኛው የዳይመንድ ሊግ የራንዌይ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት ከፍተኛ ድል እና አንጸባራቂ ውጤት አስመዝግበዋል።
በሴቶች የ1 ሺህ 500 ሜትር የሩጫ ውድድር አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ ርቀቱን በ3 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ ከ25 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት በአንደኝነት ስታጠናቅቅ፣ አትሌት ሐረገወይን ካልአዩ ደግሞ በ3 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ ከ28 ማይክሮ ሰከንድ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የሀገራቸውን የበላይነት በጋራ አስጠብቀዋል።
በተጨማሪም በሴቶች የ800 ሜትር ፉክክር አትሌት ፅጌ ድጉማ በ1 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ24 ማይክሮ ሰከንድ ፈጣን ጊዜ ሁለተኛ በመሆን አበረታች ውጤት ያስመዘገበች ሲሆን፣ አትሌት ንግስት ጌታቸው ደግሞ በ1 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ ከ58 ማይክሮ ሰከንድ 11ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
በወንዶች የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር ላይ የተሳተፈው አትሌት ሳሙኤል ፍሬው የራሱን የዓመቱን ምርጥ ሰዓት በ8 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ ከ55 ማይክሮ ሰከንድ በማሻሻል ውድድሩን በ12ኛነት ፈጽሟል።
#athletics #diamondleague #rabat #running #sport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago
ኢትዮጵያ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የወርቅ እና የነሐስ ሜዳሊያዎችን በድል አጠናቀቀች
#ethiopia | በጋና እየተካሄደ ባለው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ውድድር ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል።
በብርቱ ፉክክር በተሞላው በዚህ ርቀት አትሌት ገመቹ ጎዳና አስደናቂ የሆነ የሩጫ ብቃት በማሳየት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቆ የወርቅ ሜዳሊያውን ለሀገሩ አስገኝቷል።
ገመቹ በተለይም ወደ ማጠናቀቂያው መስመር በቀረበበት ወቅት የነበረውን ፍጥነት በመጨመርና መሰናክሎችን በብቃት በመዝለል ቀዳሚ መሆን ችሏል።
በሌላ በኩል በዚሁ የፍጻሜ ፉክክር ላይ የተሳተፈው አትሌት ሳሙኤል ፍሬው በሦስተኛነት በመጨረስ የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆኗል።
ይህ ድል ኢትዮጵያ በዚሁ የአህጉራዊ ሻምፒዮና ያገኘችው ሦስተኛው የነሐስ ሜዳሊያ ሆኖ ተመዝግቧል።
#athletics #africanathletics #goldmedal #running #ethiopianathletics #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

በኢትዮጵያ የተመዘገቡ ስኬቶች የመንግሥትና የሕዝብ የጋራ ቁርጠኝነት ውጤቶች ናቸው - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
#ethiopia | በኢትዮጵያ የተመዘገቡ ስኬቶች የመንግሥትና የሕዝብ የጋራ ቁርጠኝነት ውጤቶች ናቸው አለ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት።
አገልግሎቱ ‘ቃል በተግባር! ኢትዮጵያ እያከናወነች ነው!’ በሚል መሪ ሀሳብ ባወጣው መግለጫ፤ የተመዘገቡት ስኬቶች ኢትዮጵያ በትክክለኛ የልማትና የዕድገት ጎዳና ላይ መሆኗን የሚያረጋግጡ ናቸው ብሏል።
በዚህም ኢትዮጵያ በዜጎች ሕይወት ላይ ተጨባጭ ለውጥ የሚመጣበት የታሪክ ምዕራፍ ላይ መድረሷን ገልጿል።
አገልግሎቱ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።
ቃል በተግባር !
ኢትዮጵያ እያከናወነች ነው!
ኢትዮጵያ በተለያዩ የልማት ዘርፎች የጀመረቻቸው ግዙፍ ተግባራት የትውልድ ተስፋ ከመሆን ባለፈ፣ በተጨባጭ ስኬቶች የታጀቡና ቃል በተግባር የተፈጸመባቸው ድሎች ሆነዋል።
በግብርናው ዘርፍ፣ በተለይም በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የታየው ዐቢይ ለውጥ ሀገሪቱን ከውጪ የዕርዳታ ስንዴ ጥገኝነት አላቆ ራስን ወደ መቻል ከፍ አድርጓታል። ምርቱን ለውጭ ገበያ ማቅረብ (ኤክስፖርት) መጀመሯም፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ትግል ወደ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሮታል።
በኢንዱስትሪው መስክ የውጭ ምንዛሬ ፍሰትን ለመታደግ የተወጠነው "የተኪ ምርቶች ንቅናቄ"፣ የኢንዱስትሪ ግብአቶችንና የፍጆታ ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ በማምረት ረገድ ተስፋ ሰጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል። ይህም ሀገራዊ ምርታማነትን በማነቃቃት የኢኮኖሚውን መዋቅር እያጠናከረ ነው።
የከተሞችን ገጽታ ለማሻሻልና ለዜጎች ክብር ያለው ሕይወት ለመስጠት የተጀመረው የኮሪደር ልማት፣ አዲስ አበባን እና የክልል ከተሞችን የኮንፈረንስ ቱሪዝም መዳረሻ ከማድረግ ባለፈ፣ ምቹ የመንቀሳቀሻ መንገዶችንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሠረተ ልማቶችን እውን በማድረግ ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ላይ አዲስ ተስፋ እንዲሰንቁ አድርጓል።
የኢትዮጵያዊያን የጋራ ትብብር ማሳያ በሆነው በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም ኢትዮጵያ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በሚደረገው አለም አቀፍ ጥረት ቀዳሚ ከሆኑ አገራት ተርታ እንድትሰለፍ ያደረገ የማይደበዝዝ አሻራ ማኖር ትችሏል።
ነባር የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማደስ ፣ አዳዲስ መዳረሻዎችን በመገንባት እና የንጹህ ኢነርጂ ኢንቨስትመንቶችን በማስፋፋት ሀብቶች እንዲለዩ እንዲገለጡ እና የኢኮኖሚ መሰረት እንዲሆኑ የተሰራው ወሳኝ ሥራ ፍሬው የሚታይበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ይገኛል፡፡
እነዚህ ስኬቶች የመንግሥትና የሕዝብ የጋራ ቁርጠኝነት ውጤቶች ናቸው። ኢትዮጵያ በትክክለኛ የልማትና የዕድገት ጎዳና ላይ መሆኗን የሚያረጋግጡ ከመሆናቸውም በላይ በዜጎች ሕይወት ላይ ተጨባጭ ለውጥ የሚመጣበት የታሪክ ምዕራፍ ላይ መድረሳችንን ያሳያሉ።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

"እማዬ የሁሉ እናት" በእናቶች ቀን እማዬን እናስታውስ
#fastmereja I የደጋግ እጆች መገለጫ፣ የመልካምነት ተምሳሌት፣ የአገር ወዳድነት አብነት፣ የሴቶች መቻል ማመሳከሪያ፣ የመልካም እናትነት ውል፣ የማሕበረሰብ ማስተሳሰሪያ ገመድ፣ የቢዝነስ ፈጠራ ሞዴል አማረች ዘለቀ ሸንቁጥ (ሴንተራል)።
የሆሳዕናው ሚካዔል በአክናፉ አጅቦ፣ ከፈጣሪ የተለገሰችውን አንዲት ሕፃን "እንካችሁ! ብሎ ለዝህች ቅድስት አገር አስረከበ፡፡ በሀድያ ዞን፣ ሆሳዕና ከተማ፣ በራሱ ስም በተሰየመለት አባባቢ (ሚካዔል ሰፈር)፣ በሰኔ 21 (ዕለተ-ማርያም) 1948 ዓ.ም. የበረከት ምሳሌ ናት፤ ሴት ስትወለድ፣ የፀጋ ማሳያናት፤ እንስት በቤተሰብ ስትበቅል። የኃላፊነት ቁነጮ ናት፤ እናት በማሕበረሰብ ውስጥ ስትገኝ። ይህንን ደስታ፣ ይንን ፍስሃ፣ ይህን ሃሴት፣ ሴትን የወለደ፣ ያሳደገ፣ አብሮ የኖረ፣ ጣዕሟን የተረዳ ያውቀዋል። በዚህ ቤተሰብ፣ በዚህ ቀዬ፣ በዚህ መንደር፣ አማረች የተባለች ሕፃን ስትወለድ የሆነውም ይህ እውነት፣ ይህ ደስታ፣ ይህ ፍንደቃ ነው። ማን ያውቃል፤ የህፃኗ መዳረሻ መልካም ገዶች ተገልፆላቸውስ ቢሆን!
ማንም ልጅ ሲወልድ ተስፋ ያደርጋል፤ ማንም ፍሬ ሲያገኝ ፈጣሪውን ያመሰግናል፤ ፍሬው በእግዚአብሔር መንገድ ሲፀድቅለት ደግሞ የበለጠ ልቡን በሀሴት ይሞላል። አድጎ ተመንድጎ፣ ተምሮ ሰርቶ፣ አግብቶ ወልዶ፣ የልፋት ጥሪቱን በሃብት፣ የሰው መሆን በረከቱን በልጅና ልጅ ልጆች፣ የሕዝብ ፍቅርን፣ ባለው ደግነትና ተግባቦት ሲታገዝ ምርጥ የቢዝነስ ፈጣሪ ደግሞ፣ ከሰውነት አልፎ አንድ ግለሰብ አገር ይሆናል፡፡ ባለታሪኳ በግል ተናጠል ከማውሳት ይልቅ፣ በአገርነት ቢነገርላቸው የሚያንስባቸው እንጂ፣ አይበዛባቸውም።
እኝህ የአገርነት ተምሳሌት የሆኑት እናት የሀዋሳዋ ወ/ሮ አማረች ሴንትራል ናቸው፡፡
በተወለዱበት ሆሳዕና ከተማ አድገው፣ መደበኛ ትምህርታቸውን በዛው ከተማ ተከታትለዋል፡፡ በለጋ እድሜ፣ ገና 14 ዓመት ሲሆናቸው፣ ትዳርን “ሀ” ብለው የሚቋደሱበትን ዕድል ሕይወት አዘጋጀችላቸው፡፡ በዚሁም፣ ነፍሳቸውን ፈጣሪ በአፀደ-ገነት ያቆይልንና፣ ለሻለቃ ወልደሰንበት ዘበርጋ ማሩ ለተባሉ ኩሩ ወታደር፣ በ1962 ዓ.ም. ተዳሩ፣ ፈጣሪም ትዳራቸውን ባርኮ፣ ኑሯቸውን ጎብኝቶ፣ የፍቅራቸውን ማሰሪያ አራት ወንድና አንድ ሴት ልጆችን አፍርተዋል፡፡
የሰው ልጅ ቋሚ እግር እንጂ፣ ቋሚ አገር የለውም፤” እንደሚባለው፣ ከትዳር ምስረታ በኋላ፣ ከባለቤታቸው ሻምበል ወልደሰንበት ዘበርጋ በርካታ ክፍላተ-አገር ውስጥ ለመኖር ተገደዋል። ምክንያቱ ደግሞ ሻምበል ወልደሰንበት አገራቸውን የሚጠብቁ ቋሚ ቦታ ያልተወሰነላቸው ጀግና ወታደር በመሆናቸው ነው። በመሆኑም፣ በአዲስ አበባ፣ በአርሲ (አሰላ እና ጢቾ)፣ በጠረፍ አገር ሞያሌ፣ በመጨረሻም በሃዋሳ ከተማ በማድረግ አሳርገዋል።
ባላቤታቸው በግዳጅ ወደ ሰሜን ዕዝ በተላኩበት ግዜ፣ ወ/ሮ አማረች ቀደም ሲል ከእርሳቸው ጋር ሲኖሩ ከነበሩበት የፖሊስ ማሰልጠኛ ግቢ፣ ወደ ከፍተኛ 2 (በአሁኑ ሀይቅ ዳር ከ/ከተማ)፣ ቀበሌ 05 (አሁን ጉዱማሌ ቀበሌ) በመዛወር፣ በተሰጣቸው የቀበሌ ቤት ውስጥ በወር 24 ብር እየከፈሉ መኖር ጀመሩ።
በወታደራዊ ግዳጅ ላይ የነበሩት ጀግና ባለቤታቸው ሻምበል ወልደሰንበት ዘበርጋ በግንባር መሰዋታቸውን የተረዱት በዚሁ መኖሪያቸው ነበር። ከዚህ በኋላ፣ ልጆችን ለብቻ ማሳደግ፣ እነሱ የሰው እጅ እንዳያዩ ማድረግ፣ ጤንነታቸውን መንከባከብ፣ ማስተማርና ማብቃት የሚለው መራር እውነት እንደተጋፈጠባቸው ሲያረጋግጡ፤ ፈታኙን ሕይወት ፊት ለፊት ለመግጠም አልሰነፉም፤ ቆርጠው ተነሱ።
ይህንን ሕይወት መጋፈጥ በወቅቱ በቂ ዝግጅት ላላደረገች እንስት ምንያህል ፈታኝ እንደሚሆን መገንዘብ አይከብድም፤ በሆነው ከማዘን ይልቅ፣ የተሰበረን ልብ የሚጠግንና የሟችንም ሕልም የሚያሻግረው መፅናናት፣ መበርታት ጠንክሮ መስራት መሆኑን ያመኑት ወ/ሮ አማረች፣ በቀጥታ ያደረጉት እጃቸው ላይ ያለውን ጥበብ በመጠቀም ወደኑሮ መለወጥ ነበር።
ብዙዎች የወ/ሮ አማረችን ስም ሲጠሩ የወላጅ አባታቸውን ያህል የሚያስከትሉት መጠሪያ ነው "እሜዬ የሁሉ እናት" ይህ ልዩ መገለጫ የተሰጣቸው ልዩ በሆነ ስብዕናቸው ነው ። ያለ አንዳች ልዩነት፣ የሩቅ ሰው፣ የቅርብ ሳይሉ ሁሉንም እንደ እናት ስለሚወዱና ለሰው ያላቸው እውነተኛ ፍቅር ነው፡፡
ወ/ሮ አማረች በየዓመቱ 10 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዘመዶቻቸውን እና ሌሎች ሰዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ወጪ ችለው ያስተምራሉ፡፡ እስካሁን ከ300 በላይ ተማሪዎች ተመርቀው ወደ ስራ ተሰማርተዋል።
ወ/ሮ አማረች በየአመቱ የአካል ጉዳተኛ ለሆኑ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና ህብረተሰብ የትምህርት ቁሳቁስ ወጪ ይሸፍናሉ።
በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ 5 ትምህርት ቤቶች በየአመቱ የተለያዩ በዓላትን በሚያከብሩበት ወቅት የመስተንግዶ ወጪ ይሸፍኑ ነበር።
ወላጅ አልባ ህፃናትን እና አረጋውያንን የመንከባከብ ስራ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች ድጋፍ ያደርጉ ነበር።
ይህ የተጠቀሰው ከብዙው በጥቂቱ ነው ። ወ/ሮ አማረች "እማዬ የሁሉ እናት" የተባሉበት መገለጫቸው ከዚህም በላይ ነው።

ለአርቲስት ዳዊት ፍሬው እና አባቱ ፍሬው ኃይሉ መታሰቢያ መርሐ ግብር ተዘጋጀ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያሳረፉትን የአርቲስት ፍሬው ኃይሉ እና የልጃቸውን የአርቲስት ዳዊት ፍሬው ኃይሉን የሙያ አስተዋጽኦ ለመዘከር የተዘጋጀ ልዩ መርሐ ግብር ሊካሄድ ነው። ይህ መርሐ ግብር “ፍሬው እና ፍሬው!” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴአትር ቤቶች አስተዳደር ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
የአዘጋጆቹ ጥሪ እንደሚያመለክተው፣ የጥበብ አፍቃሪያን፣ የጥበብ ቤተሰቦች እና ሌሎችም ታዳሚዎች በሚያዝያ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ በመገኘት በመታሰቢያ መርሐ ግብሩ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል። መርሐ ግብሩ በአርቲስት ዳዊት ፍሬው 5ኛ የሙት ዓመት ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ነው።
አርቲስት ፍሬው ኃይሉ በተለይ በ1950ዎቹ እና 60ዎቹ ውስጥ በክላርኔት ተጫዋችነቱ እና በዜማ አቀናባሪነቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ ልጁ ዳዊት ፍሬውም በዚሁ መሣሪያ ላይ ከፍተኛ ክህሎት በማሳየት የአባቱን ፈለግ ተከትሎ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ታዋቂ የሙዚቃ ባለሙያዎች፣ የሙዚቃ አቀናባሪዎች፣ እና ሌሎችም ታዋቂ ግለሰቦች በመታሰቢያ መርሐ ግብሩ ላይ እንደሚገኙ ይጠበቃል። ይህ መርሐ ግብር የሁለቱ ታዋቂ አርቲስቶች ሥራዎች የሚዘከሩበት እና ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፉበት አጋጣሚ እንደሚሆን ይታመናል።
#ethiopianmusic #frewhailu #dawitfrew #clarinet #memorylane #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

♦️አዲስአበባ ግራንድ ፕሪ አዲስ ለኢትዮጵያ የፈጠረው ሌላኛው ወርቃማ ዕድል
♦️ወጣቱ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ መሀሪ ነጋሽ የአለም አትሌቲክስ ባደረገለት ጥሪ ሀገሩን ወክሎ ወደ ቦትስዋና ዛሬ ተጉዟል
♦️የአለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር መሀሪ ባለ ልዩ ተሰጦ እና በጣም አቅም ያለው ወጣት ሲሉ አመካሽተውታል
♦️በቀጣይስ ወጣቱን ባለሙያ በዓለም አትሌቲክስ በቋሚነት እናየው ይሁን ?
#ethiopia | የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በታላቅ ስኬት ያከናወነውን አዲስአበባ ግራንድ ፕሪ ውድድር ከነሀስ ወደ ወርቅ ደረጃ ከመሸጋገሩ በተጨማሪ ሌላ ወርቃማ እድል እንደ ሀገር ይዞ ተከስቷል ።
የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ወጣት መሀሪ ነጋሽ በግራንድ ፕሪ እና በተለያዩ የፌዴሬሽኑ ትልልቅ ውድድሮች ባሳየው ብቃት፣አቅም እና ስኬት በአለምአቀፍ ደረጃ ተወዳጅነትንና ተቀባይነትን አግኝቶ ፌዴሬሽኑ ከዚህ በፊት ሲወቀስበት የነበረው በዓለምአቀፍ አደባባይ የተሳትፎ እጥረትን በሰበረ መልኩ በዓለም አትሌቲክስ ጥሪ ተደርጎለት
ዛሬ ጠዋት(ከደቂቃዎች በፊት) ወደ ቦትስዋና ጋቦሮኒ አምርቷል ።
ለወጣቱ ሀላፊ በቀጥታ ከአለም አትሌቲክስ ለዚህ ዕድል ከኢትዮጵያ በብቸኝነት መጋበዙ እዩኝ እዩኝ ሳይል፣ ማንም ሳያየው በጨለማ የተደከመበትን ስራው ፣በዓለም መድረክ ፍሬው መታየት መጀመሩ ለሌሎች ወጣት ባለሙያዎችም በር ከፋች ተደርጎ ተወስዷል።
ከአዲስአበባ እስከ አለም አትሌቲክስ (World Athletics )
በውጤት፣በልፋት እና በነጮች የተሰጠ ታላቅ የተግባር ምስክርነት ማረጋገጫ ሆኖ በተወሠደው በዚህ ዕድል በአቅሙ፣በእውቀቱ እና በስነምግባሩ የተመሰከረለት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ወጣት መሀሪ ነጋሽ የአለም አትሌቲክስ (World Athletics )
እውቅና በመስጠት በአለም አቀፍ ደረጃ በቦትስዋና የሚካሄደውን የዓለም አትሌቲክስ የሚዲያ አካዳሚ ፕሮግራም(World Athletics Media Acadamy Program )ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ ቀርቦለት ዛሬ(ሠኞ) ንጋት ላይ ወደ ስፍራው አቅንቷል ።
በሚሰራው ስራ በሁሉም የተመሰገነው ወጣት መሀሪ ከአገር ባለፈ፣ የአለም አቀፍ አትሌቲክስ የውድድር ዳይሬክተር ፒርስ ኦካላጋን "ልዩ ተሰጥኦ ያላውና በጣም ጎበዝ የሚዲያ ባለሙያ(Talented
Professional PR and Media Director )"በማለትም በተደጋጋሚ አድናቆት ሲያቀርቡለትና ምስክርነት ሲሠጡለትም ተሠምቷል።
ወጣት መሀሪ ያገኘው እድል እንደ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን እንደ አገርም ኢትዮጵያ በታላላቅ የዓለም የአትሌቲክስ መድረኮች ተወካይ ሳይኖራት መቅረቱ የሚያስቆጭ ቢሆንም አሁን ግን ይሄን ቁጭት የሚያስረሳ የሚመስል ፍንጭ በመታየቱ ሁላችንንም የሚያኮራ ሆኖ ተገኝቷል።
ወጣት መሀሪ ባሳለፍነው ሳምንት ተካሂዶ በተጠናቀቀው የአዲስአበባ ግራንድ ፕሪ ውድድር "በዓለም አትሌቲክስ" ተመርጦ የውድድሩ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር በመሆን የመራ ሲሆን በተለይም ውድድሩ ዓለምአቀፍ ስታንዳርድ ይዘት ያለው እንዲሆን እና ስኬታማ እንዲሆን ላደረገው አሰተዋጽኦ በዳይሬክተሩ ተደጋጋሚ እውቅና የተሰጠውና ምስጋና የተቸረው ሲሆን በአለምአቀፍ መድረክም እንዲሳተፍ
አስችሎታል ።
ወጣት መሀሪ በእንደዚህ ዓይነት ትልቅ ምስክርነት በአለም መድረክ እንዲወጡ አቅም እና እውቀት የሚጠይቅ ቢሆንም ነገርግን በሁሉም ዘርፍ ማድረግ እንደሚቻል አሳይቷል ።
ወጣት መሀሪ በተጨማሪም ፌዴሬሽኑ ከሚድያ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት እና ተሳትፎ ከማረጋገጥ ባለፈ፣ፌዴሬሽኑ በውጭ ግንኙነት እና በስፖርት ዲፕሎማሲ የተሻለ አቅም እንዲኖረው እና በአለም አትሌቲክስ ተቀባይነት እንዲያገኝ የተለያዩ
ተግባራት አከናውኗል ።
ቀጣይ የወጣቱ ጉዞ ወዴት ይሁን? የሚለውን ...አብረን የምናየው ይሆናል ..የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ግን እንደ መሀሪ አይነት ሰው ማበራከት ይጠበቅበታል ።
ፌዴሬሽኑ ጉዞውን የተሳካ እንዲሆንና ለወጣት መሀሪ ያደረገውን ድጋፍም ከፍተኛ ምስጋና ይገበዋል ።
ወጣት መሀሪ ነጋሽ ከተለያዩ የዓለም አገራት ከተወጣጡ በድምሩ ከ12 ባለሙያዎች አንዱ ሆነህ "ኢትዮጵያ"የሚለውን ታላቅ ስም አንግበህ በዚህ መድረክ በመገኘትህ እና የልፋትህ ውጤት በመሆኑ የሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ዝግጅት ክፍል እንኳን ደስ አለህ ለማለት ይወዳል።
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

4 months ago
“ፍሬው” የተሰኘ አዲስ ቲያትር ለእይታ ሊቀርብ ነው
#ethiopia | በተሻለ ወርቁ ተደርሶና ተዘጋጅቶ የቀረበው አዲሱ “ፍሬው” የተሰኘ ቲያትር የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ፍላሚንጎ በሚገኘው አዲሱ የህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት በድምቀት ይመረቃል።
በናታይ ጌታቸው እና በሞሪያድ ኢቨንት ፕሮዲውሰርነት የቀረበው ይህ ተውኔት አንጋፋዎቹን ተሻለ ወርቁንና ካሳሁን ፍስሃን (ማንዴላ) ጨምሮ ሰለሞን ሙሄ፣ ናታይ ጌታቸው፣ የምስራች ግርማ እና ህሊና ደረጄን የመሰሉ ተወዳጅ ተዋናዮችን በአንድ መድረክ ያሳያል።
ቲያትሩ ከመዝናኛነት ባለፈ የላቀ የጥበብ ልምድ የሚቀሰምበት መሆኑን የገለጹት አዘጋጆቹ ታዳሚዎች ትኬቶችን በአሐዱ ባንክ ቅርንጫፎች፣ በግራንድ ኩዳ፣ በባኮስ ላውንጅ፣ በባልደራስ ስፖርት ባር ወይም በዕለቱ በበሩ ላይ ማግኘት እንደሚችሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
#ferew #newplay #addisababatheater #ethiopianart #comedyshow #weekendvibes

🔥🔥 “ፍሬው” መጣ! 🔥🔥
ለሳቅ ተዘጋጅተዋል?
🎭 በተዋጣላቸው የፊልም ተዋናዮች የሚቀርበው 👉 “ፍሬው” — የሳቅ እና የጥበብ ድግስ ላይ ሁላችሁም ተጋብዛችኃል"ፍሬው" አዲስ ቲያትር!
ተዋናዮች:- ተሻለ ወርቁ ካሳሁን ፍስህ (ማንዴላ) ሰለሞን ሙሄ ናታይ ጌታቸው የምስራች ግርማ ህሊና ደረጄ ድንቅ የትወና ጥበባቸውን አሳይተውበታል እናንተ የቲያትር አፍቃሪያን በቦታው በመገኘት እንድትዝናኑ ተጋብዛችኃል "ፍሬው" አድራሻ:- ፍላሚንጎ አዲሱ የህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት ላይ በታላቅ ድምቀት ሊመረቅ ነው!
ደራዲና አዘጋጅ ተሻለ ቀርቁ ፕሮዲውሰር:-ናታይ ጌታቸው እና ሞሪያድ ኢቨንት
✨ ይህ ትያትር ብቻ አይደለም…
👉 የሳቅ በር ነው
👉 የመዝናኛ ጉዞ ነው
👉 የጥበብ ትልቅ ልምድ ነው
📍 በፍላሚንጎ ያለው አዲሱ የህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት
🗓 ቅዳሜ መጋቢት 26
⏰ ከቀኑ 10:30
💥 ይህን ቀን አትርሱ — ሳቅ ይጠብቃችኋል!
📞 0911 24 47 02 |0930 30 31 89/ 092 701 4141
💬 “ጥበብ ለፈገግታ፣ ፈገግታ ለጤና!”
ትኬቶች
👉በተመረጡ አሀዱ ባንክ ቅርንጫፎች
👉 ቦሌ ብራስ ግራንድ ኩዳ ሬስቶራንት
👉 ቦሌ ሸገር ጀርባ ባኮስ ላውንድ
👉 ባልደራስ ፋሚሊ ስፓርት ባር
👉 በህለቱ በር ላይ ትኬቱን ያገኛሉ
👉 #ፍሬው #comedynight #addisababa #theater #liveshow #weekendplan #ethiopiancomedy

ወደ ስራ ገበታዬ እንዳልገባ በጥበቃ ከበር ተባረርኩኝ - አሉላ
የስፖርት ጋዜጠኛ አሉላ ፍሬው በሃይማኖታዊ አቋሙ እና በሰጠው አስተያየት ምክንያት ከስራ ገበታው መታገዱን ገለጸ።
እንደ ጋዜጠኛ አሉላ ገለጻ ከሆነ፣ ለዚህ እገዳ ዋነኛው ምክንያት በቅርቡ በነበረው የሲዲ ስፖርት ፕሮግራም ላይ በኤቨርተን እና በማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታ ትንታኔ ወቅት የሰጠው የግል አስተያየት ነው።
ጋዜጠኛው በወቅቱ፦ "የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ እና የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊ ካልሆነች ሴት ጋር ትዳር አልመሰርትም"።
ማለቱን ተከትሎ በጣቢያው ጊዜያዊ ስራ አስኪያጅ ውሳኔ ከስራ ገበታው እንዲታገድ መደረጉን ገልጿል።
አሉላ ፍሬው ለተከታዮቹ ባስተላለፈው መልእክት ፤የጣቢያው ውሳኔ የግል አቋሙን እንደማያስቀይረውና በእምነቱ እንደሚጸና ገልጿል።
የተላለፈው ውሳኔ የጣቢያውን ባለድርሻ አካላት በሙሉ የማይወክልና የጊዜያዊ ስራ አስኪያጇ የግል አመለካከት ውጤት እንደሆነ ገልጿል።
ይህ ችግር በአስቸኳይ የማይፈታ ከሆነ፣ በብዙዎች ዘንድ በሚወደደው "ሲዲ ስፖርት" ፕሮግራም ላይ የመሳተፍና ትንታኔዎችን የማቅረብ እድሉ አደጋ ላይ መውደቁን ጠቁሟል።
seledadotio

5 months ago
የኀዘን መግለጫ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የዩኒቨርስቲ ደህንነት ጥበቃ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ የነበሩት ረዳት ኮሚሸነር በላይ ከበደ ፍሬው መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ረዳት ኮሚሽነር በላይ ከበደ በሥራ ዘመናቸው ተቋማቸውንና ህዝባቸውን በታታሪነት፣ በታማኝነትና በቅንነት ሲያገለግሉ የቆዩ አመራር ነበሩ።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በረዳት ኮሚሽነሩ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል።
የረዳት ኮሚሽነሩ የቀብር ሥነ-ሥርዓት መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከ8፡00-9፡00 በመካኒሳ አቦ ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቻቸውና የሥራ ባልደረቦቻቸው በተገኙበት ይፈፀማል፡፡
Via EFP
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

🇪🇹 የአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የ23 ተጫዋቾች ስብስብ!
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) በዚህ ወር ለሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታ ዝግጅታቸውን አጠናክረዋል። ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ሀገሪቱን ወክለው ሜዳ ላይ የሚፋለሙትን 23 ተጫዋቾች ዝርዝር በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።
በስብስቡ ውስጥ ልምድ ያላቸውና በሊጉ ድንቅ ብቃት እያሳዩ ያሉ ተጫዋቾች የተካተቱ ሲሆን፣ ሙሉ ዝርዝሩም እንደሚከተለው ነው፡-
🧤 የግብ ዘብ (Goalkeepers)
መረባቸውን ለማስከበር ኃላፊነት የተሰጣቸው ግብ ጠባቂዎች፡-
* አቡበከር ኑራ
* ፍሬው ጌታሁን
* ሰይድ ሀብታሙ
🛡️ የኋላ መስመር (Defenders)
የተከላካይ ክፍሉን የሚመሩት ብርቱዎቹ ተጫዋቾች፡-
* ያሬድ ባየህ፣ ምኞት ደበበ፣ አስራት ቱንጆ፣ አለምብርሀን ይግዛው፣ ያሬድ ካሳዬ፣ አብዱሰላም የሱፍ፣ ራምኬል ጄምስ እና ግሩም ሀጎስ።
⚙️ የመሐል ሜዳ (Midfielders)
የጨዋታውን ፍሰት የሚቆጣጠሩት የሞተር ክፍሎቹ፡-
* ጋቶች ፓኖም፣ ሀብታሙ ተከስተ፣ ብሩክ እንዳለ፣ ብዙአየሁ ሰይፉ፣ ወገኔ ገዛኸኝ እና ቢኒያም አይተን።
🎯 የአጥቂ መስመር (Forwards)
ግብ ለማደን የተመረጡት ፊት አውራሪዎች፡-
* አቤል ያለው፣ ከነአን ማርክነ፣ ቸርነት ጉግሳ፣ መስፍን ታፈሰ፣ አቡበከር ሳኒ እና ከቤ ብዙነህ።
የአዘጋጁ አስተያየት፡ ይህ ስብስብ የተመጣጠነ እና በሁሉም መስመር ላይ አማራጮችን የያዘ ይመስላል። በተለይ በመሐል ሜዳ ላይ ያለው የልምድ እና የጉልበት ጥምረት ለቡድኑ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #walias #afcon #ethiopianfootball #ዮሐንስሳህሌ #ዋሊያዎቹ #ኢትዮጵያ

#ፍትህአወቅ የወንድወሰን (የሙያ ታሪክ)
በተወዳጅ ሚድያ (ዕዝራ እጅጉ )የተዘጋጀ
#ethiopia | ጋዜጠኝነት የሚድያ ሰው ፍትህአወቅ የወንድወሰን የምስራቅ አፍሪካ አርታዒያን ሶሳይቲ (EAES) ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመርጧል።
በምስራቅ አፍሪካ የሚዲያ ዘርፍ ላይ ኢትዮጵያ ያላትን ተሰሚነት የሚያጎላ አዲስ ምዕራፍ ተመዝግቧል። እ.ኤ.አ. የካቲት 28 ቀን 2026 በናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ሚዲያ ፌስቲቫል ማጠናቀቂያ ላይ፣ ፍትህአወቅ የወንድወሰን የሶሳይቲው ፕሬዝዳንት በመሆን በከፍተኛ ድምፅ ተመርጧል።
* ምክትል ፕሬዝዳንት፦ ወ/ሮ ዙቤይዳ ካኑ (ከኬንያ አርታዒያን ማህበር)
"ይህ ምርጫ ለኢትዮጵያ አርታዒያን ብቻ ሳይሆን፣ በቀጠናው ለሚገኙ ሁሉም የሙያ ባልደረቦች የጋራ እድገት ትልቅ ፋይዳ አለው።"
#ስለ ምስራቅ አፍሪካ አርታዒያን ሶሳይቲ (EAES)
የምስራቅ አፍሪካ አርታዒያን ሶሳይቲ (EAES) የአምስት ሀገራት የሚዲያ ማህበራት ጥምረት ሲሆን፣ አባላቱም ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ዩጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ናቸው። ሶሳይቲው በዋናነት በፕሬስ ነፃነት፣ በሙያ ስነ-ምግባር እና በጋራ ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሠራል።
ተወዳጅ ሚድያም የጋዜጠኞችን ታሪክ በዲጂታል ሚድያ እና በመፅሐፍ የሚሰንድ ሲሆን በዚህ መሠረት የፍትህ አወቅ ሙያዊ አስተዋፅኦ በተወዳጅ ሚድያ የመዝገበ አእምሮ ቦርድ የሚመጥ ሆኖ በመገኘቱ ታሪኩን ሰንደነዋል። ዕዝራ እጅጉ ታሪኩን እንደሚከተለው ያቀርበዋል።
፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨
አባቱ አቶ የወንድወሰን ክፍሌ ወደ ንባቡ ዓለም እንዲሳብ መሠረት ሆነውታል። እርሳቸው ጋዜጣና መፅሔት የማንበብ ልምዱ ስለነበራቸው ፍትህ ገና በታዳጊነት ህትመቶቹን እየተቀበለ ያነብ ነበር። ይህ ንባቡ ዛሬ ለያዘው ዕውቀት መነሻ ሆኖታል። ፍትህ በደንብ ማንበቡን የተረዱት አባቱ ፊልድ ደርሰው ሲመለሱ ምን አዲስ ክስተት አለ? ብለው የሚጠይቁት ፍትህን ነበር። እርሱም የቤት ውስጥ የዘጋቢነት ኃላፊነቱን እየተወጣ አለም እንዴት እንደሰነበተች ለአባቱ መረጃ ያቀርባል። አባትም በልጃቸው የመተንተን ፣ የማስረዳት አቅም እየተደሰቱ ጎሽ ልጄ ይሉት ነበር።
ታላቅ ወንድሙ ለአለም የወንድወሰን እንደሚናገረው ፍትህ በትምህርቱም እየበረታ ፣ አለምአቀፍ ዕውቀቱንም እንደያዘ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሊገባ ችሏል።
".....ፍትህ ከበፊት ጀምሮ ነገሮችን ሚዛን አስጠብቆ በማስኬድ ያምናል። የሚያነባቸው የፖለቲካል ኢኮኖሚ መፅሐፎች እገዛ ስለሚያደርጉለትም በአለም አቀፍ ጉዳይ ላይ ያለው መረዳት ከፍ ያለ ነው። ሲያወራም በቀላሉ የማሳመን ክህሎት አለው። ለእኔ 5ኛ ታናሼ ሲሆን ባለው የተለየ ዕውቀት አከብረዋለሁ።ከበፊትም ጀምሮ ለአመራር የሚሆን ሰብዕና እና አቅም እንዳለው እገነዘብ ነበር። አሁን በተግባር የማየውም ይህን የሊደርሺፕ ችሎታውን ነው። " በማለት ታላቅ ወንድሙ ምስክርነት ሰጥቷል።
ፍትህ ብዙም ሳያጠና ከሚገባቸው ጎበዝ ተማሪዎች አንዱ ነበር። ከክፍል አንደኛ ሲወጣ ተማሪዎች መቼ አጥንቶ ነው እያሉ ይገረሙበት ነበር። ፍትህ በፍልስፍና ፣ በፖለቲካ፣ በቀጠና ጉዳዮች ፣ በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ማንበብ ርካታ ይሰጣዋል። ዛሬም ቢሆን ፍትህ መፅሐፍት ከእጆቹ አይለዩም። በአገር ውስጥ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ለአንዳንድ ሚድያዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ትንታኔ ይሠጣል። ይህ እንግዲህ ከአለምአቀፍ ፖለቲካ ጋር ያለውን የቅርብ ትስስር የሚያሳየን ሲሆን እርሱም ይህን አቅሙን በየጊዜው እያዳበረ ሄዶ ዛሬ ላይ መድረስ ችሏል።
ፍትህ በአንድ ወቅት ሶማሌ ክልል ለዘገባ አቅንቶ በነበረው ውጥረት ጥይት ካረፈበት ሆቴል እንዳለፈ ይነገራል። ይህም ለሙያው የከፈለውን ዋጋ የሚያሳየን ነው።
ፍትህ በ1998 ዓ.ም ወደ ሚድያው አለም ሲቀላቀል የዜና ክፍል ኃላፊ የነበረችው ብርቱካን ሐረገወይን የፍትህአወቅን ችሎታ ታደንቅ ነበር። እንዲህ ትላለች"... ያኔ አብረውት ከተቀጠሩት መካከል የተሻለ መረዳት ነበረው። የሚፅፋቸው ዜናዎችም በሳል እንደነቀሩ አስታውሳለሁ። የሚሠራውን ዜና በሚገባ አውቆት ስለሆነ ሚዛናዊ እና በዕውቀት የተሞላ ዘገባ እናገኝ ነበር። የፖለቲካ ዘገባን በልዩ መልኩ ይገነዘብ ነበር። ደግሞም በፍጥነት ስለሚያደርስ ይደነቅ እንደነበር አስታውሳለሁ። ፎርማት በመቅረፅና እና በአመራር ቦታም ላይ ሁኖ የተቻለውን እንዳደረገ አውቃለሁ" ስትል ብርቱካን ከተወዳጅ ሚድያ ለተጠየቀችው ምላሽ ሰጥታለች።
#የሐረር ልጅ!
ታሪካዊቷ የሐረር ከተማ ካበቀለቻቸው የሚድያ ፈርጦች መካከል ይጠቀሳል። ፍትሕ ሐምሌ 23 1976 ተወለደ።ትውልድና እድገቱ በሐረር ከተማ የሆነው ፍትህአወቅ የወንድወሰን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በየሺህ እመቤት ት/ቤት፣ በልዑል ራስ መኮንን ት/ቤት እና ሐረር ኤስ ኦ ኤስ ት/ቤቶች ተከታትሏል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪውንም አግኝቷል።ሁለተኛ ዲግሪውን ያገኘው በ2007 ዓ.ም ነው።
#ጋዜጠኛው
ከተማሪነት አንስቶ በሚድያና ጥበብ ንቁ ተዋናይ የሆነው ፍትህአወቅ ሚያዝያ 1998 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ራድዮን በመቀላቀል የጋዜጠኝነት ሙያውን ጀመረ። ከኢትዮጵያ ራድዮ ዜና ፋይል አንጋፋ ጋዜጠኞች ጋር መስራቱ በአጭር ጊዜ በሙያው ከፍተኛ ብቃት እንዲላበስ እንደረዳው ይናገራል። በ2001 የኢትዮጵያ ራድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ውህደትን ተከትሎ በቴሌቪዥን ጋዜጠኝነትም ስማቸው ከሚጠቀሱ የ2000ዎቹ ጋዜጠኞች መካከል ሆነ።ከሪፖርተርነት እስከ ዋና አዘጋጅነት በቆየበት ኢቲቪ ለ12ዓመታት አገልግሏል።
ፍትህአወቅ የወንድወሰን በታላላቅ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የዲፕሎማሲ የዜና ዘገባዎቹ እና ትንታኔዎቹ የሚታወቅ ሲሆን በተለይም 'ሚድያ ዳሰሳ' እና 'ዲፕሎማሲያችን' ፕሮግራሞች ከተመልካች ቤት ደርሷል። የአፍሪካ መዲና ከሆነችው አዲስ አበባ በርካታ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤዎችን የዘገበ ሲሆን በተለያዩ የዓለም ሀገራት በመዘዋወር በርካታ ዓለም አቀፍ ዘገባዎችን አቅርቧል።
ከ2010 ዓ.ም አንስቶ ፍትህአወቅ የወንድወሰን ከባልደረቦቹ ጋር በመሆን የሚድያ ስራዎችን ማከናወኑን ቀጥሏል። በአሐዱ ራድዮ 94.3 'ቅዳሜ ገበያ' የሚሰኝ የቢዝነስና ኢኮኖሚ ሾው ዘወትር ሰኞ፣ ረቡዕ እና አርብ እያዘጋጀ ይገኛል።
ፍትህአወቅ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን አቅም ለማጎልበትና፣ ለመብታቸው ለመሟገት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ዓርታኢያን ማህበር መስራች አባል ሲሆን የማህበሩ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ በመሆን እያገለገለ ይገኛል። ከኢትዮጵያ ባሻገር በአፍሪካ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የአፍሪካ አርታኢያን ፌደሬሽን አባል ሲሆን የምስራቅ አፍሪካ አርታኢያን ሶሳይቲ የቦርድ አባል ነው። ጋዜጠኛ ፍትህአወቅ በ2026 በተደረገው ጉባኤ የምስራቅ አፍሪካ አርታኢያን ሶሳይቲ ፕሬዘዳንት ሆኖ በመመረጥ የምስራቅ አፍሪካ ጋዜጠኞችን የማገልገል ኃላፊነት ተቀብሏል።
አብዱል ሰመድ መሐመድ ከፍትህአወቅ ጋር ከ17 አመት በላይ ትውውቅ አለው። አብዱልሰመድ ፍትህን ሲገልፀው ለነገሮች ልዩ ትኩረት የሚሰጥ ጠንካራ ሰው ይለዋል።ሀሣቡንም አብራርቶ ሲገልፅ አብዱልሰመድ እንዲህ ይላል
"....ፍትህ ፖለቲካ ሳይንስ እንደማጥናቱ በአለም ፖለቲካ ላይ የመተንተን ልዩ ክህሎት አለው ። ኢቲቪ በሠራባቸው ጊዜያትም ዜና ክፍል ኃላፊ ሆኖ ይሠራ ነበር። በዚያን ወቅት የማስተባበር ችሎታው ገራሚ ነው።" በማለት አብዱልሰመድ ምስክርነት ሰጥቷል።
ፍትህ እንደተባለው ከስሩ ያሉትን ሪፖርተሮች አሰማርቶ ሁሉንም እንደ ችሎታቸው ይዞ በጥሩ አክብሮት ሲያሠራቸው እንደነበር ብዙዎች ይመሰክራሉ። አብዱልሰመድ ይህን ተባብሮ የመሥራት ችሎታውን ያደንቅለታል።
"... ፍትሕ አንድ ነገር ከጀመረ ሳያጠናቅቀው አይተኛም።አዳዲስ ፕሮግራሞች የማፍለቅ ሀሣቦችንም የማዳበር ችሎታን ታድሏል።በአሐዱ ሬድዮ የሚቀርበው ቅዳሜ ገበያ የሚለውን ስም ፍትህ እርሱ ነው ያወጣው። ፕሮግራሙም ላይ እንደ አዘጋጅ የራሱን ትልቅ አሻራ ማኖር ችሏል።ፍትህአወቅ የአርታኢያን ማህበር እንዲመሠረት ትልቅ ጥረት አድርጎ ልፋቱም ፍሬ አፍርቷል። በአርታኢያን ማህበር ላይ በውይይት መድረክ የሚነሱ ሀሣቦች ጥልቅ እንዲሆኑም የተቻለውን ጥረት አድርጓል። የምስራቅ አፍሪካ አርታኢያን ማህበር ፕሬዚዳንት ሆኖ በመመረጡም የተሰማኝን ደስታ መግለፅ እወዳለሁ" በማለት አብዱል ሰመድ ምስክርነቱን ለተወዳጅ ሚድያ ሰጥቷል።
#ነፃነት ፈለቀ ስለ ፍትህአወቅ
ነፃነት በኢቢሲ የዕቅድ ዲፓርትመንት ኃላፊ ስትሆን ስለ ፍትህ ይህን ምስክርነት ሰጥታለች።
እኔ ፍትህአወቅ የወንደወሰንን የማውቀው ኢትዮጵያ ሬዲዮ ዜና ክፍል በሪፖርተርነት ሲቀጠር ጀምሮ ነው፤ በወቅቱ የዘገባ ሥራዎቹ ጥንቅቅ ያሉ ስለነበር ትንሹ ኤዲተር ይባል ነበር። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዜናና ወቅታዊ ክፍል በነበረበት ወቅትም የዘገባ ሥራዎቹ በመረጃ የዳበሩና ጥልቀት ያላቸው ናቸው፤ በቀጥታ ዘገባ ሥራው ንግግሩ የጽሑፍ ያህል ፍሰት ያለውና የአድማጭ ተመልካቹን ቀልብ የመያዝ አቅም የነበረው ነው። ቴሌቪዥን ላይ በዜና ኤዲተርነት አሉ ከሚባሉ የይዘት ኤዲተሮች አንዱ ነው። በወቅታዊ ፕሮግራሞችም እንዲሁ። ፍትህ ዓለም አቀፍና ሀገራዊ የፖለቲካ አውዱን በሚገባ ተረድቶ ወደ ሚዲያ ይዘት የሚቀይርበት አቅም ሁሌም የሚያስደንቅ ነው። ሪፖርተሮችን የማዳመጥና የተረጋጋ ተግባቦቱ ለሌሎች አስተማሪ ነው።
ፍትህ የምስራቅ አፍሪካ የኤዲተሮች ማሕበር ፕሬዝዳንት ሆኖ መመረጡ አቅሙን ለአፍሪካውያን ወንድሞች የማጋራት ዕድል ስለሚፈጥርለት እንኳን ደስ ያለህ ማለት እፈልጋለሁ። ከዚህም በላይ ይገባሃል 🙏
#ፍሬው አበበ ስለ ፍትህአወቅ
ፍትህአወቅ የወንድወሰን የዛሬ 7 አመት ገደማ የኢትዮጵያ አርታኢያን ማኀበር ከመሰረቱ ጥቂት ጋዜጠኞች ግንባር ቀደሙ ነው። ማኀበር መመስረት ብቻም ሳይሆን ማኀበሩ በሁለት እግሩ እንዲቆም በአመራርነት የላቀ ሚናውን ተወጥቷል። በእሱና በባልደረቦቹ ጥረት በአሁን ሰአት ማኀበሩ ለአባላቱ መብትና ጥቅም መቆም የሚችልና በጎ ተጽእኖ ፈጣሪ ለመሆን ችሏል።
ፍትህአወቅ በአሁን ሰአትም የማኀበሩ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛል።
ፍሬው አበበ
የኢትዮጵያ አርታኢያን ማኀበር ቦርድ ሰብሳቢ

"ሀገር እና ዓድዋ"
ለጋራ ሀገር የጋራ ቃላት ያስፈልጉናልና!!!!
የዓድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ጀምሮ ባዘጋጀነው ዋልያ የሐሳብ እና መጻሕፍት መድረክ ልዩ ፕሮግራም ሁላችሁም በክብር ተጋብዛችኃል!!
ስለ ሀገራችን ማወቅ ያሉብንን እውነታዎች ምንድናቸው? እነሱንስ የምንገልጽባቸውን ወሳኝ ቃላት ምን ያህል እንግባባ'ባቸዋለን? ስሞችን በትክክል ካላወቅን ወይም የጋራ ስም ካልፈጠርን ለጋራ ሀገር በጋራ መሰለፋችንን እርግጠኛ መሆን ይቻላል ወይ?
ሀገር፣ ድንበር ፣ መንግሥት፣ ሕዝብ፣ ሉዓላዊነት ፣ ዜጋ፣ ጦርነት ፣ ወዘተ የሚሉ ስሞች ላይ የፖለቲካ፣ የታሪክ እና የሕግ ትንታኔ እንዲያቀርቡ ምሁራንን ጋብዘናል።
አቅራቢዎች:-
=======
ፕሮፌሰር አህመድ ዘከሪያ /ከታሪክ አንፃር/
ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ :-/ከፖለቲካ አንፃር/
የሕግ ባለሙያ አንዱዓለም በዕውቀቱ :-/ከሕግ አንፃር /
አወያይ:- ፍሬው ማዕሩፍ /ከሕግ ፍልስፍና/
የካቲት 21 - ቅዳሜ ከቀኑ 8:30 ጀምሮ
ቦታ አራት ኪሎ ዋልያ አዳራሽ - ኢክላስ ሕንጻ 4ኛ ፎቅ

በአለማችን እጅግ ውድ የሆነው ቡና የሚገኘው ከእንስሳት ሰገራ መሆኑን ያውቃሉ።
ኮፒ ሉዋክ በመባል የሚታወቀው ይህ ቡና በዋናነት በኢንዶኔዥያ የሚመረት ሲሆን የሲቬት ድመት የተባለች ትንሽ የእንስሳት ዝርያ የምታዘጋጀው ነው።
ይህች ድመት በጫካ ውስጥ ምርጥ እና ጣፋጭ የሆኑትን የቡና ፍሬዎች ትመርጣለች ፍሬውን ከበላች በኋላ የቡናው ፍሬ ሳይፈጭ በሰገራዋ አማካኝነት ይወጣል።
ገበሬዎች ይህንን የቡና ፍሬ ሰብስበው በደንብ በማጠብ ያዘጋጁታል ቡናው በድመቷ ሆድ ውስጥ ሲቆይ በሚፈጠረው ኬሚካላዊ ሂደት ምክንያት ለየት ያለ ጣዕም እንደሚኖረው ይነገራል በዚህም ምክንያት በጣም ውድ ዋጋ ያወጣል።
ነገር ግን ይህን ቡና ለማምረት ሲባል አሁን አሁን እነዚህን ድመቶች በጠባብ ቦታ አስሮ በማሰቃየት ቡና ብቻ እንዲመገቡ ማድረግ በመጀመሩ ድርጊቱ ከፍተኛ ተቃውሞ እያስነሳ ይገኛል።

የዓለማችን ውዱ የእንስሳ እዳሪ ቡና
#ethiopia | በአሜሪካ እና በተለያዩ የዓለም ሀገራት የቡና መሸጫ ቤቶች ውስጥ አንድ አስገራሚ ወሬ መነጋገሪያ ሆኗል። "አዲስ ገጽ" የተሰኘው ፕሮግራም አዘጋጅ መስፍን አሰፋ በቅርቡ የታዘበውና ያጋራው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በዓለማችን እጅግ ውዱ ቡና የሚገኘው ከእንስሳ እዳሪ ነው።
"ሲቬት" ወይም ኮፒ ሉዋክ ምንድን ነው?
ይህ ቡና ሲቬት (Civet) ወይም ኮፒ ሉዋክ (Kopi Luwak) በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ ስሙን ያገኘው "ሲቬት" ከምትባል ድመት መሳይ አጥቢ እንስሳ ነው። እንስሳዋ በብዛት በደቡብ እስያ እና በአንዳንድ የአፍሪካ አካባቢዎች የምትገኝ ሲሆን፣ ለየት ያለ ተፈጥሯዊ ስጦታ አላት።
ከጫካ እስከ ሲኒ፡ አስገራሚው ጉዞ
የዚህ ቡና ዝግጅት ሂደት ለየት የሚያደርገው የሚከተሉት ነጥቦች ናቸው፦
* ምርጥ መራጭነት፦ ሲቬት በምሽት የምትቀሳቀስ እንስሳ ስትሆን፣ ምርጥ እና የበሰሉ የቡና ፍሬዎችን የመለየት ልዩ ችሎታ አላት።
* የሆድ ውስጥ "ሂደት"፦ እንስሳዋ የቡናውን ፍሬ በምትመገብበት ወቅት የምትፈጨው የላይኛውን ልጣጭ ብቻ ነው። ፍሬው ግን ሳይሰበር በሆዷ ውስጥ አልፎ ከእዳሪዋ ጋር ይወጣል።
* ጽዳትና ዝግጅት፦ ገበሬዎች ከጫካ ውስጥ የእንስሳዋን እዳሪ በመልቀም፣ በውስጡ ያሉትን የቡና ፍሬዎች ደጋግመው በንጽህና ያጥቧቸዋል። በመቀጠልም ደርቀው
ተቆልተውና ተፈጭተው ለገበያ ይቀርባሉ።
ጣዕሙና ዋጋው
ይህንን ቡና የቀመሱ ደንበኞች እንደሚሉት፣ ቡናው እጅግ ለስላሳ፣ ተፈጥሯዊ እና የቸኮሌት ጣዕም ያለው ነው። ይህ ልዩ ጣዕሙም የዓለማችን ዝነኛ እና ውድ ቡና እንዲሆን አድርጎታል።
* ዋጋ፦ እንደ ጥራቱ ሁኔታ የአንድ ኪሎ ሲቬት ቡና ዋጋ ከ50 ዶላር (ከ8,000 ብር በላይ) ጀምሮ እስከ ሺህ ዶላሮች ይደርሳል።
ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ ይህ ቡና ጫካ ለጫካ የተጓዘ፣ በእንስሳ ሆድ ውስጥ አርፎ የመጣ እና ረጅም ጉዞ አድርጎ የእርስዎ ሲኒ ላይ የደረሰ "የተፈጥሮ ተአምር" ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ebc #civetcoffee #kopiluwak #luxurycoffee #addisgetz #coffeelovers #አስገራሚእውነታዎች #ቡና

6 months ago
በታላቅ ድምቀት በሀዋሳ ከተማ የተካሄደው 10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ !
የካቲት 7/2018 ዓ.ም
የልዩ ዘመቻ ዕዝ የተመሰረተበትን 65ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ጠዋት በሀዋሳ ከተማ የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል
በውድድሩ ላይ በርካታ ታዋቂ አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን፣ 222 ወንዶች፣ 80 ሴቶች በድምሩ 302 ኤሊት አትሌቶች በውድድሩ ላይ ተሳትፈዋል ።
በተጨማሪም ከ10,000 በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች በውድድሩ ላይ መሳተፍ ችሏል ።
በውድድሩ ከ1-5 አሸናፊ ለሆኑ አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች ከፍተኛ የተባለውን የገንዘብ ሽልማት ተሸላሚ ሆኗል ።
በዚህም መሰረት የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ውጤት :-
የወንዶች ውድድር
1ኛ አትሌት ቢኒያም መላክ ከፀደይ ባንክ 500 ሺህ ብር
2ኛ አትሌት ሣሙኤል ፍሬው ከሲዳማ ቡና 250 ሺህ ብር
3ኛ አትሌት አብዱሰላም ወርቁ በግል 100 ሺህ ብር
በሴቶች ውድድር
1ኛ አትሌት ውድነሽ ዓለሙ ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን 500 ሺህ ብር
2ኛ አትሌት ፅጌ ገብረስላማ ኢትዮ ኤሌክትሪክ 250 ሺህ ብር
3ኛ አትሌት ዝማም ማራኪ በግል 100 ሺህ ብር አሸንፈዋል።

በመዋኛ ገንዳ ውስጥ የሚገኝ የዘር ፍሬ እና የእርግዝና ስጋት
#fastmereja I በመዋኛ ገንዳ ውስጥ የሚንሳፈፍ ወይም የሚፈስ የዘር ፍሬ በውሃው ውስጥ አልፎ አንዲትን ሴት ሊያስረግዝ የሚችልበት ዕድል በሳይንሳዊ መንገድ የለም ለማለት ይቻላል። ለዚህም ዋና ዋና የሕክምና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡-
አብዛኛው የመዋኛ ገንዳዎች ንጽህናቸውን ለመጠበቅ በክሎሪን የታከሙ ናቸው። ክሎሪን ደግሞ የዘር ፍሬን በሰከንዶች ውስጥ የመግደል አቅም አለው። የዘር ፍሬው በውሃው ውስጥ እንዳረፈ ወዲያውኑ ስለሚሞት የማርገዝ አቅሙን ያጣል።
የዘር ፍሬ በሕይወት ለመቆየት እና ለመንቀሳቀስ በጣም ጥብቅ የሆነ የአየር ሙቀት እና የፈሳሽ ኬሚካላዊ ይዘት (pH balance) ይፈልጋል። ከሰውነት ውጭ በሆነ ውሃ ውስጥ ሲቀላቀል፣ የሴሎች መፈንዳት ስለሚከሰት በደቂቃ ውስጥ ይሞታሉ።
አንድ የዘር ፍሬ እርግዝና ለመፍጠር በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ቁጥር ተሰባስቦ መጓዝ ይኖርበታል። በመዋኛ ገንዳ ውስጥ ግን የዘር ፍሬው ወዲያውኑ ስለሚበታተን፣ አንዲት ሴት ማህፀን ውስጥ ገብቶ እርግዝና ለመፍጠር የሚያስችል ትኩረት አይኖረውም።
የዘር ፍሬው በራሱ ተንሳፍፎ በውሃ ውስጥ አልፎ፣ የሴቷን ብልት አልፎ፣ ወደ ማህፀን በር የመግባት አቅም የለውም። በተጨማሪም የሴት ብልት የራሱ የሆነ የመከላከያ ፈሳሽ ስላለው፣ በውሃ ውስጥ የሚገኝን ደካማ የዘር ፍሬ በቀላሉ አያስተናግድም።
ምንም እንኳ በውሃ ላይ የሚንሳፈፍ የዘር ፍሬ እርግዝና ባያስከትልም፣ በውሃ ውስጥ (በገንዳው ውስጥ) ቀጥተኛ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ከተፈጸመ ግን እርግዝና ሊከሰት ይችላል። ምክንያቱም በዚህ ጊዜ የዘር ፍሬው ከውሃው ጋር ሳይገናኝ በቀጥታ ወደ ማህፀን ስለሚገባ ነው።
#ጤና

7 months ago
የደሃ ሃገር ወጣት I ShowSpeed ን አይኮርጅም !
(የኔ ምልከታ) #ethiopia | አይሾውስፒድ 'Contentless Content' ይዞ ጥድፊያና ሁካታ ወዳድ የዓለም ዜጎችን እያስከተለ ያለ ለጋ ወጣት ነው፡፡ ዓለም የጥድፊያ እና ሁካታ (speed and chaos) መድረክ ናትና ሁካታ ወዳድ ዜጎች ቢኖሯት አይገርምም፡፡ ስፒድም መቶ ቀርቶ ሁለት መቶ ሚሊዮን ተከታይ ቢኖረውም አይደንቅም፡፡ ፍላጎት ባለበት አቅርቦት አትራፊ ነው፡፡
ባልቲሞር ውስጥ በሚገኘው የጥንቱ የቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን በ1692 ዓ.ም ተጠቅልሎ የተገኘ ዴዜዴራታ የሚባል መመሪያ እንዲህ ይላል፡፡ "በዚህ ዓለም ጥድፊያና ሁካታ ሳትበገር በርጋታ ኑር"
ዴዜዴራታ ካዛሬ 300 ዓመት በፊት የዓለምን ‘የጥድፊያና ሁካታ’ መንደርነት መዝኖ ነው በዚህ ውስጥ ለመኖር እርጋታ በጣም አስፈላጊ መሆኑን የመከረው፡፡ ረጋ ያሉ ብቻ ጥድፊያውንና ይዞት የሚመጣውን ደራሽ በዘዴ ያልፉታል፡፡
ስፒድ [ኮንቴንት ከተባለ] ኮንቴንቱ 'ጥድፊያ እና ሁካታ' ብቻ ናቸው፡፡ 'በክዋኔም፣ በንግግርም “ጥድፊያ”ን በማሳየት ነው ብራንዱን የቀረጸው ፡፡ ያንን ደግሞ ከጩኸት (ሁካታ) ጋር አስተሳስሮታል፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ኢነርጂ (ጉልበት) ጨምሮበታል፡፡ እነዚህ ሶስቱ ሲቀናጁ የርሱን ኮንቴንት ፈጥረዋል፡፡
ስለዚህ መረጋጋት የስፒድ መለያ አይደለም፡፡ ይጮሃል እንጂ አያወራም፣ ይሮጣል እንጂ አይቆምም፡፡ ዘፈቀደ እንጂ የተሰተረ ነገር (setup) አይወድም፡፡ በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ምንም መስራት አይችልም፡፡ ትክክለኛው የዚህ ዓለም ጥድፊያና ሁካታ መገለጫ ይሄ ልጅ ነው፡፡
ይህ ልጅ በልጅነቱ ወላጆቹ ‘ስፒድ’ የሚል ቅጥያ ስም ያወጡለት አለነገር አይመስለኝም፡፡ በተፈጥሮው Hyperactive የሚባል አይነት ሰው እንደሆነ ያስታውቃል፡፡ ሰውነቱ የሚያመነጨው የሚያስጨንቅ ኢነርጂ አለው፡፡ ያንን ኢነርጂውን በጩኸት እና በጥድፊያ ያወጣዋል፡፡ እሱን የሚያረጋጋውም ይኸው ነው፡፡
ባለሙያ ባልሆንም ጥቂት በማውቃት ሳይንስ ልክ …ስፒድ በግልጽ የሚታይ ADHD የተባለ የትኩረት ማጣት እና መቅበጥበጥ (አለመረጋጋት) የሚያስከትል Disorder እንዳለበት የሚያሳብቁ ምልክቶችን አይቼበታለሁ፡፡ ተረጋግቶ ቁጭ አለ ስትለው ድንገት እንደእንቁራሪት እንጣጥ ይላል፡፡ ስላሴ ቤተክርስቲያን ሲገባ የሆነውንና ያሳየውን ድርጊት ካያችሁት በቂ ነው፡፡ ያንን የተረጋጋ ስፍራ ለሰከንዶች መልመድ ተቸገረ፡፡ ራሱን ለመቆጣጠር ሲሞክር ይታያል፡፡ ውስጡ እምቢ ሲለውና ሲዘል አያችሁት፡፡ ብቻውን ጣቶቹን እየፈተለ በማይሰማ ድምጽ እያነበነበ ነበር፡፡ ከዚያ እንደወጣ የተጠራቀመ ኢነርጂውን እንዴት እንዳወጣውም ታዝባችኋል፡፡
ስፒድ ኮንተንቱን እንዲሰራ የሚመቸው ጫጫታና ጩኸት እንጂ ዝምታና እርጋታ አለመሆኑን ግብጽ ጊዛ ፒራሚዶች ውስጥ ከነበረው ‘ቶታል ሸትዳውን’ ትረዳላችሁ፡፡ የርሱ ተከታዮችም የሚፈልጉት ሁካታ ስለጠፋ ያኔ ቁጥራቸው ዝቅተኛ ነበር፡፡
በዚህ ዘመን የሰለጠነ ሃገር ውስጥ በተለይ በምዕራቡ ስልጣኔ ውስጥ ላለ ዜጋ እርጋታና ቁምነገር ቦታ የላቸውም፡፡ ምክንያቱም ያንን የርጋታ 'ስቴጅ' በትውልድ ቅብብል አልፎት መጥቷል፡፡ የህዝቡ ኑረት ከባህል፣ ወግ እና ልማድ አፈትልኮ ወጥቶ በግል አዳሪነት ላይ ተመስርቷል፡፡ ማህበረሰባዊ ደንብ የሚባል ነገር የለም፡፡ እንደእብድ ውሻ መክለፍለፍን ከምንም በላይ ዋጋ ሰጥቶ ያያል፡፡ አብርሃም ማስሎው የሰው ልጅ ፍላጎቶችን በ5 ደረጃዎች የተነተነበት ‘ማስሎው ቲየሪ’ እንደሚነግረን ከሆነ አብዛኛው በምዕራቡ ስልጣኔ ውስጥ የሚኖረው ዜጋ አሁን ያለበት ደረጃ 4ኛው “እውቅናና ክብርን ለማግኘት” የመፈለግ’ ደረጃ ነው፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት ያሉትን ሶስት ደረጃዎች በአብዛኛው አሟልቶ ‘ሳቹሬት’ አድርጓል፡፡ምግብ መጠለያ ሰላም ፍቅር ወዘተ አያሳስቡትም፡፡ ስለዚህ ዛሬ ለእርጋታና ስክነት ቦታ የለውም፡፡
ይኼ የዕድገት ‘ኢቮሉሽን’ ይዞት የመጣ ክስተት ነው፡፡ በዚህ የ GEN Z ዘመን ስክነት አይፈለግም፡፡ ባህሉና ስሪቱ ፍጥነት እና ጥሶ መሄድ ብቻ ነው ፡፡ አለም ዴዜዴራታ በተጻፈበት ዘመን ከተገለጸችበት በከፋ ሁካታና ጥድፊያ ውስጥ ናት፡፡ ስፒድ ይህንን የትውልዱን ይዘት ይዞ ቢመጣ፣ ሚሊዮን ቀርቶ ቢሊዮን ተከታዮችን ቢያፈራም አይደንቅም፡፡
እኔን ብዙዎቻችን ካደግንበት እና ከኖርንበት ባህል እና አስተዳደግ አንጻር አይደለም የአዲሱን ዘመን ጥድፊያ እና ሁካታ እየመንኩ ያለሁት፡፡ “ገና ባልደረስንበት ደረጃ ላይ ስንንጠላጠል ያልረገጥናቸው ደረጃዎች እንዳይክዱን እንጠንቀቅ” ነው እያልኩ ያለሁት፡፡ ማንንም በማይጠቅም የዲጂታል ጩኸት ላይ የተጠለፈውን ትውልድ የምመክረውም ይህንኑ ነው፡፡እንዳለመታደል ደንብና ህግ በሌለባት ሃገር ኢንተርኔት ይዞት የመጣውን ሁሉ ‘አዳፕት’ እንዲያደርግ ክፍቱት የተተወ የወጣት ጭንቅላት ስለስራ ማሰብ እየተሳነው እያየን ነው፡፡
ድሆች ነን፡፡ እንደህዝብም እንደሃገርም ከጩኸትና ሁካታ በፊት ገና ብዙ መስራት ያለብን የቤትስራዎች ይጠብቁናል፡፡ ከላይ በገለጽኩት ምክንያት ስፒድን የሚከተለውን 90 ምናምን ሚሊዮን የሞላለት የሰለጠነ ሃገር ህዝብ አይተን ‘ዘመኑ የሚጠይቀው ይህንን ነው’ ማለትና ያንኑ እዚህ አምጥቶ ‘ባህል’ ለማድረግ መሞከር ልክ አይደለም፡፡ የሰለጠነው ዓለም ዛሬ "ባዶ ቅል እና የሚንሸዋሸው ናስ' ለሚያወጣው ትርጉምየለሽ ድምጽ በጣም ያጋደለው እኛ ዛሬ ያለንበትን ደረጃ ለፍቶበት፣ ፈጥሮበት፣ ሰርቶበትና ተጠቅሞበት አልፎ ነው፡፡
ሰርቶ፣ ፍሬውን አፍርቶ፣ ጎተራ ከትቶ፣ ራሱን ከድካም አላቅቆ፣ ለልጆቹ ቀላል ህይወትን ሰጥቶ ያለፈ የቀደመ ትውልድ ነው ይህን ‘የአይሾው ስፒድ’ ተከታይ የሆነ ሚሊዮን ግሪሳ ወጣት የፈጠረው፡፡ ለብዙ መቶ አመታት በፈጠራ አዕምሮውን አስጨንቆ፣ በጠንካራ ጉልበት ፋግሮ ሃገር ሰርቷል፡፡ ስርዓት ገንብቷል፡፡ ለሚቀጥሉት ብዙ መቶ አመታት እሱና ትውልዱ የሚኖሩበትን ትሩፋት አጠራቅሟል፡፡ በዚህ ሳቢያ ዛሬ ጥያቄው እንደኛ ምግብና ሰላም ሳይሆን ‘መታወቅ’ ብቻ ነው፡፡'አይረቤ ጉዳይ ላይ' ተጠምዶ የምታዩት የልፋቱን ገጽ ስላለፈውና የእረፍቱ ገጽ ላይ ስለደረሰ ነው፡፡ ‘ኢቮሉሽኑ’ እዚህ አድርሶታል፡፡
እናም እንዳትሳሳቱ! የሰለጠነው አለም ህዝብ በጩኸትና ሁካታ ተጠምዶ ስታዩት ስሪቱ ከጅምሩ ይህ ሆኖ አይደለም፡፡ መዝናናትን የቅንጦት አድርጎ እስኪቆጥር ድረስ ላቡ ጠብ እስኪል ሰርቶ፣ ‘ኮንፋይንድ' ብቻውን አውርቶ ነው፡፡ ዛሬ በአደባባይ እንደውሻ መጮህን የሚያደንቀውና የሚያዳንቀው ያንን ደረጃ ስላለፈው ነው፡፡
እኛ ግን ገና ነን፡፡ በአይረቤ የባዶ ቅል ጩኸት ለመመሰጥ ገና ነን፡፡ ገና ምግብ አጥተን እየራበን ነው፡፡ ገና ስራ አጥተን እየደኸየን ነው፡፡ ገና ትምህርት አጥተን እየደነቆርን ነው፡፡ ገና ሰላም አጥተን እየተዋከብን ነው፡፡ ገና ገና ገና ብዙ ገናዎች አሉን፡፡ ያለንበት ደረጃ ሁሉን ትተን ለመዝናናትና ለመንዘፍዘፍ የሚያበቃን አይደለም፡፡
ስለዚህ ስፒድን ምሳሌ እያደረጋችሁ “ዘመኑ የቁምነገር አይደለም ፣ የትምህርት አይደለም፣ የስራ አይደለም፣ የልፋት አይደለም፣ የአቋራጭ 'ኮንተንት አልባነት ዘመን ነው “ የምትሉ ሰዎች ከዚህ ጠማማ መፈክራችሁን ተግ በሉ !
የቆማችሁበትን የአሸዋ መድረክ ስታዩት ዛሬ የምታዘናጉትና የምታዳንቁት የዲጂታል ትውልዱ ‘አልባሌነት’ የሚያስከፍለን የነገ ዋጋ ይገባችኋል፡፡ የቤትስራውን ጨርሶ ከሚዝናና አስተማሪ ጋር ዝላይ የሚጫወት ተማሪ መጨረሻው ተማሪም አስተማሪም እንዳይሆን በዚያው ተሰባብሮ መቅረት ብቻ ነው፡፡ እነሱና እና የሌለ ልዩነት ላይ ነን፡፡ አይናችሁን ግለጡ፡፡ አሁን ባለንበት ደረጃ ከአይሾው ስፒድ ወጣቶቻችን የሚወስዱት ትምህርትም የሚቀስሙት ልምድም የለም፡፡
ወጣቶች የስፒድን 'ኮንቴንት' እንደትሬንድ ይዘው ጥድፊያና ሁካታ ውስጥ መግባት ልክ ነው ብለው ማሰባቸውን አታበረታቱ፡፡ እንደውሻ እየጮህን ሃገራችንን እናስጠራለን ያለ ጨበሬ አይቻለሁ፡፡ በምታዳንቁት የዲጂታል ትውልድ ዘንድ እንግዲህ ሃገር ማስጠራት ትርጉሙ ይህ ነው፡፡
ሃገር ተረካቢ ናቸው ሲባሉ ትምህርትም ስራም ትተው ቤት የተቀመጡና ምንም ሳይሰሩ ስኬትን በላይክ እና ኮሜንት ብቻ የሚመዝኑ የድቡሽት ላይ ጎጆዎች በዝተዋል፡፡ በመሰረቱ እነሱም ስፒድ ለማንም ምንም አይጠቅሙም፣ ጠቅመውም አያውቁም፡፡ ከጠቀሙ ለራሳቸው ብቻ ነው፡፡ ተከታዮቻቸው ላይ እንጀራ ይጋግራሉ፡፡ አለቀ!!
ሃገር የሚያተርፈውና ራሱም የሚተርፈው ትውልድ በዲጂታሉ አለም መማርና ከረሱ አልፎ የሌሎችን ሀይወት መለወጥ የሚችል ኮንቴነት ይዞ የሚመጣው የነቃ ትውልድ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የደሃ ሃገር ወጣት ስፒድን አይኮርጅም፡፡ ስፒድ አባቶቹ የሰሩለት የተጠናቀቀ ሃገር ያለው ልጅ ነው፡፡ ሌላ ስራ የለበትም፡፡ እኛ ገና ራሳችን ሃገራችንን እንድንሰራ የምንጠበቅ የደሃ አባቶች ልጆች ነን፡፡ ከጥድፊያና ሁካታ በፊት በጣም ብዙ ስራ አለብን፡፡ ሃገርን ድቡሽት ላይ የሚገነባ ነገ መጠለያ ያጣል፡፡
ይመቻችሁ !!
መላኩ ብርሃኑ

8 months ago
የትርታ ሬዲዮ የሲዲ ስፖርት የስፖርት ጋዜጠኛ የሆነው አሉላ ፍሬው በአርሰናል ደጋፊ ስልኩ እንደተወሰደበት ገለጸ። "አንድ የአርሰናል ደጋፊ መጀመሪያ አድናቆት መስሎኝ ነበር ግን አይደለም አንተ የማንችስተር አቀንቃኝ በማለት ሊጣላኝ ወደ እኔ መጣ፣ ከዛ ጸብ ተጀመረ በዚህ መሃል ሳምሰንግ S24 አልትራን ወሰደብኝ፣ በጣም አዝኛለሁ ለበጎ ነው! እነሱ በማያውቁን እኛ እዚህ ሀገር ውስጥ እዚህ ደረጃ መድረሳችን ያሳዝናል" ብሏል።
8 months ago
የስፖርት ጋዜጠኛው አሉላ ፍሬው የአርሰናል ደጋፊዎች ማንችስተር ዩናይትድ እየቋጠሩ ነው ሲል በምሬት ተናገረ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊ እንደሆነ የሚናገረው ጋዜጠኛው
"አለም እየቋጠረበት ያለው ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ነው። ኧረ ማርያምን ይደብራል፣ አርሰናል ለዋንጫ ነው የሚጫወተው አይደል? ማንችስተር ዩናይትድ ለሻምፒየንስ ሊግ ነው የሚጫወተው። በቃ ምንድነው ተውን በቃ!" ብሏል።
"አለም እየቋጠረበት ያለው ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ነው። ኧረ ማርያምን ይደብራል፣ አርሰናል ለዋንጫ ነው የሚጫወተው አይደል? ማንችስተር ዩናይትድ ለሻምፒየንስ ሊግ ነው የሚጫወተው። በቃ ምንድነው ተውን በቃ!" ብሏል።
Sponsored by
Surafel
8 months ago
ሰክሰስ ፕላስ ድርጅት በሲዳማ ክልል ለሚገኙ የአካል ጉዳተኞች 100 የዊልቸር ድጋፍ አደረገ።
የስጦታ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በሴቶችና ማህራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ክብርት ሁሪያ አሊ በአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚሠሩ ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባቸው ገልፀዋል።
የአካል ጉዳተኞችን መብት የማስከበር ፣ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ የሁሉንም ኃላፊነት ይጠይቃል ብለዋል። ሚኒስቴር መስሪያቤቱም ድጋፎች የታለመለትን አላማ እንዲያውሉ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል ።
የሰክሰስ ፕላስ ሀገር በቀል የተራድኦ ድርጅት መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍሬው በበኩላቸው ድርጅቱ ከተመሠረተ ሁለት አመት ያስቆጠረ ቢሆንም የአካል ድጋፍ መሳሪያዎችን በተለይም ዊልቸር በመስጠት ላይ እንዳለ ጠቁመዋል። የተጀመሩ ድጋፎችንም ለመቀጠል ቃል ገብተዋል።

Comments