"ውብ አዲስ" ተከታታይ ድራማ ለተዋንያን አንድ ሚሊዮን ብር ሊሸልም ነው።
#fastmereja I በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 'ዉብ አዲስ' የተሰኘ በአይነቱ ለየት ያለ ተከታታይ ድራማ በደራሲ ተዋናይና አዘጋጅ ቴዎድሮስ ተሾመ ተፅፎ እና ተዘጋጅቶ በቅርቡ እንደሚጀምር በዛሬዉ እለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
በቅርቡ መታየት የሚጀምረው ውብ አዲስ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ለሀያ አመታት ያህል ሲታሰብ የቆየ እንደሆነ እና የድራማዉ ይዘት የፍቅር ታሪክ ያለው ሲሆን ልብ አንጠልጣይ እንደሆነም ተነግሯል።
የድራማው ቀረፃ 9ዐ በመቶ ከቤት ውጭ እንደሆነና በተመሳሳይም 90 በመቶ ቀረጻው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሲሆን ቀሪውን 1ዐ በመቶ ከአዲስ አበባ ውጭ በሞሮኮ እና ጋና እንደሚደረግ ተነግሯል።
በተመሳሳይ የሁለቱ ሀገራት የጥበብ ባለሙያዎች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት እንደሚሳተፉም ነዉ የተገለፀዉ።
በተጨማሪም የቴሌቭዥን ቀረጻው ከመከናወኑ በፊት ለጀማሪ ተዋንያን እድል ለመስጠት የአክቲንግ ስልጠናና ውድድር ይካሄዳል ተብሏል።
በስልጠናው እና በውድድሩ የሚሳተፉ ጀማሪ ተዋንያንም 5ዐ% በህዝብ ድምጽ እንዲሁም 50% በባለሙያዎች ድምጽ በሚሰጥ ውጤት መሰረት አሸናፊዎች ይለያሉ። ይህም በቀጥታ ስርጭት ለቀጣይ ሶስት ወራት የሚከናወን እንደሆነ እና አሸናፊ ለሚሆኑት አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ለእያንዳንዳቸዉ የአንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት ይሰጣል ተብሏል።
ውድድሩን ከ18-50 የእድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ መመዝገብ እና መወዳደር እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን ዉድድሩ በ12 ክፍሎች ተከፋፍሎ እንደሚከናወን ተገልጿል።
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ እንደገለፁት ይህ የሀገር ውስጥ እና የውጭ የዘርፉ ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ተከታታይ ድራማ የተደበቁ ተሰጥኦዎች እንዲታዩ በእጅጉ ይረዳል ሲሉ ገልፀዋል።
በተጨማሪም የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ እና የፊልሙ ጸሐፊና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ተሾመ አብሮ ለመስራት የሚያስችለዉን የፊርማ ሥነ ሥርዓቱን አከናዉነዋል።

8 months ago