Logo
Getu Temesgen
ሹም ሽረት
#ethiopia | "ሹም ሽረት" ፊልም ከነገ ጀምሮ በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች መታየት ይጀምራል።

2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የወጣበት የኮሜዲ ድራማ ይዘት ያለው "ሹም ሽረት" የተባለው ፊልም ከነገ ጀምሮ በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች መታየት እንደሚጀምር የፊልሙ አዘጋጆች በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በመግለጫው እንደተገለጸው ፊልሙ በዩሊያን ፊልም ፕሮዳክሽንና ከክብሪት ፒክቸርስ ጋር በጥምረት የተሰራ ነው።

ፊልሙ በደራሲና ፕሮዲዩሰር ዩሊያን ተ/ማርያም ተደርሶ የቀረበ ሲሆን ዳይሬክት ያደረገውም እራሱ ዩሊያን ተ/ማርያም እንደሆነ ተነግሯል።

በፊልሙ ላይ ታዋቂና አዳዲስ ተዋንያን የተሳተፉበት ሲሆን አድማሱ ከበደ ፣ ፍቅርተ ደሳለኝ ፣ ማስተዋል ወንደሰን ፣ ዩልያን ተክለማርያም ፣ ትዕግስት ከበደ ፣ አብይ ዲንሳ እና ሌሎች ወጣት ተዋንያን ተሳትፈውበታል ።

ሹም ሽረት ፊልም 2.5 ሚሊየን ብር እንደወጣበትና አንድ አመት እንደፈጀበት ተገልጿል

በመግለጫው እንደተነሳው ዩሊያን ፊልም ፕሮዳክሽን የተለያየ የዶክመንተሪ ፣ የሚዲያ እና የፊልም ስራዎች በመስራት ይታወቃል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.