19 days ago
እንግሊዝ በዓለም ዋንጫ፤ ለ60 ዓመታት ያልተፈታው ህልም፣ ያልተመለሰው ጥያቄ!
**************************
እንግሊዝ የዓለም ዋንጫን ዳግም ሳታነሳ ተጨማሪ 4 ዓመታት እንደሚቆጠሩ እርግጥ ከሆነ 24 ሰዓታት አለፉ። አትላንታ ላይ “ሦስቱ አናብስት” የዓለም ሻምፒዮን የመሆን ውጥን ይዘው፣ እስከ ግማሽ ፍፃሜም ተጉዘው የጀመሩት መንገድ በሊዮኔል ሜሲ አርጀንቲና ተቋርጧል። ለተጨማሪ ዓመታት እንዲወጡት የሚያስፈልግ ሌላ ዳገት፣ ሊወርዱትም የሚገባ ሌላ ቁልቁለት ‘ተበጅቶላቸዋል’።
እነዛ 60 ዓመታት በዓለም እግር ኳስ የራሷን አሻራ ላኖረችው ሀገር ብዙ መውጣትና መውረዶች፣ በርካታ ተስፋ አስቆራጭ ደግሞም ተስፋ መልሶ የለመለመባቸው ወቅቶች አልፎባቸዋል። ዓለም ዋንጫ ግን ያዝኩት ሲሉ እያመለጠ፣ ደረስኩበት ሲሉ እየራቀ “ጉም የመዝገን” ያክል ሆኖባቸዋል።
ሐምሌ 30/ 1966 እ.አ.አ ሰር ቦቢ ሙር የእንግሊዝን የመድረኩ ብቸኛ ድል፣ የቀደመውን የጁሊየስ ሪሜትስ ዋንጫ ካነሳ በኋላ ብዙ ነገሮች ባሉበት የሉም ተቀያይረዋል። እግር ኳስም፣ ራሷ እንግሊዝም ሆነ ዓለም ትላንትን አይመስሉም።
እንግሊዝ ምዕራብ ጀርመንን 4 ለ 2 አሸንፋ የመጀመሪያ ዓለም ዋንጫዋን ካነሳች በኋላ፤ 454 ተጫዋቾች ነጩን የብሔራዊ ቡድን መለያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለብሰዋል። ቀዳሚው በ1967 የተጫወተው 847ኛው ተጫዋች ጆን ሆሊንስ ሲሆን፤ የብሔራዊ ቡድኑን መለያ በመልበስ ደግሞ የመጨረሻ የሆነው 1300ኛው የሊቨርፑሉ ሪዮ ንጉምሃ ነው። በዓለም ዋንጫው ደግሞ ከውጤታማው የአልፍ ራምሴይ ቡድን ጀምሮ እሰከ አሁኑ ቶማስ ቱሄል ድረስ 161 ተጫዋቾች እንግሊዝን ወክለዋል።
በስድሰቱ አስርታት ዋንጫ አልባ ዓመታት 15 አሰልጣኞች በቋሚነት ብሔራዊ ቡድኑን መርተዋል። ሮን ግሪንዉድ፣ ሰቨን ጎራን ኤሪክሰን፣ ፋቢዮ ካፔሎ እና ጋሬት ሳውዝጌት ተጠቃሾች ናቸው። ሁሉም ግን የአልፍ ራምሴይን ውጤታማ መንገድ ማስቀጠል አልሆነላቸውም።
አለን ሺረር፣ ዴቪድ ቤካም፣ ስቴቨን ጄራርድ እና ሃሪ ኬን ባለፉት 60 ዓመታት በተካሄዱት ዓለም ዋንጫዎች ቡድኑን በአምበልነት ከመሩ ተጫዋቾች የሚጠቀሱ ናቸው።
እንግሊዝ ከ1966 ሻምፒዮንነቷ በኋላ ከተካሄዱት 15 የዓለም ዋንጫዎች በ12ቱ ተሳትፋለች። በሁሉም ግን ደርሶ የመመለስ፣ አግኝቶም የማጣት ምሳሌ ተደርጋ ቀጥላለች። በ1986 የዲዬጎ ማራዶና በ4 ደቂቃ ልዩነት ያሳየው “የእጅም የእግርም” ትርዒት፣ በ1990 ግማሽ ፍጻሜ የፖል ጋስኮኝ እንባ፣ በ1998 ዓለም ዋንጫ የዴቪድ ቤካም ቀይ ካርድ፣ በ2002 ዓለም ዋንጫ የሮናልዲንሆ ጎቾ ዝነኛ የቅጣት ምት “ወርቃማ ግብ”፣ በ2010 መስመሯን አልፋ የተሻረችው የፍራንክ ላምፓርድ ግብ፣ በ2022 ዓለም ዋንጫ ሀሪ ኬን ያባከናት የፍፁም ቅጣት ምት፣ በመጨረሻም 2026 ላይ በአትላንታ ምድር እየመሩ የነበረውን ጨዋታ የኋላ ኋላ ማጣት፤ እንግሊዞች በቁጭት የሚያስታውሷቸው አጋጣሚዎች ናቸው።
ከዚያ በኋላ የበርሊን ግንብ ፈርሷል፣ የሰው ልጅ ወደ ጨረቃ መጥቋል፣ ዓለም በበይነ መረብ ተሳስሯል፣ የስማርት ስልክ ዘመን የሰው ልጅን የዕለት ተዕለት ህይወት ፈጣን አድርጓል። እነዚህና መሰል ለውጦች በሰው ልጅ የምድር ቆይታ ቢስተናገዱም፤ የእንግሊዝ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮንነት ህልም 1966 ላይ እንደቆመ አለ።
እንግሊዝ ባስተናገደችው የ1996ቱ አውሮፓ ዋንጫ ወቅት የተዜመው “…30 የህመም ዓመታት” የሚል ሀረግ የያዘውና የ1966ቱን ዓለም ዋንጫ በማስታወስ እግር ኳስ ወደ ቤቱ እየተመለሰ እንደሆነ የሚያትተው ኅብረ ዝማሬ፣ ዛሬም አውዱን የሳተ አይመስልም። 30ዎቹ ዓመታት ሌላ 30 ዓመታትን አዋልደዋል፤ እግር ኳስም ወደ “ቤቱ” አልተመለሰም።
የብሔራዊ ቡድኑን መለያ ከለበሱት 454 ተጫዋቾች፣ በዓለም ዋንጫው ከተጫወቱት 161 እግር ኳሰኞች፣ በ15ቱ አሰልጣኞች ስር ካለፉ 7 አምበሎች የምድር ትልቁን የእግር ኳስ ሽልማት ከፍ አድርጎ ማንሳት የቻለው ቦቢ ሙር ብቻ ነው።
ትውልድ ይተካል፣ ተስፋም እየደበዘዘም ቢሆን መልሶ ይለመልማል። እንግሊዛውያንም እግር ኳሳቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በሊግ ውድድሮች በቅርቦቹ ዓመታት እንዳሳደረው ተፅእኖ፤ ብሔራዊ ቡድናቸውም ይህን የዘመናት ህልሙን እውን የሚያደርግበትን ቀን በተስፋ ይጠባበቃሉ።
የ2026ቱ የአሜሪካ ምድር መንገድ ግን ጫፍ ደርሶ ተቋርጧል። ጁድ ቤሊንግሃም “ልብ ሰባሪ ፍፃሜን ያስከተለ ውብ ጉዞ” ሲል የገለፀው የ2026 ዓለም ዋንጫ ቆይታ አብቅቷል።
በእድሪስ አህመድ
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup1966 #england #threelions #judebellingham #harrykane #semifinal #football #sports #ebc

24 days ago
እንግሊዝ በቤሊንግሃም አስደናቂ ብቃት ለግማሽ ፍጻሜ አለፈች
#ethiopia |የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች በከፍተኛ ትንቅንቅ እየቀጠሉ ይገኛሉ። ዛሬ በተደረገው እጅግ አስደናቂ ጨዋታ እንግሊዝ ኖርዌይን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜው መሸጋገሯን አረጋግጣለች።
የጨዋታው Highlights
የኖርዌይ መሪነት፡ የውድድሩ አስደናቂ ክስተት በመሆን የቀጠለችው ኖርዌይ በሽልድረፕ ግብ መሪነትን ይዛ የነበረ ቢሆንም፣ የሶስት አንበሶቹን አስፈሪ ጥቃት መቋቋም አልቻለችም። በዚህም የኖርዌይ አስደናቂ ጉዞ በሩብ ፍጻሜው ተገቷል።
የቤሊንግሃም ድምቀት፡ 120 ደቂቃ በወሰደው በዚህ አስደናቂ ፍልሚያ የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ጁድ ቤሊንግሃም ሁለቱንም የእንግሊዝን ግቦች በማስቆጠር የቡድኑ ባለውለታ ሆኗል።
ለኮከብ ግብ አስቆጣሪነት የሚደረግ ፉክክር
ቤሊንግሃም በመድረኩ በተከታታይ ሁለት ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፣ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ላይ ያስቆጠረውን አጠቃላይ የግብ ብዛት 6 አድርሷል። ይህም ለውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብር (ወርቃማው ጫማ) በግንባር ቀደምትነት እንዲፎካከር አድርጎታል።
ቀጣይ ተጋጣሚ ማነው?
ወደ ግማሽ ፍጻሜው ያለፈችው እንግሊዝ፣ ቀጣይ ተጋጣሚዋን ለማወቅ ከአርጀንቲና እና ስዊዘርላንድ ጨዋታ አሸናፊ የሚወጣውን ቡድን የምትጠብቅ ይሆናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#worldcup2026 #judebellingham #england #norway #footballnews #getutemesgen

Comments