አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 'ውብ አዲስ' የተሰኘ ተከታታይ ድራማ በቅርቡ ሊጀምር መሆኑ ተገለጸ
#ethiopia | አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤኤምኤን) በተለይም የከተማ እና ከተሜነትን በሚያሳዩ ዝግጅቶቹ የሚታወቅ ሲሆን አሁን ደግሞ በአይነቱ ልዩ የሆነውን "ውብ አዲስ" ተከታታይ የቤተሰብ ድራማ ሊያቀርብ መሆኑን አስታውቋል።
ኤኤምኤን ይህንን ፕሮጀክት ከቴዲ ስቱዲዮ (ቴዎድሮስ ተሾመ) ጋር በመተባበር ለማቅረብ የፊርማ ሥነ ሥርዓቱን በዛሬው እለት ፒያሳ በሚገኘው በአራዳ ፓርክ አካሂዷል።
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ እና የፊልሙ ጸሐፊና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ተሾመ ስምምነቱን የፈረሙ ሲሆን በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ እሸቱ ተገኝተዋል።
'ውብ አዲስ' የፍቅር ታሪክን የያዘ በከፍተኛ ልብ ሰቀላ እና ሙሉ ለሙሉ በድርጊት የተሞላ ተከታታይ ድራማ ነው።
በሁለት ትይዩ ታሪክ የሚተረከው ይህ ድራማ 4 ሲዝንና 52 ኤፒሶዶች ያሉት መሆኑ በመግለጫው ተገልጿል።
90 በመቶ ቀረጻው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሲሆን ቀሪው 10 በመቶ ደግሞ በሞሮኮ እና ጋና የሚከናወን ሲሆን የሁለቱ ሀገራት ባለሙያዎችም በድራማው ይሳተፋሉ ተብሏል።
'ውብ አዲስ' ድራማ በቅድሚያ የትወና ታለንት ውድድር በማድረግ ወጣት ተዋንያንን ከአንጋፋዎቹ ጋር በማዋሀድ የሚሰራ መሆኑ ይዘቱን ለየት ያደርገዋል።
ለጀማሪ ተዋንያን እድል ለመስጠት የአክቲንግ ሥልጠና እና ውድድር ይካሄዳል ተብሏል።
በስልጠናውና በውድድሩ የሚሳተፉ ጀማሪ ተዋንያን በ50% የሕዝብ ድምጽ እና በ50% የባለሙያዎች ድምጽ በሚሰጥ ውጤት ተመርጠው ለቀጣይ ሦስት ወራት በቀጥታ ስርጭት ይቀርባሉ።
በ12 ክፍሎች ተከፋፍሎ በሚከናወነው በዚህ ውድድር አሸናፊ ለሚሆኑ ጀማሪ ተዋንያን የአንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚሰጥ ታውቋል።
በድራማው ላይ አንጋፋዎቹ ተዋንያን ተስፋዬ ሲማ ሰለሞን ቦጋለ እና ታምሩ ብርሃኑ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከተመሰረተ ሃያ ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በሰባት ቋንቋዎች በስርጭት ላይ ይገኛል።

8 months ago