6 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ጥናታዊ ፊልም በጥቅምት ወር ይመረቃል
‘ቼኑ’ የተሰኘ በአንድ ግለሰብየ60 ዓመት እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ጥናታዊ ፊልም በመጪው ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ይመረቃል ተብሏል።
ጥናታዊ ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አራት ዓመታት መፍጀቱን የባለታሪኩ አማካሪአርቲስት ፍቃዱ ከበደ ተናግሯል።
ይህን የግለሰብ እውነተኛ ታሪክ ወደ ፊልም ለመቀየር 6 ሚሊየን ብር ወጪመደረጉን ባለታሪኩ አቶ ደጀኑ በቀለ በሰጡት መግለጫ ነግረውናል።
ለእይታ ይበቃል የተባለው ‘ቼኑ’ ጥናታዊ ፊልም የሁለት ሠአት እርዝመት እንደሚኖረውየፊልሙ ዳይሬክተር ይድነቃቸው ሀይሌ ገልጿል።
የፊልሙ ታሪክ የ60 ዓመታት የህይወት ወጣ ውረድ የሚታይበትና በእነዚህ60 ዓመታት የነበሩ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ክስተቶችን ያስቃኛል ተብሏል።
የፊልሙ ዳይሬክተር የ’ቼኑ’ ታሪክ ወደ ፊልም መቀየሩ ባለፉት ሥድስት አስርትዓመታት የነበረው የአዲስ አበባን መልክ ከማሳየት አልፎ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስሪታችን መልኩ ምን ይመስል? እንደነበር የምናይበትነው ሲል ተናግሯል።

11 months ago