Logo
Getu Temesgen
የኀዘን መግለጫ
#ethiopia | ‌‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የዩኒቨርስቲ ደህንነት ጥበቃ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ የነበሩት ረዳት ኮሚሸነር በላይ ከበደ ፍሬው መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

‎ረዳት ኮሚሽነር በላይ ከበደ በሥራ ዘመናቸው ተቋማቸውንና ህዝባቸውን በታታሪነት፣ በታማኝነትና በቅንነት ሲያገለግሉ የቆዩ አመራር ነበሩ።

‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በረዳት ኮሚሽነሩ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

‎የረዳት ኮሚሽነሩ የቀብር ሥነ-ሥርዓት መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከ8፡00-9፡00 በመካኒሳ አቦ ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቻቸውና የሥራ ባልደረቦቻቸው በተገኙበት ይፈፀማል፡፡

Via EFP

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.