27 days ago
“8 ሰዓት ተኙ’ የሚለውን ምክር በፍጹም አትቀበሉ” – አቶ ዘነበ ፍሬው
#ethiopia | «እኔ ቀደም ሲል በቀን 3 ሰዓት ብቻ ነበር የምተኛው። አሁን ግን ትንሽ ጨምሬያለሁ። 4 ወይም 5 ሰዓት እንቅልፍ በቂ ነው፤ ቢበዛም ከ6 ሰዓት በላይ መተኛት አያስፈልግም። ምክንያቱም እኛ ገና ድሆች ነን፤ ከእጅ ወደ አፍ፣ ከአፍ ወደ ሆድ የምንኖር ሰዎች ነን። በትጋት ሰርተን ሕይወታችንን ከቀየርን በኋላ ግን ያን ጊዜ የበለጠ ማረፍ ይቻላል” ብለዋል አቶ ዘነበ ፍሬው»
አቶ ዘነበ ፍሬው በኢትዮጵያ በጠንካራ የሥራ ፈጣሪነት አስተሳሰባቸው ከሚታወቁ የቢዝነስ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው። ከልጅነታቸው ጀምሮ በተለይም በመርካቶ አካባቢ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ውጤታማ የሆነ የሥራ ጉዞ አድርገዋል።
በአሁኑ ጊዜም በሪል እስቴት፣ በውሃና ፕላስቲክ ማምረት፣ በብረት ማቅለጫና በሚስማር ማምረቻ ኢንዱስትሪ የተሰማሩ ሲሆን፣ በቅርቡም ወደ አገልግሎቱ ዘርፍ [እንደገና] በመግባት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን እያስፋፉ ነው።
አቶ ዘነበ ፍሬው በሃዋሳ ከተማ መግቢያ 75 በመቶ የተጠናቀቀ ሪዞርት እየገነቡ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም በቡኢ ከተማ ሌላ የሪዞርት ፕሮጀክት ግንባታ መጀመራቸውንም ከ«መሪ ፖድካስት» ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።
ሶዶ ለማ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #zenebefirew #realestate #resort #enterpreneur #enterpreneurmindset

Comments