Logo
FastMereja
ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የወጣበት ጥናታዊ ፊልም ለእይታ ሊበቃ ነዉ
#fastmereja I እዉነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራው "ቼኑ" የተሰኘ ጥናታዊ ፊልም ለእይታ ሊበቃ መሆኑን በዛሬዉ እለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

የፊልሙ ታሪክ ደጀኑ በቀለ በሚባል አንድ የ60 አመት ኢትዮጵያዊ ግለሰብ እውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ መሰረት አድርጎ የተሰራ እንደሆነ ተነግሯል።

ቼኑ ጥናታዊ ፊልም ሰርቶ ለማጠናቀቅ አራት ዓመታትና ከስድስት ሚሊዬን ብር በላይ እንደፈጀም ተገልጿል።

ይህ በአይነቱ ለየት ያለ አቀራረብና ዝግጅት ይዞ የቀረበው "ቼኑ" ለሀገርም ለወገንም ታሪክን ቀርፆ ማስቀመጥ ያለውን ከፍተኛ ሀገራዊ ሚና የሚያሳይና ውድ የሆነ የህይወት ልምድን ለአሁኑ ትውልድ አስተምሮ የሚያልፍ ድንቅ ጥናታዊ ፊልም ነው ተብሏል።

ፊልሙ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፤ የግል ድርጅት ባለቤቶችና ባለሀብቶች፥ አንጋፋና ወጣት ተወዳጅ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።
#ኪነ_ጥበብ

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.