ግሩም ኤርሚያስ ዋና ገጸ ባህሪ አድርጎ በሻኪሶ የተሰራው ዳሎቪያ ፊልም ለእይታ ሊቀርብ ነው።
#fastmereja I ተወዳጁ ተዋናይ ግሩም ኤርሚያስ በዋና ገጸ-ባህሪነት የሚተውንበት "ዳሎቪያ" የተሰኘው አዲስ ፊልም በሚቀጥለው እሁድ ሚያዝያ 05 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድግስ በአድዋ 00 አፍሪካ አዳራሽ እንደሚመረቅ ተገለጸ። ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተመላከተው፣ ፊልሙ ከመጪው ሚያዝያ 09 ጀምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ሲኒማ ቤቶች ለዕይታ ይበቃል።
በኤልዳን ፊልምስ ተዘጋጅቶ በወርገድ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው ዶሎቪያ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የፊልሙ ፕሮዲውሰሮች፣ ዳይሬክተሮችና ተዋንያን በተገኙበት ዝርዝር መረጃው ቀርቧል። "ዳሎቪያ" በዋናነት ተወዳጁን ተዋናይ ግሩም ኤርሚያስን እና አማኑኤል ታፈሰን ጨምሮ ሌሎች አንጋፋና ወጣት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን አሳትፏል።
ፊልሙን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ ለአንድ ዓመት ከስድስት ወራት ያህል ከፍተኛ ዝግጅት የተደረገበት ሲሆን፣ ታዋቂው የፊልም ዳይሬክተር በሃይሉ እንግዳ አቀናጅቶታል። የቴክኖሎጂ አጠቃቀምንና የፊልም ኢንዱስትሪውን ዕድገት ታሳቢ ያደረገው ይህ ሥራ፣ አብዛኛው ቀረጻው የተከናወነው በሻኪሶና አካባቢው እንደሆነ ታውቋል።
የፊልሙ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ሚያዝያ 05 ቀን በአድዋ መታሰቢያ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ይከናወናል።
#ኪነ_ጥበብ

4 months ago