“ፍሬው” የተሰኘ አዲስ ቲያትር ለእይታ ሊቀርብ ነው
#ethiopia | በተሻለ ወርቁ ተደርሶና ተዘጋጅቶ የቀረበው አዲሱ “ፍሬው” የተሰኘ ቲያትር የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ፍላሚንጎ በሚገኘው አዲሱ የህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት በድምቀት ይመረቃል።
በናታይ ጌታቸው እና በሞሪያድ ኢቨንት ፕሮዲውሰርነት የቀረበው ይህ ተውኔት አንጋፋዎቹን ተሻለ ወርቁንና ካሳሁን ፍስሃን (ማንዴላ) ጨምሮ ሰለሞን ሙሄ፣ ናታይ ጌታቸው፣ የምስራች ግርማ እና ህሊና ደረጄን የመሰሉ ተወዳጅ ተዋናዮችን በአንድ መድረክ ያሳያል።
ቲያትሩ ከመዝናኛነት ባለፈ የላቀ የጥበብ ልምድ የሚቀሰምበት መሆኑን የገለጹት አዘጋጆቹ ታዳሚዎች ትኬቶችን በአሐዱ ባንክ ቅርንጫፎች፣ በግራንድ ኩዳ፣ በባኮስ ላውንጅ፣ በባልደራስ ስፖርት ባር ወይም በዕለቱ በበሩ ላይ ማግኘት እንደሚችሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
#ferew #newplay #addisababatheater #ethiopianart #comedyshow #weekendvibes

2 months ago