ነፃነት ወርቅነህ እምሩ( 1974-2018)
ማስታወሻ፦ሐምሌ ወር ላይ 2017 ነፃነት ለተወዳጅ ሚድያ ደወለ፦
"....እዝራ። ታሪካችን እኮ መሰነድ አለበት።እኔም መረጃ እልካለሁ።" በማለት ነበር ነፃነት የስነዳ ሥራው አዎንታዊ እሳቤውን የገለፀው። እኛም መረጃ ማሰባሰብ ጀምረን ነበር። ነፂ ግን"... ደርሶኛል። አየዋለሁ እዝራችን ነበር የስንብት መልዕክቱ።
ዛሬ ጥር 8 2018 ዓ.ም የሰማነው ክፉ ዜና ግን ለመስማት ይከብዳል። ነፂ ነፍስህ በሰላም ትረፍ። እንደወደድከው ታሪክህን ሰንደናል።
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
ከእነዚህ ውስጥ የሚድያ ሰዎችና የቴአትር ባለሙያዎች ይገኙበታል። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ 50 በላይ የፊልምና የቴአትር ባለሙያዎች ፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን አመራሮች እና የሚድያ ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
በዚህ ፅሑፍ የሙያ ታሪኩ የሚሰነድለት ጠንካራ ባለሙያ ነፃነት ወርቅነህ ነው። ዕዝራ እጅጉ እና ሣራ አህመድ ታሪኩን አጠናክረውታል።
#ትውልድና ልጅነት
የኪነ ጥበብ ባለሙያ ነፃነት ወርቅነህ እምሩ የካቲት 10 1974 ዓ.ም ከአባቱ ከአቶ ወርቅነህ እምሩ እና ከእናቱ ከወይዘሮ ምናለሸዋ ይፍሩ በአዲስ አበባ ከተማ በፖሊስ ሆስፒታል ተወለደ።ለቤተሰቡ አራተኛ ልጅ ሲሆን ሶስት ወንድሞች እና አንድ እህት በነበረው ቤተሰብ ውስጥ በኡራኤል ሰፈር እንዳደገ ይነገራል።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በአስፋው ወሰን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማረ ሲሆን እስከ 7ኛ ክፍል ባለው የልጅነት እና የትምህርት ቤት ቆይታው ለኪነጥበብ የተለየ ፍቅር አልነበረውም። የ8ኛ ክፍል ተማሪ እያለ "የጉሊቷ እናቴ የሚል ቲያትር ላይ የሴት ገፀ-ባህሪይ ይዞ መተወኑ ይነገራል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ምሥራቅ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል።
#ወደኪነ -ጥበብ አለም የገባበት አጋጣሚ
የ16 አመት ልጅ ሳለ ከኡራኤል መርካቶ ድረስ በእግሩ እየተመላለሰ ዩኒቲ የቴአትር ክበብን እንደተቀላቀለ ቲያትር መስራት መጀመሩ ይነገራል። የዩኒቲ ክለብ መፍረስ ቀጣዩ የነፃነት መዳረሻ የሩሲያ ባህል ማዕከል ወይም ፑሽኪን አዳራሽ እንዲሆን አደረገው። በፑሽኪን ቆይታውም በግጥሞች በወጎች መሀል የሚተላለፉ የተመልካችን ቀልብ የሚይዙ የ30 ደቂቃ ድራማዎችን ሠርቷል።በፑሽኪን ቆይታው ፍሬሸ ማን የሚለውን ድርሰቱን በ40 ደቂቃ የሚያልቅ ድራማ አድርጎ ሠርቶት ነበር።በኃላም ቲያትሩን አሻሽሎ ከአዳነች ወ/ገብርኤል ጋር መስራቱ አይዘነጋመሰ። ነፃነት በአንድ በኩል ፍሬሽ ማንን ፑሽኪን እያሳየ" የመጨረሻ ሀጢያት" የሚል በቀበሌ አዳራሽ ውስጥ የተሰራ ቲያትርም አሳይቷል።
በፑሽኪን በነበረው ቆይታ ላይ አብረውት ከሰሩት ተዋናዮች መሀከል ኢሳያስ አስራት ስለነፃነት የትወና አቅም ይህን ብሏል።
"እኔ ስለ ነጺ እመሰክራለሁ።የሚሠራውን ገና ሲወጥነው ያውቀዋል።
ፑሽኪን (የሩሲያ ባህል ማዕከል) በነበርንበት ወቅት እኔም እርሱም ተውኔት እንጽፋለን፣እናዘጋጃለን፣እንተውናለን።ፉክክር ነበር በመሀላችን።
ነፂ ግን ይለያል። አድምቶ መሥራት እና በዚያው መጠንከር እና ግቡን መምታት ያውቅበታል" በማለት መስክሯል።
ነዋሪነቱን በካናዳ ያደረገው ገዛኸኝ መኮንን ሲናገር ፦ "...ለመጀመሪያ ጊዜ በፑሽኪን ማዕከል መድረክ በግጥም መሀል በሚያቀርባቸው አጫጭር ተውኔቶች ላይ ነበር extraordinary የሆነ ችሎታ እንዳለው ያስመሰከረው።
እኔ እና ወዳጄ ሚሊዮን አየለ በጋራ ጽፈን ባዘጋጀነው ፌስታል የተሰኘች የ 5 ደቂቃ ድራማ ላይ ካስት ስናደረገው ከሙናዬ መንበሩ ጋር እንዴት በልዩ ሁኔታ እንደተጫወተው አሁንም አይረሳኝም።
ከዚያ በኋላ በጣም በርካታ ፊልሞች ላይ በመተወን አቅሙን አሳይቷል " በማለት ምስክርነት ሰጥቷል።
#የነፃነት ኪነ ጥበባዊ አበርክቶዎች
በቲያትር ዘርፍ
ነፃነት ወርቅነህ "በይቅርታ ምሽት በማዘጋጃ ቲያትር ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በቲያትር ቤት ደረጃ የሰራው ሥራ ሲሆን በመቀጠልም በብሔራዊ ቲያትር "ካብ ለካብ" የሚባል ቲያትር ላይ "የትወና ብቃቱን አሳይቷል። የዳዊት እንዚራ፤ፍሬሽ ማን፤የጓሮ ጌታ ፤የብሩክታዊት ስጦታ የተባሉ ቲያትሮች የሰራ ሲሆን ፍሬሽ ማን የራሱ ድርሰት እና በህዝብ ዘንድም ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘበት ስራው ነው።
#በቴሌቪዥን ድራማ እና በሬዲዮ ድራማ
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ በነበረው ስንቅ ፕሮግራም ላይ ባለቤትነቱ የአለልኝ መኳንንት እና የጥላሁን ዘውገ ፕሮግራም ላይ በድርሰት ፤ በአዘጋጅነት ፤ በዳይሬክተርነት እንዲሁም በተዋናይነት ሠርቷል። ጥላሁን ዘውገ ስለ ነፃነት ሲመሰክር ነፃነት ከትወና ባሻገር የማዘጋጀት ችሎታም ስለነበረው ድራማዎችን እንዲያዘጋጅ ዕድል እንሰጠው ነበር ብሏል።
በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳር ቴሌቪዥን በሚተላለፈው "መስኮት በተሰኘ የአምስት ደቂቃ ድራማዎች ላይ በበርካታ ድርሰቶች ላይ የነፃነትን አሻራ ማግኘት ይቻላል።
በሬዲዮ ድራማዎች ላይ በድርሰት በኢትዮጵያ ሬዲዮ እንዲሁም በfm 97.1 ተሳትፏል።
#የፊልሙ አለም
የመጀመሪያ ፊልሙ "የማይደረስበት" የሚለው ሲሆን ኪሳራ ላይ የጣለው ፊልም ሲሆን ከዛ በኃላ FBI1,2,3፤ የአንቺው ሌባ 1,2፤ Mr x ፤ባለቀለም ህልሞች፤ስለማይዘነጋ ውለታ፤ዕድል 20 የተሰኙ ፊልሞችን የሠራ ሲሆን የFBI 1,2,3 ፊልም ደራሲ እሱ ሲሆን፤በባለቀለም ህልሞች ላይ በዳይሬክቲንግ እንዲሁም በMr X ፊልም ላይ በድርሰት ተሳትፏል።በህዝብ ዘንድ በባለቀለም ህልሞች ፤ በአንቺው ሌባ እንዲሁም በFBI ፊልሞችየተለየ አድናቆት እና ተወዳጅነት ሊያገኝ ችሏል።
#ሌሎች ሥራዎች
ነፃነት ደራሲ ፤ተዋናይ ፤ዳይሬክተር ብቻ አልነበረም። ጎበዝ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢም ጭምር እንጂ በተለይ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚተላለፈው የቤተሰብ ጨዋታ በየፕሮግራሙ አዳዲስ ቃና እየጨመረ ለዓመታት ፕሮግራሙ በህዝብ ልብ ውስጥ እንደተወደደ እንዲሁም ሳይሰለች እንዲታይ አስችሎታል።
ከቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነቱ በተጨማሪ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን እንዲሁም መድረኮች መልዕክታቸውን ሳያጡ በሳቅ እንዲታጀቡ አድርጎ ማቅረብም ላይም የሚደርስበት የለም። በአጠቃላይ ነፃነት የዘርፈ ብዙ ሙያ ባለቤት ነበር ማለት ያስችላል።
#ልዩ ሰብዕና
ነፃነት ወርቅነህ ሌሎች ሲደሰቱ ከማንም በላይ ይደሰታል። በበርካታ ችግሮች ቢያልፍም ሳቅ ከምንም በላይ መድኃኒት ነው በሚለው አስተሳሰቡ ለዓመታት ዘልቋል። አብረውት ለሚሠሩ የኪነ -ጥበብ ባለሙያዎች ልዩ ክብር ያለው ነፃነት ለሰዎች በመድረስ የሚያምን በሰዎች የደስታና የሀዘን ጊዜም ቀድሞ የሚገኝ መሆኑን የቅርቦቹ ይመሰክራሉ።
#የትዳር ህይወት
ነፃነት ወርቅነህ፣ ከንፁህ ዘር በላይ ጋር ትዳር የመሠረተ ሲሆን የሦስት ልጆች አባት ነው። ልጆቹም የ18፤15 እና የ9 አመት ዕድሜ ሲኖራቸው የመጀመሪያ ልጁ ኦራገን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ነፃ የትምህርት ዕድል አግኝቶ እየተማረ እንደሆነ፤ሁለተኛ ልጁ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መከታተል እንደጀመረች እንዲሁም የመጨረሻዋ ለፒያኖ ፍቅር እንዳለት ከወራት በፊት ገልፆ ነበር።
ነፃነት ወርቅነህ አርብ ጥር 8 2018 44 አመቱን ሊይዝ 30 ቀናት ሲቀረው ከዚህ አለም ድካም አርፏል።

7 months ago