ወደ ስራ ገበታዬ እንዳልገባ በጥበቃ ከበር ተባረርኩኝ - አሉላ
የስፖርት ጋዜጠኛ አሉላ ፍሬው በሃይማኖታዊ አቋሙ እና በሰጠው አስተያየት ምክንያት ከስራ ገበታው መታገዱን ገለጸ።
እንደ ጋዜጠኛ አሉላ ገለጻ ከሆነ፣ ለዚህ እገዳ ዋነኛው ምክንያት በቅርቡ በነበረው የሲዲ ስፖርት ፕሮግራም ላይ በኤቨርተን እና በማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታ ትንታኔ ወቅት የሰጠው የግል አስተያየት ነው።
ጋዜጠኛው በወቅቱ፦ "የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ እና የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊ ካልሆነች ሴት ጋር ትዳር አልመሰርትም"።
ማለቱን ተከትሎ በጣቢያው ጊዜያዊ ስራ አስኪያጅ ውሳኔ ከስራ ገበታው እንዲታገድ መደረጉን ገልጿል።
አሉላ ፍሬው ለተከታዮቹ ባስተላለፈው መልእክት ፤የጣቢያው ውሳኔ የግል አቋሙን እንደማያስቀይረውና በእምነቱ እንደሚጸና ገልጿል።
የተላለፈው ውሳኔ የጣቢያውን ባለድርሻ አካላት በሙሉ የማይወክልና የጊዜያዊ ስራ አስኪያጇ የግል አመለካከት ውጤት እንደሆነ ገልጿል።
ይህ ችግር በአስቸኳይ የማይፈታ ከሆነ፣ በብዙዎች ዘንድ በሚወደደው "ሲዲ ስፖርት" ፕሮግራም ላይ የመሳተፍና ትንታኔዎችን የማቅረብ እድሉ አደጋ ላይ መውደቁን ጠቁሟል።
seledadotio

4 months ago