1 month ago
ብራዚል ከ23ኛው ዓለም ዋንጫ ተሰናበተች
**************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የ16ቱ ሀገራት ጥሎ ማለፍ መርኃ ግብር ብራዚል በኖርዌይ 2 ለ 1 ተሸንፋ ከዓለም ዋንጫው ተሰናብታለች። ኖርዌይም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሩብ ፍፃሜ አልፋለች።
የኖርዌይን የማሸነፊያ ግቦች 79ኛው እና 90ኛው ደቂቃ ላይ ኧርሊንግ ሀላንድ ከመረብ አሳርፏል። ለብራዚል ኔይማር ጁኒየር በፍፁም ቅጣት ምት 90+10 ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
በጨዋታው በብራዚል በኩል ብሩኖ ጉማሬሽ 14ኛው ደቂቃ ላይ ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ኖርዌይ በሩብ ፍፃሜው የሜክሲኮ እና እንግሊዝን አሸናፊ የምትገጥም ይሆናል።
በእድሪስ አሕመድ
#worldcup #fifaworldcup #brazil #norway #knockoutstage #football #sports

ብራዚል 0 - 0 ኖርዌይ :- የመጀመሪያ አጋማሽ ውጤት
***************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ በብራዚል እና በኖርዌይ መካከል እየተደረገ ያለው ጨዋታ የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ያለ ምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።

ብራዚል ከ ኖርዌይ፦ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ
*******************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ ብራዚል ከ ኖርዌይ የሚያደርጉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል።
ሁለቱ ቡድኖች ወደ ሜዳ ይዘው የሚገቡት የመጀመሪያ አሰላለፍ፦
#worldcup2026 #brazil #norway #roundof16 #ebc

ብራዚል ያነባች ዕለት - የጀርመኑ ዓለም ዋንጫ ትዝታዎች
****************
ያኔ ብራዚል እንዲህ ትሆናለች፣ በመሰል ደረጃ ላይ ትገኛለች ብለው ብዙዎች አልጠበቁም። ሁለት አስርት ዓመታት አልፈው ወደ ኋላ መለስ ብለው ሲያስታውሱት የሆነው ግን እንደዚያ ነው። የ2006 ዓለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ የቀደመውን አሸናፊ ፈረንሳይ እና የወቅቱን ሻምፒዮን ብራዚልን አገናኝቷል።
የ21ኛው ክፍለ ዘመን የብራዚል ወርቃማ ትውልድ፣ ኳስ የጥበብ አውድማ መሆኑን ዳግም ያስመሰከሩት ጥበበኞች ስብስብ ጀርመን ምድር ለዓለም ዋንጫው ሲዘልቁ ለ6ኛ የመድረኩ አሸናፊነት፣ ለተከታታይ ሻፒዮንነት ነው የታጩት።
ሮናልዶ ሉዊስ ናዛሪዮ ዴሊማ፣ ሮናልዲንሆ ጎቾ፣ ካካ፣ ካፉ፣ ሮቤርቶ ካርሎስ፣ አድሪያኖ እና ዚ ሮቤርቶን የመሰሉ ክዋክብት እንደ ምን ይዘነጋሉ? የሰው አዕምሮ ሊዘነጋቸው ቢፈቅድ እንኳ የእግር ኳስ ታሪክ ሊረሳቸው አይቻለውም። ትዝታቸው ርቆ ያልራቀ፣ ደብዝዞ ያልጠፋ፣ ቀጥኖ ያልተበጠሰ ህልው ነው። ከመዘንጋት የራቀ ታሪክ!
የዚያች ዕለት ግን ቀን ከነርሱ በተቃራኒ የቆመች መሰለች። የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በተለይም ዚነዲን ዚዳን በዚያች ቀን ስል፣ አስፈሪ እና ባለ ግርማ ሞገስ ሆነው ነው የቀረቡት።
ዚዳን ፀጉሩ እንደከዳው፣ የጎልማሳነት ደጃፉ ላይ እንደቆመ፣ ከእግር ኳስ የመሰናበቻ ቀናቱ እንደደረሰ ሳይሆን የ20ዎቹ አጋማሽ ላይ እንደሚገኝ ወጣት ነበር ይቦርቅ የነበረው።
በዚያ ጨዋታ ዚዳን የነበረው እንቅስቃሴ በዓለም ዋንጫ ታሪክ በግለሰብ ደረጃ ከተደረጉ እንቅስቃሴዎች ምርጡ እንደሆነ የብዙዎች እምነት ነው። የዘመን ተጋሪው ሮናልዶ ሉዊስ ናዛሪዮ ዴሊማም ያን ጨዋታ አስመልክቶ በሰጠው ቃለ-መጠይቅ “በዚያ ጨዋታ ዚዳን ያደረገው እንቅስቃሴ ያለማወላዳት በዓለም ዋንጫው ታሪክ ከታዩ ምርጥ ብቃቶች እንደ አንዱ ሊመደብ የተገባ ነው” ነበር ያለው።
ፈረንሳይ በቴሪ ሄንሪ አማካኝነት ባስቆጠረችው ግብ ጨዋታውን 1 ለ 0 አሸንፋ የወቅቱን የዓለም ሻምፒዮን ከውድድሩ አሰናበተቻት። ያኔ ብዙ አለማመኖች ነበሩ፣ የሆነው ከብዙዎቹ ጥበቃ በተቃራኒ ነው።
የ1998 ዓለም ዋንጫ አሸናፊ፣ የነ ዚነዲን ዚዳን ሀገር የወቅቱን የዓለም ሻምፒዮን ከዓለም ዋንጫ አስወጣቻት የሚለው በመጨረሻ የዳኛውን ፊሽካ ተከትሎ የተሰማው ዜና ነበር።
ያ ታሪክ በፍራንክፈርቱ ባልድ ስታዲየም የመጫወቻ ሜዳ ብቻ ተፈፅሞ ያበቃ አልሆነም። ወደ ካናሪንሀ መልበሻ ክፍልም ተከትሎ አምርቷል። በዕለቱ ልዩ የነበረው፣ ለቴሪ ሄንሪም ለግብ የምትሆነውን ኳስ አመቻችቶ ያቀበለው ዚነዲን ዚዳን ወደዚያች መልበሻ ክፍል አመራ።
አንድም ሊያፅናና አንድም በትልልቅ የእግር ኳስ መድረኮች እንደተለመደው መለያ ሊቀያየር።
‛ኤል ፌኖሜኖ’ ይህን የዚዳን ተግባር በበጎ አልተመከተውም። ሮናልዶ ከ20 ዓመታት በኋላ ሁነቱን አስመልክቶ ሲናገር “ሁላችንም ዛሬ ድረስ አብረን የቀጠልን ጓደኛሞች ነን፣ እርሱ ወደ መልበሻ ክፍል ሲገባ ግን የነበረው ድባብ አስፈሪ ነበር።
ብዙ ተጫዋቾች እያነቡ ነበር፤ እናም መለያ ለመቀያየር ወደ መልበሻ ክፍሉ የመጣበት ሰዓት ትክክለኛ እንዳልሆነና እንዲመለስ አስረግጬ ነገርኩት” ይላል።
እንደ ሮናልዶ እምነት ያች ዕለት የዓለም ዋንጫን ታሪክ ራሱን ቀይራለች። በእርግጥም በብራዚል በኩል ሆኖ ለተመለከተው ብዙ እውነት የሚመስሉ ነገሮችን የያዘ ሃሳብ ነው።
ለዓለም እግር ኳስ የስኬታማነት ናሙና የሆኑ ክዋክብትን ያበረከተችው ብራዚል ከትልቁ መድረክ አሸናፊነት እንደተናጠበች ሩብ ምዕተ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው። እነዛን ኮከቦች ግን እግር ኳስ ሊዘነጋቸው አይቻለውም።
በእርግጥ ፈረንሳይ አስከ ፍፃሜ ብትጓዝም፣ በዚነዲን ዚዳን እና ማርኮ ማታራዚ ድራማ በታጀበው ጨዋታ፣ በነ ማርሴሎ ሊፒ እና አንድሪያ ፒርሎ ጣሊያን ተረታ ለሌላ ዓለም ዋንጫ አሸናፊነት 12 ዓመታት ለመጠበቅ ተገዳለች።
ዚዳንን የ2006ቱ ዓለም ዋንጫ ‛አንተ በእግር ኳስ ስንብትህ ደጃፍ ላይ ቆመህ በእኔ ያበራህ ኮከብ ነህ’ ብሎታል።
ዓለም ዋንጫ ትዝታ ነው። ድልና ሽንፈት፣ ደስታ እና ሀዘን፣ ሳቅ እና ለቅሶ የሚመላለስበት የስፖርት አውድማ፤ የትውስታ መቼት ነው። መንገዱ ይቀጥላል!
በእድሪስ አህመድ
#worldcup #brazil #sports #japan #ebc Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት

5 months ago
ኔይማር ጁኒየር ወደ ብራዚል ብሔራዊ ቡድን ሊመለስ ነው!
#ethiopia | የብራዚል እግር ኳስ ደጋፊዎችን ያስፈነጠዘ ዜና ከሳምባ ምድር ተሰምቷል። ከ2023 ጀምሮ በጉዳትና በተለያዩ ምክንያቶች ከብሔራዊ ቡድኑ ርቆ የቆየው ድንቅ ተጫዋች ኔይማር ጁኒየር፣ በካርሎ አንቼሎቲ ለሚመራው የብራዚል ስብስብ ዳግም ጥሪ ሊደረግለት መሆኑ ተዘግቧል።
እንደ መረጃዎች ከሆነ፣ የኔይማር ዋና እቅድ በ2026 በሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ላይ ሀገሩን አገልግሎ ከእግር ኳስ ዓለም በክብር መሰናበት ነው። ለዚህም ይረዳው ዘንድ ብራዚል ከፈረንሳይ እና ከክሮሺያ ጋር ለምታደርጋቸው ታላላቅ ጨዋታዎች በስብስቡ ውስጥ እንደሚካተት ይጠበቃል።
አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ የኔይማርን ወቅታዊ አቋም ለመገምገም በሳንቶስ ቤት የሚያደርገውን ጨዋታ በስታዲየም ተገኝተው እንደሚከታተሉ የተነገረ ሲሆን፣ ሙሉው የብሔራዊ ቡድን ስብስብም በመጪው ሰኞ ይፋ ይደረጋል ተብሎ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።
የብራዚል ቁርጥ ቀን ልጅ ወደ ሜዳ መመለስ ለካናሪዎቹ አዲስ መነሳሳትን ይፈጥራል ተብሎ ታምኖበታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #neymarjr #brazil #selecao #ancelotti #worldcup2026 #footballnews #sambafootball #ኔይማር #ብራዚል #እግርኳስ

Sponsored by
Surafel
6 months ago
ኢትዮጵያ ከሶስቱ የብሪክስ አባላት ጋር ወንጀለኞችን አሳልፎ ለመስጠት ተስማማች! ⚖️🤝
#ethiopia | የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ ሀገሪቱ ከሦስቱ የብሪክስ (BRICS) አባል ሀገራት ጋር ያደረገችውን ወሳኝ የሕግ ስምምነት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።
🔹 የስምምነቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠት፦ በኢትዮጵያ፣ በቻይና፣ በብራዚል ወይም በደቡብ አፍሪካ ወንጀል ፈጽመው ወደ አንዱ ሀገር የሸሹ ግለሰቦች ተላልፈው እንዲሰጡ ያስችላል።
* ፍርደኞችን ማስተላለፍ፦ በማንኛውም የትብብር ሀገር ውስጥ ታስረው የሚገኙ ዜጎች ቀሪ ቅጣታቸውን በሀገራቸው እንዲጨርሱ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
* የሕግ ትብብር፦ በወንጀል ምርመራ እና በፍትህ ሂደት ላይ ሀገራቱ መረጃና ማስረጃ እንዲለዋወጡ የጋራ የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል።
🔹 ስምምነቱ ለምን አስፈለገ?
ኢትዮጵያ ከእነዚህ ሀገራት ጋር ያላት የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የዲፕሎማሲ ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መጥቷል። ይህንንም ተከትሎ የሚከሰቱ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል እና ፍትህን ለማረጋገጥ እንዲህ ዓይነቱ የሕግ ስምምነት አስፈላጊ መሆኑ በምክር ቤቱ ተመላክቷል።
ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነቷ የምታገኘውን የፖለቲካ እና የፍትህ ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #brics #justice #china #brazil #southafrica #legalagreement #crimeprevention #parliamentethiopia

7 months ago
ፕሬዝዳንቱ በ''ስቅታ'' ከእስር ተለቀቁ
#ethiopia | በሙስና እና በተለያዩ ወንጀሎች የ27 ዓመታት እስራት ተፈርዶባቸው የነበሩት የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ጃኢር ቦልሶናሮ፣ በገጠማቸው ስር የሰደደ የ"ስቅታ" ህመም ምክንያት ለህክምና ከእስር ተለቀዋል።
የህክምናው ዝርዝር፦
ህመሙ፦ ፕሬዝዳንቱ ላለፉት ጥቂት ወራት ባልተቋረጠ ስቅታ ሲሰቃዩ ቆይተዋል።
መፍትሄው፦ የህክምና ባለሙያዎች የአልትራሳውንድ መሳሪያን በመጠቀም የ"ፍሬኒክ ነርቭን" በመለየት ማደንዘዣ የሰጧቸው ሲሆን፣ ቀዶ ጥገናው በሰላም መጠናቀቁ ተገልጿል።
ቀጣይ ሂደት፦ ቦልሶናሮ በብራዚሊያ በሚገኝ የግል ክሊኒክ ህክምናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ፣ በቅርቡ ወደ እስር ቤት እንደሚመለሱ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#brazil #jairbolsonaro #healthnews #hiccups #justice #breakingnews

1 year ago
ለአሜሪካ የታሪፍ እርምጃ አፀፋዊ ምላሽ እንወስዳለን - የብራዚሉ ፕሬዝዳንት
*********************
የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ አሜሪካ በብራዚል ምርቶች ላይ ለምትጥለው ማንኛውም ታሪፍ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነኝ ብለዋል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከብራዚልጋር የገቡበትን እሰጣ ገባ በሚያባብስ ሁኔታ በብራዚል በተመረቱ ሸቀጦች ላይ የ50 በመቶ ቀረጥ ለመጣል ማቀዳቸውን ገልጸዋል።
ትራምፕ ለታሪፍ ጭማሪ እንደምክንያት ያነሱት ብራዚል በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዣየር ቦልሶናሮ ላይ እያደረገችው ባለው ልክ ያልሆነ አያያዝ እንደሆነ ተናግረዋል።
የቀድሞ የብራዚል ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ በ2022 በብራዚል በተደረገው ምርጫ በአሁኑ ፕሬዝዳንት ከተሸነፉ በኋላ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሞክረዋል በሚል ክስ እንደቀረበባቸው ይታወቃል።
ትራምፕ ቦልሶናሮን በዓለም ዙሪያ ካሉ መሪዎች በጣም የተከበሩ መሪ ናቸው ሲሉ ገልጸው፤ ብራዚልም በቀድሞው ፕሬዝደንት ላይ የጀመረችውን ክስም በአስቸኳይ እንድታቆም ጠይቀዋል።
የብራዚሉ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው፤ ሀገራቸው ከማንም የሚመጣን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበል እና ማንም ከሕግ በላይ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ፕሬዝዳንቱ በአንድ ወገን የሚደረግ የታሪፍ ጭማሪ እንደማይኖር እና ብራዚልም በአሜሪካ ምርቶች ላይ ተመጣጣኝ ታሪፍ እንደምትጥል አስጠንቅቀዋል።
አሜሪካ ከቻይና በመቀጠል የብራዚል ሁለተኛዋ ትልቅ የንግድ አጋር ስትሆን ከ10% ወደ 50% የሚጨመረው ታሪፍ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ሊጎዳ ይችላል ተብሏል።
በቢታንያ ሲሳይ
#ebc #america #brazil #tariffs

Comments