20 days ago
እንግሊዝ በዓለም ዋንጫ፤ ለ60 ዓመታት ያልተፈታው ህልም፣ ያልተመለሰው ጥያቄ!
**************************
እንግሊዝ የዓለም ዋንጫን ዳግም ሳታነሳ ተጨማሪ 4 ዓመታት እንደሚቆጠሩ እርግጥ ከሆነ 24 ሰዓታት አለፉ። አትላንታ ላይ “ሦስቱ አናብስት” የዓለም ሻምፒዮን የመሆን ውጥን ይዘው፣ እስከ ግማሽ ፍፃሜም ተጉዘው የጀመሩት መንገድ በሊዮኔል ሜሲ አርጀንቲና ተቋርጧል። ለተጨማሪ ዓመታት እንዲወጡት የሚያስፈልግ ሌላ ዳገት፣ ሊወርዱትም የሚገባ ሌላ ቁልቁለት ‘ተበጅቶላቸዋል’።
እነዛ 60 ዓመታት በዓለም እግር ኳስ የራሷን አሻራ ላኖረችው ሀገር ብዙ መውጣትና መውረዶች፣ በርካታ ተስፋ አስቆራጭ ደግሞም ተስፋ መልሶ የለመለመባቸው ወቅቶች አልፎባቸዋል። ዓለም ዋንጫ ግን ያዝኩት ሲሉ እያመለጠ፣ ደረስኩበት ሲሉ እየራቀ “ጉም የመዝገን” ያክል ሆኖባቸዋል።
ሐምሌ 30/ 1966 እ.አ.አ ሰር ቦቢ ሙር የእንግሊዝን የመድረኩ ብቸኛ ድል፣ የቀደመውን የጁሊየስ ሪሜትስ ዋንጫ ካነሳ በኋላ ብዙ ነገሮች ባሉበት የሉም ተቀያይረዋል። እግር ኳስም፣ ራሷ እንግሊዝም ሆነ ዓለም ትላንትን አይመስሉም።
እንግሊዝ ምዕራብ ጀርመንን 4 ለ 2 አሸንፋ የመጀመሪያ ዓለም ዋንጫዋን ካነሳች በኋላ፤ 454 ተጫዋቾች ነጩን የብሔራዊ ቡድን መለያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለብሰዋል። ቀዳሚው በ1967 የተጫወተው 847ኛው ተጫዋች ጆን ሆሊንስ ሲሆን፤ የብሔራዊ ቡድኑን መለያ በመልበስ ደግሞ የመጨረሻ የሆነው 1300ኛው የሊቨርፑሉ ሪዮ ንጉምሃ ነው። በዓለም ዋንጫው ደግሞ ከውጤታማው የአልፍ ራምሴይ ቡድን ጀምሮ እሰከ አሁኑ ቶማስ ቱሄል ድረስ 161 ተጫዋቾች እንግሊዝን ወክለዋል።
በስድሰቱ አስርታት ዋንጫ አልባ ዓመታት 15 አሰልጣኞች በቋሚነት ብሔራዊ ቡድኑን መርተዋል። ሮን ግሪንዉድ፣ ሰቨን ጎራን ኤሪክሰን፣ ፋቢዮ ካፔሎ እና ጋሬት ሳውዝጌት ተጠቃሾች ናቸው። ሁሉም ግን የአልፍ ራምሴይን ውጤታማ መንገድ ማስቀጠል አልሆነላቸውም።
አለን ሺረር፣ ዴቪድ ቤካም፣ ስቴቨን ጄራርድ እና ሃሪ ኬን ባለፉት 60 ዓመታት በተካሄዱት ዓለም ዋንጫዎች ቡድኑን በአምበልነት ከመሩ ተጫዋቾች የሚጠቀሱ ናቸው።
እንግሊዝ ከ1966 ሻምፒዮንነቷ በኋላ ከተካሄዱት 15 የዓለም ዋንጫዎች በ12ቱ ተሳትፋለች። በሁሉም ግን ደርሶ የመመለስ፣ አግኝቶም የማጣት ምሳሌ ተደርጋ ቀጥላለች። በ1986 የዲዬጎ ማራዶና በ4 ደቂቃ ልዩነት ያሳየው “የእጅም የእግርም” ትርዒት፣ በ1990 ግማሽ ፍጻሜ የፖል ጋስኮኝ እንባ፣ በ1998 ዓለም ዋንጫ የዴቪድ ቤካም ቀይ ካርድ፣ በ2002 ዓለም ዋንጫ የሮናልዲንሆ ጎቾ ዝነኛ የቅጣት ምት “ወርቃማ ግብ”፣ በ2010 መስመሯን አልፋ የተሻረችው የፍራንክ ላምፓርድ ግብ፣ በ2022 ዓለም ዋንጫ ሀሪ ኬን ያባከናት የፍፁም ቅጣት ምት፣ በመጨረሻም 2026 ላይ በአትላንታ ምድር እየመሩ የነበረውን ጨዋታ የኋላ ኋላ ማጣት፤ እንግሊዞች በቁጭት የሚያስታውሷቸው አጋጣሚዎች ናቸው።
ከዚያ በኋላ የበርሊን ግንብ ፈርሷል፣ የሰው ልጅ ወደ ጨረቃ መጥቋል፣ ዓለም በበይነ መረብ ተሳስሯል፣ የስማርት ስልክ ዘመን የሰው ልጅን የዕለት ተዕለት ህይወት ፈጣን አድርጓል። እነዚህና መሰል ለውጦች በሰው ልጅ የምድር ቆይታ ቢስተናገዱም፤ የእንግሊዝ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮንነት ህልም 1966 ላይ እንደቆመ አለ።
እንግሊዝ ባስተናገደችው የ1996ቱ አውሮፓ ዋንጫ ወቅት የተዜመው “…30 የህመም ዓመታት” የሚል ሀረግ የያዘውና የ1966ቱን ዓለም ዋንጫ በማስታወስ እግር ኳስ ወደ ቤቱ እየተመለሰ እንደሆነ የሚያትተው ኅብረ ዝማሬ፣ ዛሬም አውዱን የሳተ አይመስልም። 30ዎቹ ዓመታት ሌላ 30 ዓመታትን አዋልደዋል፤ እግር ኳስም ወደ “ቤቱ” አልተመለሰም።
የብሔራዊ ቡድኑን መለያ ከለበሱት 454 ተጫዋቾች፣ በዓለም ዋንጫው ከተጫወቱት 161 እግር ኳሰኞች፣ በ15ቱ አሰልጣኞች ስር ካለፉ 7 አምበሎች የምድር ትልቁን የእግር ኳስ ሽልማት ከፍ አድርጎ ማንሳት የቻለው ቦቢ ሙር ብቻ ነው።
ትውልድ ይተካል፣ ተስፋም እየደበዘዘም ቢሆን መልሶ ይለመልማል። እንግሊዛውያንም እግር ኳሳቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በሊግ ውድድሮች በቅርቦቹ ዓመታት እንዳሳደረው ተፅእኖ፤ ብሔራዊ ቡድናቸውም ይህን የዘመናት ህልሙን እውን የሚያደርግበትን ቀን በተስፋ ይጠባበቃሉ።
የ2026ቱ የአሜሪካ ምድር መንገድ ግን ጫፍ ደርሶ ተቋርጧል። ጁድ ቤሊንግሃም “ልብ ሰባሪ ፍፃሜን ያስከተለ ውብ ጉዞ” ሲል የገለፀው የ2026 ዓለም ዋንጫ ቆይታ አብቅቷል።
በእድሪስ አህመድ
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup1966 #england #threelions #judebellingham #harrykane #semifinal #football #sports #ebc

22 days ago
አርጀንቲና ወደ ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ አለፈች
***************
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ በአትላንታ ስታዲየም በእንግሊዝና አርጀንቲና መካከል የተካሄደው ተጠባቂ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በአርጀንቲና 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ለአርጀንቲና የአሸናፊነት ግቦቹን በ85ኛው ደቂቃ ኤንዞ ፈርናንዴዝ እንዲሁም በጭማሪ ሰዓት (90+3) ላውታሮ ማርቲኔዝ ከመረብ አሳርፈዋል። ለእንግሊዝ ብቸኛዋን ግብ በ55ኛው ደቂቃ አንቶኒ ጎርደን አስቆጥሯል።
የወቅቱ የዓለም ሻምፒዮን አርጀንቲና ለዋንጫው ክብሯን ለማስጠበቅ የፊታችን እሁድ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ታላቅ የፍፃሜ ጨዋታዋን ታደርጋለች።
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ተሸናፊዎቹ ፈረንሳይና እንግሊዝ ደግሞ የፊታችን ቅዳሜ ሌሊት 3ኛ ደረጃ ይዞ ለማጠናቀቅ የሚጫወቱ ይሆናል።
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup #england #argentina #semifinal #football #sports

እንግሊዝ 0 - 0 አርጀንቲና :- የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤት
**************
በአትላንታ ስታዲየም በእንግሊዝ እና አርጀንቲና መካከል እየተካሄደ የሚገኘው እጅግ ተጠባቂ የዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup #england #argentina #semifinal #football #sports
**************
በአትላንታ ስታዲየም በእንግሊዝ እና አርጀንቲና መካከል እየተካሄደ የሚገኘው እጅግ ተጠባቂ የዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup #england #argentina #semifinal #football #sports
23 days ago
ስፔን ፈረንሳይን አሸንፋ ለፍፃሜ አለፈች
***************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ መርኃ ግብር ስፔን ከፈረንሳይ ያደረጉት ጨዋታ፤ በስፔን 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ለስፔን የአሸናፊነት ግቦቹን ሚኬል ኦያርዛባል 22ኛው ደቂቃ ላይ በፍፁም ቅጣት ምት እንዲሁም ፔድሮ ፖሮ በ58ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል።
በዚህም በ2010 የደቡብ አፍሪካውን ዓለም ዋንጫ ያሸነፈችው ስፔን ከ16 ዓመታት በኋላ ለውድድሩ ፍፃሜ ደርሳለች።
ወደ ፍፃሜው የተሸጋገረችው ስፔን በቀጣይ ከአርጀንቲና እና እንግሊዝ አሸናፊ ጋር እሁድ የምትጫወት ይሆናል።
#worldcup2026 #fifaworldcup2026 #fifaworldcup2026 #spain #france #semifinal #football #sports #ebc

6 months ago
🇪🇹 ኢትዮጵያዊቷ ሼፍ ለታላቁ የ"ጄምስ ቢርድ" ሽልማት ታጨች! 👩🍳🏆
"የምግብ ዓለም ኦስካር በሆነው መድረክ የኢትዮጵያን ጣዕም አድምቃለች"
በሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ የሚገኘው የ"ቤተሰብ ሬስቶራንት" (Beteseb Restaurant) ባለቤት እና ሼፍ የሆነችው ዳርምየለሽ ዓለሙ፤ ለ2026 የጄምስ ቢርድ (James Beard Awards) "የሚድ-አትላንቲክ ምርጥ ሼፍ" ዕጩ ተወዳዳሪ (Semifinalist) ሆና ተመርጣለች!
ይህ ሽልማት በአሜሪካ የምግብ ኢንዱስትሪ ትልቁ እና ክብር የሚሰጠው ሽልማት ነው።
ለምን ልዩ ይሆናል?
🌟 ከ20 ዕጩዎች መካከል ከሜሪላንድ ስቴት የተመረጡት ሁለት ሲሆኑ፤ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ (Montgomery County) ደግሞ ብቸኛዋ ተወዳዳሪ እሷ ነች።
🌟 ቤተሰብ ሬስቶራንት በዋሽንግተንያን (Washingtonian) የ2026 ምርጥ 100 ሬስቶራንቶች ዝርዝር ውስጥ 46ኛ ደረጃን ይዞ ነበር።
🌟 በታዋቂው ሼፍ ማርከስ ሳሙኤልሰን የቲቪ ፕሮግራም ላይ በመቅረብ የኢትዮጵያን ምግብ አስተዋውቃለች።
በውድድሩ አሸናፊ ሆና እንድትወጣ መልካም ምኞታችንን እንግለጽላት!
ዲሲ እና ሜሪላንድ አካባቢ ያላችሁ ጎራ ብላችሁ ሙያዋን አድንቁ!
📍 አድራሻ:
8201 Georgia Ave, Silver Spring, MD
📅 የፍጻሜ ውጤት: ሰኔ 15 ይገለጻል።
#ethiopianpride #jamesbeard2026 #chefdarmyelesh #betesebrestaurant #silverspring #ethiopianfood #dmveats #semifinalist

Sponsored by
Surafel
Comments