2 months ago
ኢትዮጵያ በሩሲያ የቪዛ ነፃ የጉዞ ሥርዓት ድርድር ውስጥ ተካታ ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ
#ethiopia | የሩሲያ መንግሥት ከአፍሪካ አገራት ጋር ያለውን የዲፕሎማሲ፣ የንግድ እና የዜጎች የጉዞ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳለጥ በማሰብ፣ ከበርካታ የአህጉሪቱ አገራት ጋር ከቪዛ ነፃ የጉዞ ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችሉ ውይይቶችን እያደረገ መሆኑን የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አሌክሲ ክሊሞቭ ለስፑትኒክ የዜና ወኪል እንደገለጹት፤ ሩሲያ ከቪዛ ነፃ የጉዞ ዕድልን ለማስፋፋት ከበርካታ የአፍሪካ አገራት ጋር በድርድር ላይ ትገኛለች። ይሁን እንጂ ዳይሬክተሩ አክለውም፣ እስካሁን ድረስ በይፋ የተጠናቀቀ እና ፊርማ ያረፈበት የስምምነት ሰነድ አለመኖሩን አብራርተዋል።
ይህ የሩሲያ እንቅስቃሴ ሞስኮ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ትስስር ለማሳደግ የምታደርገው ሰፋ ያለ ስትራቴጂ አካል መሆኑን የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ታዛቢዎች ይገልጻሉ።
በአሁኑ ወቅት ለሩሲያ ዜጎች ከቪዛ ነፃ የሆኑ የአፍሪካ አገራት አሁን ባለው መረጃ መሠረት 11 የአፍሪካ አገራት ለሩሲያ ዜጎች ከቪዛ ነፃ የመጓዝ ዕድልን ፈቅደዋል። እነዚህም አገራት የሚከተሉት ናቸው፡-
🇲🇦 ሞሮኮ
🇹🇳 ቱኒዚያ
🇳🇦 ናሚቢያ
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇧🇼 ቦትስዋና
🇦🇴 አንጎላ
🇲🇺 ሞሪሸስ
🇸🇨 ሲሼልስ
🇨🇻 ኬፕ ቨርዴ
🇸🇹 ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ
🇸🇿 ኤስዋቲኒ
Credit : spuntik
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

"ስምምነቱ በ24 ሰዓት ውስጥ ይፈፀማል" - ሻሪፍ
እንደተባለው የሚሆን ከሆነ፣ የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር በአንድ ቀን ውስጥ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ተገልጿል።
የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸባዝ ሻሪፍ በገለጻቸው፣ "የኤሌክትሮኒክ ፊርማ በሰዓታት ውስጥ ይካሄዳል" ብለዋል።
ሻፊፍ በኤክስ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት አስተያየት "ስምምነቱ በ24 ሰዓት ውስጥ ይፈፀማል" ሲሉ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
"ዩናይትድስቴትስ እና ኢራን በስምምነቱ የተካተቱ ሀሳቦችን ተቀብለዋል" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰላም ስምምነቱ እንዲሳካ ሁለቱም ሀገራት ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል።
ሻሪፍ በትናንትናው እለት በሰጡት አስተያየት ዋሽንግተን እና ቴህራን በፅሁፍ ደረጃ መስማማታቸውን ተናግረዋል ያለው ቲቃህ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #spuntik # #cnn #aljazeera

3 months ago
የኢትዮጵያ የታክስ ገቢ በአምስት ዓመታት ውስጥ ከሦስት እጥፍ በላይ አድጎ 1.1 ትሪሊዮን ብር ተሻግሯል - ገቢዎች ሚኒስቴር
#ethiopia | ሚኒስቴሩ፣ የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን፣ በቀሪዎቹ ሁለት ወራት የበጀት ዓመቱን እቅድ እንደሚያሳካ አስታውቋል።
እንደ መሥራያ ቤቱ መረጃ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት የነበረው የታክስ ገቢ አሰባሰብ ዕድገት የሚከተለውን ይመስላል፦
▪️በ2014 - 336.7 ቢሊዮን ብር
▪️በ2015 - 442 ቢሊዮን ብር
▪️በ2016 - 512.8 ቢሊዮን ብር
▪️በ2017 - 900.2 ቢሊዮን ብር
▪️በ2018 (ለ9 ወራት ብቻ) - 1.1 ትሪሊዮን ብር
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #spuntik

5 months ago
የኢትዮጵያ፣ የጅቡቲ እና የሶማሊያ መሪዎች በቀጣናዊ ሰላምና በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ተጽእኖዎች ዙሪያ መከሩ
#ethiopia | 🇪🇹🇩🇯🇸🇴 የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኡመር ጊሌ እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ረቡዕ ምሽት በጅቡቲ የሀራሞስ መኖሪያ ቤት የሦስትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱ በቀጣናው ሰላም እና ደኅንነት፣ በኢኮኖሚ ውህደት ሂደት፣ ለሦስቱም ሀገራት የጋራ ፍላጎት ባላቸው ጉዳዮች እና በአካባቢው ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ትኩረት ተሰጥቶበታል።
በተጨማሪም፣ ውይይቱ በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ስላለው ግጭት እና በክልሉ ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖና ጉዳት ላይ አተኩሯል ሲሉ የጁቡቲ ፕሬዝዳንት ጊሌ በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ ጽፈዋል።
👉 በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን፣ የብልጽና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፣ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ረድዋን ሁሴን ሌሎች ባለሥልጣናት ተካተውበታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#spuntik #getutemesgen #getu #ጌጡ

ሞሪሸስ የቻጎስ ደሴቶችን ርክክብ በማዘግየት እንግሊዝን ለመክሰስ እያጤነች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሯ ገለፁ
#ethiopia | 🇲🇺🇬🇧 የደሴቲቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቪን ራምጉላም፤ ለንደን እ.ኤ.አ በግንቦት 2025 የተፈረመውን የሉዓላዊነት ሽግግር ስምምነት ላለማፅደቅ ሆን ብላ እያዘገየች ነው ሲሉ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት አስተያየት ተችተዋል።
ስልታዊው የአሜሪካ-እንግሊዝ የዲዬጎ ጋርሺያ የጦር ሠፈር መገኛ የሆነችው የሕንድ ውቅያኖሷ የደሴቶች ስብስብ፤ ይፋዊ ርክክብ እስኪከናወን ድረስ ከዓለም አቀፍ የሕግ ተቋማት ጋር ምክክር ጀምራለች።
አንኳር ነጥቦች፦
ስምምነቱ፦ ስምምነቱ የደሴቶቹን ሉዓላዊነት ለሞሪሸስ በማስተላልፍ፤ እንግሊዝ የጦር ሠፈሩን በዓመት ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ (133 ሚሊዮን ዶላር) በላይ በሆነ ክፍያ ለ99 ዓመታት ተከራይታ እንድትጠቀም ይፈቅዳል።
መዘግየቱ፦ የሞሪሸስ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ባለፈው ግንቦት ወር የተፈረመው ስምምነት እስካሁን ድረስ ተግባራዊ ባለመሆኑ "ስጋቱን" ገልጿል።
ዳራ፦ የቻጎስ ደሴቶች ሞሪሸስ ነፃነቷን ከመቀዳጀቷ ከሦስት ዓመት በፊት ማለትም እ.ኤ.አ በ1965 ነበር ከሞሪሸስ የተነጠሉት። በ2019 ዓ.ም የዓለም አቀፍ የፍትሕ ፍርድ ቤት የእንግሊዝ አስተዳደር ሕገ-ወጥ መሆኑን ወስኖ ነበር።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #spuntik

7 months ago
በኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ላይ የ38 አፍሪካ ሀገራት የአየር ኃልል አዛዦች እንደሚታደሙ ተገለፀ
🗓 ከጥር 15 እስከ 19፣ 2018 ዓ.ም በሚቆየው ዝግጅት፤ "የኢትዮጵያ አየር ኃይል የነጻነት እና የአንድነት ምልክት" በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የሩሲያ፣ የዩናይትድ አረብ ኤሚሬቶች፣ የሞሮኮ እና የቼክ ሪፐብሊክ አየር ኃይሎች የአየር ትርዒት እንደሚያሳዩ፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የ1ኛ አየር ምድብ አዛዥ ብርጋድየር ጀነራል ቡሩክ ሰይፉ ገልጸዋል፡፡
-እንደ የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘገባ፤ የሩሲያ አየር ኃይል ከ100 በላይ የልዑካን ቡድን አባላትን ያካትታል፡፡
🇷🇺🇨🇳 የሩሲያ እና የቻይናን ጨምሮ 28 የአቪዬሽን ኩባንያዎች በዓሉን አስመልክቶ በሚዘጋጀው የአቪዬሽን ኤክስፖ ላይ ምርቶቻቸውን ለእይታ እንደሚያቀርቡም ተመላክቷል።
#spuntik

8 months ago
Sponsored by
Surafel
8 months ago
በማሽን የተቆረጠ እጅ በተሳካ ሁኔታ ተቀጠለ
📌ይህን ያለው ሳምሪታን ቀዶ ሕክምና ማዕከል ነው
#ethiopia | የማእከሉ የአጥንት ቀዶ ሕክምና የከፍተኛ አደጋዎች እና መገጣጠሚያ ቅየራ ሰብ-ስፔሻሊስት ዶ/ር ቢኒያም ተሾመ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የተቆረጠ እጅን ለመቀጠል የተደረጉ የቀዶ ሕክምናዎች አለመኖራቸውን ለአገር ውስጥ የግል ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
አደጋው የደረሰው የሥጋ ማሽን ለማስተካከል ይሞክር በነበረ የ20 ዓመት ወጣት ላይ ነው፡፡
"እጁን ሙሉ በሙሉ ቆርጦትም አልቆመም፣ ደረቱን ቀዶታል፣ ወደ ውስጥ አለመግባቱ ነው እንጂ የደረቱ ጉዳት ከፍተኛ ነበር የሚሆነው።" ሲሉ ሐኪሙ የጉዳቱን ሁኔታ አብራርተዋል፡፡
ተጎጂው በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም መሄዱ፣ ጤና ተቋሙም የሚፈሰውን ደም አስቁሞ የተቆረጠውን እጅ በረዶ ውስጥ ማስቀመጡ ዳግም ለመቀጠል ወሳኝ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
6 ሠዓት የወሰደው ቀዶ ሕክምናው በስኬት ቢጠናቀቀም ቀጣይ የሕክምና ከትትሎች አስፈላጊ መሆናቸውንም ሐኪሞቹ ጠቁመዋል፡፡

🇪🇹 የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎትን ለመግዛት በርካታ ሀገራት ጥያቄ ማቅረባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ
#ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገልግሎቱን ለተለያዩ ሀገራት በክፍያ ለማቅረብ ድርድሮች በመደረግ ላይ መሆናቸውን ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ይፋ ባደረጉበት መድረክ ላይ አስታውቀዋል።
🪪 ዛምቢያን ጨምሮ በፍርድ ቤቶች፣ በኢትዮ ቴሌኮም እና በሞሰብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እየተሰጡ ያሉ ግልጋሎቶችን የጎበኙ በርካታ ሀገራት የግዢ ጥያቄ ማቅረባቸውንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።
ብዙዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ከሌሎች የውጭ ሀገራት የሚገዟቸው አገልግሎቶች እየተዘጉባቸው መሆኑን ተከትሎ “የአፍሪካን እንጠቀም የሚል ሐሳብ እየተፈጠረ” መምጣቱንም ገልጸዋል።
🆔 የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት እስካሁን ከ30 ሚሊዮን በላይ ህዝብን መመዝገቡና እስከ ሰኔ ወር ድረስ 90 ሚሊዮን ለማድረስ እየተሠራ መሆኑን በመድረኩ ላይ ተገልጿል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

ለሰላም እንጂ ለተኩስ አቁም አይደለም
እየሠራን ያለነው - የክሬምሊን ቃል አቀባይ
📌ከዲሚትሪ ፔስኮቭ መግለጫ የተገኙ ዋና ዋና ነጥቦች፦
▪️ ዘለንስኪ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጁ መሆኑን ተከትሎ ክሬምሊን ሁኔታውን በቅርበት ይከታተላል።
▪️ ዘለንስኪ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጁ መሆኑን መግለፁ "በጣም አዲስ" ነው፤ ነገር ግን ፑቲን አስፈላጊነቱ ላይ ብዙ ጊዜ ሲናገሩ ቆይተዋል።
▪️ ሩሲያ በተፈረሙ ሰነዶች ላይ የተመሠረተ የተረጋጋና ዘላቂ ሰላም ትፈልጋለች።
▪️ ክሬምሊን ትራምፕ በተለይም ሩሲያን እና የዩክሬን ሰላም ስምምነትን በተመለከተ ከፖለቲኮ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ በጥንቃቄ ተመልክቷል።
▪️ ትራምፕ የዩክሬን ግጭት መንስኤዎችን አንስተዋል።
▪️ ትራምፕ በዩክሬን የኔቶ አባልነት፣ ግዛቶች እና የኪዬቭ መሬቶች ማጣት ዙሪያ የሰጡት መግለጫዎች ከሩሲያ አቋም ጋር በጣም የሚጣጣሙ ናቸው።

🇪🇹 የአዲስ አበባ አስተዳደር በተገበረው የአንድ ጀምበር የሥራ ዕድል ንቅናቄ ለ30 ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ከንቲባዋ አስታወቁ
#ethiopia | አዳነች አቤቤ፣ “ዛሬ ወደ ሥራ ያስገባናቸው እነዚህ አዲስ ሥራ ጀማሪዎች ቀደም ሲል በተለያዩ መድረኮች ስንወያይ የሥራ ዕድል ጥያቄ የነበራቸው ወጣቶችና ሴቶች ናቸው።” ብለዋል፡፡
የሥራ ዕድል ተጠቃሚዎቹ በኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው በልዩ ሁኔታ ሥራ የጀመሩባቸው ዘርፎች ውስጥ፦
- የከተማ ግብርና፣
- ማኑፋክቸሪንግ፣
-ኮንስትራክሽን፣
- ንግድ፣
-በአገልግሎትና ሌሎችም ተጠቅሰዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች የአንድ ጀምበር የሥራ ዕድል ፈጠራ ንቅናቄ በቀጣይነት በልዩ ትኩረት እየተደገፈ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ሲሉ በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ ጽፈዋል።

ብሔራዊ ፓርኮች ሰፊ የመሠረተ ልማት ክፍተት እንዳለባቸው የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በጥናቱ አረጋገጠ
#ethiopia | ከ2014–2017 በተካሄደ የኦዲት ጥናት በዋና ዋና ፓርኮች እና የቱሪስት መዳረሻዎች መንገዶች፣ ኤሌክትሪክ፣ ውሃ፣ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶች፣ ማረፊያ ቦታዎች እና መሠረታዊ አገልግሎቶች የተበላሹ፣ ያልተሟሉ አልያም ሙሉ በሙሉ የሌሉ ሆኖ መገኘቱ ይፋ ተደርጓል።
🔍 ከሰሜን እና ባሌ ብሔራዊ ፓርኮች በስተቀር ሌሎቹ አስራ አንድ ፓርኮች መሠረታዊ የመሠረተ ልማት እና አጠቃላይ የአስተዳደር ዕቅዶች የሌላቸው አልያም በአግባቡ ያልተተገብሩ ሆነው መገኘታቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ሪፖርቱን ጠቅሶ ዘግቧል።
📑 በጥናቱ መሠረት የቱሪስት መዳረሻ መሠረተ ልማት ያልተሟላላቸው፦
✔️ የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ፣
✔️ የገራሌ ብሔራዊ ፓርክ፣
✔️ የአብያታ-ሻላ ሐይቆች ብሔራዊ ፓርክ፣
✔️ የሰንቀሌ ቆርኪዎች መጠለያ ስፍራ ተጠቅሰዋል።
የኦዲት ሪፖርቱ ዋነኛ ችግር አድርጎ የጠቀሳቸው፦
🔺የቱሪዝም ሚኒስቴር ለቱሪስት ስፍራዎች አነስተኛውን የመሠረተ ልማት ደረጃዎች አለመወሰኑ፣
🔺የቁጥጥር ማዕቀፎች ማነስ እና የዕቅድ እጥረቶች፣
🔺ፓርኮቹ ያለ ዕቅድ ወይም ደካማ አተገባበር መሥራታቸው።
“በመሠረታዊ የመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ ማሻሻያ እና ኢንቨስት ካልተደረገ፤ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ዘርፍ የሥራ ዕድል የመፍጠር፣ ኢንቨስትመንት የመሳብ እና የውጭ ምንዛሪ የማምጣት ግቡን ማሳካት እንደማይችል” ሪፖርቱ አስጠንቅቋል።

አንድ የቻይና ባንክ ለቢሾፍቱው ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ 500 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል መግባቱ ተገለፀ
#ethiopia | 🛬 ለሜጋ ፕሮጀክቱ ግንባታ የግማሽ ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ አቅርቦት መገኘቱን ያረጋገጡት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው የባንኩን ስም በይፋ ከመግለፅ ተቆጥበዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈፃሚው በሞሮኮ፤ ራባት እየተካሄደ ከሚገኘው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ፎረም ጎን ለጎን ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ ይህ ቁርጠኝነት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እየጨመረ የመጣውን ፍላጎት ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
"በሁሉም የዓለም ክፍሎች ማለትም በመካከለኛው ምስራቅ፣ ቻይና፣ ሕንድ፣ አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ ካሉ ከበርካታ የፋይናንስ ተቋማት ጋር እየተነጋገርን ነው፤ ከአበዳሪ ተቋማት እያገኘን ያለነው ምላሽም አዎንታዊ ነው" ሲሉ አስረድተዋል፡፡
🛫 በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ የሚገነባው አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ የመሬት ግዢን፣ መልሶ ማቋቋምን እና የፋይናንስ ወጪዎችን ጨምሮ 12.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስወጣ ተገምቷል።
💼 ከአጠቃላይ ወጪው ወደ 8 ቢሊዮን ዶላር ያህሉ ደግሞ በግሉ ዘርፍ የፋይናንስ አቅርቦት ይሸፈናል ተብሎ ይጠበቃል።

9 months ago
ናይጄሪያ የጅምላ አፈና መክፋቱን ተከትሎ ትምህርት ቤቶችን ዘጋች
#ethiopia | የሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል የፌደራልና የክልል መንግሥታት በኒጀር ክልል ከሚገኘው ሴንት ሜሪ ትምህርት ቤት 215 ተማሪዎች እና 12 አስተማሪዎች ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ በአስቸኳይ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ አዘዋል።
ጠለፋው ከቀናት በፊት 26 ተማሪዎች ከከቢ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መወሰዳቸውን ተከትሎ የመጣ ሁለተኛው ከፍተኛው አፈና ነው ተብሏል።
👉 ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ የመከላከያ ሚኒስትር ቤሎ ማታዋሌን በከቢ የማዳን ሥራዎችን እንዲያስተባብሩ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር 41 የኮሌጅ ካምፓሶችን ሲዘጋ፤ ኒጀር፣ ክዋራ፣ ፕላቶ፣ ቤኑ እና ካትሲና ግዛቶች የመማር ማስተማር ሥራዎችን አስቁመዋል።

የካሪቢያን እና የአፍሪካ አገራት እንግሊዝ ለባሪያ ንግድ ተጠያቂ እንድትሆን ጠየቁ
#ethiopia | የካሪቢያን ማኅበረሰብ ካሳ ኮሚሽን ልዑካን ቡድን (ካሪኮም) ከሰኞ እስከ ሐሙስ ድረስ ለከፍተኛ ደረጃ ስትራቴጂካዊ የማግባባት ተልዕኮ በለንደን ይገኛል።
👉 ይህ ጉብኝት የካሪኮም 15 አባል አገራት እና የአፍሪካ ሕብረት ፍትሕን የማስፈን ጥረት እንዲፋጠን ጥሪ ባደረጉበት ወቅት የተካሄደ ነው።
🔗 ከ15ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ባለው ጊዜ ውስጥ፣ ከ12.5 ሚሊዮን በላይ አፍሪካውያን ታፍነውና ተገድደው የተወሰዱ ሲሆን፣ ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት በብሪታንያ መርከቦች ወደ ካሪቢያን ተግዘዋል። በግዴታ የተሰደዱት አፍሪካውያን ያልተመለሱ የእኩልነት እና ሌሎች ጥያቄዎች ዛሬም ድረስ በጣም እውነተኛ ሆነው ቀጥለዋል።
ካሪኮም ለማሳካት ያቀዳቸው ጉዳዩች የሚከተሉትን ያካትታል፦
🟠 መደበኛ ይቅርታ፣
🟠 የገንዘብ ካሳ ፣
🟠 የትምህርት መረሃ ግብሮች እና
🟠 ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ መስጠት ይገኙበታል።

ግዙፉ የሩሲያ የአልሙኒየም አምራች ኩባንያ በኢትዮጵያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው
#ethiopia | 🇪🇹 🇷🇺 የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲኒግ እና የሩሲያው ሩሳል ኩባንያ 500 ሺህ ሜትሪክ ቶን ዓመታዊ የአልሙኒየም ጥቅል የማምረት አቅም ያለውን ፋብሪካ ለመገንባት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
🔊 ይህም ኢትዮጵያ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ገበያው ላይ ተወዳዳሪ አቅራቢ እንድትሆን የሚያስችላት ነው ተብሏል፡፡
የፕሮጀክቱ ዓላማ፦
🔸 በዘርፉ እየጨመረ የመጣውን ፍላጎት ማሟላት፣
🔸 የኢንዱስትሪ ልማትን ማገዝ፣
🔸 የውጭ ምንዛሬ ፍሰትን መቀንስ፡፡
💰የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስወጣ የተገለጸ ሲሆን ፋብሪካው ከሶስት እስከ አራት ዓመት ግዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተጠቅሷል፡፡
የ50 ዓመታት የአገልግሎት ዘመን የሚኖረው ፋብሪካ፤ 70 በመቶው በውጭ ብድር አቅርቦት እንደሚገነባ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲኒግ በመግለጫው ጠቁሟል፡፡
🤝 ስምምነቱን ተከትሎ ፕሮጀክቱን ወደ ተግባር ለማስገባት የጋራ የቴክኒክ ኮሚቲ መቋቋሙ ይፋ ተደርጓል፡፡
💬 “የቦታ መረጣ እና አጠቃላይ የዳሰሳ ጥናትን የሚያካትቱ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ከወዲሁ ተጀምረዋል” ሲል ተቋሙ አክሎ ገልጿል፡፡#spuntik

የመንግስት ሠራተኞች ያለማስያዣ እስከ 150 ሺህ ብር ብድር ማግኘት የሚችሉበት የዲጂታል አገልግሎት ይፋ ሆነ
#ethiopia | -የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ‘ሲቢኢ በእጄ’ በሚል ያስጀመረው አገልግሎት ወርኃዊ ደመወዝ ታሳቢ ተደርጎ ከ500 ብር ጀምሮ ብድር እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡
ቅድመ ሁኔታዎች
-የሲቢኢ ብር አካውንት፣
-መሥሪያ ቤቶች ከባንኩ ጋር አስቀድመው ውል መፈፀም ይገባቸዋል፣
-የመንግሥት ሠራተኞች ደመዝ በሲቢሲ ብር መከፈል ይኖርበታል፡፡
አገልግሎቱ ወደ ሥራ ሲገባ ስምምነት ከፈፀሙ 478 ኩባንያዎች ውስጥ ተቀባይነት ያገኙ የ83 ድርጅቶች ሠራተኞች ባለፉት ሁለት ወራት 1.6 ቢሊየን ብር መበደር መቻላቸውን ባንኩ አመልክቷል፡፡
የዲጂታል ብድር አገልግሎቱ ለዘጠኝ ወራት ሙከራ ሲደረግበት ቆይቶ ወጤታማነቱ እንደተረጋገጠ እና የመንግሥት ሠራተኞችን ቀዳሚ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡ #spuntik

ኢትዮጵያውያን ሳይንቲስቶች ሰገራን በመመርመር የሕጻናት ሳንባ ነቀርሳን የማወቅ አቅምን የሚጨምር አዲስ ግኝት ይፋ አደረጉ
#ethiopia | 🔎 ይህ ግኝት በበሽታው ምርመራ ላይ የነበረውን አስቸጋሪ እና ለአደጋ የተጋለጠ እርግጠኝነቱም ከ20 እስከ 50 በመቶ የነበረውን የአክታ ናሙና ምርመራ በተሻለ መልኩ የሚቀይር መሆኑ ተገልጿል።
በ557 ሕፃናት ላይ በተደረገው በዚህ ጥናት ከጥምር ማጣቀሻ መመዘኛዎችን ጋር ሲነፃፀር በሰገራ የሚሠራው ምርመራ በአክታ ከሚደረገው ምርመራ በበለጠ እስከ 85.5 በመቶ የደረሰ ከፍተኛ ትክክለኛነት አሳይቷል፡፡
የሰገራ ትንተና በሕጻናት ላይ የሳንባ ነቀርሳን ለመመርመር እጅግ በጣም ትክክለኛ እና ተግባራዊ ዘዴ መሆኑን በዓለም አቀፍ የሳይንስ ደረ-ገጽ ላይ የታተመው የምርመር ውጤት አስነብቧል።
ግኝቱ የአየር መተንፈሻ አካላት ናሙናዎች ለማግኘት አስቸጋሪ በሚሆኑበት ጊዜ ተስፋ ሰጪ አማራጭ ሆኗል። #spuntik

🇰🇪 ዊልያም ሩቶ ዩክሬን ውስጥ በሕገወጥ መንገድ የተቀጠሩ ኬንያውያንን እንዲለቀቁ ለዘለንስኪ ጥሪ አቀረቡ
#ethiopia | የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በዚህ ጉዳይ ላይ ከዘለንስኪ ጋር "ፍሬያማ" የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው አስነብበዋል።
ሩቶ ዘለንስኪን "በዩክሬን እስር ላይ የሚገኙ ማናቸውም ኬንያውያንን እንዲለቁ እንዲያመቻቹ" ጠይቄያለሁ ብለዋል።
👉 በሳምንቱ መጀመሪያ፣ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት “አትራፊ የሥራ ውል” ቃል ተገብቶላቸው፣ በዩክሬን ግጭት ውስጥ እንዲሳተፉ ከታለሉ 17 ዜጎቹ የእርዳታ ጥሪ መቀበሉን አስታውቆ ነበር።

እስማኤል ዑማር ጊሌ ለ2026 የጅቡቲ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲወዳደሩ ታጭተዋል ሲል የአገሪቱ ሚዲያ ዘገበ
#ethiopia | የዜና አውታሩ እንዳለው፣ ጊሌ ዕቅዱን ይፋ ያደረጉት ጅቡቲ ውስጥ በተካሄደው የገዢው “ፒፕልስ ራሊ ፎር ፕሮግረስ” ፓርቲ ጉባኤ ላይ ነው።
👉 በሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት፣ በዓለም ላይ ያሉትን “ጥልቅ ለውጦች” በማስመልከት ንቁ መሆን እንደሚያስፈልግ የተናገሩ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ ፈተናዎች ባሉበት በዚህ ወቅት አንድነት፣ መረጋጋት እና ልማት ላይ አፅንኦት ሰጥተዋል።
#spuntik
#ethiopia | የዜና አውታሩ እንዳለው፣ ጊሌ ዕቅዱን ይፋ ያደረጉት ጅቡቲ ውስጥ በተካሄደው የገዢው “ፒፕልስ ራሊ ፎር ፕሮግረስ” ፓርቲ ጉባኤ ላይ ነው።
👉 በሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት፣ በዓለም ላይ ያሉትን “ጥልቅ ለውጦች” በማስመልከት ንቁ መሆን እንደሚያስፈልግ የተናገሩ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ ፈተናዎች ባሉበት በዚህ ወቅት አንድነት፣ መረጋጋት እና ልማት ላይ አፅንኦት ሰጥተዋል።
#spuntik
Sponsored by
Surafel
9 months ago
የአፍሪካ ኅብረት በናይጄሪያ ጉዳይ ከአሜሪካ የኃይል አካሄድ ለዲፕሎማሲ ቅድሚያ እንዲሰጥ አሳሰበ
#ethiopia | የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን አሜሪካ በቅርቡ የናይጄሪያ መንግሥት ክርስቲያኖችን ያሳድዳል በሚል ከሳ፤ ስለ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ማንሳቷ እንዳሳሰበው ገልጿል።
ኅብረቱ በመግለጫው፤ ከአንድ ወገን ማስፈራሪያ ይልቅ ለዲፕሎማሲያዊ ውይይት፣ የመረጃ ልውውጥ እና የአቅም ግንባታ አጋርነቶች ጥሪ አቅርቧል።
ኅብረቱ በተጨማሪም፦
🟠 የናይጄሪያን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ፣
🟠 ለናይጄሪያ መረጋጋት እውቀት፣ የሥልጠና ፕሮግራሞች እና የክልላዊ አሠራሮችን ለማቀናጀት ዝግጁነቱን፤
🟠 ለክልላዊ መረጋጋት፣ ትስስር እና የፀረ-ሽብር ተልዕኮዎች የናይጄሪያን አስተዋጽኦ እውቅና እንደሚሰጥ በመግለጫው አስምሮበታል።

🇪🇹 ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማስተናገድ ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች
#ethiopia | ሀገሪቱ ጉባዔውን ለማስተናገድ ልምዱም አቅሙም እንዳላት የገለፁት በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ፤ ሀገራት ድጋፍ እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡
🌱 የአረንጓዴ ዐሻራ፣ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያግዙ ተግባራዊ ሥራዎችን ያከናወነችው ኢትዮጵያ፤ ጉባኤውን ለማስተናገድ ፍላጎቱም ዝግጁነቱም አላት ብለዋል፡፡
አምባሳደር ልዑልሰገድ ለማሳያነትም፦
✅ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን በማዘጋጀት የረጅም ጊዜ ልምድ እንዳካበትች፣
✅ የላቀ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዳላት፣
✅ ከ160 በላይ ለሆኑ የዲፕሎማሲ ተቋማት ጽህፈት ቤቶች መቀመጫ እንደሆነች አንስተዋል፡፡
🇧🇷 አምባሳደሩ ጥያቄውን ያቀረቡት በብራዚል እየተካሄደ በሚገኘው 30ኛው የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ነው፡፡

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኒውክሌር ሬአክተር የልህቀት ማዕከል ለማቋቋም ማቀዱ ተነገረ
#ethiopia | ማዕከሉን ከኢትዮጵያ የ10 ዓመት የልማት እቅድ ጋር በማጣመር በአህጉሪቱ በኒውክሌር ቴክኖሎጂ መሪ ለመሆን ውጥን መያዙን የዩኒቨርሲቲው የምርምርና የልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር ጌታቸው አዳም (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
በዘርፉ ብቁ ባለሙያዎችን ለማግኘት ዩኒቨርሲቲው የሰው ሀብት አቅሙን በላቁ የሥልጠና ፕሮግራሞች እና በዓለም አቀፍ ትብብር እያሳደገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
⚛️ ዕቅዱ ኒውክሌር ሳይንስን ለሰላማዊ እና ለልማታዊ ዓላማዎች ማዋልን ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከቀጣናው ሀገራት ዜጎች ባሻገር ያሉ ሀገራትንም በሥልጠናው ተደራሽ የማድረግ ራዕይ መሰነቁን ኃላፊው ገልጸዋል።
◻️ ከዓለም አቀፍ የኒውክሌር ኃይል ኤጀንሲ፣ አዲስ ከተመሠረተው የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን እና ከሌሎች ተቋማት ጋር ትብብርን ማጠናከር ዘርፉ ዓለም አቀፍ ፕሮቶኮሎችን ተከትሎ እንዲመራ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።

የሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች ከ2024 ወዲህ እጅግ ከባድ የተባለውን ጥቃት ፈፀሙ
#ethiopia | ወንበዴዎቹ በማልታ ባንዲራ ስር ቤንዚን ጭኖ ይጓዝ የነበረ የነዳጅ መርከብን ከሶማሊያ የባሕር ዳርቻ አጠገብ በኃይል መውረራቸው ተገልጿል። በመርከቧ ውስጥ የነበሩ 24 ሠራተኞች በደህንነት ክፍል ውስጥ በመደበቅ ሁኔታውን ተቆጣጥረው እንደቆዩ የተለያዩ ምንጮች ዘግበዋል።
🛳 ሄላስ አፍሮዳይት የተባለችው እና በግሪኩ ላስኮ ማሪን ማኔጅመንት ኩባንያ የምትተዳደረው መርከቧ፤ ከህንድ ሲካ ወደ ደቡብ አፍሪካ ደርባን በመጓዝ ላይ ነበረች።
ጥቃት ፈፃሚዎቹ መርከቧ ላይ ከመውጣታቸው በፊት በቁጥጥራቸው ሥር ከነበረች አነስተኛ የኢራን የሸራ መርከብ ባንቀሳቀሱት ፈጣን ጀልባ በአውቶማቲክ መሳሪያዎች እና በሮኬት ማስወንጨፊያ ተኩስ እንደከፈቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
🗺 ክስተቱ የተፈፀመው ከሶማሊያዋ ሆብዮ በግምት 550 የባሕር ማይል ርቀት ላይ እና በተለምዶ ከፍተኛ ስጋት ካለባቸው አካባቢዎች እጅግ በራቀ ቦታ ነው። በመርከቧ ላይ የታጠቁ ጠባቂዎች አልነበሩም ተብሏል።
ዓለም አቀፍ ምላሽ፦
በምላሹም በአፍሪካ ቀንድ የባሕር ውንብድናን የሚዋጋው የአውሮፓ ኅብረት አትላንታ ኦፕሬሽንየባሕር ኃይል፤ ምላሽ ለመስጠት በአቅራቢያው ያለ መርከብ አሠማርቷል። በተጨማሪም የጃፓን አውሮፕላን በአካባቢው የቅኝት በረራ አካሂዷል። #spuntik

Comments