4 days ago
ገዳይ ሲያረፋፍድ ....
#ethiopia | የኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ የትረካ ጥበብ እና የካሜራ ቴክኖሎጂን አዋህዶ በዘመናዊ አቀራረብ እያደገ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የፊልም አፍቃሪዎችን እና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ትኩረት ከሳቡ የሀገር ውስጥ የጥበብ ስራዎች መካከል «ገዳይ ሲያረፋፍድ» የተሰኘው የናኦድ ለማ ፊልም ይጠቀሳል።
ይህ ፊልም ይዘቱ፣ የገጸ-ባህሪያት አሳሳሉ እንዲሁም በፖስተሩ ላይ ከሚታየው ጥበብ የሞላበት የቀለምና የብርሃን አጠቃቀም ጀምሮ አቀራረቡ አዳዲስ የትረካ መስመሮችን የሚዳስስ ለመሆኑ ማመላከቻዎችን ያሳያል።
የፊልሙ ርዕስ፡ ገዳይ ሲያረፋፍድ (GEDAY SIYAREFAFID)
ዳይሬክተር / የፊልም አዘጋጅ፡ ናኦድ ለማ (A film by Naod Lemma)
ደራሲ - ስለሺ አምባው
ዋና ተዋንያን፡
መለስ ታደሰ
መስከረም ነጋ በበላይ
ጌታነት አዳነ
ልዑል ተፈራ
አዘጋጅ/ፕሮዳክሽን፡ ታና ኢንተርቴይንመንት (Tana Entertainment) እና አዲቃ (Adika)
የፖስተሩ ጥበባዊ ዳሰሳ እና ጭብጥ (Visual & Storyline Analysis)
የከባቢ አየር እና ድባብ (Atmosphere & Tone):
የፖስተሩ የጀርባ ቀለም (ደመናማና ብርቱካናማ የቀን መግቢያ/መውጫ ብርሃን) የጥርጣሬ፣ የጉጉት እና የድራማ ስሜትን ይፈጥራል።
በግርጌ እና በጎን የሚታዩት የሁለቱ ዋና ገጸ-ባህሪያት ፊት (መጨናነቅ፣ ቁጣ እና ጥልቅ ሀሳብ) ፊልሙ ከባድ የስነ-ልቦና ድራማ ወይም የወንጀልና የበቀል/የውጥረት (Suspense/Thriller) ታሪክ ሊኖረው እንደሚችል ያመላክታል።
ተምሳሌታዊ ምስሎች (Symbolism):
በፖስተሩ መካከለኛ ክፍል ላይ በጥቁር ጥላ (Silhouette) የሚታዩት ሁለት ሰዎች እና ትንሽ ጎጆ ቤት በፊልሙ ውስጥ ያለውን የገጠር ወይም የርቅ ቦታ ዳራ፣ እንዲሁም የሁለት ሰዎች ሚስጥራዊ ግንኙነት ወይም ግጭት ያሳያሉ።
ፊልሙ ከተለመዱት የፍቅርና የኮሜዲ መስመሮች ወጣ ባለ መልኩ የሰዎችን ጥልቅ ስነ-ልቦና እና ያልተጠበቁ ሁነቶችን (Plot Twists) በማቀናጀት የቀረበ እንደሆነ ይነገርለታል።
በተለይም የነመለስ ታደሰ እና ጌታነት አዳነ ገጸ-ባህሪያትን የማቅረብ ተፈጥሯዊ ብቃት ለፊልሙ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ይገለጻል።
በምስል ጥራት፣ በድምጽ ቅንብር እና በምስል ቅንብር (Editing) በኩል የሀገር ውስጥ ፊልም ወደ አዲስ ደረጃ ለማሸጋገር የተደረገው ጥረት አዎንታዊ ግምገማዎችን አግኝቷል።
«ገዳይ ሲያረፋፍድ» የኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስትሪ የትረካ አቅሙን እና የቴክኒክ ብቃቱን ለማሳደግ የሚያደርገውን ጉዞ የሚያሳይ፣ የፊልም አፍቃሪያን ሊመለከቱት የሚገባ አሳቢና ውጥረት አዘል የጥበብ ሥራ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

18 days ago
(ዘ-ሐበሻ መዝናኛ ዜና) ኪነ-ጥበብ ድንበር የለውም፤ የሀገርን ማንነት፣ ባህልና ታሪክ ተሸክሞ የዓለምን ማዕዘናት ሁሉ ያቋርጣል። አሁን ደግሞ ተራው የኢትዮጵያ ሲኒማ ሆኗል። በዳይሬክተር አብርሃም ገዛኸኝ ልዩ ጥበባዊ እይታ እና በፕሮዲውሰር ታማራ ማርያም ዳዊት ስልታዊ ዝግጅት የተጠነሰሰው «መሀል ሰፋሪ» የተሰኘው አዲስ የኢትዮጵያ ፊልም፣ በዓለም ፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ እጅግ ስመ-ጥር በሆነው በ83ኛው የቬኒስ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ላይ በኩራት እንዲመረጥ ሆኗል። ይህ ምርጫ ተራ ስኬት አይደለም፤ ፊልሙ በፌስቲቫሉ እጅግ ተፈላጊ በሆነው "Final Cut" መርሃ ግብር ላይ ከተመረጡ ስድስት ምርጥ የመጀመሪያ ደረጃ ኤዲቲንግ ረቂቅ ፊልሞች መካከል አንዱ መሆን መቻሉን የሚያበስር ትልቅ የታሪክ ምዕራፍ ነው።
ይህ ጥበባዊ ፍጥረት በመጪው መስከረም ወር ማራኪ ውበት ወደተላበሰችው የጣሊያን ምድር በመጓዝ፣ ለዓለም አቀፍ የፊልም ባለሙያዎች፣ የፊልም ሽያጭ ድርጅቶች፣ አከፋፋዮችና አዘጋጆች ለእይታ ይበቃል። መድረኩ በመጀርያ ደረጃ ኤዲቲንግ ላይ ለሚገኙ የፈጠራ ሥራዎች የድህረ ፕሮዳክሽን ሥራዎቻቸውን በከፍተኛ የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ አጠናቀው ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲገቡ ሰፊ በር የሚከፍት ታላቅ የዕድል ድልድይ ነው። የፊልሙ ፈጣሪዎች የኢትዮጵያን ጥልቅ ታሪክና ባህል ይዘው በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ ለመቅረብ በመቻላቸው የተሰማቸውን ታላቅ ኩራትና የላቀ ደስታ ሲገልጹ፣ ሥራው እዚህ እንዲደርስ ከጎናቸው ለቆሙትና በሀገራችን የመዝናኛ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንደ "በስንቱ" እና "የእግር እሳት" ባሉ ተወዳጅ ድራማዎች ስሙ በግንባር ቀደምትነት ለሚነሳው አብሪኮም መልቲሚዲያ፣ እንዲሁም ለጎበዝ፣ ቱ ፓይለትስ፣ ባሬንትስ እና ኒው አምስተርዳም የፊልም ኩባንያዎች የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአንድ ፊልም ነፍስ በገጸ-ባህሪያቱ ውስጥ በሚነፍሱ ተዋናዮች ላይ የተመሠረተ ነው። «መሀል ሰፋሪ» በሀገራችን የኪነ-ጥበብ አድማስ ውስጥ ትልቅ ክብርና ተወዳጅነትን ያተረፉትን የነጋሲዎቹን ተዋናዮች ብቃት ይዞ ብቅ ብሏል። ታዋቂዎቹ አርቲስቶች ግሩም ዘነበ፣ አበበ ባልቻ እና ፀደይ ፋንታሁን በፊልሙ ላይ ላሳዩት ወሳኝና ተደናቂ አስተዋጽኦ የፊልሙ አዘጋጆች ትልቅ አድናቆት የቸሯቸው ሲሆን፣ የእነሱ ድንቅ አተዋወን ፊልሙን ዓለም አቀፍ መስፈርት እንዲያሟላ ማድረጉም ይነገራል።
እ.ኤ.አ በ1932 የተመሠረተው የቬኒስ የፊልም ፌስቲቫል በዓለም ላይ ካሉ እጅግ አንጋፋና ጥንታዊ መድረኮች አንዱ እንደመሆኑ መጠን፣ «መሀል ሰፋሪ» በዚህ መድረክ ላይ መመረጡ የኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ወደ አዲስ ከፍታ እየተጋገዘ መሆኑን ያበስራል።
በሀገር ውስጥ የጥበብ አሻራውን እያኖረ ያለው አብሪኮም መልቲሚዲያ እና ቡድኑ በጣሊያን መድረክ ላይ የኢትዮጵያን ስም ከፍ አድርገው ለማንሳትና የሀገራችንን ታሪክ ለዓለም ለማስተዋወቅ በጉጉት መስከረምን እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

20 days ago
የግብጽ ሚዲያዎች ተንኮል
"ከአባይ እስከ ሩፊጂ"
*ይህ የግብጽ የቴሌቪዥን ጣበያዎች የሰሩት ዶክመንተሪ ፊልም ነው።
#ethiopia | በግብጽ ሚዲያዎች የተሰራው ይህ ዶክመንተሪ ፊልም በታንዛኒያ የተገነባውን የጁሊየስ ኔሬሬ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ ላይ ያጠነጥናል።
ግን የግብጽ ሚዲያዎች ሆን ብለው የእኛው ሀብት የሆነው የአባይ ወንዝ
የዶክመንተሪው ዋና እርዕስ አድርገው ተጠቅመውታል።
ከአባይ እስከ ሩፊጂ (From the Nile to Rufiji) በሚል ርዕስ የቀረበው ይህ ዘጋቢ ፊልም በሩፊጂ ወንዝ ላይ የተገነባውን ግድብ እና የኃይል ማመንጫ ግንባታ ሂደት እንደሚተርክ አልጀዚራ ገልጿል።
ግብፅ ይህን ፕሮጀክት በአፍሪካ አህጉር የመሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ያላትን ተሳትፎ የሚያሳይ እንደሆነ ትገልጻለች።
ዘጋቢ ፊልሙ በፕሮጀክቱ ላይ የተሳተፉ ከ12,000 በላይ መሐንዲሶችን እና ሠራተኞችን ጥረት ይዳስሳል።
በተለይም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ጨምሮ ፈታኝ በሆኑ የአየር ንብረት ሁኔታዎች ውስጥ የተከናወነውን የቴክኒክ እና የሎጂስቲክስ ስራ አጉልቶ ያሳያል።
ታድያ የግብጽ ሚዲያዎች የኢትዮጵያ ሀብት የሆነውን የአባይ ወንዝ ለምን መጠቀም ፈለጉ?
የዘርፉ ባለሙያዎች ለዚህ ጉዳይ አስታየታቸውን ሰጥተዋል።
የአባይ ወንዝ ከታንዛኒያ ግድብ ጋር የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ ባይኖርም የግብጽ ሚዲያዎች አባይን በዶክመንተሪው መግብያ ላይ የተጠቀሙበት ምክንያት መኖሩን ይናገራሉ።
ባለሙያዎቹ በዋናነት የሚያነሱት ምክንያት እንደዚህ ያሉ ርዕሶች በተመልካቹና አድማጩ ዘንድ ትኩረት ለመሳብ የተመረጡ ናቸው ይላሉ።
እንደዚሁም የፊልሙ ርዕስ የአባይን ስም መጠቀሙ ተመልካቹ ለዘጋቢ ፊልሙ የበለጠ ፍላጎት እንዲኖረው ለማድረግ ነው ብለዋል።
ከዚህ ውጭ የፊልሙ ርዕስ በአካላዊ ወይም በተፈጥሮአዊ መንገድ የኢትዮጵያን ሀብት የሆነው አባይ ወንዝ በታንዛኒያው ሩፊጂ ወንዝ ግንባታ ላይ እንደ አንድ የልማት ተዋናይ ለማያያዝ የታሰበ አይደለም ይላሉ።
ይልቁንም የግብጽ ሚዲያዎች ለአፍሪካዊያን ማስተላለፍ የፈለጉት በአባይ ወንዝ ላይ የግብጽ የፖለቲካ ፍላጎት ለማጉላት የተጠቀሙበት ስልት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #fromniletorufiji #egyptmediadocumentary #ethiopianileriver

1 month ago
4.5 ሚሊዮን ብር ወጪ የሆነበት "ሳላያት" ፊልም ተመረቀ
የሮማንቲክ ኮሜዲ ዘውግ ያለው "ሳላያት" የተሰኘ አዲስ ፊልም ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አዲሱ ህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት ተመረቀ፣ ከሰኔ 25፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ሲኒማ ቤቶች እንደሚታይ የፊልሙ ፕሮዲዩሰር ገልጸዋል።
የፊልሙ ፕሮዲዩሰር እንደገለጹት፣ ፊልሙን ለመስራት እስከ ስምንት ወር የሚጠጋ ጊዜ የፈጀ ሲሆን፣ ለፊልም ስራው ከ4.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ተገልጿል፣ ፊልሙ የሮማንቲክ ኮሜዲ ዘውግ ያለው እና የህብረተሰቡን የእለተ እለት ህይወት የሚዳስስ ነው ብለዋል።
በእውነት መልቲሚዲያ ተዘጋጅቶ በሞሪያድ ኢንተርቴመንት የቀረበው ሳላያት ፊልም አለምሰገድ ተስፋዬ፣ ናታይ ጌታቸው፣ መኮንን ለአከ፣ አስቴር አለማየሁ፣ ክላራ ሙሉጌታ፣ ሊና ካሳ እና ሌሎች ተዋናዮች የተጣመሩበት ነው።

#fastmereja | የሮማንቲክ ኮሜዲ ዘውግ ያለው "ሳላያት" የተሰኘ አዲስ ፊልም ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አዲሱ ህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት ተመረቀ፣ ከሰኔ 25፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ሲኒማ ቤቶች እንደሚታይ የፊልሙ ፕሮዲዩሰር ገልጸዋል።

''ባለቤቴ በማንኛውም ጊዜ ልትገድለኝ ትችላለች” - አክሻይ ኩማር
#ethiopia | የቦሊዉድ ታዋቂው ተዋናይ አክሻይ ኩማር ባለቤቱ ትዊንክል ኻና በሥራዎቹ ላይ እጅግ ጥብቅና ቀጥተኛ ትችት የምትሰነዝር ቀዳሚ ተቺው መሆኗን ተናገረ።
ተዋናዩ “ዌልካም ቱ ዘ ጃንግል” የተሰኘውን አዲስ ፊልሙን በማስተዋወቅ ላይ በነበረበት ወቅት በሙያዊም ሆነ በግል ሕይወቱ ውስጥ ከማንም በላይ የእሷ አስተያየት ትልቅ ቦታ እንደሚሰጠውና የእሷ ግልጽ ምላሽ ሁልጊዜም መሬት እንዲረግጥ እንደሚያደርገው ገልጿል።
በቅርቡ ከቦምቤይ ታይምስ ላውንጅ ጋር ባደረገው ቆይታ በጣም አስቸጋሪው ተቺህ ማን ነው ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ ያለምንም ማንገራገር የሕይወት አጋሩን ስም የጠራው አክሻይ የእሷን የትችት ደረጃ በሳቅ የታጀበ ማብራሪያ ሰጥቶበታል።
ባለቤቱ በሥራዎቹ ላይ የምትሰጠውን አስተያየት “እጅግ ጨካኝ” ሲል የገለጸው አክሻይ ኩማር ''እሷ ጨካኝ ስትሆን ወሰን የላትም፤ በማንኛውም ጊዜ በትችቷ ልትገድለኝ ትችላለች እሷ ፊት ምንም መከላከያ የለህም” በማለት ሁኔታውን አስረድቷል። ይሁን እንጂ በቅርቡ ያጋጠመውና እጅግ ያስደሰተው አንድ ያልተጠበቀ ክስተት መኖሩን አልሸሸገም።
''ባለቤቱ ወዳሴ አታበዛም' '፤ለሌላ ፊልሙ ድምፅ በመቅረጽ ላይ እያለ ባለቤቱ ትዊንክል አዲስ ለሚወጣው ፊልሙ ማስታወቂያ ያላትን አድናቆት የገለጸችበትን መልዕክት እንደላከችለት ተናግሯል።
ይህ ከእሷ እምብዛም የማይገኝ ብርቅዬ መወድስ በመሆኑ የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ ለፊልም ዳይሬክተሩ ጭምር “ባለቤቴ የፊልሙን ማስታወቂያ እንደወደደችው መልዕክት ስለላከችልኝ ዛሬ በጣም ደስተኛ ነኝ” በማለት ገልጾለታል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago
ዓለም አቀፍ ትኩረትን የሳበው የሐጀር አጭር ፊልም
#ethiopia | በደራሲና ዳይሬክተር ነፃለም አብዲ ተፅፎ የተዘጋጀው እንዲሁም በኢን ፊልምስ (IN Films) ወደ ስራ የተቀየረው ሐጀር የተሰኘው አጭር ፊልም በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍተኛ መነጋገሪያ መሆን ችሏል።
በዚህ የፊልም ስራ ላይ ከሃያ በላይ የሚሆኑ አንጋፋና ባለሙያ የኢትዮጵያ የሲኒማ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን የላቀ ብቃታቸውንም በተግባር አስመስክረውበታል።
የፊልሙ ታሪክ የሚያጠነጥነው ከ4,200 ዓመታት በፊት ነብዩ ኢብራሂም ሁለተኛ ባለቤታቸውን ሐጀርንና ጨቅላ ልጃቸውን ነብዩ ኢስማኤልን ይዘው ከተሰደዱ በኋላ አሁን መካ ከተማ የተቆረቆረችበት በረሃማ ስፍራ ላይ ትተዋቸው ወደተመለሱበት ታሪካዊ ወቅት ላይ ነው።
በወቅቱ ሐጀር ከፍተኛ የውሃ ጥም ስላጋጠማት ውሃ ፍለጋ በሶፋ እና በመርዋ ተራሮች መካከል ትመላለስና ትሯሯጥ ነበር። በመጨረሻም በአላህ እዝነትና ቸርነት ከሕፃኑ ኢስማኤል እግር ስር የዘምዘም ውሃ ሊፈልቅ ችሏል።
ይህ የፊልም ስራ ዓለም አቀፍ የሲኒማ ደረጃን ጠብቆ የተሰራ ከመሆኑም ባሻገር በማንኛውም የዓለም ክፍል የሚኖር ሰው በቀላሉ እንዲረዳው ተደርጎ ያለምንም ንግግር (Dialogue free) የተዘጋጀ ነው።
በተጨማሪም የእስልምናን ሥርዓትና አደብ በጠበቀ መልኩ የነብያትን ክብር ለመጠበቅ ሲባል ቀደም ሲል በዓለም ላይ ከተሰሩ ሃይማኖታዊ ፊልሞች በተለየ አዲስ የፊልም አሰራር ጥበብን ተጠቅሟል።
በዚህም መሰረት ገጸ ባህሪያቱ በአካል ሳይታዩ ነገር ግን ታሪካቸው በሚገባ በሚገለጽበት መንገድ ተቀርጾ ቀርቧል።
የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር ይህንን ስራ ለመስራት የተነሳሳበት ዋናው ምክንያት ለአስራ አንድ ዓመታት ያህል ጊዜ ወስዶ ያዘጋጀውንና በንጉስ ነጃሺ ሙሉ የህይወት ታሪክ ላይ የሚያተኩረውን ነጃሺ የተሰኘውን ታላቅ የፊልም ፅሁፍ ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ ለማውጣት የሚያስችለውን መንገድ ለመጥረግ በማሰብ እንደሆነ ታውቋል።
በፊልሙ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የተለያዩ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተገኝተው ሰፊ ዘገባ የሰሩለት ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ በሲኤንኤን (CNN)፣ ቢቢሲ (BBC) እና ሮይተርስ (Reuters) ባሉ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ የሚታወቀው ዝነኛው ጋዜጠኛ ጂም ስቴንማን (Jim Stenman) ሆርን ሆራይዘን (Horn Horizon) በተሰኘው ጋዜጣው እንዲሁም በሊንክድኢንና በሰብስታክ ገጾቹ ላይ ስለዚህ ድንቅ ስራ በሰፊው አስነብቧል።
https://www.linkedin.com/p...
#hajarshortfilm #ethiopiancinema #infilms #netsalemabdi #kingnejashi #jimstenman #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Sponsored by
Surafel
3 months ago
«ሂዶቴ» አዲስ ፊልም ለተመልካቾች ሊቀርብ ነው
#ethiopia | በሴት ልጅ ጥቃትና አስከፊው የሴት ልጅ ግርዛት ዙሪያ የሚያጠነጥነው «ሂዶቴ» የተሰኘው አዲስ ፊልም በቅርቡ ለተመልካቾች ይቀርባል ተብሏል።
ፊልሙ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እና በጀርመን ፍራይቡርግ ከተማ በልዩ ስነ-ስርዓት ለእይታ ይበቃል።
«ሂዶቴ» የወላይትኛ ቃል ሲሆን «ተስፋ» ማለት ነው።
የፊልሙ ዋና ዓላማ ማህበረሰቡ ከሴቶች ጎን እንዲቆም ማነቃቃትና ግርዛትን መዋጋት ነው።
ፊልሙን ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ ለመስራት ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ሆኖበታል።
በሳሙኤል ተሻገር ተፅፎና ዳይሬክት ተደርጎ በታምራት በርሄ ፕሮዲውሰርነት የተዘጋጀ ነው።
ፊልሙ 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ የሚረዝም ሲሆን ለመስራትም 1 ዓመት ፈጅቷል።
75% በወላይታ ዞን እና 25% በሀዋሳ ከተማ የተከናወነ ሲሆን 1 ወር ፈጅቷል።ፅናት ተረፈ፣ ሄኖክ አለማየሁ፣ አማኑኤል የሺወንድና ናርዶስ አንትዋ በዋናነት ተሳትፈዋል።
170 አጃቢ ተዋንያንና 24 ባለሙያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 215 ሰዎች ተሳትፈውበታል።
ፊልሙ በእንግሊዝኛና ጀርመንኛ ንዑስ ርዕስ (Subtitles) የተዘጋጀ ነው።
ከአገር ውስጥ ምርቃት በኋላ ወደ ታላላቅ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ያመራል።
በተጨማሪም በአገር ውስጥ ሲኒማ ቤቶችና በተመረጡ የአፍሪካ አገራት ይታያል።
በአውሮፓ ለሚኖረው ስርጭትም «ግሩምበርግ ፊልም» ከተሰኘ የጀርመን ኩባንያ ጋር የ3 ዓመት የሽያጭ ስምምነት ተፈርሟል።
📷 kebede mekibeb
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

ድንቁ ሔኖክ
#ethiopia | የሔኖክ የመጀመርያ ፊልም "ትራፊኳ.." የተሰኘው ፊልም ነበር። ከሜሮን ጌትነት ጋር ነበር አብረው የሰሩት። እዛ ፊልም ላይ የተመለከትነው የሔኖክ Acting የመጀመርያ ፊልሙ ሁላ አይመስልም ነበር። ይህ ማለት ከዛሬ 12 እና 13 አመት በፊት ነው።
ከዛ በኋላ በርካታ ፊልሞች ላይ በትወና ተሳትፏል። በሂደት ደግሞ ፊልሞችን እና የሙዚቃ ቪዲዮዎችንም ጭምር ዳይሬክት ማድረግ ጀመረ። ከታሪኩ [ ባባ ] ጋር እና ከማንዴላ ጋር የሰራው አንድ ፊልም አለ - በጣም የሚመቸኝ። እነ አለምሰገድ ተስፋዬን፣ ሙሉአለም ጌታቸው፣ ማንዴላን ካነሳን ሔኖክንም በእነሱ ምድብ ልናካትተው የምንችል ምርጥ የፊልም ተዋናይ ነው። ትናንትና በ Seifu on EBS ላይ ቀርቦ እሱ ራሱ እንደተናገረው ከሆነ የሔኖክ ወንድሙ ህይወት በ 2 ይከፈላል። የመጀመርያው ፈረጃ የተሰኘውን አዲሱን ፊልም መስራት ከመጀመሩ በፊት ያለው ህይወቱ ነው - ቀጥሎ ደግሞ ከፈረጃ በኋላ ያለው ህይወት።
ሔኖክ አዲስ ለሚሰራው ፊልም ብዙ ዋጋ ከፍሏል። የሚታዩም - የማይታዩም ብዙ መስእዋትነቶች ተከፍለዋል። ለዚህ ፊልም Character ብሎ ከሰውነቱ ላይ 41 ኪሎ ቀንሷል። የፊልሙ ገፀባህሪ የሰውነት አቋም ስላስገደደው።
ሔኖክ "ፈረጃ.." ፊልምን ሲሰራ 4 ነገሮችን ነው አብሮ የሚሰራው። የፊልሙ መሪ ተዋናይ ነው ፤ ደራሲ ነው ፤ ዳይሬክተር ነው ፤ Executive Producer ነው። ይህንን ፊልም እውን ለማድረግ ደግሞ 6 አመታት ያህል ፈጅቶበታል። ሌላ ስራ ሳይሰራ - ሙሉ ትኩረቱን "ፈረጃ.." ላይ ብቻ አድርጎ።
በገንዘብም ቢሆን - ብዙ አውጥቶበታል። መኪናውን እስከመሸጥ ድረስ ደርሷል። ፊልሙ በአጠቃላይ የፈጀው 7.5 ሚሊየን ብር ነው።
ከህዝብ [ ከ 1,200 ሰዎች ] የተዋጣው ገንዘብ ግን 3 ሚሊየን ብር ብቻ ነበር። እውነት ለመናገር ሔኖክ ያሰበው ሀሳብ በጣም ገራሚ ሀሳብ ነው።
"ህዝብ አምስት - አምስት ብር አዋጥቶ ፊልም እንስራ ከዛ በኋላ በዚህ ፊልም ሽያጭ ደግሞ ሌላ ፊልም ይሰራል ፤ ህዝቡን የማስቸግረው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
ሁለተኛው ፊልም ከመጀመርያው ገቢ ነው የሚሰራው። ሶስተኛው ፊልም ደግሞ ከሁለተኛው ፊልም ገቢ። እንደዚህ እያልኩ - 50 ፊልሞችን የመስራት እቅድ አለኝ.." ብሏል። በጣም እኮ ፀዴ ሀሳብ ነው።
ሔኖክ ያመጣው "ህዝብ አምስት - አምስት ብር አዋጥቶ ፊልም መስራት.." የሚለው ሀሳብ በአለም አቀፍ ደረጃ Crowd funding የሚባለው እና ብዙ ትልልቅ ስራዎች የሚሰሩበት መንገድ ነው።
በሀገራችን ይሄንን ተጠቅሞ የፊልም ኢንዱስትሪውን Self-sustaining [ ራሱን በራሱ የሚደግፍ ኢንዱስትሪ ] ለማድረግ ማሰቡ ትልቅ አብዮት ነው። ይህ ሀሳብ ፊልምን ከባለሀብቶች ጥገኝነት አውጥቶ የህዝብ ንብረት የሚያደርግ ግሩም ሀሳብ ነው።
ህዝቡ 5 ብር ሲያዋጣ ዝም ብሎ ተመልካች ሳይሆን የፊልሙ ባለቤት እና ደጋፊ ይሆናል ማለት ነው። እኛ ሀገር ለአንድ የጥበብ ስራ 6 አመት ሙሉ ተግቶ መስራት እብደት ሊመስል ይችላል ፤ ነገር ግን እውነተኛ ጥበብ የሚወለደው እንዲህ አይነት ትጋት ውስጥ ነው።
ሔኖክ ለጥበብ የከፈለውን መስዋዕትነት [ ገንዘቡን፣ አካሉን እና ጊዜውን ] የምንክሰው እኛ ተመልካቾች ይሄንን ራእይ ስንደግፍና ሀሳቡን ስንገዛ ብቻ ነው።
በተለይ በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ ለገፀ-ባህሪ [ Character ] ተብሎ 41 ኪሎ መቀነስ እና መኪና እስከመሸጥ ድረስ መድረስ - የኪነጥበብን ፍቅርና ቁርጠኝነትን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
በፍራኦል ሀበሻ

ለፊልሙ እድገት እየተከፈለ ያለ ዋጋ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ ለሙያ የሚከፈልን እውነተኛ መስዋዕትነት በተግባር ያሳየ አንድ ወጣት ባለሙያ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል። ተዋናይና የፊልም ባለሙያ ሄኖክ ወንድሙ "ፈረጃ" የተሰኘውን አዲስ ፊልሙን ለተመልካች ለማብቃት ያለፈባቸው ረጅም ዓመታት፣ በትዕግሥትና በፅናት የተሞሉ ነበሩ። ሄኖክ ለዚህ ፊልም ስኬትና ለሚወክለው ገጸ-ባህሪ ተአማኒነት ሲል ብቻ፣ የሰውነቱን ክብደት እጅግ አደገኛ እስከሚባል ደረጃ ድረስ በመቀነስ ለሙያው ያለውን ጥልቅ ፍቅር በተግባር አሳይቷል።
ይህ ወጣት የጀመረውን ፊልም ዳር ለማድረስ የገጠመው የገንዘብ እጥረት ሳይበግረው፣ በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ በማሰባሰብና የሰዎችን ፊት በማየት ጭምር ስራውን ለመቀጠል ተገዷል።
በምስሉ ላይ እንደሚታየው፣ ሄኖክ ለገጸ-ባህሪው ሲል የደረሰበት አካላዊ ለውጥ ለሙያው የሰጠውን ትልቅ ዋጋና ቁርጠኝነት በግልጽ ይመሰክራል። ዛሬ ላይ ትልቁና ዋናው የፊልሙ ቀረጻ ተጠናቆ ለማጠቃለያ መድረሱ የተሰማ ሲሆን፣ ይህ ስኬት ደግሞ በብዙ ውጣ ውረድና በመከራ ውስጥ ላለፈው ባለሙያ ትልቅ እፎይታ ነው።
የሄኖክ ታሪክ ለኢትዮጵያ የጥበብ ሰዎች ትልቅ አርአያነት ያለው ነው።
ጥበብ ዝም ብሎ መታየት ብቻ ሳይሆን፣ እንዲህ ያለውን እራስን የመስጠትና የመለወጥ ጥበብን እንደሚጠይቅ ሄኖክ በተግባር አሳይቶናል።
በቅርቡ ለዕይታ ይበቃል ተብሎ የሚጠበቀው "ፈረጃ" ፊልም፣ ከጀርባው እንዲህ ያለውን የሰባት ዓመታት የፅናት ታሪክ አዝሎ የሚመጣ በመሆኑ ለተመልካች ልዩ ስሜት እንደሚፈጥር ጥርጥር የለውም።
ኢትዮ ሊድ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

4 months ago
ግሩም ኤርሚያስ ዋና ገጸ ባህሪ አድርጎ በሻኪሶ የተሰራው ዳሎቪያ ፊልም ለእይታ ሊቀርብ ነው።
#fastmereja I ተወዳጁ ተዋናይ ግሩም ኤርሚያስ በዋና ገጸ-ባህሪነት የሚተውንበት "ዳሎቪያ" የተሰኘው አዲስ ፊልም በሚቀጥለው እሁድ ሚያዝያ 05 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድግስ በአድዋ 00 አፍሪካ አዳራሽ እንደሚመረቅ ተገለጸ። ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተመላከተው፣ ፊልሙ ከመጪው ሚያዝያ 09 ጀምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ሲኒማ ቤቶች ለዕይታ ይበቃል።
በኤልዳን ፊልምስ ተዘጋጅቶ በወርገድ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው ዶሎቪያ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የፊልሙ ፕሮዲውሰሮች፣ ዳይሬክተሮችና ተዋንያን በተገኙበት ዝርዝር መረጃው ቀርቧል። "ዳሎቪያ" በዋናነት ተወዳጁን ተዋናይ ግሩም ኤርሚያስን እና አማኑኤል ታፈሰን ጨምሮ ሌሎች አንጋፋና ወጣት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን አሳትፏል።
ፊልሙን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ ለአንድ ዓመት ከስድስት ወራት ያህል ከፍተኛ ዝግጅት የተደረገበት ሲሆን፣ ታዋቂው የፊልም ዳይሬክተር በሃይሉ እንግዳ አቀናጅቶታል። የቴክኖሎጂ አጠቃቀምንና የፊልም ኢንዱስትሪውን ዕድገት ታሳቢ ያደረገው ይህ ሥራ፣ አብዛኛው ቀረጻው የተከናወነው በሻኪሶና አካባቢው እንደሆነ ታውቋል።
የፊልሙ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ሚያዝያ 05 ቀን በአድዋ መታሰቢያ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ይከናወናል።
#ኪነ_ጥበብ

ስቲቨን ኮልበርት አዲሱን የ'ሎርድ ኦፍ ዘ ሪንግስ' ፊልም ሊጽፍ ነው
ታዋቂው የቶክ ሾው አቅራቢ ስቲቨን ኮልበርት "The Lord of the Rings: Shadow of the Past" የተሰኘ አዲስ የፊልም ስክሪፕት መጻፍ መጀመሩ ተነገረ።
የፊልሙ ዳይሬክተር ፒተር ጃክሰን እንደገለጸው፣ ታሪኩ የሚጀምረው ፍሮዶ ከሞተ ከ14 ዓመታት በኋላ ነው።
ፊልሙ ሳም፣ ሜሪ እና ፒፒን የቀደመ ጀብዷቸውን ለመቃኘት የሚያደርጉትን ጉዞ ይከተላል። በተጨማሪም የሳም ልጅ ኤሌኖር የ"ሪንግ ዎር" ምስጢር ላይ የምታደርገው ጥናት የፊልሙ ማዕከል ይሆናል።
ይህ አዲስ ስራ ቀደም ሲል በፊልም ያልተካተቱ የመጽሐፉን ምዕራፎች መሰረት ያደረገ መሆኑ ተጠቁሟል።
ምንጭ: BGNES

5 months ago
ዳናሽ -
#ethiopia | ይህ ፊልም በአጭር ጊዜ ውስጥ ያገኘው የተመልካች ቁጥር (በ 4 ቀናት ውስጥ ከ430 ሺህ በላይ) በጣም አስገራሚ ነው!
የናሆም መልቲሚዲያ ዩቲዩብ ቻናል ጥራት ያላቸው ስራዎችን በማቅረብ የሚታወቅ በመሆኑ፣ ይህ "ዳናሽ" የተሰኘው የፍቅር ፊልምም የብዙዎችን ቀልብ መሳቡ አይገርምም።
በተለይ "ልብ አንጠልጣይ" መባሉ የፊልሙን የታሪክ ጥንካሬ እና ተመልካችን እስከመጨረሻው የማቆየት ብቃቱን ያሳያል።
ስለ ፊልሙ አንዳንድ ነጥቦች፦
* የታሪኩ ዘውግ፦
የፍቅር እና ድራማ (Romance/Drama)
* የእይታ ፍጥነት፦
በአራት ቀናት ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ለኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ትልቅ ስኬት ነው።
* የቀረበበት መድረክ፦
በናሆም መልቲሚዲያ (Nahom Multimedia) የዩቲዩብ ገጽ ላይ።
https://youtu.be/Tyl5PGNU4...

7 months ago
የሳራ ዶላታባዲ ፈረንሳዊ-ኢራናዊት የምስል ጥበብ ባለሙያ
ሥራዋ በኢትዮጵያ ቤተመንግሥት ሲኒማ ቤት እየታየ ነው
#ethiopia | መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ያደረጉ ኢምባሲዎች፤ ጥሪ የተደረገላቸው 200 እንግዶች ዘጋቢ ፊልሙን በመመልከት ላይ ናቸው
***
ስለ ዳይሬክተሯ
ፊልም፡ ጉጉቱ፣ አትክልት ቦታው እና ፀሃፊው (An Owl, A Garden and the Writer)
ሳራ ዶላታባዲ (Sara Dolatabadi)
የፊልም ዳይሬክተር፣ የምስል ጥበብ ባለሙያ (Visual Artist) እና ጸሐፊ
ሳራ ዶላታባዲ ፈረንሳዊ-ኢራናዊት የምስል ጥበብ ባለሙያ እና የመልቲሚዲያ ፊልም ሰሪ ናት። በልጅነቷ የኢራን እስላማዊ አብዮት እና የኢራን-ኢራቅ ጦርነት በህይወቷ ላይ ተፅእኖ አሳድሮባታል። እነዚህን ታሪካዊ ክስተቶች በልጅነት አይኖቿ ተመልክታለች። እነዚህ ትዝታዎች በምስል ጥበብ ባለሙያነቷ እና በፊልም ሰሪነቷ ላይ የራሳቸውን አሻራ ያሳረፉ ሲሆን፤ ስራዎቿ የግል ሕይወት (Microcosm) እና የፖለቲካው ዓለም (Macrocosm) የሚገናኙበት ነጥብ ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ።
ከቴህራን አዛድ የስነ-ጥበብ ዩኒቨርሲቲ (Azad Art University) ከተመረቀች በኋላ፣ ለአሥር አመታት በቶኪዮ፣ ፓሪስ እና ኒው ዮርክ በመስራት እና ስራዎቿን ለእይታ በማቅረብ አሳልፋለች። በኒው ዮርክ በሚገኘው ሃንተር ኮሌጅ (Hunter College) በስነ-ጥበብ የማስተርስ ዲግሪዋን (MFA) አግኝታለች። ለድህረ-ምረቃ መመረቂያ ጽሁፏ፣ ስለ ቤተሰቧ የሚያወሳ "Summer Light" (የበጋ ብርሃን) የተሰኘ አጭር ዶክመንተሪ ፊልም ዳይሬክት አድርጋ አዘጋጅታለች።
በመቀጠልም "An Owl, A Garden and the Writer" (ጉጉቱ፣ አትክልት ቦታው እና ጸሐፊው) የተሰኘውን ዶክመንተሪ ፊልም የሰራች ሲሆን፤ ፊልሙ እ.ኤ.አ. በ2023 በቪዥን ዱ ሪል (Vision du Réel) ፌስቲቫል ላይ ለእይታ በቅቷል። ይህ ፊልም በቡሳን የፊልም ፌስቲቫል (Busan Film Festival) እና በሴንተር ፖምፒዱ ኤክስትራ ፌስቲቫልን ጨምሮ በተለያዩ መድረኮች እና ፌስቲቫሎች ላይ ታይቷል።
በተጨማሪም ፊልሙ በዶክ ሊዝቦአ 2023 (Doc Lisboa) "የመብት እና ነጻነት ሽልማት" (Rights and Freedom Award) እንዲሁም በ2024 በሞንትሪያል በተካሄደው ዓለም አቀፍ የኪነ-ጥበብ ፊልም ፌስቲቫል ላይ "ምርጥ የቁም-ምስል ሽልማት" (Best Portrait Award) አሸንፏል።
በጋቦን ለሦስት ዓመታት በቆየችበት ጊዜ በሊብሬቪል (ሲሲባ) ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አካባቢዎች ትምህርትን ለማስፋፋት የሚሠራ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት (NGO) ከመሰረቱት መካከል አንዷ ስትሆን፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ትኖራለች፣ ትሰራለችም።
***
ስለ ሀበሻ ቪው (habeshaview)
በ2015 (እ.ኤ.አ) የተመሰረተው ሀበሻ ቪው (habeshaview)፤ ዋና መቀመጫውን አሜሪካ ቨርጂኒያ ያደረገ ሲሆን፣ በእንግሊዝ ለንደን እና በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ቢሮዎች አሉት። በተጨማሪም በኔዘርላንድ የዳታ ማዕከል (Data center) እና የቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አለው።
ሀበሻ ቪው ዘርፈ-ብዙ የሚዲያ፣ የመዝናኛ እና የላቀ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው። ኩባንያው ለተጠቃሚዎች ምቹ የሆነ የኦቲቲ (OTT) ፕላትፎርም እና አፕሊኬሽኖችን በማልማት ደረጃውን የጠበቀ የመመልከት ልምድን ያቀርባል።
የሚያቀርባቸው አገልግሎቶችም የቀጥታ የዜና ቻናሎችን፣ የመዝናኛ ጣቢያዎችን፣ እንደ ፍላጎት የሚታዘዙ ፊልሞችን (Video On Demand)፣ ጨዋታዎችን እና የኦዲዮ ቻናሎችን ያካትታሉ።
በተጨማሪም ከዓለም ዙሪያ ከተውጣጡ የተለያዩ ስቱዲዮዎች የተገኙ ኦሪጂናል የሆኑ ፕሮግራሞችን በብዙ የቋንቋ አማራጮች፣ በተመጣጣኝ ዋጋ እና ያለፉ ፕሮግራሞችን መልሶ የመመልከት (catch-up service) አማራጭ ጭምር ያቀርባል።
ሀበሻ ቪው ከዚህም በተጨማሪ ዓለም አቀፍ የፊልም አከፋፋይ ነው።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተሰሩ ጥራት ያላቸውን እና ኦሪጂናል ፊልሞችን በመምረጥ፣ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫሎች እና የሲኒማ ቤቶች በማቅረብ ያስተዋውቃል።
በረጅም ጊዜ እቅዱም ከአፍሪካ አህጉር የሚገኙ ሌሎች ይዘቶችን በማሰራጨት በፓን-አፍሪካ የመዝናኛ እና የስትሪሚንግ ኢንዱስትሪ መሪ ለመሆን ራዕይ ሰንቋል።
***
የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት
የሀበሻ ቪው ቴክኖሎጂ እና መልቲሚዲያ (habeshaview Technology and Multimedia) ተባባሪ መስራች እንደመሆኔ፣ ሞቅ ያለ ሰላምታዬን ሳቀርብላችሁ ታላቅ ክብር ይሰማኛል።
የጉዞአችን ተካፋይ ስለሆናችሁ እጅግ ደስ ብሎኛል። ዛሬ አዲሱን የስራ ዘርፋችንን "ሀበሻ ቪው ሲኒማ" (habeshaview Cinema) በምናስጀምርበት በዚህ ወቅት፣ እንኳን ወደ ደማቁ የመዝናኛ፣ የባህል እና የፈጠራ ዓለማችን በሰላም መጣችሁ ለማለት እወዳለሁ። ይህ በየወሩ የሚካሄድ የፊልም ክበብ፤ የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ከተቀረው ዓለም የተውጣጡ ፊልሞችን ለእይታ የሚያቀርብ ነው።
ትዕግስት ከበደ
ተባባሪ መስራች፣
***
ፊልም፡ ጉጉቱ፣ አትክልት ቦታው እና ፀሃፊው (An Owl, A Garden, & The Writer)
የፕሬስ ማስታወሻ እና ሽልማቶች
"እጅግ ዜማዊ እና ረቂቅ፣ ሆኖም ግን ጉልበት ያለው ስራ፤ እጅግ ታላቅ የሆነውን የፀሃፊውን ስብእና ሰብአዊ በሆነ መንገድ እያሳየን፣ ስላለፉት አስርት ዓመታት የኢራን ጨካኝ ስርዓት የሚያስተምረን ፊልም ነው።"
— ቢዝነስ ዶክ ዩሮፕ (BUSINESS DOC EUROPE)
ፌስቲቫሎች እና ሽልማቶች
ቪዥንስ ዱ ሪል 2023 (Visions du Réel): በርኒንግ ላይትስ ውድድር (የዓለም የመጀመሪያ እይታ)
ፖምፒዱ ሴንተር (Pompidou Centre): (የፈረንሳይ የመጀመሪያ እይታ)
ቡሳን ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል 2023 (Busan IFF): (ዓለም አቀፍ የመጀመሪያ እይታ)
ዶክ ሊዝቦአ 2023 (Doclisboa): የመብት እና ነጻነት ሽልማት አሸናፊ
ኦዛ (OZA) የዘመናዊ ዶክመንተሪ ፊልም ፌስቲቫል 2024: የዳኞች ልዩ ሽልማት
ፊፋ 2024 (FIFA): ምርጥ የቁም-ምስል (Portrait) ሽልማት
ካርሎቪ ቫሪ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል 2021: በሂደት ላይ ያሉ ስራዎች (Works in Progress) የድህረ-ምርት ልማት ሽልማት አሸናፊ
አይዲኤፍኤ ፎረም (IDFA Forum)
የአዘጋጆች መግለጫ [አሚር ናደሪ - ዋና አዘጋጅ (Executive Producer)]
ኢራናዊው ፊልም ሰሪ አሚር ናደሪ፤ "ቬጋስ፡ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ" (2008)፣ "ማንሃተን በቁጥሮች" (1993) እና "ዘ ረነር" (1985) በመሳሰሉ ፊልሞቹ ይታወቃል። እ.ኤ.አ. በ2016 በቬኒስ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ላይ ለዘመናዊ ሲኒማ ፈጠራ እና እድገት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ለሚሰጠው "Jaeger-LeCoultre Glory to the Filmmaker" የተሰኘ ክቡር ሽልማት ባለቤት ሆኗል።
"[የፊልሙ ባለታሪክ] በዘመናችን ካሉ እጅግ ታዋቂ ኢራናውያን ደራሲያን አንዱ ነው። በስራዎቹ የሀገሩን ልብ እና ነፍስ መተረክ ችሏል። በፋርስ ቋንቋ ንጹህ እና ጠንካራ ድምጽ ያለው ይህ ደራሲ፤ በልብ ወለዶቹ እና በታሪኮቹ ውስጥ የህዝቡን ታሪክ መዝግቦ አስቀምጧል። ስለሆነም፣ በተለይም አሁን ካለው የዓለም እና የኢራን ሁኔታ አንጻር፣ የእሱን ህይወት እና ስራዎች መዝግቦ ማቅረብ (Document ማድረግ) ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው።"
***
ሀበሻ ቪው ቴክኖሎጂ እና መልቲሚዲያ
በሀበሻ ቪው፤ ለኢትዮጵያ ስነ-ጥበብ፣ ባህል እና ተሰጥኦ ትልቅ ቦታ እና ክብር አለን። ተልዕኳችንም ይህንን የባህል ሀብት ከዘመናዊ እና ከላቀ ቴክኖሎጂ ጋር በማዋሃድ ለክቡራን ደንበኞቻችን ልዩ እና ተመስጦን የሚፈጥር ልምድ ማቅረብ ነው።
በባህል እና በዘመናዊነት መካከል ድልድይ መሆን እንዳለብን እናምናለን፤ የፈጠራ ባለሙያዎቻችንን ድንቅ ተሰጥኦ ለዓለም ገበያ በማሳየት የኢትዮጵያን ስራዎች ለዓለም አቀፍ መድረክ ለማብቃት እንተጋለን።
እስካሁን ያደረግነው ጉዞ እጅግ አስደናቂ ነበር፤ ይህ ስኬትም ያለ እናንተ ያልተቋረጠ ድጋፍ ሊታሰብ አይችልም ነበር። አሻራችንን እያሰፋን እና እያደግን ስንሄድ፣ ለዋና እሴቶቻችን ጸንተን እንቆማለን።
እነዚህም፦ የኢትዮጵያን ባህል ማስተዋወቅ እና ማልማት፣ የሀገር ውስጥ ተሰጥኦን ማሳደግ፣ እንዲሁም የቅርሶቻችንን እና የባህላችንን ተደራሽነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ማጎልበት ናቸው።

ነፃነት ወርቅነህ እምሩ( 1974-2018)
ማስታወሻ፦ሐምሌ ወር ላይ 2017 ነፃነት ለተወዳጅ ሚድያ ደወለ፦
"....እዝራ። ታሪካችን እኮ መሰነድ አለበት።እኔም መረጃ እልካለሁ።" በማለት ነበር ነፃነት የስነዳ ሥራው አዎንታዊ እሳቤውን የገለፀው። እኛም መረጃ ማሰባሰብ ጀምረን ነበር። ነፂ ግን"... ደርሶኛል። አየዋለሁ እዝራችን ነበር የስንብት መልዕክቱ።
ዛሬ ጥር 8 2018 ዓ.ም የሰማነው ክፉ ዜና ግን ለመስማት ይከብዳል። ነፂ ነፍስህ በሰላም ትረፍ። እንደወደድከው ታሪክህን ሰንደናል።
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
ከእነዚህ ውስጥ የሚድያ ሰዎችና የቴአትር ባለሙያዎች ይገኙበታል። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ 50 በላይ የፊልምና የቴአትር ባለሙያዎች ፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን አመራሮች እና የሚድያ ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
በዚህ ፅሑፍ የሙያ ታሪኩ የሚሰነድለት ጠንካራ ባለሙያ ነፃነት ወርቅነህ ነው። ዕዝራ እጅጉ እና ሣራ አህመድ ታሪኩን አጠናክረውታል።
#ትውልድና ልጅነት
የኪነ ጥበብ ባለሙያ ነፃነት ወርቅነህ እምሩ የካቲት 10 1974 ዓ.ም ከአባቱ ከአቶ ወርቅነህ እምሩ እና ከእናቱ ከወይዘሮ ምናለሸዋ ይፍሩ በአዲስ አበባ ከተማ በፖሊስ ሆስፒታል ተወለደ።ለቤተሰቡ አራተኛ ልጅ ሲሆን ሶስት ወንድሞች እና አንድ እህት በነበረው ቤተሰብ ውስጥ በኡራኤል ሰፈር እንዳደገ ይነገራል።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በአስፋው ወሰን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማረ ሲሆን እስከ 7ኛ ክፍል ባለው የልጅነት እና የትምህርት ቤት ቆይታው ለኪነጥበብ የተለየ ፍቅር አልነበረውም። የ8ኛ ክፍል ተማሪ እያለ "የጉሊቷ እናቴ የሚል ቲያትር ላይ የሴት ገፀ-ባህሪይ ይዞ መተወኑ ይነገራል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ምሥራቅ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል።
#ወደኪነ -ጥበብ አለም የገባበት አጋጣሚ
የ16 አመት ልጅ ሳለ ከኡራኤል መርካቶ ድረስ በእግሩ እየተመላለሰ ዩኒቲ የቴአትር ክበብን እንደተቀላቀለ ቲያትር መስራት መጀመሩ ይነገራል። የዩኒቲ ክለብ መፍረስ ቀጣዩ የነፃነት መዳረሻ የሩሲያ ባህል ማዕከል ወይም ፑሽኪን አዳራሽ እንዲሆን አደረገው። በፑሽኪን ቆይታውም በግጥሞች በወጎች መሀል የሚተላለፉ የተመልካችን ቀልብ የሚይዙ የ30 ደቂቃ ድራማዎችን ሠርቷል።በፑሽኪን ቆይታው ፍሬሸ ማን የሚለውን ድርሰቱን በ40 ደቂቃ የሚያልቅ ድራማ አድርጎ ሠርቶት ነበር።በኃላም ቲያትሩን አሻሽሎ ከአዳነች ወ/ገብርኤል ጋር መስራቱ አይዘነጋመሰ። ነፃነት በአንድ በኩል ፍሬሽ ማንን ፑሽኪን እያሳየ" የመጨረሻ ሀጢያት" የሚል በቀበሌ አዳራሽ ውስጥ የተሰራ ቲያትርም አሳይቷል።
በፑሽኪን በነበረው ቆይታ ላይ አብረውት ከሰሩት ተዋናዮች መሀከል ኢሳያስ አስራት ስለነፃነት የትወና አቅም ይህን ብሏል።
"እኔ ስለ ነጺ እመሰክራለሁ።የሚሠራውን ገና ሲወጥነው ያውቀዋል።
ፑሽኪን (የሩሲያ ባህል ማዕከል) በነበርንበት ወቅት እኔም እርሱም ተውኔት እንጽፋለን፣እናዘጋጃለን፣እንተውናለን።ፉክክር ነበር በመሀላችን።
ነፂ ግን ይለያል። አድምቶ መሥራት እና በዚያው መጠንከር እና ግቡን መምታት ያውቅበታል" በማለት መስክሯል።
ነዋሪነቱን በካናዳ ያደረገው ገዛኸኝ መኮንን ሲናገር ፦ "...ለመጀመሪያ ጊዜ በፑሽኪን ማዕከል መድረክ በግጥም መሀል በሚያቀርባቸው አጫጭር ተውኔቶች ላይ ነበር extraordinary የሆነ ችሎታ እንዳለው ያስመሰከረው።
እኔ እና ወዳጄ ሚሊዮን አየለ በጋራ ጽፈን ባዘጋጀነው ፌስታል የተሰኘች የ 5 ደቂቃ ድራማ ላይ ካስት ስናደረገው ከሙናዬ መንበሩ ጋር እንዴት በልዩ ሁኔታ እንደተጫወተው አሁንም አይረሳኝም።
ከዚያ በኋላ በጣም በርካታ ፊልሞች ላይ በመተወን አቅሙን አሳይቷል " በማለት ምስክርነት ሰጥቷል።
#የነፃነት ኪነ ጥበባዊ አበርክቶዎች
በቲያትር ዘርፍ
ነፃነት ወርቅነህ "በይቅርታ ምሽት በማዘጋጃ ቲያትር ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በቲያትር ቤት ደረጃ የሰራው ሥራ ሲሆን በመቀጠልም በብሔራዊ ቲያትር "ካብ ለካብ" የሚባል ቲያትር ላይ "የትወና ብቃቱን አሳይቷል። የዳዊት እንዚራ፤ፍሬሽ ማን፤የጓሮ ጌታ ፤የብሩክታዊት ስጦታ የተባሉ ቲያትሮች የሰራ ሲሆን ፍሬሽ ማን የራሱ ድርሰት እና በህዝብ ዘንድም ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘበት ስራው ነው።
#በቴሌቪዥን ድራማ እና በሬዲዮ ድራማ
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ በነበረው ስንቅ ፕሮግራም ላይ ባለቤትነቱ የአለልኝ መኳንንት እና የጥላሁን ዘውገ ፕሮግራም ላይ በድርሰት ፤ በአዘጋጅነት ፤ በዳይሬክተርነት እንዲሁም በተዋናይነት ሠርቷል። ጥላሁን ዘውገ ስለ ነፃነት ሲመሰክር ነፃነት ከትወና ባሻገር የማዘጋጀት ችሎታም ስለነበረው ድራማዎችን እንዲያዘጋጅ ዕድል እንሰጠው ነበር ብሏል።
በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳር ቴሌቪዥን በሚተላለፈው "መስኮት በተሰኘ የአምስት ደቂቃ ድራማዎች ላይ በበርካታ ድርሰቶች ላይ የነፃነትን አሻራ ማግኘት ይቻላል።
በሬዲዮ ድራማዎች ላይ በድርሰት በኢትዮጵያ ሬዲዮ እንዲሁም በfm 97.1 ተሳትፏል።
#የፊልሙ አለም
የመጀመሪያ ፊልሙ "የማይደረስበት" የሚለው ሲሆን ኪሳራ ላይ የጣለው ፊልም ሲሆን ከዛ በኃላ FBI1,2,3፤ የአንቺው ሌባ 1,2፤ Mr x ፤ባለቀለም ህልሞች፤ስለማይዘነጋ ውለታ፤ዕድል 20 የተሰኙ ፊልሞችን የሠራ ሲሆን የFBI 1,2,3 ፊልም ደራሲ እሱ ሲሆን፤በባለቀለም ህልሞች ላይ በዳይሬክቲንግ እንዲሁም በMr X ፊልም ላይ በድርሰት ተሳትፏል።በህዝብ ዘንድ በባለቀለም ህልሞች ፤ በአንቺው ሌባ እንዲሁም በFBI ፊልሞችየተለየ አድናቆት እና ተወዳጅነት ሊያገኝ ችሏል።
#ሌሎች ሥራዎች
ነፃነት ደራሲ ፤ተዋናይ ፤ዳይሬክተር ብቻ አልነበረም። ጎበዝ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢም ጭምር እንጂ በተለይ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚተላለፈው የቤተሰብ ጨዋታ በየፕሮግራሙ አዳዲስ ቃና እየጨመረ ለዓመታት ፕሮግራሙ በህዝብ ልብ ውስጥ እንደተወደደ እንዲሁም ሳይሰለች እንዲታይ አስችሎታል።
ከቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነቱ በተጨማሪ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን እንዲሁም መድረኮች መልዕክታቸውን ሳያጡ በሳቅ እንዲታጀቡ አድርጎ ማቅረብም ላይም የሚደርስበት የለም። በአጠቃላይ ነፃነት የዘርፈ ብዙ ሙያ ባለቤት ነበር ማለት ያስችላል።
#ልዩ ሰብዕና
ነፃነት ወርቅነህ ሌሎች ሲደሰቱ ከማንም በላይ ይደሰታል። በበርካታ ችግሮች ቢያልፍም ሳቅ ከምንም በላይ መድኃኒት ነው በሚለው አስተሳሰቡ ለዓመታት ዘልቋል። አብረውት ለሚሠሩ የኪነ -ጥበብ ባለሙያዎች ልዩ ክብር ያለው ነፃነት ለሰዎች በመድረስ የሚያምን በሰዎች የደስታና የሀዘን ጊዜም ቀድሞ የሚገኝ መሆኑን የቅርቦቹ ይመሰክራሉ።
#የትዳር ህይወት
ነፃነት ወርቅነህ፣ ከንፁህ ዘር በላይ ጋር ትዳር የመሠረተ ሲሆን የሦስት ልጆች አባት ነው። ልጆቹም የ18፤15 እና የ9 አመት ዕድሜ ሲኖራቸው የመጀመሪያ ልጁ ኦራገን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ነፃ የትምህርት ዕድል አግኝቶ እየተማረ እንደሆነ፤ሁለተኛ ልጁ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መከታተል እንደጀመረች እንዲሁም የመጨረሻዋ ለፒያኖ ፍቅር እንዳለት ከወራት በፊት ገልፆ ነበር።
ነፃነት ወርቅነህ አርብ ጥር 8 2018 44 አመቱን ሊይዝ 30 ቀናት ሲቀረው ከዚህ አለም ድካም አርፏል።

8 months ago
ቴዎድሮስ ተሾመ ተመሰገነ
ዕዝራ እጅጉ(ተወዳጅ ሚድያ)
#ethiopia | 'የ1990ዎቹ የኢትዮጵያ ፊልም ማርሽ ቀያሪ' የሚል ስያሜ የተሰጠው የፊልም ባለሙያ ቴዎድሮስ ተሾመ ልዩ የምስጋና መርሀ ግብር ሐሙስ ታህሳስ 9 2018ዓ.ም ተደረገለት።
በጎልደን ቱሊፕ ሆቴል ምሽት ላይ በተደረገው የምስጋና መርሀ- ግብር የቴዎድሮስ ተሾመ ቤተሰቦች፣አድናቂዎች እና የቅርብ ጓደኞች የተገኙ ሲሆን በቴዲ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ዶክመንተሪም ለዕይታ ቀርቧል።
በዕለቱ ለቴዎድሮስ ተሾመ ወዳጆቹ ልዩ ስጦታ በማበርከት ያላቸውን ፍቅር የገለፁለት ሲሆን ሙያው ላይ ያለማቋረጥ በፅናት መቆሙንም በአድናቆት አይተውታል።
ይህ የምሥጋና የእራት ምሽት እንዲዘጋጅ የቴዲ የቅርብ ሰዎች ዮኒ ቬጋስ(ሀሣብ በማመንጨት) እና ሳምሶን ማሞ ቀዳሚውን ድርሻ የሚወስዱ ናቸው። ሌሎች የቴዎድሮስ አድናቂዎችም መርሀ ግብሩ የተሳካ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አበርክተዋል ።
ቴዎድሮስ ተሾመ በአገሩ ልጆች መመስገኑ የሃሴት ስሜት እንደሰጠው ተናግሮ ያለፈበት የኑሮ ውጣ ውረድ ብዙ እንዳስተማረው ገልጿል። ሰው ታግሶ የሚፈልገውን ለማግኘት ከፀና ከስኬት ማማ ላይ መድረሱ አይቀርም ሲልም ምክር ለግሷል።
በኪነ -ጥበቡ ዓለም አጠቃላይ 30 ዓመት የዘለቀው ቴዎድሮስ ተሾመ በ1989 ዓ.ም ከሠራው ከግልብጥ ፊልም ዓለም አንስቶ እስከ ስለ እናት ምድር ፊልም ድረስ ለሲኒማው ኢንዱስትሪ ትልቅ ዋጋ የከፈለ ባለሙያ መሆኑን የቅርብ ሰዎቹ መስክረዋል።
የፊልም ሰው ቴዎድሮስ ተሾመ ለእናት አገሩ ከፍተኛ ፍቅር እንዳለው የተናገረ ሲሆን በተለይም ለአገር መከላከያ ሠራዊቱ ልዩ አክብሮት የሚሰጥ መሆኑን አፅንዖት ሰጥቶ አስረድቷል ።
የፊልም ባለሙያው ቴዎድሮስ ተሾመ ታኅሳስ 29 ቀን ገና ሲመጣ 56ኛ ዓመቱን የሚያከብር ሲሆን ትውልዱም ጅማ ከተማ ነው።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በጅማ ከተማ ሄርማታ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል። የ16 ዓመት ልጅ ሳለም፥ ወጣቶች በግዳጅ የሚወሰዱበትን ብሔራዊ ውትድርና ሽሽት አየር ወለድን ተቀላቀለ። ነገር ግን አንድ ዓመት ሳይቆይ አምልጦ ወጣ። በኋላም ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ትምህርቱን ቀጥሎ ሽመልስ ሀብቴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቷል። ከዛም ተሻግሮ በአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ ትምህርቱን ማጠናቀቁን ቴዎድሮስ ለመዝገበ አእምሮ መፅሐፍ በሰጠው መረጃ ተናግሯል።
ቴዲ ሥራ የጀመረው በፎቶግራፍ ባለሞያነት መሆኑን የሚያስረዳ ሲሆን ይህም ለፊልም ጥበብ ፍቅር አሳድሮበታል።
ቴዲ ‘ግልብጥ ዓለም’ የተሰኘ የመጀመሪያ ፊልሙን ጽፎ፣ አዘጋጅቶና ፕሮድዩስ አድርጎ ለዕይታ ካበቃ በኃላ ደግሞ የተሻለ ሥራ ለማቅረብ ትጋት አሳየ።
ከኹለት ዓመታት በኋላ በ1990 ‘ሲኦል’ የተሰኘ ሁለተኛ ፊልሙን ሠራ። ይህም ሥራው የሚድሮክ ኢትዮጵያን ትኩረት መሳብ በመቻሉ፥ በኩባንያው የሙሉ ጊዜ የዘጋቢ ፊልም አዘጋጅ ሆኖ ተቀጠረ። በዛ መደበኛ ሥራውን እየሠራ ሳለ ነው ‘ቀዝቃዛ ወላፈን’ የተሰኘውን ፊልም ያዘጋጀው። ከዚህ በኋላም ሙሉ ጊዜውን ለፊልም ሙያ በመስጠት ‘ቀዝቃዛ ወላፈን’፣ ቀጥሎም ራሱ መሪ ተዋናይ ሆኖ የተሳተፈበትን ‘ፍቅር ሲፈርድ’ ፊልሞች ያዘጋጀው። “እንደተመኘሁት ስኬታማ አልሆነልኝም” የሚለው ’ቀይ ስህተት’ የተሰኘ ፊልሙን የሠራው ከዚህ በኋላ ነበር።
አላበቃም፥ ስኬታማ ዕይታና ውጤት ያመጣለት ‘ዐባይ ወይስ ቬጋስ’ን ለዕይታ አበቃ። በኋላም ‘ሦስት ማዕዘን’ የተሰኘ ፊልም በኹለት ክፍሎች ለዕይታ አቀረበ።
ቴዎድሮስ በተለይ በ’ሦስት ማዕዘን’ ፊልም ከሀገር ውጭ በርከት ያሉ ሽልማቶችን አግኝቷል። በሀገር ውስጥ ደግሞ' ዝምታዬ' በተሰኘው ፊልም በ2017ቱ የጉማ ሽልማት በምርጥ ረዳት ተዋናይነት ተሸልሟል።
የኢትዮጵያ የኦድዮ ቪዥዋል ፕሮድዮሰሮች ማኅበር ፕሬዝዳንት ሆኖ ያገለገለው ቴዎድሮስ፥ በ90ዎቹ ከፍቶ ይሠራበት ከነበረው ከቴዲ ስቱድዮ ጀምሮ፣ አሁን ላይ ሊሠራ ያዘጋጀው ውብ አዲስ ተከታታይ ፊልም ድረስ ለሙያው ጊዜውን እና ዕውቀቱ መሰዋት የቻለ ነው።
በሀገር ፍቅርና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ያተኮረው የቴዎድሮስ ተሾመ"ስለ እናት ምድር" ፊልም የአፍሪካ የፊልም አካዳሚ ሽልማትን ለማግኘትም ችሏል።
ትኩረቱን በሀገር ፍቅርና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረገው እና በዳይሬክተር ቴዎድሮስ ተሾመ የተዘጋጀው "ስለ እናት ምድር" የተሰኘው ፊልም የዕይታ ጥበባት ውጤቶች (Visual Effects) ዘርፍ ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
ዛሬ በተደረገው የቴዎድሮስ የምሥጋና መርሀ ግብር ላይ እንደተነገረው ይህ ባለሙያ የአገሩን ስም በአለምአቀፍ መድረክ ላይ ያስጠራ በመሆኑ በመንግሥት ደረጃ ዕውቅና ሊሰጠው ይገባል።
በዕለቱ፣ ለዕይታ የበቃው በቢኒ ምዕራፍ የተዘጋጀው ዶክመንተሪ ላይ ባለሙያዎች እንዳሉት ቴዎድሮስ ተሾመ ለሰዎች ቅን፣ የሚያስብ፣ ህልሙን ለማሳካት ሌት ተቀን የሚለፋ፣ በተለይ የፊልሙ ኢንዱስትሪ ፊታውራሪ ሊባል እንደሚገባው በሙሉ አንደበታቸው መስክረዋል።

የክብር የእራት ግብዣ
* "ስለ እናት ምድር" ፊልም አህጉራዊ ሽልማት
#ethiopia | 21ኛው የአፍሪካ የፊልም አካዳሚ ሽልማት (AMAA 2025) በናይጄሪያ ሌጎስ ተካሄዷል።
በሀገር ፍቅርና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ያተኮረው "ስለ እናት ምድር" ፊልም የአፍሪካ የፊልም አካዳሚ ሽልማትን አግኝቷል።
ትኩረቱን በሀገር ፍቅርና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረገው እና በዳይሬክተር ቴዎድሮስ ተሾመ የተዘጋጀው "ስለ እናት ምድር" የተሰኘው ፊልም የዕይታ ጥበባት ውጤቶች (Visual Effects) ዘርፍ አሸንፏል።
ሽልማቱን የፊልሙ ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ተሾመ ተቀብሏል።
በአርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ በተዘጋጀው “ስለ እናት ምድር” ፊልም ላይ 30ሺ ሰዎች ተሳትፈውበታል።
መድረኩን የመራችው ታዋቂዋ ጋዜጠኛና አዘጋጅ ቪምባይ ሙቲንሂሪ እኛ በቀኝ ካልተገዛችው ኢትዮጵያ የምንማረው ብዙ ጉዳይ አለን ብላለች።
ኢትዮጵያውን በራሳቸው የውስጥ አቅም የገነቡት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የራሳቸውን የሃይል ፍላጎት ማሟላት ችለዋል ያለችው ቪምባይ የዚህ ዓይነቱ ተሞክሮ ለናይጄሪያ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሳ እንኳን ደስ ያላችሁ ብላለች፡፡
“ስለ እናት ምድር” ሽልማት ከተሰጠባቸው 26 ዘርፎች በስምንቱ እጩ ሆኖ ቀርቦ ነበር።
ይህንን አስመልክቶ ዛሬ በጎልደን ቱሊፕ ( ቦሌ መድኃኔዓለም) ከምሽቱ 12:00 ሰዓት የክብር የእራት ፕሮግራም ተዘጋጅቷል።
የኪነጥበብ ቤተሰቦች በክብር ተጋብዛችኋል
AFRICA MOVIE ACADEMY AWARDS 2025
AAMA 2025 Award for Best Visual Effect
Winner:
Theodros Teshome
WWA ACHIEVEME VISLIAL EFFECH
You're Invited to a Special Celebration
The acclaimed Ethiopian filmmaker, for his outstanding achievement in winning the AAMA 2025 Award for Best Visual Effect This occasion also celebrates his exceptional contribution to the Ethiopian film industry, where his vision, dedication, and groundbreaking works have played a significant role in shaping and elevating Ethiopian cinema on the global stage.
Friends, celebrities, and distinguished guests will gather to mark this milestone, and your presence will be greatly appreciated.
December 18 at 6:00 PM
Golden Tulip Hotel, Bole Medhanialem

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 'ውብ አዲስ' የተሰኘ ተከታታይ ድራማ በቅርቡ ሊጀምር መሆኑ ተገለጸ
#ethiopia | አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤኤምኤን) በተለይም የከተማ እና ከተሜነትን በሚያሳዩ ዝግጅቶቹ የሚታወቅ ሲሆን አሁን ደግሞ በአይነቱ ልዩ የሆነውን "ውብ አዲስ" ተከታታይ የቤተሰብ ድራማ ሊያቀርብ መሆኑን አስታውቋል።
ኤኤምኤን ይህንን ፕሮጀክት ከቴዲ ስቱዲዮ (ቴዎድሮስ ተሾመ) ጋር በመተባበር ለማቅረብ የፊርማ ሥነ ሥርዓቱን በዛሬው እለት ፒያሳ በሚገኘው በአራዳ ፓርክ አካሂዷል።
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ እና የፊልሙ ጸሐፊና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ተሾመ ስምምነቱን የፈረሙ ሲሆን በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ ተገኝተዋል።
'ውብ አዲስ' የፍቅር ታሪክን የያዘ በከፍተኛ ልብ ሰቀላ እና ሙሉ ለሙሉ በድርጊት የተሞላ ተከታታይ ድራማ ነው።
በሁለት ትይዩ ታሪክ የሚተረከው ይህ ድራማ 4 ሲዝንና 52 ኤፒሶዶች ያሉት መሆኑ በመግለጫው ተገልጿል።
90 በመቶ ቀረጻው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሲሆን ቀሪው 10 በመቶ ደግሞ በሞሮኮ እና ጋና የሚከናወን ሲሆን የሁለቱ ሀገራት ባለሙያዎችም በድራማው ይሳተፋሉ ተብሏል።
'ውብ አዲስ' ድራማ በቅድሚያ የትወና ታለንት ውድድር በማድረግ ወጣት ተዋንያንን ከአንጋፋዎቹ ጋር በማዋሀድ የሚሰራ መሆኑ ይዘቱን ለየት ያደርገዋል።
ለጀማሪ ተዋንያን እድል ለመስጠት የአክቲንግ ሥልጠና እና ውድድር ይካሄዳል ተብሏል።
በስልጠናውና በውድድሩ የሚሳተፉ ጀማሪ ተዋንያን በ50% የሕዝብ ድምጽ እና በ50% የባለሙያዎች ድምጽ በሚሰጥ ውጤት ተመርጠው ለቀጣይ ሦስት ወራት በቀጥታ ስርጭት ይቀርባሉ።
በ12 ክፍሎች ተከፋፍሎ በሚከናወነው በዚህ ውድድር አሸናፊ ለሚሆኑ ጀማሪ ተዋንያን የአንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚሰጥ ታውቋል።
በድራማው ላይ አንጋፋዎቹ ተዋንያን ተስፋዬ ሲማ ሰለሞን ቦጋለ እና ታምሩ ብርሃኑ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከተመሰረተ ሃያ ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በሰባት ቋንቋዎች በስርጭት ላይ ይገኛል።

"ውብ አዲስ" ተከታታይ ድራማ ለተዋንያን አንድ ሚሊዮን ብር ሊሸልም ነው።
#fastmereja I በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 'ዉብ አዲስ' የተሰኘ በአይነቱ ለየት ያለ ተከታታይ ድራማ በደራሲ ተዋናይና አዘጋጅ ቴዎድሮስ ተሾመ ተፅፎ እና ተዘጋጅቶ በቅርቡ እንደሚጀምር በዛሬዉ እለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
በቅርቡ መታየት የሚጀምረው ውብ አዲስ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ለሀያ አመታት ያህል ሲታሰብ የቆየ እንደሆነ እና የድራማዉ ይዘት የፍቅር ታሪክ ያለው ሲሆን ልብ አንጠልጣይ እንደሆነም ተነግሯል።
የድራማው ቀረፃ 9ዐ በመቶ ከቤት ውጭ እንደሆነና በተመሳሳይም 90 በመቶ ቀረጻው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሲሆን ቀሪውን 1ዐ በመቶ ከአዲስ አበባ ውጭ በሞሮኮ እና ጋና እንደሚደረግ ተነግሯል።
በተመሳሳይ የሁለቱ ሀገራት የጥበብ ባለሙያዎች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት እንደሚሳተፉም ነዉ የተገለፀዉ።
በተጨማሪም የቴሌቭዥን ቀረጻው ከመከናወኑ በፊት ለጀማሪ ተዋንያን እድል ለመስጠት የአክቲንግ ስልጠናና ውድድር ይካሄዳል ተብሏል።
በስልጠናው እና በውድድሩ የሚሳተፉ ጀማሪ ተዋንያንም 5ዐ% በህዝብ ድምጽ እንዲሁም 50% በባለሙያዎች ድምጽ በሚሰጥ ውጤት መሰረት አሸናፊዎች ይለያሉ። ይህም በቀጥታ ስርጭት ለቀጣይ ሶስት ወራት የሚከናወን እንደሆነ እና አሸናፊ ለሚሆኑት አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ለእያንዳንዳቸዉ የአንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት ይሰጣል ተብሏል።
ውድድሩን ከ18-50 የእድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ መመዝገብ እና መወዳደር እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን ዉድድሩ በ12 ክፍሎች ተከፋፍሎ እንደሚከናወን ተገልጿል።
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ እንደገለፁት ይህ የሀገር ውስጥ እና የውጭ የዘርፉ ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ተከታታይ ድራማ የተደበቁ ተሰጥኦዎች እንዲታዩ በእጅጉ ይረዳል ሲሉ ገልፀዋል።
በተጨማሪም የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ እና የፊልሙ ጸሐፊና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ተሾመ አብሮ ለመስራት የሚያስችለዉን የፊርማ ሥነ ሥርዓቱን አከናዉነዋል።

ሹም ሽረት
#ethiopia | "ሹም ሽረት" ፊልም ከነገ ጀምሮ በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች መታየት ይጀምራል።
2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የወጣበት የኮሜዲ ድራማ ይዘት ያለው "ሹም ሽረት" የተባለው ፊልም ከነገ ጀምሮ በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች መታየት እንደሚጀምር የፊልሙ አዘጋጆች በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
በመግለጫው እንደተገለጸው ፊልሙ በዩሊያን ፊልም ፕሮዳክሽንና ከክብሪት ፒክቸርስ ጋር በጥምረት የተሰራ ነው።
ፊልሙ በደራሲና ፕሮዲዩሰር ዩሊያን ተ/ማርያም ተደርሶ የቀረበ ሲሆን ዳይሬክት ያደረገውም እራሱ ዩሊያን ተ/ማርያም እንደሆነ ተነግሯል።
በፊልሙ ላይ ታዋቂና አዳዲስ ተዋንያን የተሳተፉበት ሲሆን አድማሱ ከበደ ፣ ፍቅርተ ደሳለኝ ፣ ማስተዋል ወንደሰን ፣ ዩልያን ተክለማርያም ፣ ትዕግስት ከበደ ፣ አብይ ዲንሳ እና ሌሎች ወጣት ተዋንያን ተሳትፈውበታል ።
ሹም ሽረት ፊልም 2.5 ሚሊየን ብር እንደወጣበትና አንድ አመት እንደፈጀበት ተገልጿል
በመግለጫው እንደተነሳው ዩሊያን ፊልም ፕሮዳክሽን የተለያየ የዶክመንተሪ ፣ የሚዲያ እና የፊልም ስራዎች በመስራት ይታወቃል።

🎯🎯 ፀሀይ 🎯🎯 አዲስ ፊልም በኤልያና ኢንተርቴመንት ተዘጋጅቶ የቀረበው ፊልማችን ሕዳር 26 (አርብ )( ኤግዚቢሽን ማዕከል ) ጎን በሚገኘው (ፊላሚንጎ) አዲሱ ሕፃናትና ወጣቶች ቲአትር አዳራሽ ከ ቀኑ 11:30 ጀምሮ በቀይ ምንጣፍ ስነ-ስርዓት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ሚዲያዎች እና የኪነ - ጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።
ሕዳር 26 ፣27፣28 በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች በታላቅ ድምቀት ይመረቃ።
ተዋንያን እና የፊልሙ ክሩዎች
maramawit_abat
mulualem.getachew
danieltegegn
mahletfekadu_mahi
Elias_fantahun
tes_lomi
_frita_12
emanuel_jp14
Executive producer eliana_entertement
Cinematography fuad_mustefa1
Production manager kiy_aking
Light lamsegn_aleka
Gaffer Selomon_bayu
Continuity & Costume lieltitsegay21
Makeup _frita_12
Sound kingoentertainment
Editor yoseph_balcha
Final Editor & Colorist yoftahe_mesfin
Poster design jemal_kassahun_official
Writer tesfaye_ababu
Director ameha_duguma_tsehaye
Line producer tommy_.match
Line producer dereje_sitotaw
Screen play alemseged12asefa mulualem.getachew ameha_duguma_tsehaye
ስፖንሰሮች እና አጋር ድርጅቶች
goferiehairtransplantation
lakipay
lakiremit
ripsime_furniture
yes_multimedia_
tedlaambulance
shegersuit
classic_photo_studios
habesha_decor_sami2

🎯🎯 ፀሐይ 🎯🎯 አዲስ ፊልም በኤልያና ኢንተርቴመንት
ሕዳር 26 (አርብ )( ኤግዚቢሽን ማዕከል ) ጎን በሚገኘው (ፊላሚንጎ) አዲሱ ሕፃናትና ወጣቶች ቲአትር አዳራሽ ከ ቀኑ 11:30 ጀምሮ በቀይ ምንጣፍ ስነ-ስርዓት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ሚዲያዎች እና የኪነ - ጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።

9 months ago
ከኬ-ፖፕ የአጋንንት አዳኞች ፊልም ምን እንማራለን?
አንዳንድ ጊዜ በተለይ የፖለቲካ ጉዳዮች ሲሆኑ፣ ዓለም የተሰራችው ከመልካም እና ከክፉ ብቻ ነው ብሎ ማመን ያጓጓል፤ በመሠረቱ ከመላእክት ወገን የሆኑ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ፣ አጋንንትም እንዳሉ እናምናለን።
እኛ መላእክት ነን፣ ሌሎች ደግሞ ልናድናቸውና ከኅብረተሰቡ ልናስወግዳቸው የሚገባን አጋንንት ናቸው ብለን ልናስብ እንችላለን። እንዲህ ዓይነት ስሜት ውስጥ ስንሆን፣ መጥፎ የሆኑ ሰዎች እና ጥሩ አጋንንት — ወይም ግማሽ ሰው ግማሽ አጋንንት የሆኑ ፍጥረታት ሊኖሩ እንደሚችሉ እምብዛም አናስብም።
"KPop Demon Hunters" እንዲህ ያሉትን ችግሮች በጥልቀት ይመለከታል።
ይህ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን ያተረፈው የኔትፍሊክስ አኒሜሽን ቅዠታዊ ፊልም ላይ፣ ሩሚ ፣ ሚራ እና ዞዪ ‘ሃንትሪክስ’ የተሰኘውን የኬ-ፖፕ የሴቶች ቡድን የሚመሰርቱ የአጋንንት አዳኞች ሦስቱ ናቸው።
ተልዕኳቸው አጋንንት ወደዚህ ዓለም እንዳይሻገሩ በዘፈኖቻቸው ‘ሆንሙን’ን መዝጋት ነው። ተቀናቃኛቸው ‘ሳጃ ቦይስ’ ደግሞ ጁኖን እና በሰው ተመስለው የመጡ ሌሎች አጋንንትን ያካትታሉ። በእነርሱ መካከል በሚካሄደው ጦርነት፣ የጦር መሣሪያዎቻቸው ጦር ወይም ሽጉጥ ሳይሆን ዘፈኖች ናቸው።
የሃንትሪክስ መሪ የሆነችው ሩሚ፣ አባቷ አጋንንት ስለነበር በመላ ሰውነቷ ላይ እንግዳ የሆኑ ቅርጾች አሏት። በዚህ ምልክት ታፍራለች እናም ሚስጥር አድርጋ ትይዘዋለች። ዋና ተቀናቃኟ የሆነው የሳጃ ቦይስ አባል ጁኖም፣ እሱም ግማሽ ሰው ግማሽ አጋንንት በመሆኑ ተመሳሳይ ቅርጾች አሉት።
በሰውነታቸው ላይ ያሉት እነዚህ የአጋንንት ቅርጾች ፈጽሞ ሊያመልጡት የማይችሉትን ውርደት ያለማቋረጥ የሚያስታውሷቸው ናቸው።
ልምምድ እያደረገች ሳለ፣ ሩሚ በድንገት ድምጿን ታጣለች። “መላ ሕይወቴን የሆንኩትን ይህን ምስጢር፣ ይህን ውርደት እየደበቅኩ አሳለፍኩ። እናም ይህን ውርደት በደበቅኩት መጠን፣ የዓላማዬ መሠረት የሆነውን አንድ ነገር (ድምፄን) እስከሚያጠፋ ድረስ እያደገ፣ እያደገ ሄደ” ስትል ትመሰክራለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሩሚና ጁኖ እርስ በርሳቸው መሳሳብ ይጀምራሉ።
በጁኖ ድጋፍና ምክር ምስጋና ይግባውና ሩሚ በራስ መተማመንን እና ድምጿን መልሳ ታገኛለች።
ሩሚ ከጁኖ ጋር በመሆን እንዲህ በማለት ትዘፍናለች፡- “አሁን መለወጥ እንደምንችል አውቃለሁ/ አንተም ጨለማ ጎን አለህ/ ሁለታችንም ከምንሸሸው ነገር ጋር ለመታገል ብንሞክርስ?/ ካልገጠምነው ልንፈታው አንችልም/ እሱን ለማምለጥ መንገድ ብናገኝስ?/ ነጻ፣ ነጻ መሆን እንችላለን!/ ያለፈው ክብደቱ እስኪቀንስ ድረስ ያለፈ ይሁን።”
ውብ የሆነውን የሁለቱን የፍቅር ዘፈን ስሰማ፣ ከሩሚ እና ከጁኖ በተቃራኒ፣ ዛሬ ያሉ አንዳንድ ፖለቲከኞቻችን ከጨለማው ያለፈው ጫና ለመላቀቅ እንዴት እንደማይሞክሩ፣ ይልቁንም ተስፋ በሌለው ሰንሰለት እንደታሰሩብት አስገረመኝ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ለችግራቸው መውቀሻ እና የበቀል እርምጃቸውን ለማጽደቅ ፍየል የሚሆኑ አጋንንትን ይፈጥራሉ።
“KPop Demon Hunters” የሚያስተምረን ከጠላቶቻችን ወይም ከፖለቲካ ተቀናቃኞቻችን ጋር መታረቅ እርስ በርስ ከመጋፈጥ ይልቅ የተሻለ ውጤት እንደሚያስገኝ ነው።
ይህንን ብሩህ ተስፋ የተላበሰ መልእክት የሚያጠናክሩ ብዙ ምስሎች በፊልሙ ውስጥ አሉ። ለሃንትሪክስ እና ለሳጃ ቦይስ ደጋፊዎች በተደረገ የአውቶግራፍ ፊርማ ሥነ ሥርዓት ወቅት፣ ደጋፊዎቻቸው መጀመሪያ ላይ ተከፋፍለው ለየብቻ ተሰልፈው ነበር። ነገር ግን ሁለቱ የኬ-ፖፕ ቡድኖች ጎን ለጎን ለመቀመጥ ሲወስኑ ደጋፊዎቻቸው በአንድ ቦታ ተሰብስበው ዝግጅቱን የተሳካና የተስማማ አድርጎታል።
ፊልሙ በሦስት ቁልፍ ጭብጦች ላይ ያተኩራል፡-
1. ዓለም በቀላሉ ከመልካም እና ከክፉ ወይም ከመላእክት እና ከአጋንንት የተሰራች አይደለችም።
2. ልዩነቶችን አትፈርባቸው።
3. ቅልቅል መሆን (Hybridity) ድክመት ሳይሆን ጥንካሬ ነው። ይሁን እንጂ ፊልሙ ተመልካቾችን በእጅጉ የሚያነቃቁ ውስብስብ፣ አስደናቂ ጭብጦች እንዳሉት የጠቀሱ ጥቂቶች ናቸው። ስለ ፊልሙ ትልቅ ስኬት እና ከፍተኛ ተወዳጅነት ብቻ ያወራሉ። የፊልሙ አስደናቂ ስኬት የማይካድ ነው፣ ይህም በጠንካራ ሁኔታ ሁላችንንም በሚስቡት በእነዚያ አሳማኝ ጭብጦች ውስጥ ስር የሰደደ ነው።
ፊልሙ እንደሚያሳየን በሰው እና በአጋንንት መካከል ያለው መስመር ቀጭን ነው። በኅብረተሰባችን ውስጥ፣ የሁለትዮሽ ተቃርኖ (either/or) ከሚያመጣው ክፍፍል ነጻ የሆኑ፣ መሀል ላይ ያሉ ሰዎችም አሉ። እነሱም እጅግ የራቁትን ተቃራኒዎች መተቸትም ሆነ መቀበል ይችላሉ። ድንበሮችን ማለፍ እና ከተለያዩ ባህሎች እና የተለያዩ ሰዎች ጋር መቀላቀል የሚችሉ መንፈሳዊ ቅይጥ ፍጥረታት አሉ።
በፊልሙ ውስጥ፣ የሁለቱ የሙዚቃ ቡድኖች መሪዎች፣ ሩሚ እና ጁኖ፣ ግማሽ ሰው እና ግማሽ አጋንንት ናቸው። እነሱም ቅይጥ መሆን እና ልዩነት ጥቅሞች እንጂ ጉዳቶች አለመሆናቸውን ያሳያሉ። በተመሳሳይ፣ ኬ-ፖፕም ቢሆን በዋነኛነት ለዓለም ይግባኝ ማለት የቻለው የኮሪያን ውዝዋዜ እና የምዕራባውያን ዓይነት ዘፈንን በብልሃት በማጣመር የተፈጠረ ቅይጥ የባህል አካል በመሆኑ ነው።
“KPop Demon Hunters” ሌሎችን እንደ አጋንንት የምንቃወምበት፣ የባህልና የዘር ልዩነቶችን የምናጣጥልበት፣ እንዲሁም ቅይጥ መሆንን እንደ ስህተት የምንቆጥርበትን የኅብረተሰባችንን ጥልቅ ግንዛቤ የሚሰጥ እና ኃይለኛ ትችትም ነው። ፊልሙ ጥላቻን እና በቀልን ወደ ጎን በመተው፣ ዓለምን ለመኖር የተሻለ ቦታ ለማድረግ ከእኛ የተለዩትን እንድንቀበል እና እገዛ የሚያስፈልጋቸውን ሌሎች እንድንጠብቅ ይጠቁማል።
“KPop Demon Hunters”ን ስንመለከት፣ እራሳችንን እንደ መላእክት፣ ሌሎችን ደግሞ ልናድናቸውና ልናጠፋቸው የሚገቡ አጋንንት እንደሆኑ አድርገን በማሰብ ጻድቅ መሆናችንን ከልክ በላይ ካመን፣ ሳናስበውና በመጨረሻ እኛ ራሳችን አጋንንት መሆን እንደምንችል እንገነዘባለን። ይህ ማራኪ ፊልም ኬ-ፖፕ እርቅን የሚያመለክቱ መልእክቶችን ማሰራጨት እና ስነ-ልቦናዊ ቁስላችንን በዘፈኖች መፈወስ እንደሚችል ይጠቁማል።
ይህ ፅሁፍ የተፃፈው በኪም ሶንግ-ኮን ሲሆን በሴኡል ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛ ፕሮፌሰር ናቸው።

10 months ago
የኢትዮጵያን ሲኒማ ያስመሰገነው
ሲኒማቶግራፈር እና ፕሮዲዪሰር ታምራት መኮንን
(ያሬድ ሹመቴ)
~ ኢትዮጵያዊው "የደሴቷ ጠባቂ" ፊልም የአፍሪካ ብቸኛው እጩ እና አሸናፊ ሆኗል!
~ እንዴት አንድ ፊልም ከ11 ዓመታት በላይ ልፋት ሊጠይቅ ይችላል?
#ethiopia | ታምራት መኮንን ተወልዶ ያደገው በባህርዳር ከተማ ነው። ከልጅነቱ ጀምሮ ለሲኒማ ከነበረው ጥልቅ ፍቅር የተነሳ በፎቶግራፍ አንሺነት የምስል ነገራ ሙያን ተቀላቀለ።
አዲስ አበባ በገባ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ስመ ጥር ሲኒማቶግራፈር እና ዳይሬክተር ኦፎ ፎቶግራፊ በመኾን ከፍተኛ ተወዳጅነትን ማትረፍ በቻሉ ፊልሞች ውስጥ እጁን ማሳረፍ ችሏል።
ለ አብነት ያህልም "አሸንጌ" ፤ "ቀይ ስህተት" እና የበርካታ ተመልካቾችን ቀልብ ለዓመታት መግዛት የቻለው "ስርየት" የተሰኘው ፊልም ከስራዎቹ መሐል ተጠቃሽ ናቸው።
ታምራት መኮንን አሜሪን አገር ኒውዮርክ ከተማ በሚገኘው ኒውዮርክ ፊልም አካዳሚ የሲኒማቶግራፈርነት ትምህርቱን ተከታትሎ በከፍተኛ ውጤት ለመመረቅ በቅቷል።
ለትምህርት በሄደበት አጋጣሚም ከእውቅ ፕሮዲዪሰሮች ጋር ተገናኝቶ እዚያው አሜሪካ ውስጥ ሲኒማቶግራፈር በመኾን ከተወሰኑ ኢንዲፔንደንት ፊልም ሰሪዎች ጋር እና Styles P ከተባለ ከተባለ አሜሪካዊ ዕውቅ ራፐር ጋር የሙዚቃ ቪዲዮ እስከ መስራት ደርሷል።
ታምራት በዓለም አቀፍ መድረክ አገሩን የሚያስጠራ ፊልም ለመስራት አቅዶ ወደ አገሩ በተመለሰ ማግስት የቤተሰቦቹን እና የቅርብ ወዳጆቹን አቅም አሰባስቦ "የደሴቷ ጠባቂ" የተሰኘ ፊልም ፕሮዲዪስ ለማድረግ ተነሳ።
ከ11 ዓመታት በፊት በአገር ውስጥ አቅም ከዚህ ቀደም ባልተደፈረ መልኩ በ5k የጥራት ደረጃ ቀረጻ ለማካሄድ መሳሪያዎችን እና ሙያተኞችን ማሰባሰብ ጀመረ።
የቅርብ ወዳጆቹ ዝነኛዋ ተዋናይት ረቂቅ ተሾመ እና ዝነኛው የፊልም ዳይሬክተር ሰውመኾን ይስማው "የደሴቷ ጠባቂ" የተሰኘውን ፊልም ወጥ ድርሰት ጻፉ። እውቁ አርቲስት ተስፋዬ ወንድማገኝ በፕሮዳክሽን ዲዛይነርነት ቡድኑን ተቀላቀለ። በሰውመኾን ይስማው የዝግጅት መሪነት ታምራትን የተከተሉ ሙያተኞች በጥቂት በጀት ግዙፍ ህልም የያዘውን ፊልም ለማምረት ወደ ባህርዳር አቀኑ።
በደምስ አያሌም ተዋንያን መልማይነት፤ አንተነህ አስረስ ፣ ሚካኤል ሚልዮን ፣ ፍቅረየሱስ ዘውዴ ፣ ሃና ፀጋው ፣ ፍሬሕይወት ገረመው ፣ አቢቹ እና ሌሎችም በርካታ ተወዳጅ እና እውቅ ተዋንያን በታምራት መኮንን ሲኒማቶግራፈርነት እና ፕሮዲዩሰርነት "የደሴቷ ጠባቂ" ፊልም ለመስራት ከዛሬ 11 ዓመት በፊት የባህርዳር ከተማን፣ የዘጌ ደሴትን እና ሰከላን ቤታቸው አድርገው ለወራት ከረሙ።
መቼቱን በአብዮቱ ዘመን ያደረገው "የደሴቷ ጠባቂ" ፊልም በከፍተኛ የጥራት ደረጃ እና ጥበባዊ አቅም ከወራት ትግል በኋላ ቀረጻው ቢጠናቀቅም፤ ሙሉ ፊልሙን በታለመው አቅም አጠናቆ ወደ ተመልካች ለማድረስ ግን ለፍጻሜ የሚያበቃውን በጀት ማግኘት የማይታሰብ ሆነ። ቀሪ የፖስት ፕሮዳክሽን ስራዎችን ከአገር ውጪ ለመጨረስ የሚጠይቀው የበጀት መጠን በአንጻራዊነት በአገር ውስጥ አንድ ፊልም ሰርቶ ለመጨረስ የሚያስፈልግውን ያህል ነበር።
የበጀት ምንጮችን ሲያፈላልግ የቆየው ፕሮዲውሰሩ ታምራት መኮንን፤ ለጊዜውም ቢሆን መፍትሄ ሆኖ ያገኘው በአገር ውስጥ የሚገኙ የንግድ ተቋማትን ማስታወቂያዎች በመስራት ከእነሱ የሚያገኘውን ክፍያ ስራው ላይ ማዋል ነበር።
በዚህም ሰበብ የሃበሻ ቢራ፣ የአዋሽ እና ዳሽን ባንክ፣ የፔፕሲ፣ የኩል ውሃ፣ የአንበሳ ጫማ እና የድል ቀለምን ማስታወቂያዎች ሰርቷል። ታምራት ከእነዚህ ተቋማት ያገኘውን ክፍያ ወደ ሌላ ዘርፍ ከማዋል ይልቅ የፊልሙን ወጪዎች እየደጎመ ለዓመታት መታገልን መረጠ።
በዚህ መሐል ጀርመን አገር ሃምቡርግ ከተማ ውስጥ የሚገኝ በጅምር ላይ ያሉ ፊልሞችን በፌስቲቫሉ ላይ ለሙያተኞች አቅርቦ አሸናፊ ለሚሆን ፊልም የፍጻሜ በጀት ግራንት የሚያደርግ ፌስቲቫል የሚካሄድ መኾኑ ከአንድ ባለሙያ ሰማ።
ይህን ጊዜ ታምራት ተስፈኛ በመኾን ፊልሙን ፌስቲቫሉ ላይ ለማቅረብ የሚያስችል ዝግጅት አድርጎ ቅጂውን እንደያዘ ያልጠበቀውን መርዶ ሰማ። ፊልሙን የማስገቢያ ጊዜ ከአንድ ቀን በፊት አልፎበት ነበር።
በዚህ ጊዜ ይህንን ፌስቲቫል የጠቆመው የ"ልጄስ" ፊልም ደራሲ እና ዳይሬክተር ሰማኝጌታ አይችሉህም የደረሰለት።
ሰማኝጌታ በግሉ ባደረገው ንግግር የፌስቲቫሉን አዘጋጆች ቀኑ ያለፈበት ቢሆን እንኳ የምስሉን ይዘት ተመልክተው እንዲወስኑ አግባባቸው። ፈቃዳቸውንም ሰጡ። የፊልሙ ቅንጭብ ተልኮላቸውም ዐዩት። በፌስቲቫሉ ላይ እንዲቀርብም በይፋ ወሰኑ።
ታምራት መኮንን ለ11 ዓመታት ያህል የታገለበትን ፊልም ይዞ ወደ ሃምቡርግ አቀና።
ቅድመ ልየታውን አልፈው ከመላው ዓለም ከተሰባሰቡ 28 አገራት ጋር "የደሴቷ ጠባቂ" አፍሪካን የወከለ ብቸኛ የኢትዮጵያ ፊልም ሆኖ ቀረበ።
"ሰኞ ዕለት የሌሎች አገራት ሙያተኞች ፊልማቸውን እያቀረቡ በዳኞቹ ፊት ቆመው ፒች (ገለጻዊ ሙግት) ሲያደርጉ የምገባበት ጠፋኝ..." ይላል ታምራት የገጠመውን ጭንቀት ሲያስረዳ።
"... ከኖርዌይ፣ ከብራዚል፣ ከአሜሪካ፣ ከፈረንሳይ፣ ከፔሩ፣ ከግሪክ እና ከሌሎች መሰል አገራት ከፍተኛ ጥበባዊ ደረጃ ያላቸው ፊልሞቻቸውን በዳኞች ፊት እያቀረቡ የእያንዳንዱ አገራት የባህል ሚንስቴር እና የፊልም ፈንድ አድራጊ ተቋማት በስራዎቻቸው እምነት አድሮባቸው ስላደረጉላቸው በጀት ድጋፍ በኩራት ሲናገሩ፦ እኔ ምን መናገር እንዳለብኝ ግራ በመጋባት ፈዝዤ ቀረሁ...
... በዓለም አቀፍ መድረክ የሚቀርቡ ፊልሞች ከፊልም ሰሪው በላይ የሚወክሉት አገራቸውን በመኾኑ 'አገሬ አልወከለችኝም። ያገኘሁትም ምንም ድጋፍ የለም' ብሎ መናገር የሚያመጣው ትርጉሙ ምን እንደሆነ ግራ አጋባኝ...
... በማግስቱ ማክሰኞ ፊልሜን አቅርቤ ከዳኞች የሚቀርቡልኝን ጥያቄዎች ለመመለስ መድረኩ ላይ ስቆም ስለምናገረውን ነገር እርግጠኛ አልነበርኩም። ሆኖም ሃቁን ተናገርኩ። ፊልሙን የሰራሁት በቤተሰቦቼ መጠነኛ እገዛ በጓደኞቼ ከፍተኛ ርብርብ እና ማስታወቂያ እየሰራን ባገኘነው ገንዘብ ብቻ መኾኑን ተናገርኩ።
... ዳኞቹ ፊልማችንን ካዩ እና የኔን ገለጻ ካደመጡ በኋላ "The Father of African Cinema" ተብሎ የሚጠራውን ኦስማን ሲንቤንን በስም እየጠሩ፤ የሰራነውን ፊልም የደረጃ ከፍታ በአቻ ንጽጽሮሽ እያመሰጠሩ አድናቆት እና ምስክርነታቸውን ሲሰጡ፤ የኢትዮጵያ ሲኒማ በአፍሪካ ውክልና ደረጃ ከፍ አድርገው አድናቆታቸውን ሲቸሩ፤ ይሰማኝ የነበረው ስሜት እየሆነ ያለው ነገር ምናባዊ እንጂ ዕውናዊ መኾኑን እስከ መጠራጠር በመድረስ ነበር።" ሲል ታምራት የገጠመውን ድብልቅልቅ ስሜት ያስታውሳል።
"የደሴቷ ጠባቂ" ፊልም በ'ምርጥ ምስል' (Best Picture)፤ በምርጥ አጨዋወት (Best Performance) እና በምርጥ ጭብጥ (Best Theam) የፌስቲቫሉ አሸናፊ ከመኾን ባሻገር የቀረውን የፍጻሜ ስራ ሙሉ ለሙሉ እንዲያጠናቅቅ የሚያስችለውን European Work in Progress GRUVI Award አሸናፊ ሆኖ በድል ተወጥቷል።
በዚህም "የደሴቷ ጠባቂ" ፊልም የ30 ሺህ ዶላር (በግምት 4,345,680.00 አራት ሚልየን ገደማ) የሚያወጣ የፖስት ፕሮዳክሽን ፍጻሜ በጀት ግራንት አሸናፊ መኾን ችሏል።
ታምራት መኮንን "በቃ እዚህ ድረስ ነው የቻልኩት" ብሎ ተስፋ ሳይቆርጥ ለዓመታት ከጓደኞቹ ጋር የለፋበት ስራ "ስንነሳ ያሰብነው ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃውን ካልጠበቀ አላወጣውም!" በማለት ዛሬ ላይ ደርሶ ከእነ "ጤዛ"፤ "Lumb" ፤ እና "አትሌቱ" ፊልሞች በኋላ በታላላቅ ዓለም አቀፍ መድረኮች አገራችንን ዳግሞ የሚወክል ግዙፍ ስራ ይዞ መቅረብ የሚችልበት የተስፋ ብርሐን ወለል ብሎ ተከፍቶለታል።
በመጨረሻ የምትለው ነገር ካለህ ብዬ ጥያቄ አቅርቤለት ነበር፦
"ይሄ ፊልም ለዚህ ስኬት የበቃው፤ ይሄ ቀን እንደሚመጣ በባዶ ሜዳ በታያቸው ፊልሙ ላይ በተሳተፉ ባለራዕይ ጓደኞቼ እና መላው የፊልም ቡድን አባላት ምክንያት ነውና እንኳንም ትልቁን ራዕይ አመናችሁበት! እንኳንም ደስ ያላችሁ በልልኝ" ብሎኛል።
እኔም "የፊልም ሥራ የሚጠይቀውን ቀና ትብብር ላልነፈጉ ቅኖች፤ በድንቅ ትወናቸው ዘውትር ለሚያስደንቁን ከያንያን የአገር ልጆች፤ በድርሰት በዝግጅት እና በሁሉም የሙያ ዘርፍ ተሳትፈው ታሪክ ለሚሰሩ ብርቱ እጆች፤ እንዲሁም በግል ጥረታቸው የአገርን ክብር ዘውትር ለሚያስጠብቁ ጠቢባን ምስጋናም ደስታም ይሁን!!" ብዬ ልቋጨው።
#europeanworkinprogressgruviaward
Tamirat Mekonen
Sewmehon Yismaw Sendekie
Rekik Teshome
Tesfaye Wondmagegn
Anteneh Asres
Michael Million
Dereje Woldemariam
Yared Shumete - ያሬድ ሹመቴ

11 months ago
6 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ጥናታዊ ፊልም በጥቅምት ወር ይመረቃል
‘ቼኑ’ የተሰኘ በአንድ ግለሰብየ60 ዓመት እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ጥናታዊ ፊልም በመጪው ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ይመረቃል ተብሏል።
ጥናታዊ ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አራት ዓመታት መፍጀቱን የባለታሪኩ አማካሪአርቲስት ፍቃዱ ከበደ ተናግሯል።
ይህን የግለሰብ እውነተኛ ታሪክ ወደ ፊልም ለመቀየር 6 ሚሊየን ብር ወጪመደረጉን ባለታሪኩ አቶ ደጀኑ በቀለ በሰጡት መግለጫ ነግረውናል።
ለእይታ ይበቃል የተባለው ‘ቼኑ’ ጥናታዊ ፊልም የሁለት ሠአት እርዝመት እንደሚኖረውየፊልሙ ዳይሬክተር ይድነቃቸው ሀይሌ ገልጿል።
የፊልሙ ታሪክ የ60 ዓመታት የህይወት ወጣ ውረድ የሚታይበትና በእነዚህ60 ዓመታት የነበሩ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ክስተቶችን ያስቃኛል ተብሏል።
የፊልሙ ዳይሬክተር የ’ቼኑ’ ታሪክ ወደ ፊልም መቀየሩ ባለፉት ሥድስት አስርትዓመታት የነበረው የአዲስ አበባን መልክ ከማሳየት አልፎ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስሪታችን መልኩ ምን ይመስል? እንደነበር የምናይበትነው ሲል ተናግሯል።

ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የወጣበት ጥናታዊ ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነዉ
#fastmereja I እዉነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራው "ቼኑ" የተሰኘ ጥናታዊ ፊልም ለእይታ ሊበቃ መሆኑን በዛሬዉ እለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
የፊልሙ ታሪክ ደጀኑ በቀለ በሚባል አንድ የ60 አመት ኢትዮጵያዊ ግለሰብ እውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ መሰረት አድርጎ የተሰራ እንደሆነ ተነግሯል።
ቼኑ ጥናታዊ ፊልም ሰርቶ ለማጠናቀቅ አራት ዓመታትና ከስድስት ሚሊዬን ብር በላይ እንደፈጀም ተገልጿል።
ይህ በአይነቱ ለየት ያለ አቀራረብና ዝግጅት ይዞ የቀረበው "ቼኑ" ለሀገርም ለወገንም ታሪክን ቀርፆ ማስቀመጥ ያለውን ከፍተኛ ሀገራዊ ሚና የሚያሳይና ውድ የሆነ የህይወት ልምድን ለአሁኑ ትውልድ አስተምሮ የሚያልፍ ድንቅ ጥናታዊ ፊልም ነው ተብሏል።
ፊልሙ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፤ የግል ድርጅት ባለቤቶችና ባለሀብቶች፥ አንጋፋና ወጣት ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።

📣ታላቅ የፊልም ፌስቲቫል🎉 💥
ሁላችሁም በነፃ ተጋብዛችኋል🔥
ጳጉሜን .. በፊልም የትዝታ ሳምንት .. ብለን እየጠበቅናችሁ ... ነዉ ...
ዩቶጲያ ቢዝነስ እና ኮሙኒኬሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአክብሮት ጋብዟችኋል
የ90 ዎቹ ተወዳጅ እና .. የጉማ ምርጦች የተካተቱበት የሀገራችን .. ፊልሞች በልዩ የትዝታ ሳምንት .. ከጳጉሜ 01 ቀን ጀምሮ .. በየቀኑ .. በ7.00 .... በ9.00 .. በልዩ ዝግጅት ... ይቀርባሉ ...
ወዳችሁ ደግመን ባየናቸዉ የምትሏቸዉን ... የሆሊዉድ ፊልሞች ... በ3D ቴክኖሎጂ በተሟላላቸዉ ... የሲኒማ አዳራሾች .. ምስልና ድምፅማ .. እንዲህ ነዉ .. እንድትሉ .. ለአምስት ቀን .. በ7.00 ... በ9.00 .. ሰዓት ጋብዘናችኃል ...
የህንድ የቦሊዉድ ፊልሞች .. ለናፈቃችሁ .. ለእናንተ .. የተመረጡ .. ፊልሞች መርጠን አዘጋጅተን .. እየጠበቅናችሁ ... እንገኛለን...
በገዘፈዉ የታሪክ ማዕከል .. ዓድዋ ድል መታሰቢያ ... በመዝናኛ ማዕከሉ .. ዓድዋ ሲኒማን .. በመጎብኘት አስደሳች ጊዜ እንድታሳልፉ ...
ሲኒማ…ውበት፣ ጥበብ፣ ለዛ፣ ታሪክ፣ ምስል
…#ቀንጃ!!!
ሲኒማ ለምትወዱ ሁሉ ስጋብዛችሁ እንደምታመሰግኑኝ ተማምኜ ነው። ደማም የፊልም ዝግጅት፤ ሸጋ ምስል፣ ብርሃን፣ ደምፅ። አሁንም ቸሬና መስኪ ድንቅ ናችሁ👌🏽👌🏽 የፊልሙ ሥራ አባላት በሙሉ ይመቻችሁ👏🏽👏🏽👏🏽
በ8.00 .. በ10.00 .. በ12.00 ... በልዩነት የተሰራዉን ... ቀንጃ. .. ፊልምን ይዘን እንጠብቃችኃለን ...
ጋባዣችሁ .. ዓድዋ ሲኒማ .. .
የበየነች ልጅ ዘርይሁን ...
0934 211884 // 0983 010211

Comments