2 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የጀርመን የጂኦ-ሳይንስ ምርምር ማዕከል ባወጣው መረጃ መሰረት፣ በግብጽ የ5.4 ማግኒቲዩድ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ ከመሬት ወለል በታች 10 ኪሎ ሜትር (6 ማይል) ጥልቀት ላይ የተከሰተ መሆኑን ማዕከሉ አረጋግጧል።
የመሬት መንቀጥቀጡ በግብጽ ብቻ ሳይወሰን፣ አቋርጦ በማለፍ በደቡባዊ እና መካከለኛው እስራኤል ክፍሎችም ድረስ በስፋት ተሰምቷል።
የግብጽ ቀይ ጨረቃ ማህበር አደጋው በተሰማባቸው ግዛቶች ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ እቅዱን ወደ ተግባር ማስገባቱን አስታውቋል። ይሁን እንጂ ማህበሩ እስካሁን ባለው መረጃ የደረሰ የሰው ህይወት መጥፋትም ሆነ የንብረት ውድመት ሪፖርት እንዳልደረሰው ገልጿል።
ባለሥልጣናቱ አጠቃላይ ሁኔታውን ማጣራታቸውን እስኪጨርሱ ድረስ፣ ነዋሪዎች የመሰነጣጠቅ ወይም የጉዳት ምልክት ከሚያሳዩ ሕንፃዎች ርቀው እንዲቆዩ እና ይፋዊ መረጃዎችን ብቻ እንዲከታተሉ ቀይ ጨረቃ ማህበር አጥብቆ አሳስቧል።

3 days ago
ለጥገና ሥራ የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናዎን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦
✅ ከጠዋቱ 2፡00-11፡00
👉ቀጨኔ ሰብስቴሽን፣ችሎት አደባበይ፣ ሰሜን ማዘጋጃ፣ ሸገር መናፈሻ፣ ዕንቁላል ፋብሪካ፣
👉አባዲና፣ ሩፋኤል ቤ/ክ፣ ሚኒሊክ ሆስፒታል፣ ጀርመን ድልድይ፣ እና አካባቢው፣
👉 ጋርመንት፣ በግ ተራ፣ ጎፋ ካምፕ ኮንዶሚኒየም፣ ጀርመን አደባባይ፣ ካፍ ነዳጅ ማደያ እና አካባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 2፡00 - 10፡00
👉 ሳሪስ ነጋ ቦንገር፣ ጀሶ ፋብሪካ፣ ብሔረፅጌ፣ ቆዳ ፋብሪካ ፣ ፓስታና መኮረኒ እና አካባቢው፣
✅ ከጠዋቱ 2፡00 - 10፡00
👉በወልዲያ ሪጅን አዳጎ፣ ውድሜን፣ ሰዋሜዳ፣ ውርጌሳ፣ጊራና እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪ መለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

4 days ago
የአርሰናል ደጋፊዎችን የሚያገናኝ "ገነርስ" የተሰኘ ማህበር ተመሠረተ
#ethiopia | የእግር ኳስ ፍቅርን ከአባላት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ጋር የሚያስተሳስረው አዲሱ ዓለም አቀፍ ተቋም "ገነርስ"የሚል ስያሜ የተሰጠው ማህበር በኢትዮጵያ፣ በጀርመን እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መሠረቱን ጥሎ በይፋ ሥራ መጀመሩን አሳወቀ።
ተቋሙ በአለም ዙሪያ የሚገኙ የአርሰናል ክለብ ደጋፊዎችን በአንድ ጠንካራ ማህበረሰብ ስር በማሰባሰብ፣ አባላቱ በህይወታቸው እርስ በርስ እንዲደጋገፉ እና አዲስ የዕድል በሮች እንዲከፈቱላቸው የሚያስችል ዘላቂ ስርዓት ዘርግቷል።
ከደጋፊነት ማዕቀፍ ባለፈም ከመንግስታዊ እና ከግል ተቋማት ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት በመመስረት ለአባላቱ ተጨባጭ ጥቅሞችን፣ የሥራ ዕድሎችን እና የንግድ አማራጮችን ለማስፋፋት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።
አባላቱ በዕለት ተዕለት ኑሯቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሰፊ አገልግሎቶችን የሚዘረጋው ገርነስ ማህበር ፤ ከግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች ግብይት ጀምሮ እስከ ጤና፣ ሆቴል፣ ቱሪዝም እና የጉዞ አገልግሎቶች ድረስ በተመረጡ አጋር ተቋማት ልዩ ቅናሾችንና መስተንግዶዎችን እያቀረበ ይገኛል።
ከዚህም በተጨማሪ አባላትን የሚያዝናኑ፣ ጠቃሚ መረጃዎችን የሚያጋሩ ሳቢ የዲጂታል ሚዲያ ይዘቶችን በማዘጋጀት የማህበረሰብ ትስስሩን ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመድረኩ ላይ ተገልጿል።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#gunners #arsenal #arsenalethiopia #gunners #ethiopiangunners

5 days ago
📞✨ዲያስፖራው ባለበት ሁሉ ኢትዮ-ኮል እየመጣ ነው!
ማንኛውንም የሞባይል ወይም የመደበኛ ስልክ ላይ በታላቅ ቅናሽ መደወል ያስችላል።
🇺🇸 አሜሪካ 🇮🇱 እስራኤል
🇨🇦 ካናዳ 🇾🇪 የመን
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ 🇰🇪 ኬንያ
🇮🇹 ጣሊያን 🇩🇪 ጀርመን
🇮🇳 ሕንድ 🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇷🇼 ሩዋንዳ 🇸🇴 ሶማሊያ
መተግበሪያውን ያውርዱ: https://onelink.to/ethioca...
ወደ አገርቤት በቅናሽ ይደውሉ፤ በገዙት ጥቅል ደዋዮች ሳይቆጥርባቸው በነፃ ይቀበሉ!
#ethiocall #ethiotelecom #telebirr #telebirrsuperapp #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

የአየር ንብረት ለውጥ አውሮፓን እያመሰ ነው
* በከፍተኛ ሙቀት እና በሰደድ እሳት ሺዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል
#ethiopia | የአየር ንብረት ለውጥ በአውሮፓ ከፍተኛ ሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ-ምህዳራዊ ቀውስ እያስከተለ መሆኑን የቅርብ ጊዜ ዓለም አቀፍ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በሰኔ መጨረሻ እና በሐምሌ ወር የተከሰቱ ከባድ የሙቀት ማዕበሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሕልፈት ዳርገዋል፤ በበርካታ አገራት ደግሞ ሰደድ እሳቶች መኖሪያ ቤቶችን፣ ደኖችንና የግብርና መሬቶችን አውድመዋል።
የአውሮፓ በሽታ መከላከያ ማዕከል (ECDC) እና የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በሚደግፉት የEuroMOMO የሞት ክትትል መረጃ መሠረት፣ በሰኔ 22 እስከ 28 ቀን 2026 ብቻ ከ10 ሺህ በላይ ተጨማሪ ሞቶች ተመዝግበዋል።
ከእነዚህ ውስጥ ከ9 ሺህ በላይ የሚሆኑት ዕድሜያቸው 65 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ናቸው። ባለሙያዎች ይህን ያልተለመደ የሞት ጭማሪ በዋነኝነት ከከፍተኛ ሙቀት ጋር ያያይዙታል።
በጀርመን ብቻ በ2026 እስከ ሐምሌ መጨረሻ ድረስ 9,800 የሚጠጉ ከሙቀት ጋር የተያያዙ ሞቶች መመዝገባቸው ተገልጿል።
በእንግሊዝ ደግሞ 2,800 በላይ ሰዎች በሙቀት ምክንያት መሞታቸው ተነግሯል፤ ይህም የ2022 ሪከርድን ሊበልጥ እንደሚችል ባለሥልጣናት አስጠንቅቀዋል።
በፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ግሪክ፣ ጣሊያን እና ፖርቱጋል የተቀሰቀሱ ሰደድ እሳቶች በመቶ ሺዎች ሄክታር የሚቆጠር ደን እንዲቃጠል አድርገዋል።
በፈረንሳይ ብቻ ከ220 ሺህ በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፤ በግሪክ ደግሞ ሶስት የአደጋ አደራሽ ሠራተኞች በእሳት ማጥፋት ስራ ላይ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ሳይንቲስቶች እንደሚገልጹት፣ በሰኔ መጨረሻ የተመዘገበው የሙቀት ማዕበል የሰው ልጅ የፈጠረው የአየር ንብረት ለውጥ ባይኖር ሊከሰት ፈጽሞ የማይችል ነበር።
አውሮፓ በዓለም ላይ ከሌሎች አህጉራት በበለጠ ፍጥነት እየሞቀች ያለች አህጉር መሆኗም ችግሩን እያባባሰው ነው።
በዚህ ሁኔታ የአውሮፓ መንግሥታት የሙቀት አደጋ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶችን ማጠናከር፣ ለአረጋውያንና ለተጋላጭ ማኅበረሰቦች የጤና ጥበቃን ማሳደግ፣ እንዲሁም የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ የበለጠ ቁርጠኛ እርምጃ እንዲወስዱ ተጠይቀዋል።
በሌላ በኩል፣ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በ"አረንጓዴ ዐሻራ" መርሃ ግብር ባለፉት ሰባት ዓመታት ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የደን ሽፋኗን ለማሳደግና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ ጥረት እያደረገች ትገኛለች።

11 days ago
ዘማሪት ኢየሩሳሌም አየለ «የጄሪ ጩኮ»ን ጨምሮ ባህላዊ ምግቦችን ለኤክስፖርት አቀረበች!
#fastmereja I ታዋቂዋ ዘማሪ ኢየሩሳሌም አየለ (ጄሪ) የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦችን(ጩኮ) እና የቅመማ ቅመም ምርቶችን ለውጭ ሀገር ገበያ (Export) ለማቅረብ ያዘጋጀችውን አዲስ የንግድ ስራ እና የምርት አይነቶች በይፋ አስተዋወቀች።
በእናትና አባቷ የሼፍነት ሙያ እና በቤተሰብ የሙያ ውርስ ላይ ተመስርቶ የተጀመረው ይህ የንግድ ስራ፤ በዋናነት «ጄሪ»በሚል የምርት ስም የሚታወቅ ሲሆን፣ የቦቆጂን የሳር እና የጦስኝ ለጋ ቅቤ በመጠቀም የተዘጋጀውን «የጄሪ ጩኮ» ጨምሮ አነባበሮ፣ በቅቤ የታሸገ ቆሎ፣ ዳጣ እና ሚጥሚጣን ለገበያ አቅርቧል።
ዘማሪ ኢየሩሳሌም እንደገለፀችው፣ ምርቶቹ ሙሉ በሙሉ በቤት ውስጥ በከፍተኛ ንፅህና እና ጥንቃቄ በራሳቸው እጅ የሚዘጋጁ መሆናቸዉን ገልፃለች።
ዘማሪ እየሩሳሌም አክላም ምርቶቹ አለም አቀፍ የኤክስፖርት መስፈርትን (Export Standard) አሟልተው የተሰሩ በመሆናቸው ቀዝቃዛ ቦታ ላይ በመጠበቅ ከ1 ወር እስከ 1 ዓመት ድረስ ሳይበላሹ መቆየት እንደሚችሉ ገልፃ በተለይም በቅቤ የታሸገው ቆሎ የምርቱን ትኩስነት እና ጥራት ለመጠበቅ ሲባል በልዩ ትዕዛዝ ብቻ የሚዘጋጅ መሆኑ ገልፃለች።
የምርቱ"ዋና አላማ ከሀገር ውስጥ አልፎ የኢትዮጵያን ባህላዊ ጣዕሞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስተዋወቅ ነው" ስትል የተናገረችው ዘማሪ ኢየሩሳሌም፤ በአሁኑ ወቅት ወደ ካናዳ፣ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ እና ጀርመን ምርቶቹን ለመላክ የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ገልጻለች።
በአሁኑ ወቅት በቤተሰብ ደረጃ እየተከናወነ የሚገኘው ይህ ኢንተርፕራይዝ፣ ስራው ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ድካም የሚይዝ ቢሆንም ምርቶቹን ለተጠቃሚው በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ መታቀዱ ተገልጿል።
በመጨረሻም ድርጅቱ ወደፊት አቅሙን በማስፋፋት ለበርካታ ዜጎች ተጨማሪ የሥራ ዕድል የመፍጠር እና አዳዲስ ባህላዊ ምርቶችን ወደ ገበያ የማስገባት እቅድ እንዳለው ነዉ የተገለፀዉ።

Sponsored by
Surafel
13 days ago
ዛሬ የኢትዮጵያ የመጨረሻው ንጉሥ የልደት ቀን ነው
#ethiopia | ቁመታቸው ከ1 ሜትር ከ 60 ሴንቲ ሜትር አይበልጥም፣ክብደታቸውም ከ50 ኪግ የሚዘል አይደለም፡፡በጣም አጭር እና ቀጭን ነበሩ፡፡
ግን ግርማ ሞገሳቸው ልዮ ነው፡፡ ቤተሰቦቻቸው 8 ጊዜ ወልደው ከእርሳቸው በስተቀር አላደገላቸውም፡፡በእርግጥ እናታቸው ወይዘሮ የሺእመቤትም በልጅነታቸው ስለሞቱባቸው ያለ እናት፣በአባት ብቻ አድገዋል፡፡
አባታቸው ራስ መኮንን በባዶ እግራቸው በሮም አደባባይ ኢትዮጵያን ብሎም አፍሪካን የሸመገሉ መሪ ነበሩ።ግርማዊነታቸው ከአባታቸው ዲፕሎማሲን ተምረዋል፡፡በዓለም ላይ ከ 160 በላይ ሀገራትን የጎበኙ እሳቸው ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡የሁለተኛው የዓለም ጦርነት በአሜሪካ አሸናፊነት ሲያከተም፣የሂትለር ባድማ ጀርመን ዓለም ፊቱን አዞረባት፡፡ጀርመን እንደ ሲኦል መንደር ተቆጠረች፡፡ጃንሆይ ግን የተዘጋ በር ከፍተው ጀርመንን ጎብኝተዋል፡፡አስታርቀዋል፡፡አሜሪካ ከጆርጅ ዋሽንግተን እስከ ትራምፕ ድረስ 45 ፕሬዝዳንቶችን ሹማለች፡፡
እነዚህ ፕሬዝዳንቶች በሙሉ አየር ማረፊያ ድረስ ሂደው የሀገር መሪ አይቀበሉም፡፡ጃንሆይን ግን ፕሬዝዳንት ኬኔዲ መንገድ ወጥተው ተቀብለዋቸዋል፡፡ለጥቁር የነፃነት አውጭ ናቸው፡፡
ኤርትራን ከኢትዮጵያ አዋህደዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ከግብፅ ጣልቃገብነት ነፃ አውጥተዋል፡፡የፊውዳሊዝም ሥርዓትን አሻሽለዋል፡፡ስነፁሁፍ እንዲያድግ ነፃነትን ሰጥተዋል፡፡1960 ዎቹ ወርቃማው የስነፁሁፍ ዘመን ነበር፡።
የተፃፈ ህግን፣ ህገመንግስትን ጨምሮ አሰንደዋል፡፡ ከአፍሪካ ህብረት እስከ ተመድ ድረስ እንዲመሰረት ዋና ተዋናይ ነበሩ፡፡
የኒወክርክ ታይምስ ጋዜጣ ጃንሆይን የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ንጉስ አድርጎ ከማውጣቱም ባለፈ፣የኖቤል ሽልማት ሊሸለሙ እያለ በ 1953 ዓም በተነሳው አለመረጋጋት ምክንያት ሽልማቱ አልፏቸዋል ፡፡
የአፍሪካ መስራች ቢሆኑም፣ሀውልት ለጃንሆይ ሳይገነባ ለጋናዊው ክዋሜ ንኩርማህ ብቻ ተገንብቶ ቆይተዋል፡፡በሗላ ከመሸምቢሆን የአፍሪካ ህብረት የጃን ሀውልት በግቢው አቁሟል።
ለነባር ዕውቀት ዕድገት ተግተዋል፡፡
ጃንሆይ ለፈረንጅ የማያጎበድዱ ይልቁንም ጃንሆይ ና ህዝቦቻቸው ለነጭ ንቀት ያላቸው ብቸኛ የዓለማችን ሰዎች ናቸው ይላሉ ፈረንጀች፡፡እንዳውም ፈረንጆች አማርኛ ቋንቋ እንዲናገሩ ይገደዳሉ፡፡የኢትዮጲያን ባህል እንዲላበሱ ይወተወታሉ።
በእርግጥም ጃንሆይ፣ሀገር በቀል እውቀት እንዲለማ ከጣና ገዳማት እስከ አክሱም ፅዮን ያሉ አብያተክርስቲያናት እንዲታደሱ እና ለታሪክ ምርምር እንዲውሉ አድርገዋል፡፡
የዓለም ስልጣኔ መነሻው ውሃ እንደሆነ በመረዳት አባይን ከመገደብ ጀምረው ጣናን እስከ ማልማት እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር፡፡ግን በነሩሲያ የፖለቲካ ጫና እና በነጣሊያን ውስጣዊ ሴራ መክኗል፡፡
ለሙስሊም ህብረተሰብ የሀይማኖቱን ምሁራንን ከየአካባቢው በመሰብሰብ ቁርዐንን ከአረብኛ ወደ አማርኛ እንዲተረጉሙ ታላቅ ድጋፍ እና አስተዋፅዎ አድርገዋል።
ጃንሆይ ሀምሌ 16 ቀን 1884 ዓም በሀረርጌ ኤጀርሳ ጎሮ ተወለዱ፡፡ ሐምሌ 16 የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉስ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የልደት በዓላቸው ነው፡፡ራስታዎችም( ጃይማካዎች) የጃንን ልደት ይዘክራሉ።
ደጋፊና ነቃፊዎቻቸው መሳ ለመሳ ቢሄዱም ሟች አይወቀስምና ምንዳው ምንዳው ብቻ ተጻፈ
📸 ተስፋዬ ወልደሚካሄል
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

18 days ago
ህንድ በሃይድሮጂን የሚሰራ የመጀመሪያ ባቡሯን አስተዋወቀች
****************
ህንድ ከከባቢ አየር ብክለት የጸዳ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥና የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ የምታደርገው ጥረት አካል የሆነውን፣ በሃይድሮጂን ኃይል የሚሰራ የመጀመሪያ ባቡሯን በይፋ ሥራ አስጀምራለች።
በዚህም አገሪቱ በካይ ጋዝ ከማያመነጩ የቴክኖሎጂ አማራጮች መካከል እጅግ ዘመናዊ የሆነውን ሥርዓት በባቡር መስመሮቿ ላይ በተሳካ ሁኔታ ጥቅም ላይ ካዋሉ ጥቂት የዓለም አገራት ተርታ ለመደመር በቅታለች።
የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለአገልግሎት የበቃውን ይህንን የሃይድሮጂን ባቡር መርቀው ሥራ ባስጀመሩበት ወቅት፤ ይህ አረንጓዴ ቴክኖሎጂ ሕንድ ራሷን ለመቻልና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ለምታደርገው አገራዊ ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ ነው ብለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ስም ጥምረት በመውሰድ "ናሞ ግሪን ሬይል" የተሰኘው ይህ ባቡር፤ በሀርያና ግዛት ውስጥ በሚገኙት በጂንድ እና ሶኒፓት ከተሞች መካከል ባለው የ90 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ላይ በቀን ሁለት ጊዜ የደርሶ መልስ ጉዞ ማድረግ መጀመሩ ተነግሯል።
ይህ ባለ 10 ጎታች ባቡር በሰዓት እስከ 75 ኪሎ ሜትር የመጓዝ ፍጥነት ያለው ሲሆን፣ በአንድ ጊዜ 2,600 የሚጠጉ ተሳፋሪዎችን የመያዝ ከፍተኛ አቅም አለው ተብሏል።
ሙሉ በሙሉ በሕንድ መሐንዲሶች ዲዛይኑ ተሠርቶ እዚያው አገር ውስጥ የተገነባው "ናሞ" ባቡር፤ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ሙቀትና ንጹሕ የውሃ ትነት ብቻ ወደ አየር የሚለቅ በመሆኑ፣ ከአየር በካዩ የናፍጣ ባቡር እጅግ የተሻለ አማራጭ ያደርገዋል ነው የተባለው።
ሕንድ በአሁኑ ወቅት በዓለም ካሉት ታላላቅ የባቡር መስመሮች አንዱ የሆነውን የ70,000 ኪሎ ሜትር አጠቃላይ የባቡር ኔትወርኳን ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ለማገናኘት የተቃረበች ቢሆንም፤ አዲሱ የሃይድሮጂን ቴክኖሎጂ የኤሌክትሪክ መስመር መዘርጋት በማይቻልባቸው አስቸጋሪ ቦታዎች ላይ ያለውን ክፍተት ለመድፈን ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደረግ መገለፁን አልጀዚራ ዘግቧል።
በሃይድሮጂን የሚሠሩ ባቡሮችን በሥራ ላይ ቀድመው ካዋሉ አገራት መካከል ጀርመን፣ ቻይና፣ ጃፓን እና አሜሪካ ይጠቀሳሉ፡፡
በመሀመድ ፊጣሞ
#ebc #india #hydrogentrain #greentechnology #ecofriendly

19 days ago
እንግሊዝ በዓለም ዋንጫ፤ ለ60 ዓመታት ያልተፈታው ህልም፣ ያልተመለሰው ጥያቄ!
**************************
እንግሊዝ የዓለም ዋንጫን ዳግም ሳታነሳ ተጨማሪ 4 ዓመታት እንደሚቆጠሩ እርግጥ ከሆነ 24 ሰዓታት አለፉ። አትላንታ ላይ “ሦስቱ አናብስት” የዓለም ሻምፒዮን የመሆን ውጥን ይዘው፣ እስከ ግማሽ ፍፃሜም ተጉዘው የጀመሩት መንገድ በሊዮኔል ሜሲ አርጀንቲና ተቋርጧል። ለተጨማሪ ዓመታት እንዲወጡት የሚያስፈልግ ሌላ ዳገት፣ ሊወርዱትም የሚገባ ሌላ ቁልቁለት ‘ተበጅቶላቸዋል’።
እነዛ 60 ዓመታት በዓለም እግር ኳስ የራሷን አሻራ ላኖረችው ሀገር ብዙ መውጣትና መውረዶች፣ በርካታ ተስፋ አስቆራጭ ደግሞም ተስፋ መልሶ የለመለመባቸው ወቅቶች አልፎባቸዋል። ዓለም ዋንጫ ግን ያዝኩት ሲሉ እያመለጠ፣ ደረስኩበት ሲሉ እየራቀ “ጉም የመዝገን” ያክል ሆኖባቸዋል።
ሐምሌ 30/ 1966 እ.አ.አ ሰር ቦቢ ሙር የእንግሊዝን የመድረኩ ብቸኛ ድል፣ የቀደመውን የጁሊየስ ሪሜትስ ዋንጫ ካነሳ በኋላ ብዙ ነገሮች ባሉበት የሉም ተቀያይረዋል። እግር ኳስም፣ ራሷ እንግሊዝም ሆነ ዓለም ትላንትን አይመስሉም።
እንግሊዝ ምዕራብ ጀርመንን 4 ለ 2 አሸንፋ የመጀመሪያ ዓለም ዋንጫዋን ካነሳች በኋላ፤ 454 ተጫዋቾች ነጩን የብሔራዊ ቡድን መለያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለብሰዋል። ቀዳሚው በ1967 የተጫወተው 847ኛው ተጫዋች ጆን ሆሊንስ ሲሆን፤ የብሔራዊ ቡድኑን መለያ በመልበስ ደግሞ የመጨረሻ የሆነው 1300ኛው የሊቨርፑሉ ሪዮ ንጉምሃ ነው። በዓለም ዋንጫው ደግሞ ከውጤታማው የአልፍ ራምሴይ ቡድን ጀምሮ እሰከ አሁኑ ቶማስ ቱሄል ድረስ 161 ተጫዋቾች እንግሊዝን ወክለዋል።
በስድሰቱ አስርታት ዋንጫ አልባ ዓመታት 15 አሰልጣኞች በቋሚነት ብሔራዊ ቡድኑን መርተዋል። ሮን ግሪንዉድ፣ ሰቨን ጎራን ኤሪክሰን፣ ፋቢዮ ካፔሎ እና ጋሬት ሳውዝጌት ተጠቃሾች ናቸው። ሁሉም ግን የአልፍ ራምሴይን ውጤታማ መንገድ ማስቀጠል አልሆነላቸውም።
አለን ሺረር፣ ዴቪድ ቤካም፣ ስቴቨን ጄራርድ እና ሃሪ ኬን ባለፉት 60 ዓመታት በተካሄዱት ዓለም ዋንጫዎች ቡድኑን በአምበልነት ከመሩ ተጫዋቾች የሚጠቀሱ ናቸው።
እንግሊዝ ከ1966 ሻምፒዮንነቷ በኋላ ከተካሄዱት 15 የዓለም ዋንጫዎች በ12ቱ ተሳትፋለች። በሁሉም ግን ደርሶ የመመለስ፣ አግኝቶም የማጣት ምሳሌ ተደርጋ ቀጥላለች። በ1986 የዲዬጎ ማራዶና በ4 ደቂቃ ልዩነት ያሳየው “የእጅም የእግርም” ትርዒት፣ በ1990 ግማሽ ፍጻሜ የፖል ጋስኮኝ እንባ፣ በ1998 ዓለም ዋንጫ የዴቪድ ቤካም ቀይ ካርድ፣ በ2002 ዓለም ዋንጫ የሮናልዲንሆ ጎቾ ዝነኛ የቅጣት ምት “ወርቃማ ግብ”፣ በ2010 መስመሯን አልፋ የተሻረችው የፍራንክ ላምፓርድ ግብ፣ በ2022 ዓለም ዋንጫ ሀሪ ኬን ያባከናት የፍፁም ቅጣት ምት፣ በመጨረሻም 2026 ላይ በአትላንታ ምድር እየመሩ የነበረውን ጨዋታ የኋላ ኋላ ማጣት፤ እንግሊዞች በቁጭት የሚያስታውሷቸው አጋጣሚዎች ናቸው።
ከዚያ በኋላ የበርሊን ግንብ ፈርሷል፣ የሰው ልጅ ወደ ጨረቃ መጥቋል፣ ዓለም በበይነ መረብ ተሳስሯል፣ የስማርት ስልክ ዘመን የሰው ልጅን የዕለት ተዕለት ህይወት ፈጣን አድርጓል። እነዚህና መሰል ለውጦች በሰው ልጅ የምድር ቆይታ ቢስተናገዱም፤ የእንግሊዝ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮንነት ህልም 1966 ላይ እንደቆመ አለ።
እንግሊዝ ባስተናገደችው የ1996ቱ አውሮፓ ዋንጫ ወቅት የተዜመው “…30 የህመም ዓመታት” የሚል ሀረግ የያዘውና የ1966ቱን ዓለም ዋንጫ በማስታወስ እግር ኳስ ወደ ቤቱ እየተመለሰ እንደሆነ የሚያትተው ኅብረ ዝማሬ፣ ዛሬም አውዱን የሳተ አይመስልም። 30ዎቹ ዓመታት ሌላ 30 ዓመታትን አዋልደዋል፤ እግር ኳስም ወደ “ቤቱ” አልተመለሰም።
የብሔራዊ ቡድኑን መለያ ከለበሱት 454 ተጫዋቾች፣ በዓለም ዋንጫው ከተጫወቱት 161 እግር ኳሰኞች፣ በ15ቱ አሰልጣኞች ስር ካለፉ 7 አምበሎች የምድር ትልቁን የእግር ኳስ ሽልማት ከፍ አድርጎ ማንሳት የቻለው ቦቢ ሙር ብቻ ነው።
ትውልድ ይተካል፣ ተስፋም እየደበዘዘም ቢሆን መልሶ ይለመልማል። እንግሊዛውያንም እግር ኳሳቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በሊግ ውድድሮች በቅርቦቹ ዓመታት እንዳሳደረው ተፅእኖ፤ ብሔራዊ ቡድናቸውም ይህን የዘመናት ህልሙን እውን የሚያደርግበትን ቀን በተስፋ ይጠባበቃሉ።
የ2026ቱ የአሜሪካ ምድር መንገድ ግን ጫፍ ደርሶ ተቋርጧል። ጁድ ቤሊንግሃም “ልብ ሰባሪ ፍፃሜን ያስከተለ ውብ ጉዞ” ሲል የገለፀው የ2026 ዓለም ዋንጫ ቆይታ አብቅቷል።
በእድሪስ አህመድ
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup1966 #england #threelions #judebellingham #harrykane #semifinal #football #sports #ebc

20 days ago
የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክን ምቹ ለማድረግ በ300 ሚሊዮን ብር የሚገነቡ ሰፋፊ ፕሮጀክቶች ይፋ ሆኑ
#ደባርቅ — የተፈጥሮ ቅርሳችን የሆነውን የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክን ምቹ፣ ተደራሽና ዘመናዊ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በ300 ሚሊዮን ብር ወጪ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማከናወን ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የፓርኩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
ይህ በጀርመን መንግሥት የልማት ባንክ (KfW) የገንዘብ ድጋፍ የሚከናወነው ሰፊ ፕሮጀክት፥ የፓርኩን ጥበቃና የሥራ ከባቢ ከማሻሻል ባሻገር የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ ለማራዘም ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
በዚሁ መሠረት በፓርኩ ውስጥና በዙሪያው የሚከናወኑት ዋና ዋና የልማት ፕሮጀክቶች በሚከተሉት ዘርፎች ተከፋፍለዋል፦
1. የአስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ
አዳዲስ የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ግንባታ፦
በጃናሞራ መካነ ብርሃን ከተማ እና በበየዳ ድልይብዛ ከተማ ለፓርኩ ቅጂ ጽሕፈት ቤቶች የሚውሉ ዘመናዊ ቢሮዎች ይገነባሉ።
የተሽከርካሪዎች ጥገና ማዕከል፦
በፓርኩ ዋና ጽሕፈት ቤት ውስጥ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አነስተኛ የመኪና መጠገኛ ጋራዥ ይገነባል።
2. የቱሪዝም መሠረተ ልማት እና አገልግሎቶች
ሦስት ዘመናዊ የመግቢያ በሮች፦
በደባርቅ ሚሊገብሳ፣ በጉልቱ እና በሰኒ ወንዝ ዋና ዋና መግቢያ በሮች ይገነባሉ።
የጨነቅ የማኅበረሰብ ሎጅ፦
የጎብኚዎችን ምቾት በጠበቀ መልኩ በዘመናዊና በዓለም አቀፍ የቱሪስቶች ስታንዳርድ መሠረት እንደገና ይገነባል።
ዘመናዊ የካምፕ ሳይት፦
ቱሪስቶች በተፈጥሮ መካከል አስደሳች ጊዜ እንዲያሳልፉ የሚያስችል ደረጃውን የጠበቀ የቱሪስት ካምፕ ሳይት ይዘጋጃል።
3. የፓርክ ጥበቃና ደህንነት
የስካውት መጠለያዎች፦
የፓርኩን የተፈጥሮና የዱር እንስሳት ሀብት ሌሊትና ቀን ለሚጠብቁት ስካውቶች (ጥበቃዎች) አገልግሎት የሚውሉ ሁለት ተጨማሪ ዘመናዊ የስካውት መጠለያዎች ይገነባሉ።
የፓርኩ ጽሕፈት ቤት በሰጠው መግለጫ፦
"እነዚህ ፕሮጀክቶች መገንባታቸው የፓርኩ ሠራተኞችና ጠባቂዎች ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት እንዲሰጡ ምቹ የሥራ አካባቢ ከመፍጠሩም በላይ፣ የጎብኚዎችን ምቾት በአስተማማኝ ሁኔታ በመጠበቅ በፓርኩ ውስጥ የሚኖራቸውን የቆይታ ጊዜ ለማራዘም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።"

25 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በታይላንድ ባንኮክ በተካሄደው ታላቅ የውበትና የሞዴሊንግ ውድድር ላይ ሀገሯን ኢትዮጵያን ወክላ የተሳተፈችው ሞዴል ሩት ሸዋታጠቅ የ"Miss Classy Model Earth 2026" አሸናፊ በመሆን አኩሪ ስኬት አስመዝግባለች።
ይህ ስኬት ለሩት የመጀመሪያዋ አይደለም። ከዚህ ቀደም የ"Miss Popularity" አሸናፊ መሆን የቻለች ሲሆን፣ በ"Miss International Ethiopia" እና በ"Miss ውበት Ethiopia" የውበት ውድድሮች ላይም ተሳትፋ የክብር ዘውድ ለመድፋት በቅታለች።
ሩት ሸዋታጠቅ ለስኬቶቿ ሁሉ መሠረት የሆኑትን ሁለገብ ስብዕናዎቿን ስታብራራ፣ በፈጣሪ ላይ ያላት ጠንካራ እምነት፣ በታዋቂው የናዝሬት ትምህርት ቤት ያሳለፈችው የትምህርት ቆይታ፣ በልጅነቷ በጀርመን ሀገር መኖሯ፣ እንዲሁም ሁለቱም ዶክተር ከሆኑት እናት እና አባቷ ያገኘችው አስተዳደግና ድጋፍ ለዛሬ ማንነቷ መገንባት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ለዘ-ሐበሻ ገልጻለች።
ከተሳካው የሞዴሊንግ ህይወቷ ባሻገር በትምህርቷ እጅግ አስደናቂ ውጤት ያላት ሩት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርቷን በማዕረግ ያጠናቀቀች ሲሆን፣ በሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ላይም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የህግ ዲግሪ ባለቤት መሆን ችላለች። አሁን ላይም የህክምና ባለሙያ የሆነውን የአባቷን ፈለግ በመከተል በህክምና ትምህርት ዘርፍ የ"C2" ተማሪ ሆና ትምህርቷን እየተከታተለች ትገኛለች። በቆይታዋም የህክምና ተማሪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት በመሆን በምርጫ ተሰይማ በተሳካ ሁኔታ አገልግላለች።
ከእነዚህ ሙያዎቿ በተጨማሪ በስነ-ጥበብ ዘርፍ የዘፈንና የቅኔ (ግጥም) ተሰጥኦ ያላት ሲሆን፣ በተለይም በማህበራዊ ኃላፊነት ላይ በንቃት እየተሳተፈች ትገኛለች። ሩት "Ruth Drops" የተሰኘ የበጎ አድራጎት ተቋም በመመስረት በርካታ የህክምና እና ማህበራዊ ድጋፎችን ለህብረተሰቡ እያበረከተች ሲሆን፣ ከተግባራቶቿም መካከል በተስፋ አዲስ የካንሰር ማዕከል፣ በብሔራዊ የደም ባንክ እና በተለያዩ ሆስፒታሎች የሚገኙ ህሙማንን በቁርጠኝነት መርዳቷ በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው።
እንኳን ደስ ያለሽ፣ ሩት!

26 days ago
አስደናቂ ጉዞ ላይ የሚገኘው ሃሪ ኬን…
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ጥምር አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው በ2026 የዓለም ዋንጫ ምርጥ ጊዜ እያሳለፉ ከሚገኙ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሃሪ ኬን፡፡
እንግሊዝ በዓለም ዋንጫ ከ1966 በኋላ ዋንጫውን ለማሳካት በምታደርገው ጉዞ ውስጥ የ32 ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋች ሃሪ ኬን ትልቁን ሚና እየተወጣ ይገኛል፡፡
በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ እስካሁን ድረስ ካደረገቻው አምስት ጨዋታዎች መካከል በአራቱ ግብ ማስቆጠር ችሏል፡፡
ሃሪ ኬን በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ ውድድር 6 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፤ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ለመጨረስ እና የወርቅ ጫማው ባለቤት ለመሆን እየተፋለመ ይገኛል፡፡
ሃሪ ኬን በፈረንጆቹ 2018 ሩሲያ ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ በ6 ግቦች ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የወርቅ ጫማውን ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
ገና ከአሁኑ በ2026 የዓለም ዋንጫ 6 ግቦችን ያስቆጠረው ኬን ሀገሩ እንግሊዝ በውድድሩ የምትቆይ ከሆነ የግብ መጠኑን ከፍ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
ሃሪ ኬን በእግር ኳስ ሕይወቱ በአጠቃላይ በዓለም ዋንጫ ውድድር ብቻ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ያስቆጠረውን የግብ መጠን ደግሞ 14 አድርሷል፡፡
በዚህም የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ተጫዋች ገርድ ሙለርን ክብረ ወሰን በዓለም ዋንጫ የተጋራ ሲሆን፤ ገርድ ሙለር በዓለም ዋንጫ 14 ግቦችን በማስቆጠር ከምንጊዜም የዓለም ዋንጫ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች መካከል አንዱ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ገርድ ሙለር በሁለት የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ በ13 ጨዋታዎች ነው 14 ግቦችን ያስቆጠረው፤ ሃሪ ኬን በበኩሉ በሦስተኛ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎው በ16 ጨዋታዎች ነው 14 ግቦችን ማስቆጠር የቻለው፡፡
በቀጣይ እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሃሪ ኬን ሁለት ግቦችን በዓለም ዋንጫው የሚያስቆጥር ከሆነ የግብ መጠኑን ወደ 16 ከፍ በማድረግ ሮናልዶ ሉዊስ ናዛሪዮን በአንድ ግብ በመብለጥ የሚሮስላቭ ክሎስን ክብረ ወሰን የሚጋራ ይሆናል፡፡
ሃሪ ኬን እንግሊዝ ከፈረንጆቹ 1966 በኋላ የዓለም ዋንጫን ለማሳካት ለምታደርገው ጉዞ ትልቁን ሚና እየተወጣ ይገኛል፡፡
የ32 ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋች በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ታሪክ በዓለም ዋንጫ ውድድር ከፍተኛው ግብ አስቆጣሪ ነው፡፡እስካሁን ድረስ በመድረኩ 14 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል፡፡
ሃሪ ኬን ከዚህ በተጨማሪም ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን እስካሁን ድረስ 119 ጨዋታዎችን አድርጎ 85 ግቦችን በማስቆጠር የምን ጊዜም የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ግብ አስቆጣሪ ተጫዋች ነው፡፡
እንግሊዝ በቀጣይ በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ከኖርዌይ ጋር የምትጫወት ሲሆን ሃሪ ኬን ተጠባቂው ተጫዋች ነው፡፡
የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በሃሪ ኬን እየተመራ ከፈረንጆቹ 1966 በኋላ የዓለም ዋንጫን ያሳካ ይሆን የሚለው ይጠበቃል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ

27 days ago
#ጀርመን በድንች ተጥለቀለቀች-ለፈለገው ሁሉ በነፃ እየታደለ ነው❗
በአውሮፓ ምድር ታይቶ የማይታወቅ አስገራሚ ክስተት ተከስቷል። ጀርመን ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ አይታው የማታውቀውን እጅግ ከፍተኛ የድንች ምርት በመሰብሰቧ፣ አገሪቱ በድንች ክምር ተጥለቀለቀች! ይህም ክስተት በአካባቢው "ካርቶፍል-ፍሉት" (የድንች ጎርፍ) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።
ነገሩ እንዲህ ነው፤ በአንድ የጀርመን የለንደን (ላይፕዚግ) አካባቢ የሚገኝ ገበሬ ያመረተውን 4 ሚሊዮን ኪሎ (4,000 ቶን) ድንች የሚገዛው ትልቅ ነጋዴ ውል በማፍረሱ፣ ምርቱ እንዳይበላሽና እንዳይበሰብስ ለአካባቢው ህዝብ በነፃ ለማደል ተገዷል።
ይህን ተከትሎም የበርሊን ጋዜጦችና "ኤኮሲያ" የተባለው የኢንተርኔት መፈለጊያ ተቋም ከተባባሪ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመሆን በዋና ከተማዋ በርሊን 174 የነፃ ድንች ማከፋፈያ ጣቢያዎችን አቋቁመዋል።
አሁን ላይ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የአረጋውያን መርጃ ማዕከላትና አልፎ ተርፎም የበርሊን የእንስሳት ማደሪያ (ዙ) በጆንያና በጋሪ እየመጡ የፈለጉትን ያህል ድንች በነፃ እያጋዙ ይገኛሉ።
አልፎ ተርፎም ሁለት ትላልቅ የጭነት መኪናዎች ሙሉ ድንች ለዩክሬን በዕርዳታ ተልኳል።
ይህ በነፃ የሚታደለው ድንች በገበያ ላይ ያለውን የድንች ዋጋ እንዳያረክሰውና ሌሎች ገበሬዎችን ኪሳራ ውስጥ እንዳይከት ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።
በአንድ በኩል በዓለም ዙሪያ የምግብ እጥረትና ረሃብ ባለበት በዚህ ዘመን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የተረፈረፈ ምርት የሚጣልበት ቦታ አጥቶ በነፃ መታደሉ፤ የዓለማችን የምግብ ስርጭት ስርዓት ምን ያህል የተዛባ መሆኑን ትልቅ ማሳያ ሆኗል።
Seledadotio

28 days ago
ዶናልድ ትራምፕ በኔቶ ጉባኤ ላይ ከኢራን ጋር የተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ማክተሙን አስመልክቶ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ ነው።
በምስሉ ላይ የምታዩት የጀርመን ኮሎኝ ዋጋ ነው።
በምስሉ ላይ የምታዩት የጀርመን ኮሎኝ ዋጋ ነው።
28 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተደረገውን የጥቃት ልውውጥ ተከትሎ አሁን ያለው የተኩስ አቁም ስምምነት ማክተሙን ዛሬ ረቡዕ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም ዛሬ ምሽት በኢራን ላይ ተጨማሪ የአየር ጥቃቶችን ሊፈጽሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።
በቱርክ አንካራ እየተካሄደ ባለው የኔቶ (NATO) ስብሰባ ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ትራምፕ፣ "ስምምነቱ ያበቃ ይመስለኛል። ከእነሱ ጋር ዳግም መነጋገር አልፈልግም፤ አጭበርባሪዎች ናቸው" ብለዋል። ይህ መግለጫ አሜሪካ እና ኢስራኤል የጀመሩትን ጦርነት ለማስቆም ከኢራን ጋር የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ተከትሎ የመጣ ድንገተኛ የአቋም ለውጥ ነው።
"ትናንት ምሽት ጠንካራ ጥቃት ፈጽመንባቸዋል፤ ምናልባትም ዛሬ ማታም እንደግመዋለን" ያሉት ትራምፕ፣ አሜሪካ አሁንም በከፍተኛው ደረጃ ጥቃት እንዳላደረሰች በመግለጽ የኤሌክትሪክ እና የውሃ ማጣሪያ ተቋማትን ኢላማ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተናግረዋል። የሲቪል መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ማድረስ የጦር ወንጀል ሊያስብል እንደሚችል ቢነገርም፣ ትራምፕ ግን አስፈላጊ ከሆነ እንደሚያደርጉት ገልጸዋል። በተጨማሪም በኢራን ላይ የባህር ላይ እገዳን ዳግም ስለመጣልም አንስተዋል።
ይህ የትራምፕ መግለጫ በዓለም ገበያ ላይ ወዲያውኑ ተጽዕኖ ያሳደረ ሲሆን፣ የነዳጅ ዋጋም መጨመር ጀምሯል። የሰላም ንግግሩን በተመለከተ ዋና የአሜሪካ ተደራዳሪዎች የሆኑት ስቲቭ ዊትኮፍ እና የፕሬዝዳንቱ አማች ጃሬድ ኩሽነር ድርድሩን መቀጠል ቢፈልጉም፣ ትራምፕ ግን "ውሸታሞች ስለሆኑ ከእነሱ ጋር ጊዜ ማጥፋት ነው" በማለት አጣጥለውታል።
የውጥረቱ መባባስ የተከሰተው ኢራን በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ በሚገኙ ሶስት የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት መክፈቷን ተከትሎ አሜሪካ የአጸፋ እርምጃ መውሰዷን ተከትሎ ነው። ለዚህም የኢራን አብዮታዊ ዘብ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች በሚገኙባቸው ኩዌት እና ባህሬን ላይ በሚሳኤል እና ድሮን ጥቃት ምላሽ መስጠቱ ይታወሳል።
በሌላ በኩል ፕሬዝዳንቱ በኔቶ አባል ሀገራት ላይ ያላቸውን ቅሬታ አሰምተዋል። አውሮፓውያን ለራሳቸው መከላከያ በቂ በጀት እየመደቡ አይደለም ያሉት ትራምፕ፣ ኢጣሊያ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ አሜሪካ ከኢራን ጋር በገባችበት ጦርነት ድጋፍ እንዳልሰጧት በግልጽ ተችተዋል።
ሆኖም ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ዩክሬን የፓትሪዮት (Patriot) ሚሳኤሎችን በራሷ እንድታመርት አሜሪካ ፈቃድ እንደምትሰጥ አስታውቀዋል። የቱርኩን ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋንን ባገኙበት ወቅት ደግሞ፣ የአሜሪካ ኮንግረስ እገዳ ቢኖርም ኤፍ-35 (F-35) የጦር አውሮፕላኖችን ለቱርክ ስለመሸጥ መወያየታቸው ተዘግቧል።

1 month ago
"E.V.A.G.N" የኢትዮጵያ ሠዓሊያንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊያስተዋውቅ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያን የሥነ-ጥበብ አድማስ ለማስፋትና የሠዓልያንን የፈጠራ ውጤቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው "Ethiopian Visual Arts Global Network" (E.V.A.G.N) የተሰኘው ግዙፍ የመረጃ ቋት (Database) የማስተዋወቂያ ፕሮግራም ቅዳሜ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በሐገር ውስጥ የሚገኙ ሠዓሊያን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተካሄደ።
ይህን ለአንድ ዓመት ያህል ሲደራጅ የቆየውን የመረጃ ቋት ያዘጋጀው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘው **የአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት** ነው።
ከስነ-ስርዓቱ የተደመጡ ንግግሮች
አቶ አገኝሁ አዳነ
(የአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ዳይሬክተር):
ፕሮግራሙን በይፋ ሲከፍቱ እንደተናገሩት፣ ይህ ግዙፍ የመረጃ ቋት ለኢትዮጵያውያን ሠዓሊያን እጅግ ከፍ ያለ ጠቀሜታ አለው። የሥነጥበብ ትምህርት ቤቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን ፕሮጀክቱ ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያስፈልገውን ድጋፍና እገዛ እንደሚያደርጉም አረጋግጠዋል።
ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን:
የዚህ ኔትወርክ እውን መሆን ለሥነጥበብ ባለሙያው ዓለም ዛሬ በደረሰበት የቴክኖሎጂ አማካኝነት በየትኛውም የዓለም ክፍል ከሚገኝ ባለሙያና መሰል የትምህርት ተቋማት ጋር ግንኙነት እንዲፈጥር እንዲሁም ሥራዎቹን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲያስተዋውቅ ትልቅ በር የሚከፍት መሆኑን ገልጸዋል።
"ይህ ኔትወርክ የኢትዮጵያ ሥነ-ጥበብን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በቴክኖሎጂ ለማገናኘት ትልቅ ድልድይ ነው::"
የቴክኖሎጂው በስተጀርባ እና አስተዋጽዖ አበርካቾች
ይህንን ዘመናዊ የመረጃ ቋት የገነባው በትምህርት ዘርፍ፣ በሶፍትዌርና ሃርድዌር ቴክኖሎጂ፣ በስልጠናና ማማከር ላይ የተሰማራውና መቀመጫውን በኢትዮጵያ ያደረገው "INFNOVA Technologies" የተሰኘው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው።
የኩባንያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ልደቱ ታደሰ ስለ መረጃ ቋቱ ጠቀሜታና እስከ አሁን ስለተከናወኑት ሥራዎች ዝርዝር ማብራሪያ ለታዳሚው የሰጡ ሲሆን፣ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል።
ይህን ፕሮጀክት እውን ለማድረግ ከአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ጋር በመሆን ለአንድ ዓመት ያህል ሲያስተባብሩ የነበሩት ሠዓሊ ሳምሶን መረሳ በበኩላቸው፣ ለሥራው መሳካት አስተዋፅኦ ያደረጉ ግለሰቦችን በሙሉ አመስግነዋል።
በተጨማሪም በጀርመን አገር የሚኖረው **ሠዓሊ ግርማቸው የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክቱን በድምፅ ለታዳሚው አስተላልፏል።
የሠዓሊያን ምዝገባና ጥሪ
የመረጃ ቋቱ ይፋ ከተደረገ በጥቂት ቀናት ውስጥ በርካታ የሐገር ውስጥና የውጭ አገር ኢትዮጵያውያን ሠዓሊያን ኔትወርኩን የተቀላቀሉ ሲሆን፣ እስከ አሁን ከሁለት መቶ (200) በላይ ባለሙያዎች ምዝገባ አከናውነዋል።
በማስተዋወቂያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት ሠዓሊያንም በሙሉ በዕለቱ የኔትወርኩ አካል ሆነዋል።
በትምህርት ቤቱ አስተባባሪዎች የቀረበው ጥሪ እንደሚያመለክተው፦
* በሐገር ውስጥና በመላው ዓለም የሚገኙ የአለ ሥነ-ጥበብ ትምህርት ቤት ምሩቃን፣
* በሌሎች ተቋማት የሠለጠኑ ባለሙያዎች፣ እና
* የልምድ ሠዓሊያን በሙሉ፣
ማንነታቸውንና የሥራ ልምዳቸውን የሚገልጽ መሠረታዊ መረጃቸውን ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ወይም የተዘጋጀውን ባርኮድ ስካን በማድረግ ቅጹን እንዲሞሉና የዚህ ዓለም አቀፍ መረብ አካል እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
የምዝገባ ቅጽ ሊንክ: https://forms.gle/gWHXpKub...
#በይትባረክ ዋለልኝ

በኢትዮኮል ወደ አገርቤት በቅናሽ ይደውሉ፤ በነፃ ይቀበሉ!!
📞 ማንኛውንም የሞባይል ወይም የመደበኛ ስልክ ላይ መደወል ያስችላል
💰 በታላቅ ቅናሽ
🔄 ወደ ኢትዮጵያ መደወል ብቻ ሳይሆን፣ ጥሪዎችን በገዙት ጥቅል መነሻነት በነፃ መቀበል ይችላሉ።
🇺🇸 አሜሪካ 🇮🇱 እስራኤል
🇨🇦 ካናዳ 🇾🇪 የመን
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ 🇰🇪 ኬንያ
🇮🇹 ጣሊያን 🇩🇪 ጀርመን
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
መተግበሪያውን ያውርዱ:
App store: https://bit.ly/42Zg6jx
Play store: https://bit.ly/4u12uPu
#ethiocall #ethiotelecom #telebirr #telebirrsuperapp #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
📞 ማንኛውንም የሞባይል ወይም የመደበኛ ስልክ ላይ መደወል ያስችላል
💰 በታላቅ ቅናሽ
🔄 ወደ ኢትዮጵያ መደወል ብቻ ሳይሆን፣ ጥሪዎችን በገዙት ጥቅል መነሻነት በነፃ መቀበል ይችላሉ።
🇺🇸 አሜሪካ 🇮🇱 እስራኤል
🇨🇦 ካናዳ 🇾🇪 የመን
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ 🇰🇪 ኬንያ
🇮🇹 ጣሊያን 🇩🇪 ጀርመን
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
መተግበሪያውን ያውርዱ:
App store: https://bit.ly/42Zg6jx
Play store: https://bit.ly/4u12uPu
#ethiocall #ethiotelecom #telebirr #telebirrsuperapp #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
1 month ago
ለልጁ እንኳን የማይራራው ጆሴፍ ስታሊን
#ethiopia | የቀድሞው የሶቪየት ሕብረት መሪ ጆሴፍ ስታሊን የበኩር ልጅ ያኮቭ ድዙጋሽቪሊ ከአባቱ ጋር በነበረው እጅግ የሻከረ ግንኙነት ምክንያት ለከፍተኛ ስሜታዊ ጫና ተዳርጎ እንደነበር ይነገራል።
ያኮቭ ካልተሳካ ትዳር እና ለዓመታት ከዘለቀ የስነ-ልቦና ቀውስ በኋላ በ1920ዎቹ ዕድሜው ላይ ደረቱ ላይ በመተኮስ ራሱን ለማጥፋት ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቷል። በርካታ የታሪክ ተመራማሪዎች ለዚህ የራሱን ሕይወት ለማጥፋት የዳረገው አስከፊ ሙከራና ለደረሰበት የተስፋ መቁረጥ ስሜት ብቸኛው ምክንያት ባይሆንም ከአባቱ ከስታሊን ጋር የነበረው አስቸጋሪ ግንኙነት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ያምናሉ።
ስታሊን ለልጁ የራስ ማጥፋት ሙከራ የሰጠው ምላሽ ነው ተብሎ የሚነገረውና “ቀጥ አድርጎ መተኮስ እንኳን አይችልም” የሚለው ዝነኛ አባባል በተለያዩ የሕይወት ታሪክ መጻሕፍትና ማስታወሻዎች ውስጥ ተጠቅሷል።
የያኮቭ አሳዛኝ የሕይወት ታሪክ ይበልጥ የከፋ መልክ የያዘው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጀርመን ኃይሎች እጅ በተማረከበት ጊዜ ነው። ጀርመኖች ያኮቭን በከፍተኛ ደረጃ ላይ በሚገኝ የጀርመን የጦር ምርኮኛ ለመለወጥ ያቀረቡትን የምርኮ ልውውጥ ጥያቄ ስታሊን “ጄኔራልን በልጅ አልለውጥም” በማለት ውድቅ ማድረጉ ተገልጿል።
በመጨረሻም ያኮቭ በ1943 በጀርመን የጦር ምርኮኞች ካምፕ ውስጥ ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን ይህም የጦርነቱ ሰለባ ከሆኑት በርካታ ወገኖች መካከል አንዱ አድርጎታል።

ሀምበርግ ላይ በብቸኝነት የተገኙት ኢትዮጵያዊቷ ቤዛ በሻህ የአለምአቀፉን ማህበረሰብ አሳሰቡ‼️
የሆፕ ስፓይና ቢፊዳ እና ሃይድሮሴፋለስ (HOPE-SBH) ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ቤዛ በሻህ ኃይሌ፣ በጀርመን ሀምበርግ በተካሄደው የ2026ቱ የሃምበርግ ዘላቂ ልማት ኮንፈረንስ (Hamburg Sustainability Conference - HSC) በመገኘት በነርቭ ዘንግ አፈጣጠር ችግሮች መከላከል ዙሪያ ዓለም አቀፍ ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ አቀረቡ።
የሃምበርግ ዘላቂ ልማት ኮንፈረንስ በአለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን የጂኦፖለቲካዊ ውጥረት በመሻገር፣ በፖለቲካ፣ በቢዝነስ፣ በሳይንስ እና በሲቪል ማህበረሰብ መሪዎች መካከል አዳዲስ ስምምነቶችን እና አጋርነቶችን ለመፍጠር የተቋቋመ ዓለም አቀፍ መድረክ ነው። ወ/ሮ ቤዛ በኮንፈረንሱ ማዕቀፍ ውስጥ፣ ከጀርመን የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ፌዴራል ሚኒስትር ወ/ሮ ሬም አላባሊ-ራዶቫን (Reem Alabali Radovan) ንግግር በመቀጠል ዋና ንግግር አድርገዋል።
ወ/ሮ ቤዛ በንግግራቸው ወቅት፣ በሕይወት የመጀመሪያዎቹ 1,000 ቀናት ላይ የተመጣጠነ ምግብን ለማረጋገጥ የሚደረግ ኢንቨስትመንት የእናቶችንና የሕጻናትን ጤና ለማሻሻል ወሳኝ ስትራቴጂ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በአለም አቀፍ መድረኩ ላይ፤ "ከእያንዳንዱ የምግብ እጥረት አኃዛዊ መረጃ ጀርባ የሚሰቃዩ ሕፃናት እና ቤተሰቦች መኖራቸውን ማስታወስ ይገባል" ብለዋል። በተጨማሪም "የተደበቀ ረሃብ" በመባል የሚታወቀው የንጥረ-ነገር እጥረት (micronutrient deficiencies) በእናቶች እና በሕፃናት ላይ የሚያደርሰውን ዘላቂና ከባድ ተጽዕኖ በዝርዝር አስረድተዋል። ከዚህም ባለፈ፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ግለሰቦችን ከመጉዳት በተጨማሪ ለሰው ልጆች ካፒታል፣ ለኢኮኖሚ ዕድገት እና ለዘላቂ ልማት ትልቅ እንቅፋት እንደሚሆን አብራርተዋል። በሕይወት የመጀመሪያዎቹ 1,000 ቀናት የሚደረግ ኢንቨስትመንት ከጤናም በተጨማሪም ለትምህርት ጥራት፣ ለኢኮኖሚ ምርታማነት እና ለዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት መሠረት መሆኑን አስገንዝበዋል።
ይህንን አሳሳቢ ችግር ለመቅረፍም፣ ድርጅታቸው ሆፕ ኤስ.ቢ.ኤች (HOPE-SBH) ላለፉት 10 ዓመታት በትኩረት የሰራባቸውን ዋና ዋና መፍትሄዎች ጠቁመዋል። በተለይም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በመተግበር ላይ የሚገኘውን ምግብን በጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የማበልጸግ ሥራ በምሳሌነት በማንሳት፤ በሀገር በቀል ጥናትና ምርምር የታገዘውንና ትልቅ ስኬት ያስመዘገበውን ጨውን በአዮዲን እና በፎሊክ አሲድ በጋራ የማበልጸግ ሂደት (Double Salt Fortification) በልዩ አርአያነት አጉልተው አሳይተዋል። ለዚህ ብሔራዊ የፖሊሲ ስኬት መሳካትም የመንግሥት ተቋማት፣ የልማት አጋሮች፣ የግሉ ዘርፍ እና የሲቪል ማኅበረሰብ በቅንጅት መሥራታቸው ወሳኝ ሚና እንደነበረው ገልጸዋል።
ወ/ሮ ቤዛ በማጠቃለያቸው፣ የሃምበርግ ዘላቂ ልማት ኮንፈረንስ እንደሚያንፀባርቀው ሁሉ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከአጠቃላይ የፖሊሲ ውይይቶች ባለፈ ተጨባጭና ዘላቂ ውጤት ወደሚያመጡ ተግባራዊ አጋርነቶች መሸጋገር እንዳለበት ጥሪያቸውን አቅርበዋል። በሕፃናት የመጀመሪያዎቹ 1,000 ቀናት የተመጣጠነ ምግብ ላይ ኢንቨስት ማድረግ፣ ከማኅበረሰብ ጤና መሻሻል ባለፈ ለትምህርት ጥራት፣ ለኢኮኖሚ ዕድገት እና ለዘላቂ ልማት ዋነኛ መሠረት መሆኑንም ዳግም አረጋግጠዋል።

ሊዮኔል ስካሎኒ በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት 100ኛ ጨዋታውን ያደርጋል
**************************
የ“አልበ ሰልስቴ”ዎቹ ወርቃማ ትውልድ ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል። ለሌላ የዓለም ሻምፒዮንነት የጀመረውን መንገድ በአስገራሚ ሁኔታ እየተጓዘ ነው። የ48 ዓመቱ ሰው በሊዮኔል ሜሲ ዙሪያ የተገነባውን ቡድን በአህጉር እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ ስኬታማነት እያመላለሰው ነው።
ከ2018ቱ ዓለም ዋንጫ በኋላ ስካሎኒ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን አሰልጣኝነት ሲረከብ በዓለም እግር ኳስ በጉልህ የሚጠራ ስም አልነበረውም። ሆኖም አሰልጣኙ የጎላ የአሰልጣኝነት ልምድ ሳይኖረው የኳታሩን ዓለም ዋንጫ ጨምሮ ሁለት የኮፓ አሜሪካ ክብሮችን አሳክቷል። የፋይናሊዝማ ዋንጫም የስኬቱ አካል ነው።
ያኔ ከስምንት ዓመታት በፊት ስካሎኒ የሆርጌ ሳምፓውሊን መንበር ሲረከብ ታላቁን ማራዶና ጨምሮ ብዙዎች በጥርጣሬ ነበር የተመለከቱት። ልምዱ ታላቋን የእግር ኳስ ሀገር በአሰልጣኝነት ለመምራት ብቁ አይደለም የሚለው የጥርጣሬው መነሻ ነበር።
ማራዶና ኃይለ ቃላትን ጭምር ተጠቅሞ ስካሎኒን የተቸው ጄራርዶ ማርቲኖ ወደ ቀድሞ አሰልጣኝነታቸው መመለሳቸውን በመሻትም ጭምር ነው።
የቀድሞ የዲፖርቲቮ ላካሮኛ እና ላዚዮ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ለብሔራዊ ቡድንም ቢሆን ከሰባት ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ውጭ ኣላሸነፈም። ከሊዮኔል ሜሲ ጋር አብረው የተጫወቱበት የ2006 የጀርመን ዓለም ዋንጫ በተጫዋችነት ትልቁ ዓለም አቀፍ ተሳትፎው ነው።
የአሰልጣኝነት ትልቁ ልምዱ ግን በ2018 ዓለም ዋንጫ በ16ቱ ጥሎ ማለፍ በተሰናበተው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የሆርጌ ሳምፖሊ ረዳት ሆኖ ሲሰራ ይጀምራል። የሳምፖሊ መሰናበት ደግሞ ለስካሎኒ አዲስ ዕድል ይዞለት መጣ።
“አልበ ሰልስቴ”ዎቹን በዋና አሰልጣኝነት የመምራት ዕድል። በዚህም ጊዜያዊ አሰልጣኝ በኋላም ዋና አሰልጣኝ ሆኖ በቅርብ ዓመታት ከታዩ ውብ እግር ኳስ ከሚጫወቱ ብሔራዊ ቡድኖች አንዱን አሳየ።
“ስካሎኒታ” አሁን በተጫዋችነት ዘመኑ ያላገኘውን ክብር በአሰልጣኝነት ተቀዳጅቷል። ስካሎኒ ብሔራዊ ቡድኑን እየመራ ካደረጋቸው 99 ጨዋታዎች 72 አሸንፏል፣ በ18 አቻ ተለያይቷል፣ በ9 ጨዋታዎች ደግሞ ተሸንፏል። ከ2019 – 2022 የተጓዘበት በ36 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞውም የመንገዱ አካል ነው።
ነገ ሚያሚ ላይ የሚደረገው የ32ቱ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ለሊዮኔል ስካሎኒ 100ኛ መርኃ ግብር ሆኖ ይመዘገባል። አርጀንቲና ሲሆን አስከ ሻምፒዮንነት ካልሆነ ግን እስከ ፍፃሜ ትጓዛለች ተብላ በምትጠበቅበት በዚህ ዓለም ዋንጫ መሃል ስለ 100ኛ ጨዋታው ተጠይቆ፤ ያኔ 100ኛ ጨዋታው ላይ እደርሳለሁ ብሎ አስቦ እንዳልነበር ነው የተናገረው።
ሆኖም ይህ በህይወቱ አስቦት የማያውቀው ደረጃ ቢሆንም ዋነኛ ትኩረቱ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን ለተከታታይ የዓለም ሻምፒዮንነት ማብቃት መሆኑን ገልጿል።
ይህን በዓለም እግር ኳስ የስኬታማነት ምሳሌ የሆነ ታሪካዊ ቡድንን መምራት እና ይህን ያህል ርቀት መጓዝ ልዩ ስሜት እንደሚፈጥር ግን አልሸሸገም።
ትሁቱ ሰው የ21ኛው ክፍለ ዘመን የእግር ኳስ ክስተት ሜሲንም ሆነ ብሔራዊ ቡድኑን ውጤታማ በሚያደርግ አግባብ በእርሱ ዙሪያ የገነባው ቡድን ለስኬታማነቱ በምክኒያትነት የሚጠቀስ ዋነኛ ጉዳይ ነው።
የዓለም ዋንጫውን ኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ከኪሊያን ምባፔ ጋር በስድስት ግቦች እየመራ የሚገኘው ሊዮኔል ሜሲ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ የዘመኑን ውጤታማ ጊዜያት በስካሎኒ አሰልጣኝነት ስር ነው ያሳለፈው።
በ74 ጨዋታዎች 58 ጊዜ ኳስና መረብን አገናኝቷል። በ128 ጨዋታዎች 65 ግቦች ካስቆጠረበት የቀደመው ጊዜ ጋር ተነፃፅሮ በጨዋታዎች ብዛት ሲሳላ በእጅጉ ያነሰ ነው።
በመጀመሪያው 0.51 በሁለተኛው ደግሞ 0.78 በአማካይ በየጨዋታው ያስቆጠራቸው ግቦች ናቸው። ይህ ቁጥር ስካሎኒ በሜሲ ዙሪያ የሚያጠነጥን ቡድን ለመገንባቱ ጉልህ ማሳያ ነው።
የአሰልጣኙ ውል በቀጣይ ዓመት ታህሳስ ወር ላይ ያበቃል። የአርጀንቲና እግር ኳስ ፌደሬሽንም የአሰልጣኙን ውል ለተጨማሪ አምስት ዓመታት ለማራዘም እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል።
የ48 ዓመቱ ሊዮኔል ስካሎኒ በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት 100ኛ ጨዋታውን የዓለም ዋንጫው ክስተት ከሆነችው ኬፕቨርዴ ጋር ነገ ሌሊት 7፡00 ሰዓት በሚያሚው ሃርድ ሮክ ስታዲየም ያደርጋል።
በእድሪስ አህመድ
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #messi #argentina #football

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኒው ጀርሲው የሚያቃጥል ፀሐይ ስር የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እድለ-ቢሷን ስዊድንን 3 ለ 0 በማፈራረስ አስፈሪነቱን በድጋሚ በተግባር አስመስክሯል። በዚህ ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን አዲስ ታሪክ ጽፏል። አጥቂው በሁለቱም አጋማሾች ባስቆጠራቸው ግቦች በጥሎ ማለፍ ያስቆጠራቸውን ግቦች መጠን ወደ 10 ከፍ አድርጓል። በተጨማሪም በዘንድሮው ውድድር 6ኛ ግቡን በማስቆጠር ከአርጀንቲናው ሊዮኔል ሜሲ ጋር የወርቅ ጫማውን ፉክክር በጋራ መምራት ጀምሯል።
ኒው ጀርሲ ላይ የነበረው ከፍተኛ ሙቀት ፈረንሳዮቹን ከማጥቃት አላቆማቸውም። ገና ከጅምሩ በስዊድን ግብ ክልል ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠር ጀመሩ። በ20ኛው ደቂቃ የምባፔ ግብ ከጨዋታ ውጪ (ኦፍሳይድ) ተብሎ ሲሻርበት፣ ብዙም ሳይቆይ ከጁልስ ኩንዴ የተሻገረለትን ወርቃማ ኳስ የግቡን ቋሚ ገጭቶበታል። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ማይክል ኦሊሴ በድንቅ የመቀስ ምት የሞከረው ኳስ የግቡን ቋሚ ታኮ ሲወጣ፣ የተመለሰውን ኳስ ዴምቤሌ ሞክሮ ወደ ውጪ ሰዶታል። የስዊድኑ ግብ ጠባቂ ጃኮብ ዊዴል ዜተርስትሮም ተከታታይ ኳሶችን በማዳን ፈረንሳዮቹን ቢያበሳጭም፣ የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ሲል ግን ምባፔን ማስቆም አልቻለም።
ዴምቤሌ ያቀበለውን ኳስ ይዞ የገባው ምባፔ፣ የስዊድኑን ተከላካይ ቪክቶር ጂዮከረስን በአስደናቂ ፊንታ በማታለል ኳሷን መረብ ላይ አሳርፏል።ስዊድኖች ወዲያውኑ አቻ ለመሆን የሚያስችል አጋጣሚ አግኝተው የነበረ ቢሆንም፣ ኤሊዮት ስትሮውድ ከግቡ 12 ያርድ ርቀት ላይ ያገኘውን ኳስ አባክኖታል። ይህ ሙከራ የስዊድን የመጨረሻው ተስፋ ሆኖ ነው ያለፈው።በሁለተኛው አጋማሽ ፈረንሳይ ይበልጥ አስፈሪ ሆና ቀረበች። ጨዋታው በተጀመረ በስምንተኛው ደቂቃ፣ ብራድሌይ ባርኮላ ከማይክል ኦሊሴ የተሻገረለትን ኳስ በአቅራቢያው ባለው ቋሚ በኩል መረብ ላይ በማሳረፍ መሪነታቸውን አጠናከረ።
ዴምቤሌ በቀኝ በኩል አክርሮ የመታውን ኳስ እና ኦሊሴ ፊት ለፊት ተገናኝቶ የሞከረውን ኳስ የስዊድኑ ግብ ጠባቂ ዜተርስትሮም በድንቅ ሁኔታ ቢያድንም፣ በ74ኛው ደቂቃ ላይ ግን ያው የተለመደው የፈረንሳይ ጥምረት ደገመ፤ ኦሊሴ በድጋሚ ያቀበለውን ኳስ ምባፔ አክርሮ በመምታት የፈረንሳይን 3ኛ እና የማረጋገጫ ግብ አስቆጠረ።የቀድሞዋ የስኮትላንድ ተከላካይ ጄን ቢቲ ከኒው ጀርሲ ስታዲየም ሆና በሰጠችው አስተያየት የፈረንሳይን ብቃት አድንቃለች። "ፈረንሳይ በዓለም ዋንጫው መድረክ ላይ ማሸነፍን እንዲህ ቀላል አድርጋ ማሳየቷ እጅግ የሚያስፈራ ነው። አጨራረሳቸው ፍጹም ድንቅ ነበር፤ ተቀያይረው የሚገቡትን ጨምሮ ሙሉ ስብስባቸውን የሚጠቀሙበት መንገድ አስገራሚ ነው። ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸው ሙሉ በሙሉ የሚገባቸው ነው። የፊት መስመራቸው በኮከቦች የተሞላ ነው፤ ለዋንጫው ዋነኛ ግምት የተሰጣቸው ያለ ምክንያት እንዳልሆነ ዛሬ በተግባር አይተናል" ስትል ተናግራለች።
የስፖርት ጋዜጠኛው ኒል ጆንስተንም በበኩሉ "በዚህ የፈረንሳይ የጥበብ ትርኢት መሸነፍ ለስዊድኑ አሰልጣኝ ግርሃም ፖተርም ሆነ ለስዊድን ቡድን ምንም የሚያሳፍር አይደለም። ፖተር ጨዋታው ሲጠናቀቅ ዲዲዬ ዴሻምፕን አቅፎታል። ፈረንሳይ በዚህ አስፈሪ አቋሟ ላይ ስትሆን ማን ሊያቆማት ይችላል?" በማለት የፈረንሳይን ልዕልና ገልጿል።ይህንን አስደናቂ ድል ተከትሎ ወደ ምርጥ 16ቱ የተቀላቀለችው ፈረንሳይ፣ ሰኞ ዕለት ጀርመንን በመለያ ምት አሸንፋ ትልቅ ጀብዱ ከሰራችው ፓራጓይ ጋር ቅዳሜ ጁላይ 4 በፊላደልፊያ የምትፋለም ይሆናል!

ብራዚል ያነባች ዕለት - የጀርመኑ ዓለም ዋንጫ ትዝታዎች
****************
ያኔ ብራዚል እንዲህ ትሆናለች፣ በመሰል ደረጃ ላይ ትገኛለች ብለው ብዙዎች አልጠበቁም። ሁለት አስርት ዓመታት አልፈው ወደ ኋላ መለስ ብለው ሲያስታውሱት የሆነው ግን እንደዚያ ነው። የ2006 ዓለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ የቀደመውን አሸናፊ ፈረንሳይ እና የወቅቱን ሻምፒዮን ብራዚልን አገናኝቷል።
የ21ኛው ክፍለ ዘመን የብራዚል ወርቃማ ትውልድ፣ ኳስ የጥበብ አውድማ መሆኑን ዳግም ያስመሰከሩት ጥበበኞች ስብስብ ጀርመን ምድር ለዓለም ዋንጫው ሲዘልቁ ለ6ኛ የመድረኩ አሸናፊነት፣ ለተከታታይ ሻፒዮንነት ነው የታጩት።
ሮናልዶ ሉዊስ ናዛሪዮ ዴሊማ፣ ሮናልዲንሆ ጎቾ፣ ካካ፣ ካፉ፣ ሮቤርቶ ካርሎስ፣ አድሪያኖ እና ዚ ሮቤርቶን የመሰሉ ክዋክብት እንደ ምን ይዘነጋሉ? የሰው አዕምሮ ሊዘነጋቸው ቢፈቅድ እንኳ የእግር ኳስ ታሪክ ሊረሳቸው አይቻለውም። ትዝታቸው ርቆ ያልራቀ፣ ደብዝዞ ያልጠፋ፣ ቀጥኖ ያልተበጠሰ ህልው ነው። ከመዘንጋት የራቀ ታሪክ!
የዚያች ዕለት ግን ቀን ከነርሱ በተቃራኒ የቆመች መሰለች። የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በተለይም ዚነዲን ዚዳን በዚያች ቀን ስል፣ አስፈሪ እና ባለ ግርማ ሞገስ ሆነው ነው የቀረቡት።
ዚዳን ፀጉሩ እንደከዳው፣ የጎልማሳነት ደጃፉ ላይ እንደቆመ፣ ከእግር ኳስ የመሰናበቻ ቀናቱ እንደደረሰ ሳይሆን የ20ዎቹ አጋማሽ ላይ እንደሚገኝ ወጣት ነበር ይቦርቅ የነበረው።
በዚያ ጨዋታ ዚዳን የነበረው እንቅስቃሴ በዓለም ዋንጫ ታሪክ በግለሰብ ደረጃ ከተደረጉ እንቅስቃሴዎች ምርጡ እንደሆነ የብዙዎች እምነት ነው። የዘመን ተጋሪው ሮናልዶ ሉዊስ ናዛሪዮ ዴሊማም ያን ጨዋታ አስመልክቶ በሰጠው ቃለ-መጠይቅ “በዚያ ጨዋታ ዚዳን ያደረገው እንቅስቃሴ ያለማወላዳት በዓለም ዋንጫው ታሪክ ከታዩ ምርጥ ብቃቶች እንደ አንዱ ሊመደብ የተገባ ነው” ነበር ያለው።
ፈረንሳይ በቴሪ ሄንሪ አማካኝነት ባስቆጠረችው ግብ ጨዋታውን 1 ለ 0 አሸንፋ የወቅቱን የዓለም ሻምፒዮን ከውድድሩ አሰናበተቻት። ያኔ ብዙ አለማመኖች ነበሩ፣ የሆነው ከብዙዎቹ ጥበቃ በተቃራኒ ነው።
የ1998 ዓለም ዋንጫ አሸናፊ፣ የነ ዚነዲን ዚዳን ሀገር የወቅቱን የዓለም ሻምፒዮን ከዓለም ዋንጫ አስወጣቻት የሚለው በመጨረሻ የዳኛውን ፊሽካ ተከትሎ የተሰማው ዜና ነበር።
ያ ታሪክ በፍራንክፈርቱ ባልድ ስታዲየም የመጫወቻ ሜዳ ብቻ ተፈፅሞ ያበቃ አልሆነም። ወደ ካናሪንሀ መልበሻ ክፍልም ተከትሎ አምርቷል። በዕለቱ ልዩ የነበረው፣ ለቴሪ ሄንሪም ለግብ የምትሆነውን ኳስ አመቻችቶ ያቀበለው ዚነዲን ዚዳን ወደዚያች መልበሻ ክፍል አመራ።
አንድም ሊያፅናና አንድም በትልልቅ የእግር ኳስ መድረኮች እንደተለመደው መለያ ሊቀያየር።
‛ኤል ፌኖሜኖ’ ይህን የዚዳን ተግባር በበጎ አልተመከተውም። ሮናልዶ ከ20 ዓመታት በኋላ ሁነቱን አስመልክቶ ሲናገር “ሁላችንም ዛሬ ድረስ አብረን የቀጠልን ጓደኛሞች ነን፣ እርሱ ወደ መልበሻ ክፍል ሲገባ ግን የነበረው ድባብ አስፈሪ ነበር።
ብዙ ተጫዋቾች እያነቡ ነበር፤ እናም መለያ ለመቀያየር ወደ መልበሻ ክፍሉ የመጣበት ሰዓት ትክክለኛ እንዳልሆነና እንዲመለስ አስረግጬ ነገርኩት” ይላል።
እንደ ሮናልዶ እምነት ያች ዕለት የዓለም ዋንጫን ታሪክ ራሱን ቀይራለች። በእርግጥም በብራዚል በኩል ሆኖ ለተመለከተው ብዙ እውነት የሚመስሉ ነገሮችን የያዘ ሃሳብ ነው።
ለዓለም እግር ኳስ የስኬታማነት ናሙና የሆኑ ክዋክብትን ያበረከተችው ብራዚል ከትልቁ መድረክ አሸናፊነት እንደተናጠበች ሩብ ምዕተ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው። እነዛን ኮከቦች ግን እግር ኳስ ሊዘነጋቸው አይቻለውም።
በእርግጥ ፈረንሳይ አስከ ፍፃሜ ብትጓዝም፣ በዚነዲን ዚዳን እና ማርኮ ማታራዚ ድራማ በታጀበው ጨዋታ፣ በነ ማርሴሎ ሊፒ እና አንድሪያ ፒርሎ ጣሊያን ተረታ ለሌላ ዓለም ዋንጫ አሸናፊነት 12 ዓመታት ለመጠበቅ ተገዳለች።
ዚዳንን የ2006ቱ ዓለም ዋንጫ ‛አንተ በእግር ኳስ ስንብትህ ደጃፍ ላይ ቆመህ በእኔ ያበራህ ኮከብ ነህ’ ብሎታል።
ዓለም ዋንጫ ትዝታ ነው። ድልና ሽንፈት፣ ደስታ እና ሀዘን፣ ሳቅ እና ለቅሶ የሚመላለስበት የስፖርት አውድማ፤ የትውስታ መቼት ነው። መንገዱ ይቀጥላል!
በእድሪስ አህመድ
#worldcup #brazil #sports #japan #ebc Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት

ጀርመን ከዓለም ዋንጫ ተሰናበተች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ፓራጓይ የ4 ጊዜ ሻምፒዮኗን ጀርመንን በመለያ ምት በማሸነፈ 16ቱን ተቀላቅላለች።
በጨዋታው ኢንሲሶ ፓራጓይን ቀዳሚ ሲያደርግ ካይ ሀቨርትዝ ደግሞ ጀርመንን አቻ አድርጓል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ እና ተጨማሪ 30 ደቂቃውን 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቅቀዋል፡፡
አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠ የመለያ ምትም ፓራጓይ የ4 ጊዜ ሻምፒዮኗን ጀርመንን 4 ለ 3 በማሸነፍ 16ቱን መቀላቀል ችላለች፡፡
ፓራጓይ በቀጣዩ ዙር ጨዋታ የፈረንሳይ እና የስዊድንን አሸናፊ የምትገጥም ይሆናል።

የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና አሸናፊዎች ተለዩ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና በዛሬው እለት ተጠናቋል።
በቀዳሚነት በተካሄደው ውድድር ቤተልሔም ዳንኤል በ80 ኪ.ሜ የሴቶች ኤሊት ውድድር አንደኛ በመውጣት አሸንፋለች።
እንዲሁም ፍሊሞን ዘርአ ብሩክ በ140 ኪ.ሜ የወንዶች ኤሊት ውድድር ቀዳሚ ሆኗል።
ሁለቱም አሸናፊዎች በካናዳ ሞንትሪያል ለሚካሄደው የዓለም ብስክሌት ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክለው ይሳተፋሉ።
ውድድሩ በካናዳ ሞንትሪያል ለሚካሄደው የዓለም ብስክሌት ሻምፒዮና (ሀCI) ላይ ሀገራችንን ወክለው የሚሳተፉ ምርጥ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ የተደረገ ዋና መድረክ እንደሆነ ተነግሯል።
ባለፉት ዓመታት በተደረጉ መሰል ብሔራዊ ሻምፒዮናዎች ላይ የተገኙ ውጤቶች ስፖርተኞቻችን በጀርመን እና በቻይና ፕሮፌሽናል ክለቦችን እንዲቀላቀሉ ዕድል የፈጠሩ ነበር ተብሏል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#የኢትዮጵያብስክሌትሻምፒዮና #ካናዳሞንትሪያል #ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን #getutemesgenmediacommunication

የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና በደመቀ ሁኔታ ተጠናቀቀ!
አሸናፊዎቹ ወደ ካናዳ ያመራሉ!
#fastmereja I የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ከጆርካ ኢቨንትስ ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና ከ200 በላይ ድንቅ ተወዳዳሪዎች የተሳተፉበት የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።
ከሰኔ 17 ቀን ጀምሮ ሲካሄድ የቆየዉ ይህ ታላቅ ብሔራዊ ውድድር፣ ዛሬ በተደረገው ማራኪና አጓጊ የጎዳና ላይ ፉክክር ፍጻሜውን አግኝቷል።
ይህ ውድድር በካናዳ ሞንትሪያል ለሚካሄደው የዓለም ብስክሌት ሻምፒዮና (ሀCI) ላይ ሀገራችንን ወክለው የሚሳተፉ ምርጥ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ የተደረገ ዋና መድረክ በመሆኑ በከፍተኛ የፉክክር መንፈስ የተከናወነ ሲሆን፣ ዛሬ በወንዶችም በሴቶችም አሸናፊ የሆኑት ስፖርተኞች ወደ ካናዳ የሚያመሩ ይሆናል።
ዛሬ ረፋድ ላይ መነሻውን ቦሌ ኤድናሞል (ከሸገር ሕንፃ አጠገብ) አድርጎ በተካሄደው የፍጻሜ ውድድር ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርየስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መክዩ መሐመድ፣ የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን እና የአፍሪካ ብስክሌት ኮንፌደሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ሐይሌ፣ የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ኃላፊዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በስፍራው ተገኝተው ውድድሩን አስጀምረዋል።
እልህ አስጨራሽ በነበረውና 80 ኪሎ ሜትር በሸፈነው የሴቶች ኤሊት የመንገድ ውድድር፣ በተለይም የመጨረሻዎቹን ሦስት ዙሮች ብቻዋን በሰፊ ልዩነት በመምራት ብስክሌተኛዋ ቤተልሔም ዳንኤል አንደኛ በመሆን ዉድድሩን አጠናቃለች።
በሌላ በኩል፣ 140 ኪሎ ሜትር በሸፈነውና ከፍተኛ ትንቅንቅ በታየበት የወንዶች ኤሊት የመንገድ ውድድር ብስክሌተኛው ፊሊሞን ዘርአ ብሩክ ተፎካካሪዎቹን በብቃት በመቅደም በአንደኝነት አጠናቋል።
ባለፉት ዓመታት በተደረጉ መሰል ብሔራዊ ሻምፒዮናዎች ላይ የተገኙ ውጤቶች ስፖርተኞቻችን በጀርመን እና በቻይና ፕሮፌሽናል ክለቦችን እንዲቀላቀሉ ዕድል የፈጠሩ ሲሆን፣ የዛሬው ውድድርም ለአሸናፊዎቹ የዓለም ሻምፒዮና በርከመክፈቱ ባሻገር ለቀጣይ ዓለም አቀፍ የፕሮፌሽናል ዕድሎች ትልቅ መሠረት እንደሚሆን ተጠቅሷል።
በውድድሩ ማጠቃለያ ላይም ለዚህ ታላቅ ብሔራዊ ስፖርታዊ ኩነት መሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የተለያዩ አካላትና ደጋፊዎች የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቷል።

ኢትዮጵያ፣ አውሮፓ ኅብረት ወደ አገራቸው ሊባረሩ የማይችሉ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለመላክ ከመረጣቸው አገራት መካከል አንዷ መኾኗን ሂውማን ራይትስ ዎች ገለጠ።
ተቋሙ፣ ኅብረቱ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሦስተኛ አገራት ለመላክ አዲስ ስልቶችን እየቀየሠ ይገኛል በማለት ወቅሷል።
ጀርመን፣ ኦስትሪያ፣ ዴንማርክ፣ ግሪክ እና ኔዘርላንድስ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለመላክ ከመረጧቸው አገራት መካከል፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ቱኒዚያ፣ ግብጽ፣ ሊቢያ እና ሞሪቴኒያ እንደሚገኙበት ተቋሙ ጠቅሷል።
ተቋሙ፣ ተቀባይ አገራት የጥገኝነት ጠያቂዎቹን ሰብዓዊ መብት ያከብሩ፣ ወደ ትውልድ አገራቸው ይመልሷቸው ወይም ያስሯቸው እንደኾነ ግልጽ አይደለም ሲል ስጋቱን ገልጧል።
የኅብረቱ አገራት ይህንኑ እቅድ እንዲተውት ያሳሰበው ተቋሙ፣ ይህ ካልሆነ ግን እቅዱ ተግባራዊ ከመኾኑ በፊት ኅብረቱ ቢያንስ በተቀባይ አገራት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ጥብቅ ግምገማ እንዲያደርግ እቅዱን የሚቃወሙት የፈረንሳይና ስፔን መሪዎች ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቋል።

የ32ቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ እየተካሄደ በሚገኘው የ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቅቀዋል።
ከየምድቦቻቸው 1ኛ እና 2ኛ በመሆን 24 ሀገራት በቀጥታ እንዲሁም ተጨማሪ 8 ሀገራት ምርጥ 3ኛ በመሆን የ32ቱን ጥሎ ማለፍ ተቀላቅለዋል።
በዚህም መሰረት የ32ቱ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ከምድብ 1 እና 2 ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቁት ደቡብ አፍሪካ እና አዘጋጇ ሀገር ካናዳ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀምራል።
ምድብ ሦስትን በበላይነት ያጠናቀቀችው ብራዚል ከጃፓን እንዲሁም የምድብ 5 አሸናፊዋ ጀርመን ከፓራጓይ ተደልድለዋል።
ኔዘርላንድስ ከሞሮኮ፣ ኮትዲቯር ከኖርዌይ፣ ፈረንሳይ ከስዊድን፣ ሜክሲኮ ከኢኳዶር፣ እንግሊዝ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ እንዲሁም ቤልጂዬም ከሴኔጋል ይገናኛሉ።
አሜሪካ ከቦሲኒያ ሄርዞጎቪና፣ ስፔን ከኦስትሪያ፣ ፖርቹጋል ከክሮሺያ፣ ስዊዘርላንድ ከአልጄሪያ፣ አውስትራሊያ ከግብጽ፣ አርጀንቲና ከኬፕቨርዴ እንዲሁም ኮሎምቢያ ከጋና ተደልድለዋል።

የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች:-
✅ ከጠዋቱ 4፡00-ቀኑ 9፡30
👉 ሜክስኮ፣ ብሔራዊ ፣ ሰንጋተራ 40/60 ኮንዶሚኒየም፣ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፣ ኩባ ፓርክ፣ ተ/ሃይማኖት፣ በርበሬ በረንዳ፣ ዲአፍሪካ እና አካባቢያቸው ፣
✅ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 8፡00
👉ጎፋ ካምፕ፣ ጀርመን አደባባይ፣መከኒሳ አረቄ ፋብሪካ፣ላፍቶ፣ ቄራ፣ቆሼ፣ ዘነበወርቅ፣ጎፋ እና አካባቢያቸው ፣
✅ ከጠዋቱ 3፡00-10፡30
👉ሸገር ዳቦ፣ ኤሞሌስ ፋብሪካ፣ ለገ ጣፎ ከተማ ፣ የካሰዴ፣የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም፣ወሰን ግሮሰሪ፣ ሲኤምሲ ሚካኤል፣ ካራሎ፣ለገጣፎ፣ ሲዲሲ ፣ ኮሰሮ፣ ለገዳዲ፣ ሰንዳፋ፣ 44 ማዞሪያ፣ ሲሬ ጎዩ፣ የካ ሰዴ፣ድሬ ሰኩር እና አካባቢያቸው፣
👉 ጁኒፐር ግላስ፣ ደጋ ውሃ፣ ቻንግልዶንግራን፣ ፊበላ፣ ቦልት ማልት፣ ሃዋ ትሬዲንግ፣ ብራውን ፉድ ፣ ማማ ዱኬት ፋብሪካዎች እና አካባቢያቸው ፣
✅ ከለሊቱ 6፡00-ቀኑ 6፡00
👉 ድሬደዋ ውሃ፣ ፓይነር ሲሚንቶ፣ ቱሬ ሲሚንቶ፣ ሀረር ውሃ፣ ማረሚያ፣ ኩርቱ፣ በለዋ፣ ቃልቻ፣ ቢሻን በሄ፣ ሃሎብሳ፣ ለጎዳ፣ አሳሊሶ፣ ኢንዱስትሪ ኮንዶሚኒየም፣ ሻሎም ኢንጂነሪንግ፣ መልካ፣የኢንዱስትሪ እና አካባቢያቸው፣
✅ ከጠዋቱ 1፡30-5፡00
👉አዳማ ከወንጂ ቀበሌ ኮንዶሚኒየም እና አካባቢያቸው ፣
✅ ከጠዋት 12፡00-12፡00
👉በአሰላ፣ አዳሚቱሉ፣ ቡታጅራ፣ ወራቤ እና አካባቢው
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ውድ ደንበኞቻችን፤ የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስከሚመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን ትብብራችሁን እንጠይቃለን፡፡

በመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋ በአንድ ነጥብ የተሰናበተችው ኩራሳኦ …
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ዋንጫ የተሳተፈችው ሀገር ኩራሳኦ በአንድ ነጥብ እና በስምንት የግብ ዕዳ የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋን አጠናቅቃ ወደ ሀገሯ ተመልሳለች፡፡
በዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችው ሀገር ኩራሳኦ በዓለም ዋንጫ መድረክ የራሷን ታሪክ ፅፋ ከውድድሩ ተሸኝታለች፡፡
ኩራሳኦ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ በአራት ጊዜ የመድረኩ ሻምፒዮን ሀገር ጀርመን 7 ግብ ቢቆጠርባትም አንድ ግብ አስቆጥራ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በጨዋታው በርካታ ግብ ብታስተናግድም በዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዋ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ ግብ ማስቆጠር ችላለች፡፡
በጀርመን ከደረሰባት የ7 ለ 1 ሽንፈት በኋላ በሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ኢኳዶርን የገጠመቸው ኩራሳኦ 0 ለ 0 በመለያየት በመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋ አንድ ነጥብ ማሳካቷ ይታወሳል፡፡
ኩራሳኦ ከኢኳዶር በነበራት የምድብ 2ኛ ጨዋታ የ37 አመቱ ግብ ጠባቂ ሩም አስደናቂ ብቃት በማሳየት 15 ያለቀላቸው ኳሶችን በማዳን በደሴቲቱ ሀገር ትዝታ ውስጥ ለረጅም ጊዜ የማይፋቅ ታሪክ ጽፏል፡፡
ግብ ጠባቂው በካንሳስ ሲቲ ስታዲየም በ68 ሺህ 98 ደጋፊዎች ፊት ስሙን በዓለም ዋንጫ ታሪክ በእግር ኳስ ትልቁ መድረክ ላይ በአጠቃላይ 27 ሙከራዎችን በማዳን የኢኳዶር ተጫዋቾች ግብ ሳያስቆጥሩ እንዲወጡ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡
ግብ ጠባቂው ድንቅ እንቅስቀሴ ማሳየቱን ተከትሎ በወቅቱ በስፖርት ቤተሰብ አድናቆት እንደተቸረገው ይታወሳል፡፡
ኩራሳኦ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዋን ከኮትዲቯር ጋር አድርጋ 2 ለ 0 ተሸንፋ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋን አጠናቅቃለች፡፡
ኩራሳኦ በዓለም ዋንጫ ካደረገቻቸው ሦስት የምድብ ጨዋታዎች ሁለቱን ተሸንፋ በአንዱ አቻ ተለያይታ 9 ግቦች ተቆጥረውባት አንድ ግብ ብቻ አስቆጥራለች፡፡
በዓለም ዋንጫ በመሳተፍ ትንሿ ሀገር በመሆን በቀዳሚነት የተቀመጠችው ኩራሳኦ በአንድ ነጥብ እና በስምንት የግብ ዕዳ የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋን ጨርሳለች፡፡
በዓለም ዋንጫ በመሳተፍ ትንሿ ሀገር በመሆን አዲስ ታሪክ የጻፈችው ኩራሳኦ በድጋሚ በዓለም ዋንጫ መድረክ ትገኝ ይሆን የሚለው ይጠበቃል፡፡

Comments