Logo
Getu Temesgen
ድንቁ ሔኖክ
#ethiopia | የሔኖክ የመጀመርያ ፊልም "ትራፊኳ.." የተሰኘው ፊልም ነበር። ከሜሮን ጌትነት ጋር ነበር አብረው የሰሩት። እዛ ፊልም ላይ የተመለከትነው የሔኖክ Acting የመጀመርያ ፊልሙ ሁላ አይመስልም ነበር። ይህ ማለት ከዛሬ 12 እና 13 አመት በፊት ነው።

ከዛ በኋላ በርካታ ፊልሞች ላይ በትወና ተሳትፏል። በሂደት ደግሞ ፊልሞችን እና የሙዚቃ ቪዲዮዎችንም ጭምር ዳይሬክት ማድረግ ጀመረ። ከታሪኩ [ ባባ ] ጋር እና ከማንዴላ ጋር የሰራው አንድ ፊልም አለ - በጣም የሚመቸኝ። እነ አለምሰገድ ተስፋዬን፣ ሙሉአለም ጌታቸው፣ ማንዴላን ካነሳን ሔኖክንም በእነሱ ምድብ ልናካትተው የምንችል ምርጥ የፊልም ተዋናይ ነው። ትናንትና በ Seifu on EBS ላይ ቀርቦ እሱ ራሱ እንደተናገረው ከሆነ የሔኖክ ወንድሙ ህይወት በ 2 ይከፈላል። የመጀመርያው ፈረጃ የተሰኘውን አዲሱን ፊልም መስራት ከመጀመሩ በፊት ያለው ህይወቱ ነው - ቀጥሎ ደግሞ ከፈረጃ በኋላ ያለው ህይወት።

‎ሔኖክ አዲስ ለሚሰራው ፊልም ብዙ ዋጋ ከፍሏል። የሚታዩም - የማይታዩም ብዙ መስእዋትነቶች ተከፍለዋል። ለዚህ ፊልም Character ብሎ ከሰውነቱ ላይ 41 ኪሎ ቀንሷል። የፊልሙ ገፀባህሪ የሰውነት አቋም ስላስገደደው።

ሔኖክ "ፈረጃ.." ፊልምን ሲሰራ 4 ነገሮችን ነው አብሮ የሚሰራው። የፊልሙ መሪ ተዋናይ ነው ፤ ደራሲ ነው ፤ ዳይሬክተር ነው ፤ Executive Producer ነው። ይህንን ፊልም እውን ለማድረግ ደግሞ 6 አመታት ያህል ፈጅቶበታል። ሌላ ስራ ሳይሰራ - ሙሉ ትኩረቱን "ፈረጃ.." ላይ ብቻ አድርጎ።

በገንዘብም ቢሆን - ብዙ አውጥቶበታል። መኪናውን እስከመሸጥ ድረስ ደርሷል። ፊልሙ በአጠቃላይ የፈጀው 7.5 ሚሊየን ብር ነው።

ከህዝብ [ ከ 1,200 ሰዎች ] የተዋጣው ገንዘብ ግን 3 ሚሊየን ብር ብቻ ነበር። እውነት ለመናገር ሔኖክ ያሰበው ሀሳብ በጣም ገራሚ ሀሳብ ነው።

"ህዝብ አምስት - አምስት ብር አዋጥቶ ፊልም እንስራ ከዛ በኋላ በዚህ ፊልም ሽያጭ ደግሞ ሌላ ፊልም ይሰራል ፤ ህዝቡን የማስቸግረው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።

ሁለተኛው ፊልም ከመጀመርያው ገቢ ነው የሚሰራው። ሶስተኛው ፊልም ደግሞ ከሁለተኛው ፊልም ገቢ። እንደዚህ እያልኩ - 50 ፊልሞችን የመስራት እቅድ አለኝ.." ብሏል። በጣም እኮ ፀዴ ሀሳብ ነው።

‎ሔኖክ ያመጣው "ህዝብ አምስት - አምስት ብር አዋጥቶ ፊልም መስራት.." የሚለው ሀሳብ በአለም አቀፍ ደረጃ Crowd funding የሚባለው እና ብዙ ትልልቅ ስራዎች የሚሰሩበት መንገድ ነው።

በሀገራችን ይሄንን ተጠቅሞ የፊልም ኢንዱስትሪውን Self-sustaining [ ራሱን በራሱ የሚደግፍ ኢንዱስትሪ ] ለማድረግ ማሰቡ ትልቅ አብዮት ነው። ይህ ሀሳብ ፊልምን ከባለሀብቶች ጥገኝነት አውጥቶ የህዝብ ንብረት የሚያደርግ ግሩም ሀሳብ ነው።

ህዝቡ 5 ብር ሲያዋጣ ዝም ብሎ ተመልካች ሳይሆን የፊልሙ ባለቤት እና ደጋፊ ይሆናል ማለት ነው። እኛ ሀገር ለአንድ የጥበብ ስራ 6 አመት ሙሉ ተግቶ መስራት እብደት ሊመስል ይችላል ፤ ነገር ግን እውነተኛ ጥበብ የሚወለደው እንዲህ አይነት ትጋት ውስጥ ነው።

ሔኖክ ለጥበብ የከፈለውን መስዋዕትነት [ ገንዘቡን፣ አካሉን እና ጊዜውን ] የምንክሰው እኛ ተመልካቾች ይሄንን ራእይ ስንደግፍና ሀሳቡን ስንገዛ ብቻ ነው።

በተለይ በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ ለገፀ-ባህሪ [ Character ] ተብሎ 41 ኪሎ መቀነስ እና መኪና እስከመሸጥ ድረስ መድረስ - የኪነጥበብን ፍቅርና ቁርጠኝነትን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

በፍራኦል ሀበሻ

18 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.