21 days ago
የግብጽ ሚዲያዎች ተንኮል
"ከአባይ እስከ ሩፊጂ"
*ይህ የግብጽ የቴሌቪዥን ጣበያዎች የሰሩት ዶክመንተሪ ፊልም ነው።
#ethiopia | በግብጽ ሚዲያዎች የተሰራው ይህ ዶክመንተሪ ፊልም በታንዛኒያ የተገነባውን የጁሊየስ ኔሬሬ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ ላይ ያጠነጥናል።
ግን የግብጽ ሚዲያዎች ሆን ብለው የእኛው ሀብት የሆነው የአባይ ወንዝ
የዶክመንተሪው ዋና እርዕስ አድርገው ተጠቅመውታል።
ከአባይ እስከ ሩፊጂ (From the Nile to Rufiji) በሚል ርዕስ የቀረበው ይህ ዘጋቢ ፊልም በሩፊጂ ወንዝ ላይ የተገነባውን ግድብ እና የኃይል ማመንጫ ግንባታ ሂደት እንደሚተርክ አልጀዚራ ገልጿል።
ግብፅ ይህን ፕሮጀክት በአፍሪካ አህጉር የመሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ያላትን ተሳትፎ የሚያሳይ እንደሆነ ትገልጻለች።
ዘጋቢ ፊልሙ በፕሮጀክቱ ላይ የተሳተፉ ከ12,000 በላይ መሐንዲሶችን እና ሠራተኞችን ጥረት ይዳስሳል።
በተለይም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ጨምሮ ፈታኝ በሆኑ የአየር ንብረት ሁኔታዎች ውስጥ የተከናወነውን የቴክኒክ እና የሎጂስቲክስ ስራ አጉልቶ ያሳያል።
ታድያ የግብጽ ሚዲያዎች የኢትዮጵያ ሀብት የሆነውን የአባይ ወንዝ ለምን መጠቀም ፈለጉ?
የዘርፉ ባለሙያዎች ለዚህ ጉዳይ አስታየታቸውን ሰጥተዋል።
የአባይ ወንዝ ከታንዛኒያ ግድብ ጋር የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ ባይኖርም የግብጽ ሚዲያዎች አባይን በዶክመንተሪው መግብያ ላይ የተጠቀሙበት ምክንያት መኖሩን ይናገራሉ።
ባለሙያዎቹ በዋናነት የሚያነሱት ምክንያት እንደዚህ ያሉ ርዕሶች በተመልካቹና አድማጩ ዘንድ ትኩረት ለመሳብ የተመረጡ ናቸው ይላሉ።
እንደዚሁም የፊልሙ ርዕስ የአባይን ስም መጠቀሙ ተመልካቹ ለዘጋቢ ፊልሙ የበለጠ ፍላጎት እንዲኖረው ለማድረግ ነው ብለዋል።
ከዚህ ውጭ የፊልሙ ርዕስ በአካላዊ ወይም በተፈጥሮአዊ መንገድ የኢትዮጵያን ሀብት የሆነው አባይ ወንዝ በታንዛኒያው ሩፊጂ ወንዝ ግንባታ ላይ እንደ አንድ የልማት ተዋናይ ለማያያዝ የታሰበ አይደለም ይላሉ።
ይልቁንም የግብጽ ሚዲያዎች ለአፍሪካዊያን ማስተላለፍ የፈለጉት በአባይ ወንዝ ላይ የግብጽ የፖለቲካ ፍላጎት ለማጉላት የተጠቀሙበት ስልት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #fromniletorufiji #egyptmediadocumentary #ethiopianileriver

Comments