ሊዮኔል ስካሎኒ በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት 100ኛ ጨዋታውን ያደርጋል
**************************
የ“አልበ ሰልስቴ”ዎቹ ወርቃማ ትውልድ ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል። ለሌላ የዓለም ሻምፒዮንነት የጀመረውን መንገድ በአስገራሚ ሁኔታ እየተጓዘ ነው። የ48 ዓመቱ ሰው በሊዮኔል ሜሲ ዙሪያ የተገነባውን ቡድን በአህጉር እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ ስኬታማነት እያመላለሰው ነው።
ከ2018ቱ ዓለም ዋንጫ በኋላ ስካሎኒ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን አሰልጣኝነት ሲረከብ በዓለም እግር ኳስ በጉልህ የሚጠራ ስም አልነበረውም። ሆኖም አሰልጣኙ የጎላ የአሰልጣኝነት ልምድ ሳይኖረው የኳታሩን ዓለም ዋንጫ ጨምሮ ሁለት የኮፓ አሜሪካ ክብሮችን አሳክቷል። የፋይናሊዝማ ዋንጫም የስኬቱ አካል ነው።
ያኔ ከስምንት ዓመታት በፊት ስካሎኒ የሆርጌ ሳምፓውሊን መንበር ሲረከብ ታላቁን ማራዶና ጨምሮ ብዙዎች በጥርጣሬ ነበር የተመለከቱት። ልምዱ ታላቋን የእግር ኳስ ሀገር በአሰልጣኝነት ለመምራት ብቁ አይደለም የሚለው የጥርጣሬው መነሻ ነበር።
ማራዶና ኃይለ ቃላትን ጭምር ተጠቅሞ ስካሎኒን የተቸው ጄራርዶ ማርቲኖ ወደ ቀድሞ አሰልጣኝነታቸው መመለሳቸውን በመሻትም ጭምር ነው።
የቀድሞ የዲፖርቲቮ ላካሮኛ እና ላዚዮ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ለብሔራዊ ቡድንም ቢሆን ከሰባት ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ውጭ ኣላሸነፈም። ከሊዮኔል ሜሲ ጋር አብረው የተጫወቱበት የ2006 የጀርመን ዓለም ዋንጫ በተጫዋችነት ትልቁ ዓለም አቀፍ ተሳትፎው ነው።
የአሰልጣኝነት ትልቁ ልምዱ ግን በ2018 ዓለም ዋንጫ በ16ቱ ጥሎ ማለፍ በተሰናበተው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የሆርጌ ሳምፖሊ ረዳት ሆኖ ሲሰራ ይጀምራል። የሳምፖሊ መሰናበት ደግሞ ለስካሎኒ አዲስ ዕድል ይዞለት መጣ።
“አልበ ሰልስቴ”ዎቹን በዋና አሰልጣኝነት የመምራት ዕድል። በዚህም ጊዜያዊ አሰልጣኝ በኋላም ዋና አሰልጣኝ ሆኖ በቅርብ ዓመታት ከታዩ ውብ እግር ኳስ ከሚጫወቱ ብሔራዊ ቡድኖች አንዱን አሳየ።
“ስካሎኒታ” አሁን በተጫዋችነት ዘመኑ ያላገኘውን ክብር በአሰልጣኝነት ተቀዳጅቷል። ስካሎኒ ብሔራዊ ቡድኑን እየመራ ካደረጋቸው 99 ጨዋታዎች 72 አሸንፏል፣ በ18 አቻ ተለያይቷል፣ በ9 ጨዋታዎች ደግሞ ተሸንፏል። ከ2019 – 2022 የተጓዘበት በ36 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞውም የመንገዱ አካል ነው።
ነገ ሚያሚ ላይ የሚደረገው የ32ቱ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ለሊዮኔል ስካሎኒ 100ኛ መርኃ ግብር ሆኖ ይመዘገባል። አርጀንቲና ሲሆን አስከ ሻምፒዮንነት ካልሆነ ግን እስከ ፍፃሜ ትጓዛለች ተብላ በምትጠበቅበት በዚህ ዓለም ዋንጫ መሃል ስለ 100ኛ ጨዋታው ተጠይቆ፤ ያኔ 100ኛ ጨዋታው ላይ እደርሳለሁ ብሎ አስቦ እንዳልነበር ነው የተናገረው።
ሆኖም ይህ በህይወቱ አስቦት የማያውቀው ደረጃ ቢሆንም ዋነኛ ትኩረቱ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን ለተከታታይ የዓለም ሻምፒዮንነት ማብቃት መሆኑን ገልጿል።
ይህን በዓለም እግር ኳስ የስኬታማነት ምሳሌ የሆነ ታሪካዊ ቡድንን መምራት እና ይህን ያህል ርቀት መጓዝ ልዩ ስሜት እንደሚፈጥር ግን አልሸሸገም።
ትሁቱ ሰው የ21ኛው ክፍለ ዘመን የእግር ኳስ ክስተት ሜሲንም ሆነ ብሔራዊ ቡድኑን ውጤታማ በሚያደርግ አግባብ በእርሱ ዙሪያ የገነባው ቡድን ለስኬታማነቱ በምክኒያትነት የሚጠቀስ ዋነኛ ጉዳይ ነው።
የዓለም ዋንጫውን ኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ከኪሊያን ምባፔ ጋር በስድስት ግቦች እየመራ የሚገኘው ሊዮኔል ሜሲ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ የዘመኑን ውጤታማ ጊዜያት በስካሎኒ አሰልጣኝነት ስር ነው ያሳለፈው።
በ74 ጨዋታዎች 58 ጊዜ ኳስና መረብን አገናኝቷል። በ128 ጨዋታዎች 65 ግቦች ካስቆጠረበት የቀደመው ጊዜ ጋር ተነፃፅሮ በጨዋታዎች ብዛት ሲሳላ በእጅጉ ያነሰ ነው።
በመጀመሪያው 0.51 በሁለተኛው ደግሞ 0.78 በአማካይ በየጨዋታው ያስቆጠራቸው ግቦች ናቸው። ይህ ቁጥር ስካሎኒ በሜሲ ዙሪያ የሚያጠነጥን ቡድን ለመገንባቱ ጉልህ ማሳያ ነው።
የአሰልጣኙ ውል በቀጣይ ዓመት ታህሳስ ወር ላይ ያበቃል። የአርጀንቲና እግር ኳስ ፌደሬሽንም የአሰልጣኙን ውል ለተጨማሪ አምስት ዓመታት ለማራዘም እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል።
የ48 ዓመቱ ሊዮኔል ስካሎኒ በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት 100ኛ ጨዋታውን የዓለም ዋንጫው ክስተት ከሆነችው ኬፕቨርዴ ጋር ነገ ሌሊት 7፡00 ሰዓት በሚያሚው ሃርድ ሮክ ስታዲየም ያደርጋል።
በእድሪስ አህመድ
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #messi #argentina #football

1 month ago