3 days ago
ዓለም አቀፍ ትኩረትን የሳበው የሐጀር አጭር ፊልም
#ethiopia | በደራሲና ዳይሬክተር ነፃለም አብዲ ተፅፎ የተዘጋጀው እንዲሁም በኢን ፊልምስ (IN Films) ወደ ስራ የተቀየረው ሐጀር የተሰኘው አጭር ፊልም በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍተኛ መነጋገሪያ መሆን ችሏል።
በዚህ የፊልም ስራ ላይ ከሃያ በላይ የሚሆኑ አንጋፋና ባለሙያ የኢትዮጵያ የሲኒማ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን የላቀ ብቃታቸውንም በተግባር አስመስክረውበታል።
የፊልሙ ታሪክ የሚያጠነጥነው ከ4,200 ዓመታት በፊት ነብዩ ኢብራሂም ሁለተኛ ባለቤታቸውን ሐጀርንና ጨቅላ ልጃቸውን ነብዩ ኢስማኤልን ይዘው ከተሰደዱ በኋላ አሁን መካ ከተማ የተቆረቆረችበት በረሃማ ስፍራ ላይ ትተዋቸው ወደተመለሱበት ታሪካዊ ወቅት ላይ ነው።
በወቅቱ ሐጀር ከፍተኛ የውሃ ጥም ስላጋጠማት ውሃ ፍለጋ በሶፋ እና በመርዋ ተራሮች መካከል ትመላለስና ትሯሯጥ ነበር። በመጨረሻም በአላህ እዝነትና ቸርነት ከሕፃኑ ኢስማኤል እግር ስር የዘምዘም ውሃ ሊፈልቅ ችሏል።
ይህ የፊልም ስራ ዓለም አቀፍ የሲኒማ ደረጃን ጠብቆ የተሰራ ከመሆኑም ባሻገር በማንኛውም የዓለም ክፍል የሚኖር ሰው በቀላሉ እንዲረዳው ተደርጎ ያለምንም ንግግር (Dialogue free) የተዘጋጀ ነው።
በተጨማሪም የእስልምናን ሥርዓትና አደብ በጠበቀ መልኩ የነብያትን ክብር ለመጠበቅ ሲባል ቀደም ሲል በዓለም ላይ ከተሰሩ ሃይማኖታዊ ፊልሞች በተለየ አዲስ የፊልም አሰራር ጥበብን ተጠቅሟል።
በዚህም መሰረት ገጸ ባህሪያቱ በአካል ሳይታዩ ነገር ግን ታሪካቸው በሚገባ በሚገለጽበት መንገድ ተቀርጾ ቀርቧል።
የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር ይህንን ስራ ለመስራት የተነሳሳበት ዋናው ምክንያት ለአስራ አንድ ዓመታት ያህል ጊዜ ወስዶ ያዘጋጀውንና በንጉስ ነጃሺ ሙሉ የህይወት ታሪክ ላይ የሚያተኩረውን ነጃሺ የተሰኘውን ታላቅ የፊልም ፅሁፍ ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ ለማውጣት የሚያስችለውን መንገድ ለመጥረግ በማሰብ እንደሆነ ታውቋል።
በፊልሙ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የተለያዩ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተገኝተው ሰፊ ዘገባ የሰሩለት ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ በሲኤንኤን (CNN)፣ ቢቢሲ (BBC) እና ሮይተርስ (Reuters) ባሉ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ የሚታወቀው ዝነኛው ጋዜጠኛ ጂም ስቴንማን (Jim Stenman) ሆርን ሆራይዘን (Horn Horizon) በተሰኘው ጋዜጣው እንዲሁም በሊንክድኢንና በሰብስታክ ገጾቹ ላይ ስለዚህ ድንቅ ስራ በሰፊው አስነብቧል።
https://www.linkedin.com/p...
#hajarshortfilm #ethiopiancinema #infilms #netsalemabdi #kingnejashi #jimstenman #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments