19 hours ago
እኔ ውሸታም ወይም አታላይ አይደለሁም!
#ethiopia | የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የሶሺዮሎጂ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ጄሰን አርደይ የሌሎች ምሁራን ጽሑፎች ያለ አግባብ ተጠቅመዋል በሚል ክስ ቀረበባቸው።
ክሱ በዋናነት የተነሳው በፈረንጆቹ 2015 ባዘጋጁት የመመረቂያ ጽሑፏቸው ላይ ሲሆን በዚህ ጽሁፋቸው የምሁራን ጥናቶች በቀጥታ ያለ ምንጭ ተጠቅመዋል የሚል ነው።
ፕሮፌሰሩም በፒኤችዲ ቴሲሳቸው እና ባሳተሟቸው አካዳሚያዊ ጥናቶች ላይ የቀረበባቸውን የጽሑፍ ስርቆት ክስ አስተባብለዋል።
ፕሮፌሰሩ በጥናቶቻቸው ላይ ጥቂት የአሰራር እና የቴክኒክ ስህተቶች መከሰታቸውን አምነው እኔ ግን ውሸታም ወይም አታላይ አይደለሁም ሲሉ ራሳቸውን ተከላክለዋል።
በቀደሙት ሥራዎቼ ላይ የቴክኒክና የምንጭ አጠቃቀም ስህተቶች መኖራቸውን እቀበላለሁ ለሰራኋቸው ስህተቶችም ኃላፊነቱን እወስዳለሁ ብለዋል።
ነገር ግን አካዳሚያዊ ማጭበርበር ወይም የፁሁፍ ስርቆት ፈፅመሀል የሚለው ውንጀላ ፍፁም ከእውነት የራቀና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ በሰጠው መግለጫ የቀረቡት አቤቱታዎች ላይ ጥልቅ ምርመራ መደረጉንና ፕሮፌሰሩ ምንም የፈፀሙት ስህተት የለም ብሏል።
ዩኒቨርሲቲው ውንጀላውን የፕሮፌሰሩን ስም ለማጠልሸት ሆን ተብሎ የተደረገ ነው ሲል ገልጾታል።
በተጨማሪም በርካታ ምሁራንና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ለፕሮፌሰሩ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
ክሱ በጥቁር ምሁራን ስኬት ላይ ያተኮረ ፖለቲካዊና ርዕዮተ ዓለማዊ ጫና እንደሆነ ተናግረዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #england #cambridgeuniversity #professor

8 days ago
የቀብር አስፈጻሚው የፈፀመው አስደንጋጭ ወንጀል
*35 አስክሬኖች ሳይቀበሩ በተቋሙ ህንፃ ውስጥ ተከማችተው ተኝተዋል።
#ethiopia | የቀብር አስፈጻሚ ድርጅት ባለቤት የሆኑት የ48 ዓመቱ ሮበርት ቡሽ የሟቾችን አስክሬን ክብር ባለው መልኩ ባለማሳረፍ እና ሌሎች 68 ወንጀሎች በመፈፀም ጥፋተኛ ተብለዋል።
ግለሰቡ የተሳሳተ የሟች አመድ ለቤተሰቦች በመስጠት ማታለል በመፈጸምና ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገንዘብ በመቀበል ወንጀል ጥፋተኛ መሆናቸውን አምነዋል ሲል ፍ/ቤት ገልጿል።
ድርጊቱ ለዓመታት የተፈጸመ ሲሆን ግለሰቡ ለገንዘብ ጥቅም ሲል በከፍተኛ ሀዘን ላይ የነበሩ ቤተሰቦችን እምነት አላግባብ በመጠቀም የማይጠገን በደል ፈጽሟል ሲል ፖሊስ ገልጿል።
35 አስክሬኖች ሳይቀበሩ በተቋሙ ህንፃ ውስጥ ተከማችተው ተኝተዋል።
ለበርካታ ዓመታት የሟች ቤተሰቦች የተቃጠለው አስክሬን አመድ ነው ተብሎ የተሰጣቸው አመድ የሌላ ሰው እንደነበር ወይም ተደባልቆ የተሰጠ እንደነበር ተደርሶበታል።
ግለሰቡ የፈፀመውን ነገር የሰሙ የሟች ቤተሰቦች እንደተናገሩት የአባታችንን የቀብር ሥነ ሥርዓት ፈጽመን አመዱን ተቀብለናል ብለን በምናስብበት ወቅት አስክሬኑ አሁንም በተቋሙ ህንፃ ውስጥ ይገኛል መባላችን በቃላት ልንገልጸው የማንችለው ድንጋጤ ፈጥሮብናል ብለዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #england #funeraldirector #police #court

17 days ago
በዓለም ዋንጫ የደረጃ ጨዋታ እንግሊዝ ፈረንሳይን አሸነፈች
**********************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ 3ኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ በግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚዎቹ ሀገራት መካከል የተካሄደው የደረጃ ጨዋታ፤ በእንግሊዝ 6 ለ 4 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
አስር ግቦች በተቆጠሩበት ጨዋታ፤ ለእንግሊዝ ዲክላን ራይስ፣ ኤዝሪ ኮንሳህ፣ ጁድ ቤሊንግሃም እንዲሁም ቡካዮ ሳካ(ሦስት) አስቆጥረዋል።
የፈረንሳይን ግቦች ደግሞ ኪሊያን ምባፔ(ሁለት)፣ ብራድሊ ባርኮላ እና ኡስማን ዴምቤሌ ከመረብ አሳርፈዋል።
በዚህም 3ኛ ደረጃን ያገኘችው እንግሊዝ የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።
በጨዋታው ሁለት ግቦችን ያስቆጠረው ኪሊያን ምባፔ ደግሞ፤ በምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት 22ኛውን በዚህ ዓለም ዋንጫ ደግሞ 10ኛውን በማስመዝገብ የወርቅ ጫማ ሽልማት ፉክክሩን ከሊዮኔል ሜሲ በመላቅ አስቀድሞ መምራት ጀምሯል።
ማይክል ኦሊሴ በዓለም ዋንጫ ሰባት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል በፔሌ ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን አሻሽሏል።
#worldcup #fifaworldcup #fifaworldcup2026 #3rdplaceplayoff #england #france #football #sports

ከስንብት ሐዘን ማግስት የሚደረግ የክብር ፍልሚያ
*******************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ዋዜማ ላይ ቆመናል። ዓለም ዋንጫ በግማሽ ፍፃሜ በለስ ያልቀናቸውን፣ ድል ከነርሱ ጋር ያልነበረውን እንዲሁ አያሰናብትም። ለሦስተኝነት ማዕረግ ዳግም ያፋልማል።
23ኛው ዓለም ዋንጫ ፍሎሪዳ ላይ የግማሽ ፍፃሜ ተሸናፊዎቹን ዛሬ እኩለ ሌሊት 6 ሰዓት ፍሎሪዳ ሚያሚ ላይ ያፎካክራል። በእርግጥ በብዙዎች፣ በተለይም በተሸናፊ ብሔራዊ ቡድኖች ዘንድ የደረጃው ጨዋታ ለመጫወት የተመረጠ አይደለም።
የዛሬው መርኃ ግብር ግን ብሔራዊ ቡድኖቹ ከሚያደርጉት ፉክክር ባልተናነሰ፣ በኮከብ ግብ አስቆጣሪነት በመላቅ የወርቅ ኳስ ሽልማቱን ለማግኘት ባለው ፉክክር ለውጥ እንደሚያስከትል ይጠበቃል። ከሊዮኔል ሜሲ ጋር የኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ፉክክሩን በ8 ግቦች እየመራ የሚገኘው ኪሊያን ምባፔ እንዲሁም እያንዳንዳቸው ስድስት ግቦች ያስቆጠሩት ጁድ ቤሊንግሃም እና ሀሪኬን ከባለ አምስት ግቡ የዓለም ኮከብ ኡስማን ዴምቤሌ ጋር በሚያደርጉት የኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ፉክክር ላይ አንዳች ለውጥ ሊያስከትል የሚችል ጨዋታ እንደሚሆን ታምኗል።
በዚህ መሀል ግን ከሽንፈት ማግስት የሚደረግ፤ ከዓለም ዋንጫ ስንብት ሀዘንም ሳያገግሙ የሚመጣ መርኃ ግብር መሆኑ የተጫዋቾችን ተነሳሽነት መቀነሱ፣ የተመልካቾችን ጉጉትም ማሳነሱ አይቀርም። ቶማስ ቱሄል ይህን የሚያስረግጥ ሃሳብ ነው የሰነዘሩት። "የእኛም ሆነ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ይህን ጨዋታ የማድረግ ፍላጎት የላቸውም" በማለት በውድድሩ ሙሉ የለፉትና የተዘጋጁት ለዓለም ሻምፒዮንነት በመሆኑና፤ ያም ባለመሳካቱ ለዚህ ጨዋታ የሚኖራቸውን ጉጉትና ፍላጎት እንደቀነሰው ተናግረዋል።
ቱሄል ይህንን ቢሉም የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዲዲየር ዴሻው ግን ከዚህ በአንፃራዊነት የተለየ ሃሳብ ነው የሰነዘሩት። 3ኛ ደረጃም ቢሆን የተሻለ መሆኑን በማንሳት፤ እርሱን ለማሳካት የቻሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። አክለውም የተፈጠረው ሀዘን የዓለም ሻምፒዮን ከመሆን ፅኑ መሻት የመጣ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሆነውን ከመቀበል ውጪ አማራጭ የለንም ብለዋል።
በግማሽ ፍፃሜው እንግሊዝ እየመራች የነበረችውን ጨዋታ የኋላ ኋላ በአርጀንቲና 2 ለ 1 ተሸንፋ የፍፃሜ መንገዷ ሲቋረጥ፤ በአንፃሩ ፈረንሳይ ባልተጠበቀ ሁኔታ በስፔን ፍፁም ብልጫ ተወስዶባት 2 ለ 0 ተረታ ነው ከፍፃሜው የቀረችው።
የ23ኛው ዓለም ዋንጫ 103ኛው ጨዋታ በሁለት ሃሳቦች መሀል፤ የጨዋታውን አስፈላጊነት ተጠይቅ ውስጥ በሚከቱና የኮከብ ግብ አግቢነት ፉክክሩ ላይ የሚኖረውን ሚና በሚያጎሉ መሀል ሆኖ፤ እኩለ ሌሊት 6፡00 ሰዓት በሚያሚ ጋርደን ሀርድ ሮክ ስታዲየም ይካሄዳል።
በእድሪስ አህመድ

Sponsored by
Surafel
19 days ago
እንግሊዝ በዓለም ዋንጫ፤ ለ60 ዓመታት ያልተፈታው ህልም፣ ያልተመለሰው ጥያቄ!
**************************
እንግሊዝ የዓለም ዋንጫን ዳግም ሳታነሳ ተጨማሪ 4 ዓመታት እንደሚቆጠሩ እርግጥ ከሆነ 24 ሰዓታት አለፉ። አትላንታ ላይ “ሦስቱ አናብስት” የዓለም ሻምፒዮን የመሆን ውጥን ይዘው፣ እስከ ግማሽ ፍፃሜም ተጉዘው የጀመሩት መንገድ በሊዮኔል ሜሲ አርጀንቲና ተቋርጧል። ለተጨማሪ ዓመታት እንዲወጡት የሚያስፈልግ ሌላ ዳገት፣ ሊወርዱትም የሚገባ ሌላ ቁልቁለት ‘ተበጅቶላቸዋል’።
እነዛ 60 ዓመታት በዓለም እግር ኳስ የራሷን አሻራ ላኖረችው ሀገር ብዙ መውጣትና መውረዶች፣ በርካታ ተስፋ አስቆራጭ ደግሞም ተስፋ መልሶ የለመለመባቸው ወቅቶች አልፎባቸዋል። ዓለም ዋንጫ ግን ያዝኩት ሲሉ እያመለጠ፣ ደረስኩበት ሲሉ እየራቀ “ጉም የመዝገን” ያክል ሆኖባቸዋል።
ሐምሌ 30/ 1966 እ.አ.አ ሰር ቦቢ ሙር የእንግሊዝን የመድረኩ ብቸኛ ድል፣ የቀደመውን የጁሊየስ ሪሜትስ ዋንጫ ካነሳ በኋላ ብዙ ነገሮች ባሉበት የሉም ተቀያይረዋል። እግር ኳስም፣ ራሷ እንግሊዝም ሆነ ዓለም ትላንትን አይመስሉም።
እንግሊዝ ምዕራብ ጀርመንን 4 ለ 2 አሸንፋ የመጀመሪያ ዓለም ዋንጫዋን ካነሳች በኋላ፤ 454 ተጫዋቾች ነጩን የብሔራዊ ቡድን መለያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለብሰዋል። ቀዳሚው በ1967 የተጫወተው 847ኛው ተጫዋች ጆን ሆሊንስ ሲሆን፤ የብሔራዊ ቡድኑን መለያ በመልበስ ደግሞ የመጨረሻ የሆነው 1300ኛው የሊቨርፑሉ ሪዮ ንጉምሃ ነው። በዓለም ዋንጫው ደግሞ ከውጤታማው የአልፍ ራምሴይ ቡድን ጀምሮ እሰከ አሁኑ ቶማስ ቱሄል ድረስ 161 ተጫዋቾች እንግሊዝን ወክለዋል።
በስድሰቱ አስርታት ዋንጫ አልባ ዓመታት 15 አሰልጣኞች በቋሚነት ብሔራዊ ቡድኑን መርተዋል። ሮን ግሪንዉድ፣ ሰቨን ጎራን ኤሪክሰን፣ ፋቢዮ ካፔሎ እና ጋሬት ሳውዝጌት ተጠቃሾች ናቸው። ሁሉም ግን የአልፍ ራምሴይን ውጤታማ መንገድ ማስቀጠል አልሆነላቸውም።
አለን ሺረር፣ ዴቪድ ቤካም፣ ስቴቨን ጄራርድ እና ሃሪ ኬን ባለፉት 60 ዓመታት በተካሄዱት ዓለም ዋንጫዎች ቡድኑን በአምበልነት ከመሩ ተጫዋቾች የሚጠቀሱ ናቸው።
እንግሊዝ ከ1966 ሻምፒዮንነቷ በኋላ ከተካሄዱት 15 የዓለም ዋንጫዎች በ12ቱ ተሳትፋለች። በሁሉም ግን ደርሶ የመመለስ፣ አግኝቶም የማጣት ምሳሌ ተደርጋ ቀጥላለች። በ1986 የዲዬጎ ማራዶና በ4 ደቂቃ ልዩነት ያሳየው “የእጅም የእግርም” ትርዒት፣ በ1990 ግማሽ ፍጻሜ የፖል ጋስኮኝ እንባ፣ በ1998 ዓለም ዋንጫ የዴቪድ ቤካም ቀይ ካርድ፣ በ2002 ዓለም ዋንጫ የሮናልዲንሆ ጎቾ ዝነኛ የቅጣት ምት “ወርቃማ ግብ”፣ በ2010 መስመሯን አልፋ የተሻረችው የፍራንክ ላምፓርድ ግብ፣ በ2022 ዓለም ዋንጫ ሀሪ ኬን ያባከናት የፍፁም ቅጣት ምት፣ በመጨረሻም 2026 ላይ በአትላንታ ምድር እየመሩ የነበረውን ጨዋታ የኋላ ኋላ ማጣት፤ እንግሊዞች በቁጭት የሚያስታውሷቸው አጋጣሚዎች ናቸው።
ከዚያ በኋላ የበርሊን ግንብ ፈርሷል፣ የሰው ልጅ ወደ ጨረቃ መጥቋል፣ ዓለም በበይነ መረብ ተሳስሯል፣ የስማርት ስልክ ዘመን የሰው ልጅን የዕለት ተዕለት ህይወት ፈጣን አድርጓል። እነዚህና መሰል ለውጦች በሰው ልጅ የምድር ቆይታ ቢስተናገዱም፤ የእንግሊዝ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮንነት ህልም 1966 ላይ እንደቆመ አለ።
እንግሊዝ ባስተናገደችው የ1996ቱ አውሮፓ ዋንጫ ወቅት የተዜመው “…30 የህመም ዓመታት” የሚል ሀረግ የያዘውና የ1966ቱን ዓለም ዋንጫ በማስታወስ እግር ኳስ ወደ ቤቱ እየተመለሰ እንደሆነ የሚያትተው ኅብረ ዝማሬ፣ ዛሬም አውዱን የሳተ አይመስልም። 30ዎቹ ዓመታት ሌላ 30 ዓመታትን አዋልደዋል፤ እግር ኳስም ወደ “ቤቱ” አልተመለሰም።
የብሔራዊ ቡድኑን መለያ ከለበሱት 454 ተጫዋቾች፣ በዓለም ዋንጫው ከተጫወቱት 161 እግር ኳሰኞች፣ በ15ቱ አሰልጣኞች ስር ካለፉ 7 አምበሎች የምድር ትልቁን የእግር ኳስ ሽልማት ከፍ አድርጎ ማንሳት የቻለው ቦቢ ሙር ብቻ ነው።
ትውልድ ይተካል፣ ተስፋም እየደበዘዘም ቢሆን መልሶ ይለመልማል። እንግሊዛውያንም እግር ኳሳቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በሊግ ውድድሮች በቅርቦቹ ዓመታት እንዳሳደረው ተፅእኖ፤ ብሔራዊ ቡድናቸውም ይህን የዘመናት ህልሙን እውን የሚያደርግበትን ቀን በተስፋ ይጠባበቃሉ።
የ2026ቱ የአሜሪካ ምድር መንገድ ግን ጫፍ ደርሶ ተቋርጧል። ጁድ ቤሊንግሃም “ልብ ሰባሪ ፍፃሜን ያስከተለ ውብ ጉዞ” ሲል የገለፀው የ2026 ዓለም ዋንጫ ቆይታ አብቅቷል።
በእድሪስ አህመድ
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup1966 #england #threelions #judebellingham #harrykane #semifinal #football #sports #ebc

20 days ago
አርጀንቲና ወደ ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ አለፈች
***************
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ በአትላንታ ስታዲየም በእንግሊዝና አርጀንቲና መካከል የተካሄደው ተጠባቂ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በአርጀንቲና 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ለአርጀንቲና የአሸናፊነት ግቦቹን በ85ኛው ደቂቃ ኤንዞ ፈርናንዴዝ እንዲሁም በጭማሪ ሰዓት (90+3) ላውታሮ ማርቲኔዝ ከመረብ አሳርፈዋል። ለእንግሊዝ ብቸኛዋን ግብ በ55ኛው ደቂቃ አንቶኒ ጎርደን አስቆጥሯል።
የወቅቱ የዓለም ሻምፒዮን አርጀንቲና ለዋንጫው ክብሯን ለማስጠበቅ የፊታችን እሁድ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ታላቅ የፍፃሜ ጨዋታዋን ታደርጋለች።
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ተሸናፊዎቹ ፈረንሳይና እንግሊዝ ደግሞ የፊታችን ቅዳሜ ሌሊት 3ኛ ደረጃ ይዞ ለማጠናቀቅ የሚጫወቱ ይሆናል።
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup #england #argentina #semifinal #football #sports

99'- 🏴 England 1-2 Argentina 🇦🇷
አርጀንቲና በአለቀ ሰዓት እንግሊዝን 2 ለ 1 በመርታት ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ አለፈች
#አትላንታ — በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ለረጅም ዘመናት ከሚታወሱት እጅግ አስገራሚና አስደናቂ ጨዋታዎች መካከል አንዱ በዛሬው ዕለት በአትላንታ ስታዲየም ተመዝግቧል።
የዓለም ሻምፒዮን አርጀንቲና እስከ ጨዋታው ማጠናቀቂያ 85ኛው ደቂቃ ድረስ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ስትመራ ብትቆይም፣ በአስደናቂ ብቃትና መነሳሳት ባስቆጠረቻቸው ሁለት ፈጣን ግቦች እንግሊዝን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ መድረሷን አረጋግጣለች።
በዚህም መሠረት አርጀንቲና በተከታታይ ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ማለፍ የቻለች ሲሆን፣ ዋንጫውን በድጋሚ ለማንሳትና የበላይነቷን ለማስጠበቅ በታላቁ የፍፃሜ ፍልሚያ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር የምትገናኝ ይሆናል።
ጨዋታው ከመጀመሪያው አጋማሽ ጀምሮ እጅግ ማራኪና ታክቲካዊ ጥንቃቄ የበዛበት የነበረ ቢሆንም፣ በሁለተኛው አጋማሽ የእንግሊዙ ተቀይሮ የገባ ኮከብ አንቶኒ ጎርደን ባስቆጠራት አስደናቂ ግብ 1 ለ 0 መምራት ችለው ነበር።
እንግሊዝ እስከ 85ኛው ደቂቃ ድረስ ውጤቱን አስጠብቃ በመጓዝ ወደ ፍፃሜው ለመድረስ እጅግ ተቃርባ የነበረ ቢሆንም፣ የአርጀንቲናውያን የአሸናፊነት ሥነ-ልቦና ጨዋታውን በአጭር ደቂቃዎች ውስጥ ገልብጦታል።
የቼልሲው አማካይ ኢንዞ ፈርናንዴዝ የአርጀንቲናን ተስፋ ያለመለመችውን ወሳኝ ግብ ከመረብ አሳርፏል። ለዚህች ግብ መገኘት ደግሞ ታላቁ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ድንቅ የሆነ የኳስ አመቻችቶ ማቀበል (Assist) ሥራ ሰርቷል።
የአሸናፊነቷ ግብ (90+')፦ ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰዓት ያመራል ተብሎ በሚጠበቅበት በአለቀ ሰዓት፣ ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው የኢንተር ሚላኑ አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ እንግሊዝን ሙሉ በሙሉ ያስደነገጠችውንና ለአርጀንቲና የፍፃሜ ትኬት የቆረጠችውን ድንቅ የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል።
ይህን አስገራሚና ድራማዊ ጨዋታ ተከትሎ ታዋቂ የዓለም አቀፍ ስፖርት ሚዲያዎች ዘገባዎቻቸውን አውጥተዋል፦
"አርጀንቲናዎች ፈፅሞ እጅ እንደማይሰጡ በድጋሚ አሳይተዋል። ሜሲና የቡድን አጋሮቹ በመጨረሻዎቹ አምስት ደቂቃዎች የፈጠሩት ተአምር የዓለም ዋንጫን ታላቅነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው፤ እንግሊዝ በሰራችው ጥቂት መዘናጋት ዋጋ ከፍላለች።"
— ESPN
"ሊዮኔል ሜሲ ግብ ባያስቆጥርም ጨዋታውን የመቆጣጠርና የመምራት ብቃቱ አሁንም ወደር የለሽ መሆኑን አስመስክሯል። ለኢንዞ ፈርናንዴዝ ያቀበላት ኳስ የአርጀንቲናን የሞተ ተስፋ ቀስቅሳለች። አርጀንቲና አሁን አይኗን በተከታታይ የዓለም ዋንጫ ክብር ላይ ጥላለች።"
- BBC Sport
"የእንግሊዝ የልብ ስብራት! አንቶኒ ጎርደን በእንግሊዝ ደጋፊዎች ዘንድ ጀግና ለመሆን ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ቀርተውት ነበር። ነገር ግን ላውታሮ ማርቲኔዝ በአስገራሚ አጨራረስ የእንግሊዝን ህልም አክስሟል።"
— Sky Sports*
በአትላንታው ስታዲየም የታየው ይህ አስደናቂ ፍልሚያ ለአርጀንቲና ደጋፊዎች ታላቅ ደስታን ሲያበረክት፣ ለእንግሊዞች ግን እጅግ ልብ ሰባሪ ሽንፈት ሆኖ አልፏል።
አርጀንቲና ዋንጫውን በተከታታይ ለማንሳት ከስፔን ጋር የምታደርገው የፍፃሜ ጨዋታ ሌላው በጉጉት የሚጠበቅ ታላቅ መድረክ ይሆናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

እንግሊዝ 0 - 0 አርጀንቲና :- የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤት
**************
በአትላንታ ስታዲየም በእንግሊዝ እና አርጀንቲና መካከል እየተካሄደ የሚገኘው እጅግ ተጠባቂ የዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup #england #argentina #semifinal #football #sports
**************
በአትላንታ ስታዲየም በእንግሊዝ እና አርጀንቲና መካከል እየተካሄደ የሚገኘው እጅግ ተጠባቂ የዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።
#worldcup #fifaworldcup2026 #fifaworldcup #england #argentina #semifinal #football #sports
Sponsored by
Surafel
24 days ago
እንግሊዝ በቤሊንግሃም አስደናቂ ብቃት ለግማሽ ፍጻሜ አለፈች
#ethiopia |የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች በከፍተኛ ትንቅንቅ እየቀጠሉ ይገኛሉ። ዛሬ በተደረገው እጅግ አስደናቂ ጨዋታ እንግሊዝ ኖርዌይን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜው መሸጋገሯን አረጋግጣለች።
የጨዋታው Highlights
የኖርዌይ መሪነት፡ የውድድሩ አስደናቂ ክስተት በመሆን የቀጠለችው ኖርዌይ በሽልድረፕ ግብ መሪነትን ይዛ የነበረ ቢሆንም፣ የሶስት አንበሶቹን አስፈሪ ጥቃት መቋቋም አልቻለችም። በዚህም የኖርዌይ አስደናቂ ጉዞ በሩብ ፍጻሜው ተገቷል።
የቤሊንግሃም ድምቀት፡ 120 ደቂቃ በወሰደው በዚህ አስደናቂ ፍልሚያ የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ጁድ ቤሊንግሃም ሁለቱንም የእንግሊዝን ግቦች በማስቆጠር የቡድኑ ባለውለታ ሆኗል።
ለኮከብ ግብ አስቆጣሪነት የሚደረግ ፉክክር
ቤሊንግሃም በመድረኩ በተከታታይ ሁለት ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፣ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ላይ ያስቆጠረውን አጠቃላይ የግብ ብዛት 6 አድርሷል። ይህም ለውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብር (ወርቃማው ጫማ) በግንባር ቀደምትነት እንዲፎካከር አድርጎታል።
ቀጣይ ተጋጣሚ ማነው?
ወደ ግማሽ ፍጻሜው ያለፈችው እንግሊዝ፣ ቀጣይ ተጋጣሚዋን ለማወቅ ከአርጀንቲና እና ስዊዘርላንድ ጨዋታ አሸናፊ የሚወጣውን ቡድን የምትጠብቅ ይሆናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#worldcup2026 #judebellingham #england #norway #footballnews #getutemesgen

እንግሊዝ ለግማሽ ፍፃሜው ደረሰች
*******************
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ እንግሊዝ ኖርዌይን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለግማሽ ፍፃሜው ደርሳለች።
ከሌሊቱ 6 ሰዓት የተጀመረው የሁለቱ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ በደበኛው ሰዓት (በ90 ደቂቃ) 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ነው የተጠናቀቀው።
አንድሪያስ ሼልድረፕ ኖርዌይን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ በ36ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር ጁድ ቤሊንግሃም እንግሊዝን 45+2 ደቂቃ ላይ አቻ አድርጓል።
መደበኛ ሰዓቱ በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ 30 ደቂቃ ያመሩ ሲሆን ጁድ ቤሊንግሃም እንግሊዝን አሸናፊ ያደረገችውን ግብ 93ኛ ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
በዓለም ዋንጫው ለሀገሩ የመጀመሪያ ተሳትፎ እያደረገ ያለው ጁድ ቤሊንግሃም እስካሁን ባደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን ሲያስቆጥር አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
#ebc #ebcsport #worldcup #worldcup2026 #england

1 month ago
እንግሊዝ ዲሞክራቲክ ኮንጎን 2 ለ 1 በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቀለች
**************************
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ እንግሊዝ ዲሞክራቲክ ኮንጎን 2 ለ 1 በመርታት ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ ተሸጋግራለች።
እንግሊዝን ለድል ያበቋትን ሁለት ግቦች ሃሪ ኬን በ75ኛው እና በ86ኛው ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥር፤ ለዲሞክራቲክ ኮንጎ ብሪያን ሲፔንጋ በ7ኛው ደቂቃ ላይ ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።
እንግሊዝ በቀጣይ ዙር ጨዋታዋ ከሜክሲኮ ጋር የምትገናኝ ይሆናል።
#worldcup #england #drcongo #sports #ebc #fifa2026

እንግሊዝ እና ጋና ያለ ግብ ተለያዩ
#ethiopia | በ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ 12 ሁለተኛ ጨዋታ፣ እንግሊዝ እና ጋና በቦስተን ስታዲየም ያደረጉት ፉክክር 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን በድል የጀመሩት ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በዚህ ጨዋታ ነጥብ በመጋራት ወደ 4 ነጥብ ከፍ ብለዋል።
እንግሊዝ በተለይም በጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ተደጋጋሚ የግብ ሙከራዎችን ብታደርግም፣ የጋናን ጠንካራ መከላከል እና የግብ ጠባቂውን ጥሩ ብቃት ተሻግራ ግብ ማስቆጠር አልቻለችም።
በዚህ ውጤት እንግሊዝ በ4 ነጥብ የምድቡን መሪነት ስትይዝ፣ በካርሎስ ኪሮሽ የምትመራው ጋናም በተመሳሳይ 4 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።
የሁለቱም ቡድኖች ወደ ጥሎ ማለፍ ለማድረስ ያላቸው ዕድል አሁንም ጠንካራ ሲሆን፣ የመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ውጤት የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ እንደሚወስን ይጠበቃል።
#worldcup2026 #england #ghana #threelions #blackstars #football #fifaworldcup

6 months ago
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ባለሙያዎችን ወደ ውሳኔ ሰጪነት አመጣ፦ የፖሊሲ ነፃነት ወይስ የሉዓላዊነት ስጋት?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአዲሱ አዋጁ መሠረት፣ በገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው (MPC) ውስጥ ሁለት ታዋቂ የውጭ ሀገር የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎችን መሾሙን አስታውቋል። ይህ እርምጃ በኢትዮጵያ የባንክ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ለውጥ ተደርጎ ተወስዷል።
ሳይንሳዊ ውሳኔ፦ የፖሊሲ ውሳኔዎች ከፖለቲካ ተጽዕኖ ነፃ ሆነው በማስረጃ እና በሳይንሳዊ ትንተና ላይ እንዲመሰረቱ ያደርጋል።
ዓለም አቀፍ ተቀባይነት፦ እንደ እንግሊዝ ማዕከላዊ ባንክ (Bank of England) ያሉ ተቋማት ልምድን በመቀመር፣ ለዓለም አቀፍ አበዳሪዎችና ባለሀብቶች ባንኩ ነፃ መሆኑን ያሳያል።
የሃሳብ ብዝሃነት፦ በውሳኔ አሰጣጥ ወቅት አንድ አይነት አስተሳሰብን (Groupthink) በመቀነስ፣ አማራጭ የኢኮኖሚ መፍትሄዎችን ያመነጫል።
እነዚህ ባለሙያዎች የሚቀላቀሉት የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ (MPC)፣ በሀገሪቱ ያለውን የወለድ መጠን የመወሰን፣ የገንዘብ ስርጭትን የመቆጣጠር እና የዋጋ ግሽበትን የማረጋጋት ከፍተኛ ስልጣን ያለው አካል ነው።
ይህም ባንኩ ከመንግስት ካዝና ጠባቂነት ወጥቶ፣ ገለልተኛ የኢኮኖሚ ተዋናይ እንዲሆን ለጀመረው ማሻሻያ ትልቅ እገዛ ያደርጋል።
⚖️አዎንታዊ ጎኑ፦
ባንኩ "የማኔጂመንት ጥራት" (Institutional Quality) እንዲኖረውና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ገበያ አመኔታ እንዲያገኝ ያደርጋል። ይህም የውጭ ኢንቨስትመንት እንዲሳብ በር ይከፍታል።
ሊታሰቡ የሚገቡ ስጋቶች፦
የሀገር በቀል እውቀት ክፍተት፦ የውጭ ባለሙያዎቹ የኢትዮጵያን ተጨባጭ መዋቅራዊ ችግሮች (ለምሳሌ የጥቁር ገበያ ባህሪ እና የማህበረሰቡን የፍጆታ ዘይቤ) በውል ካልተረዱ፣ የሚያመጧቸው መፍትሄዎች "ንድፈ-ሃሳባዊ" ብቻ ሊሆኑ ይችላሉ።
የሉዓላዊነት ጥያቄ፦ የሀገሪቱን ቁልፍ የኢኮኖሚ ውሳኔዎች ለውጭ ዜጎች አሳልፎ መስጠት፣ በፖለቲካዊ ረገድ "የውጭ ተጽዕኖ" የሚል ትችት ሊያስነሳ ይችላል።
🎯 ዋና ዓላማው፦ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር እና አገሪቱ የጀመረችውን ሰፊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በስኬት ማጠናቀቅ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያው ዘመናዊ የነዳጅ እና የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማደያ ተመረቀ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ አየር ማረፊያ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በቡልቡላ መንገድ ያስገነባውና በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ ቀዳሚ የሆነው ዘመናዊ የነዳጅ ማደያ እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ማዕከል በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
🌍 ዓለም አቀፍ ተሞክሮና የቤተክርስቲያን ልማት
ይህ ዓይነቱ የቤተክርስቲያን የልማት ተሳትፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለመደና ውጤታማነቱ የተመሰከረለት ነው። ለምሳሌ፦
በእንግሊዝ (Church of England): በርካታ አብያተ ክርስቲያናት በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያ (EV Chargers) በግቢያቸው ውስጥ በመትከል ለአካባቢ ጥበቃና ለገቢ ማስገኛነት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።
በቫቲካን (Vatican City): ቫቲካን ሙሉ በሙሉ በታዳሽ ኃይል ለመጠቀም በምታደርገው ጥረት፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችንና የኃይል መሙያ ማዕከላትን በስፋት በማስገንባት ግንባር ቀደም ሆናለች።
በግሪክና ሩሲያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት: አብያተ ክርስቲያናቱ ሰፋፊ መሬቶቻቸውን ለነዳጅ ማደያ፣ ለገበያ ማዕከላትና ለኢንዱስትሪዎች በማዋል ራሳቸውን ለመቻል የሚጠቀሙበት ዋነኛ መንገድ ነው።
የፕሮጀክቱ ይዘት
ዘመናዊ የነዳጅ አገልግሎት: ቤንዚንና ናፍጣ።
የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ: ለዘመናዊ መኪኖች ተመራጭ አገልግሎት።
ገቢ ማመንጫ: ለደብሩ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች ቋሚ የገቢ ምንጭ።
👥 የምርቃቱ ታዳሚዎች
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ እና ሌሎች ከፍተኛ የቤተክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል።
"ቤተክርስቲያናችን በመንፈሳዊው አገልግሎት ጎን ለጎን በልማት ሥራዎች ራሷን መቻልና ለሀገር ኢኮኖሚ የበኩሏን ድርሻ መወጣት እንዳለባት ማሳያ ነው" — ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
ምንጭ፦ EOTC TV / የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

10 months ago
አንድ ታላቅ ሰው ወደቀ !
ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ጥር 1 ቀን 1963 ዓም አዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ። አባታቸው አቶ ታደሰ ሮበሌ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ ወ/ሮ (አሁን እማሆይ) እማሙ ገቢ ይባላሉ።
የመጀመሪያና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሃዋሳ ታቦር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በሃዋሳ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያጠናቀቁ ከመሆናቸውም በላይ በ1980 ዓም የተሰጠውን ሃገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ወይንም ESCLC እጅግ ከፍ ያለ ነጥብ በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ With Great Distinction ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።
መንግስት በወቅቱ በሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎችን በሚመድብበት የጎንደር ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተመድበው በ1981 የ Common Course ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ፋኩልቲ ካጠናቀቁ በኋላ ከ1982 ዓም ጀምሮ እስከ 1987 ድረስ ለስድስት ዓመታት የህክምና ትምህርታቸውን ተከታትለው በማዕረግ ወይም በ Distinction በሐኪምነት ለመመረቅ በቅተዋል።
ወደ ስራው አለም በመሰማራትም ከ1987 ዓም እስከ 1988 ዓም ድረስ በተመደቡበት የሆሳዕና ሆስፒታል በጠቅላላ ሐኪምነት፣ ከ1988 ዓም ጀምሮ ደግሞ ወደተማሩበት እና ወደተመረቁበት የጎንደር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዝውውር በማድረግ በቀዶ ጥገና ክፍል ረዳት መምህርነት እና ጠቅላላ ሐኪም በመሆን ለሶስት አመታት ወገኖቻቸውን አገልግለዋል።
ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር በሚገኘው የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰጠውን የሶስት ዓመታት የድህረ ምረቃ ትምህርት በመከታተል የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ሐኪም ሆነው ከመመረቃቸውም በላይ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግም አግኝተዋል። በመቀጠልም ህንድ ሃገር በሚገኘው ቬሎር ክርስቲያን ሜዲካል ኮሌጅ ውስጥ የፌሎውሺፕ ትምህርታቸውን ተከታትለው በ1999 ዓም የህፃናት ቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሻሊስት በመሆን ተመርቀዋል።
ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ከዚህ ሁሉ ትምህርት ጎን ለጎን በህክምናው ዘርፍም ከተመረቁበት ጊዜ አንስቶ እስከ 1988 ዓም ድረስ የሆሳዕና ከተማ እና የአካባቢውን ማህበረሰብ፣ ከዚያም እስከ ህዳር 2002 ዓም ድረስ ደግሞ የጎንደር ከተማና የአካባቢውን ማህበረሰብ፣ ከ2002 ዓም በኋላ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ ከመላው ኢትዮጵያ የሚመጡ ህሙማንን በተለይም ደግሞ ህፃናት ታካሚዎችን ከፈጣሪያቸው በተሰጣቸው ጥበብና ፀጋ አማካይነት ቀዶ ጥገና በማከናወን እንዲፈወሱ የሚያደርጉ ደከመኝን የማያውቁ ታታሪ የህክምና ባለሙያና ምሁር ነበሩ።
በሌላ በኩል ደግሞ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለማስተማር የሚያስችላቸውን የከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም Higher Diploma Program ተከታትለው ያጠናቀቁ ከመሆናቸውም በላይ በ2011 ዓም ደግሞ በጤና ባለሙያዎች ትምህርት Health Professional Education ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞም የቀዶ ጥገና ተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግም አግኝተዋል።
ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ በርካታ ስልጠናዎችንና የአጭር ጊዜ ኮርሶችን የወሰዱ ሲሆን ከነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ ከዚህ የሚከተሉት ናቸው።
እንግሊዝ ሃገር በሚገኘው Paediatric Surgery at Leicester Royal Infirmary,
እስራኤል ሃገር በሚገኘው University of Negev, Beersheba Soroka Medical Center,
ሲያትል አሜሪካ በሚገኘው University of Washington Institute of Simulation and Interpersonal Skills, Royal College of Surgeons of England and David Nutt Foundation በጋራ ባዘጋጁት Surgery in Austere Environment Course in Manchester University,
እንግሊዝ ሃገር በሚገኘው Global Surgery Course at University of Oxford ይጠቀሳሉ።
ፕሮፌሰር አመዘነ በሰሩባቸው ተቋማት ውስጥ ህክምና ከመስጠት ጎን ለጎን በተለያዩ ደረጃዎች ሃገራቸውን ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ከነዚህም ውስጥ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቀዶ ጥገና ክፍል ሃላፊ፣ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የህፃናት ቀዶ ጥገና ክፍል ሃላፊ፣ የSurgical Skills Lab ተባባሪ ዳይሬክተር፣ የSimulation Center of College of Social Sciences ተባባሪ ሊቀመንበር፣ በድህረ ምረቃ ትምህርት ክፍል የድህረ ምረቃ ኮሚቴ ሊቀመንበር፣ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ምክትል ፕሬዘዳንት፣ የምስራቅ፣ መካከለኛው እና ደቡባዊ አፍሪካ የህፃናት ቀዶ ጥገና ፕሮግራም Panel Head፣ እንዲሁም የአሜሪካ የቀዶ ህክምና ኮሌጅ አባል ነበሩ።
በአካዳሚክ ዘርፉም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ፣ በጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ እና በሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ External Examiner የነበሩ ሲሆን የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል በመሆን አገልግሎት እየሰጡ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ሞምባሳ ኬንያ፣ ማፑቶ ሞዛምቢክ፣ ኪጋሊ ሩዋንዳ እንዲሁም ካምፓላ ዩጋንዳ ለሚገኙ የህክምና Examiners በተለያዩ ጊዜያት ስልጠና ሲሰጡ ቆይተዋል።
በምርምር ረገድም 34 አርቲክሎችን እና የመፅሃፍ ክፍሎችን አገር አቀፍ እና አለም አቀፍ እውቅና ባላቸውና በተገመገሙ ጆርናሎች ላይ ፅሁፎቻቸውን ከማሳተማቸውም በላይ ስድስት ፅሁፎቻቸው ለመታተም በሂደት ላይ ነበሩ። ከዚሁ ጋር ተያይዞም የተወሰኑ ፅሁፎቻቸውን በሃራሬ ዚምባቡዌ እንዲሁም በካልጋሪ ካናዳ ያቀረቡ ሲሆን የ Surgical Platform የኢትዮጵያ ተወካይ እና Health System Strengthening in Sub-Saharan Africa በሚለው የ ASSET project ውስጥ ተባባሪ ተመራማሪ ነበሩ።
ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ከዚህ በላይ ለተጠቀሱት ዋና ዋና እና ሌሎችም አገልግሎታቸው ከበርካታ ተቋማት ሽልማቶች የተበረከቱላቸው ሲሆን ከነዚህም መካከል
Award for Presenting Best Scientific Paper entitled ‘Implementing Ultrasound Guided Hydrostatic Reduction of Intussusception in a Low Resource Countries, Larry J. Anderson Award for Outstanding Public Health Science in the United States of America, Winner of International Guest Scholars by the American College of Surgeons, Chicago, USA ዋና ዋናዎቹ ናችው።
በአጠቃላይ በህፃናት ቀዶ ጥገና በሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በሃገራችን ከሚገኙት ሁለት የህክምና ምሁራን ውስጥ አንዱ ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ነበሩ።
በመጨረሻም ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ከትምህርታቸው እና ስራቸው ባሻገር ባለው ህይወታቸውም ከዶ/ር ራሔል ደምሰው ጋር ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በትዳር በመጣመር ደስተኛ ህይወት ይመሩ የነበረ ሲሆን ከዚሁ ትዳራቸውም ሁለት ወንዶች ልጆች እና አንዲት ሴት ልጅ በድምሩ ሶስት ልጆችን አፍርተዋል።
ከዚህ ሁሉ ልፋት በኋላ እኚህ የሚሊዮኖችን ህይወት ሲታደጉ የኖሩት የሃገር መድሐኒት ለራሳቸው የሚሆን መድሐኒት ሊያገኙ ባለመቻላቸው ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአሜሪካን ሃገር እና በኢትዮጵያ ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቢቆዩም የፈጣሪ ጥሪ ደርሷቸው በርካታ አገልግሎት ሊሰጡ በሚችሉበት ዕድሜ ላይ እያሉ ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓም ልክ ከረፋዱ 5 ሰዓት ከሩብ ላይ በተወለዱ በ54 ዓመት ዕድሜያቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የፕሮፌሰር አመዘን ታደሰ አስክሬን ሽኝት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፡ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተካሂዷል ፣ሥርዓተ ቀብራቸው አርብ ጥቅምት 7/2018 ዓ,ም በሀዋሳ ከተማ ይፈፀማል ።
ልዑል እግዜብሔር ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን፣ አሜን።

1 year ago
ከ 100 ዓመት በላይ እድሜ ያለውን ታዋቂ ዛፍ የቆረጡት ግለሰቦች በእስር ተቀጡ
#ethiopia | በእንግሊዝ ኒውካስል ከተማ አቅራቢያ ይገኝ የነበረውንና ከ100 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረውን ታሪካዊ ዛፍ በቆረጡ ሁለት ሰዎች ላይ የኒውካስል ከተማ ፍርድ ቤት የእስር ቅጣት አስተላልፏል።
ዳንኤል ግራሃም እና አዳም ካሩዘርስ የተባሉት እነዚህ ገለሰቦች ላይ ዛሬ ቅጣቱ የተላለፈው፤ በ2023 ላይ ከሚኖሩበት ከተማ ለአርባ ደቂቃ ያህል ተጉዘው ሲካሞር ጋፕ በመባል የሚታወቀውን ታሪካዊው ዛፍ በማሽን በመታገዝ በመቁረጣቸው ነው።
በወቅቱ አነጋጋሪ በነበረው በዚህ ድርጊት አንደኛው ዛፉን ሲቆርጥ፤ ሌላኛው በተንቀሳቃሽ ስልክ ከቀረፀ በኋላ ቦታውን ለቀው መሄዳቸውን ፖሊስ አስታውቆ ነበር።
የተከሳሾቹ ጠበቃ በበኩሉ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ሳያስቡበት በመጠጥ ኃይል ተገፋፍተው ይህን በመፈጸማቸው ይቅርታ ሊደረግላቸው ይገባል ሲል የቅጣት ማቅለያ ቢያቀርብም፤ ጉዳዩን ለወራት ይከታተል የነበረው ፍርድ ቤት ሆን ተብሎ የተፈፀመ የሥርዓት አልበኝነት ድርጊት በመሆኑ የአራት ዓመት ከሶስት ወር እስራት ፈርዶባቸዋል።
አካባቢውን የጎበኙ ሁሉ ፎቶ ይነሱበት የነበረው ተወዳጅ ዛፍ በእንግሊዝ በሚገኙ የተለያዩ ፖስተሮች ላይ የሚገኝ የአካባቢው ልዩ ምልክትና ቅርስ የነበረ ዛፍ ነው።
#ebc #england #trees

Comments